• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኢትዮጵያ፤ የውይይትና መፍትሔ መድረክ መግለጫ

December 18, 2017 11:38 pm by Editor 1 Comment

የሃገራችን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ አሳሳቢ ሆኗል። ኢትዮጵያውያን በተለይ ላለፉት ሶስት ዓመታት በተከታታይና በመረረ ሁኔታ መንግስታቸውን ሲቃወሙ ይታያል። እንዲህ ያለ በተከታታይና በቆራጥነት የተካሄደ ሕዝባዊ ተቃውሞ በሃገራችን ታሪክ አልታየም። ገበሬዎች ሰልፍ ወጥተው “የህወሓት አገዛዝ በቃን” እያሉ ነው። የትናንሽ ከተማ ነዋሪዎች በነቂስ እየወጡ በመረረ ሁኔታ ሲጮሁ ይሄው ሶስት ዓመት ሆነ። ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው አየወጡ ለውጥ እንፈልጋለን ሲሉ ይታያል። ነጋዴው ሱቁን እየዘጋ ተቃውሞውን ያሰማል። ኢትዮጵያውያን ያለ ልክ ለውጥ የፈለጉ መሆናቸውን የሚያሳይ መራራ ተቃውሞ በሃገሪቱ በሰፊው በየቀኑ ይታያል። ይሁን እንጂ ተቃውሞ በሚነሳባቸው አካባቢዎች የመንግስት ታማኝ ወታደሮች፤ በተለይ አጋዚ፤ የፌደራል ፖሊስና ልዩ ታጣቂዎች፤ ደህንነት በሚወስዱት ግብታዊ ርምጃ በየሰልፉ ላይ የንጹሃን ህጻናት፣ ወጣቶችና አረጋውያን ደም ይፈሳል። መንግስት ተቃውሞ በሚነሳባቸው አካባቢዎች ሁሉ ወታደር እየጫነ እየወሰደ ዝም ሊያሰኝ ቢሞክርም ተቃውሞው እየበረታ መጥቷል። መንግስት በሚወስደው ርምጃ በነዚህ ሶስት ዓመታት ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል። ከአስራ አንድ ሽህ በላይ ታስረዋል፤ ሌሎች እንዲሰወሩ ተደርጓል። ባለፈው ጊዜ በኦሮምያ ክልል በኢሬቻ በዓል ቀን ብቻ ወደ ሰባት መቶ ሰዎች እንደሞቱ ይታወቃል። በአማራው ክልል የተገደሉት ወገኖቻችን ቁጥር በቅጡ ባይታወቅም፤ ብዙ መቶዎች እንደተጨፈጨፉ ተነግሯል። በቅርቡ በጨለንቆ አካባቢ ብዙ ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉ ዜናዎች ተሰምተዋል። በአዲግራት የሚማሩ የአማራ፤ የኦሮሞና ሌሎች የትግራይ ብሄር አባል ያልሆኑ ተማሪዎች ተገድለዋል።

ባላፈው ሶስት ዓመት ውስጥ ባለው ተከታታይ ተቃውሞ በተለይ በገጠሩ አካባቢ ከሚገመተው በላይ ሰው እንደሚሞት እንገምታለን። ሃገሪቱ በመረጃ መረብ የዳበረ ግንኙነት ስለሌላት፣ ጋዜጠኞች ግጭት ወዳለበት አካባቢ እንዳይሄዱ ስለሚከለከልና ብዙ የሲቪክ ድርጅቶች ስለተዘጉ መረጃዎች አይወጡም እንጂ በየቀኑ የሚሞተው ሰው ከሚገመተው  በለይ እንደሚሆን አያጠራጥርም።

ሃገራችን ኢትዮጵያ ከገጠማት አሳሳቢ ነገር አንዱ ደግሞ የወቅቱን የብሄርና የጎሳ ፖለቲካ ተከትሎ በመጣው የመተማመን መውረድ ጋር ተያይዞ የብሄር ግጭቶች በሰፊው ይታያሉ። ህዝቡ በአንድ በኩል ከመንግስት ጋር እየታገለ በሌላ በኩል ስርዓቱ ያፈራቸው ጽንፈኛ ብሄርተኞች ደግሞ ሌላ የሃገር ህልውና ስጋት ሆነውበታል። በቅርቡ በኦጋዴን አካባቢ ብቻ ከሰማንያ  ሺህ በላይ የሚገመቱ የኦሮሞ ብሄር አባላት ከሶማሊያ ክልል ተፈናቅለው ዓለም ደንግጧል። ይህ ብቻ ሳይሆን የትምህርት ሚንስቴር በቅርቡ ከሱማሌ ክልል ተወላጅ ውጭ የሆኑትን የሌላ ብሄር ተወላጆች ሶማሊያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እንዳይማሩ መደረጉ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ግራ ያጋባ፣ ያሳሰበ ነገር ነበር። ከሁሉ በላይ ኢትዮጵያውያን በነጻነት በአሜሪካ፣ በብሪታኒያ፣ በኖርወይ፣ በአውስትሬሊያ፣ በካናዳ፣ በስዊድን፣ በጀርመንና በሌሎች አገሮች ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እየተማሩ በሃገራቸው ምድር በብሄራቸው ብቻ በነጻነት መማር ያለመቻላቸው የብሄር ግጭት በኢትዮጵያ የደረሰበትን ደረጃ ያሳያል። በርግጥ ይህ ዜና ለብዙ ኢትዮጵያውያን አሳፋሪ ነው።

ባለፉት ጥቂት ቀናት ደግሞ ሃገሪቱ ተስፋ ከምትጥልበት የትምህርት ተቋም ውስጥ የብሄርየጎሳ ግጭት እየታየ መምጣቱ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል። አስራ ሁለት በሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ተቃውሞዎች እየተሰሙ ሲሆን በአንዳንድ የትግራይ፣ የአማራና የኦሮሞ ዩኒቨርሲቲዎች ብሄር ተኮር ግጭቶች ታይተዋል። ይህ ግጭት የለጋ ተማሪዎችን ህይወት ቀጭቷል። የብሄር ተኮር ግጭቱ በተለይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካባቢ መታየየቱ ነው የበለጠ አሳሳቢ ያደረገው።

በተለይ ባለፉት ሶስተ ዓመታት ካለው ሰፊ ህዝባዊ ተቃውሞ የተነሳ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ክፉኛ ተጎድቷል። የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ረሃብ በሰፊው ይታያል። ስደትና መፈናቀል በየቤቱ ገብቷል። ወጣቶች ሃገር ጥለው ይጠፋሉ። በየመንና በሊቢያ ለባርነት እየተሸጡ ነው። የሃገር ውስጥ መፈናቀሉ ቀጥሏል። ይሁን እንጂ ሃገሪቱ በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ ወድቃ፣ መንግስት በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ ተዘፍቆ፣ ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብም ሆነ ለኢትዮጵያውያን ችግሩን ማንሳትና መሰረታዊ ችግሮችን ለመፍታት ኣይፈልግም። ይህ የመረረው ህዝብ አንድ ቀን ጮሆ ጮሆ ሲበቃው ዝም ይላል ብሎ ይጠብቅ እንደሆነአናውቅም። መንግስት ዘላቂ የሆነ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት ሲሰራ  አይታይም። አገር ቤትና ከሃገር ውጭ ካሉ  ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ውይይትና ድርድር ለማድረግ አልፈለገም። ይህ ሁሉ መራራ ተቃውሞ እያለ፣ የዚህ ሁሉ ህዝብ እንባ ሲፈስ እያየ ገዢው መንግስት ልቡ ሲሰበር ኣናይም።  መንግስት ይህ ሁሉ ችግር እያለበት“በተሃድሶ ጎዳና” ላይ ነን ይላል። ይህ የመንግስት ዝንባሌ እጅግ አሳሳቢ ሆኖ እናያለን።

የኢትዮጵያ የውይይትና መፍትሄ መድረክ የሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ አሳብ ላይ ስለጣለን የሚከተለውን መልእክት ለሚመለከታቸው ሁሉ ማስተላለፍ እንሻለን።

ሀ. ለኢትዮጵያውያን ያለን ጥሪ

  1. ኢትዮጵያ ውስጥ የለውጥ ባቡር በጉዞ ላይ ነው። ኢትዮጵያውያን ሽግግር ፈልገዋል። ግፍ፣ ዘረኝነትና፣ አምባገነን ስርዓት አንገሽግሿቸዋል። የህዝቡ ጥያቄ በሃገሩ ህግም ይሁን በዓለም ዓቀፍ ህጎች ተቀባይነት ያለው ነው። ስለሆነም ህዝቡ ትግሉን በሰላማዊ መንገድ እንዲገልጽ እያበረታታን፤ ነገር ግን በትግሉ ወቅት ብሄር ተኮር ግጭቶች ሲነሱ ጽንፈኞችን መታገል ይኖርበታል። ያለመታደል ሆኖ ትግሉ አምባገነን ስርዓትን ለመጣል ብቻ ሳይሆን የብሄር ፖለቲካው ያፈራቸው ጽንፈኞችም ህዝባዊ ኣመጾችን ተገን እያደረጉ የብሄር ግጭት ስለሚያነሱ ይህንን ህዝቡ ነቅቶ እንዲጠብቅ እንመክራለን።
  2. በየትኛውም የስልጣን ርከን ላይ ያላችሁ የመንግስት ባለስልጣናት የዚህ ህዝብ እንባ ግድ ሊላችሁ ይገባል። በመሆኑም በየመስሪያ ቤታችሁ ህዝቡ ድምጹ ይሰማ ዘንድ ጥያቄዎችን እንድታነሱ፣ ከህዝብ ጥያቄ ጎን እንድትቆሙ ያስፈልጋል። ይህ ወቅት ታሪካዊ ወቅት ነውና በዚህ ታሪካዊ ወቅት ከህዝቡ ጎን ቆማችሁ ሃገራችሁን እንድትታደጉ እንጠይቃለን። በተለይ በወታደሩና በጸጥታው ክፍል ውስጥ ያላችሁ ወገኖች መንግስት የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን የሚጠቀምበት ዋና መሳሪያ በመሆናችሁ በዚህ ወቅት ከህዝብ ጎን ትቆሙ ዘንድ እንጠይቃለን።
  3. በሃገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያላችሁ ተማሪዎች፤ ትግላችሁን እናደንቃለን፤ ሳይማር ያስተማራችሁን አባታችሁን፣ ሳትማር ያስተማረቻችሁን እናታችሁን፣ ተስፋ የሚያደርጋችሁን ገበሬ አስቡ። ሃገራችን ይህን ተቋም ነው ተስፋ የምታደርገው። የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ፣ ዘረኝነትንና ኣድልዎን ኣጥፍቶ ፍትህን ለማምጣት፣ ከድሃነት ወጥተን ለራሳችን የምንበቃ እንድንሆን ሃዋርያት ትሆናላችሁ ተብላችሁ የምትጠበቁ ብርቅየ ልጆች ናችሁ። ታዲያ በዚህ ተስፋ ከተጣለበት ተቋም ውስጥ የብሄር ግጭት የሚያስነሱ ጽንፈኞች ሲነሱ ልትዋጉት ይገባል። የሚያጋጫችሁ ሃይል የኢትዮጵያን የሽግግር ወቅት ለማበላሸት፣ የኢትዮጵያውያንን የለውጥ ጥያቄ ለማበላሸት ነውና ይህንን ጸንታችሁ ታገሉ። በአንድነት ተነስታችሁ የህዝቡን የለውጥ ጥያቄ አስተጋቡ።
  4. የተለያዩ የሲቪክ ማህበራትና የፖለቲካ ድርጅቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ በህብረት የኢትዮጵያውያንን የለውጥ እንቅስቃሴ መደገፍ ያስፈልጋል። የብሄር ግጭት ሲታይ ጽንፈኝነት ሲታይ ይህንን በማውገዝ ቀዳሚ ትሆኑ ዘንድ እንጠይቃለን።
  5. የሃይማኖት ተቋማት በኢትዮጵያ የለውጥ ትግል ውስጥ ልትሳተፉ ይገባል። በማስታረቅ፣ የለውጥ ጥያቄውን በመደገፍና በጸሎት የኢትዮጵያውያንን የለውጥ ትግል እንድትደግፉ በአክብሮጥ ጥሪ እናደርጋለን።

ለ. ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ያለን ጥሪ

  1. ኢትዮጵያ ባሳለፈቻቸው የህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ከጎን በመሆን፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል በመደገፍ መግለጫ ስታወጡ ህማማችንን ስትካፈሉ ለነበራችሁ ዲፕሎማቶች፣ የዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ልዑካን ሁሉ ምስጋናችን ብዙ አድናቆታችንም እጥፍ ድርብ ነው። በግልጽ ከምታደርጉት በጋዜጣ ከምናነበው ውጭ የኢትዮጵያን መንግስትን በመምከር አቅጣጫ በማሳየት እንደምትደክሙ ይሰማናል። ይሁን እንጂ መንግስት የሚሰጠውን ምክር ችላ እያለ፣ የሚሰጣቸውን የለውጥ ተስፋዎች እያዘገየ፣ እያስረሳና እያዘናጋ ጊዜ መፍጀት ብቻ ነው የሚፈልገው። ለእውነተኛና ሁሉን አቀፍ ምክክር ልቡን አይሰጥም። በመሆኑም እንደምታዩት ዛሬ በየዩኒቨርሲቲው የብሄር ተኮር ግጭት ሳይቀር መታየት ጀምሯል። ሩዋንዳ ውስጥ አንድ ትምህርት ቤት የተነሳ ግጭት ሃገሪቱን በጥቂት ጊዜ አዳርሶ ዓለም የዘገነናትን ወንጀል አይተናል። በአሁኑ ሰዓት የዘር ፍጅት ተግባራት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካባቢ እየታየ በመሆኑ ይህ ጉዳይ የሚያሳስባችሁ እንደሆነ እናውቃለን። በመሆኑምከፍተኛውን ተግባራዊ ርምጃ በመውሰድ ይህን መንግስት ወደ ድርድር እንዲመጣ ተጽእኖ እንድትፈጥሩ በትህትና እንጠይቃለን።
  1. እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ለዓለም ስጋት ከሆነው የሽብር ጥቃት በተለይም ለአልሸባብ እንቅስቃሴ የተጋለጠች አገር ናት። ይህን ሃይል ለማዳከም ብሎም ቀጣናውን ከሽብር ስጋት ነጻ ለማድረግ ኢትዮጵያ ትልቅ ሃላፊነት ትከሻዋ ላይ አለ። ፔንታጎን በዚህ ቀጣና ያለውን አሸባሪ ለማጥፋት የሚያደርገውን ንቅናቄ እያደነቅን ኢትዮጵያ በዚህ ቀጣና ሽብር የመከላከል አቅሟ ከፍ ይል ዘንድ የውስጥ መረጋጋትና ሁሉን አቀፍና ዲሞክራሳዊ መንግሥት ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ የውስጥ አለመረጋጋት በአንድም በሌላም መንገድ ለሽብር እንቅስቃሴ መጋቢ ችግር ስለሚፈጥርና በቀጣናው ሰላም ላይ አሉታዊ ጫና ስለሚኖረው በአንድም በሌላም መንገድ ፔንታጎን ከኢትዮጵያውያን የለውጥ ፍላጎትና ጥያቄ ጋር እንዲቆምልን በአክብሮት እንጠይቃለን።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ኣስከባሪ ክፍሉም በኢትዮጵያ ውስጥ መረጋጋትን ያላመጣ መንግስት ጸረሽብር ስራ ሊሰራ ስለማይችል ሁኔታውን ተረድቶ በግንኙነት መስመሮቹ ሁሉ ለውጥ በኢትዮጵያ እንዲመጣ እንዲታገልልን እንጠይቃለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት ይጠናከር!!

የኢትዮጵያ፤ የውይይትና መፍትሔ መድረክ (ኢውመመ)

9900 Greenbelt RD. E#343 – Lanham, 

MD 20706

Tel: 1-202-641-5517


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: eprdf, Ethiopia, meles, Right Column - Primary Sidebar, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    December 21, 2017 11:54 pm at 11:54 pm

    ኢህአድግ ውስጥ ምንም ችግር የለም!!ጎልቶ የሚታይ ማለቴ ነው!! መንግስት ይቀየር: ነጻ ውይይት: ገበያ ይውጣ: ዋጋውን እንተምን:ቅርጫ ይሻላል: ጊዜው ፍልሰታ ነው !!! ወሬ! ወሬ! ያስተዳደር ችግር አለ!! ሻጥር አለ ያንን ማስተካከል ነው!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am
  • የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው December 7, 2020 12:38 am
  • የቆሰሉ ወታደሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጎበኙ December 6, 2020 11:41 pm
  • “ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ December 2, 2020 12:24 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule