• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጀርመናዊው የገደላት ሰብለ ከአንድ አመት በኋላ በመኖርያ ቤትዋ ተቀብራ ተገኘች

July 19, 2015 10:38 pm by Editor Leave a Comment

ሰብለ (ሚሚ) ዲትሪች ለመጨረሻ ግዜ የታየችው እ.ኤ. አ. ጁላይ 10 2014 (ባለፈው አመት) ነበር።  የሶስት ልጆች እናት የነበረች  የዚህች ኢትዮጵያዊት በድንገት መሰወር ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኖ ሰንብቷል።  ለአመት የጠፋችው ይህች ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሴት በህይወት እንደማትኖር በርካቶች ቢጠረጥሩም፣ ማንንም ሳታማክር በድብቅ ወደ ሃገርዋ ገብታለች የሚሉ አልጠፉም።  አለም አቀፍ ፖሊስ በአለም ዙርያ ፍለጋውን ተያያዘው።

በካናዳ ኪችነር ከተማ ቫንኮቨር ድራይቭ የተገኘው አጽም ግን የሁሉንም እንቆቅልሽ ፈታው። ሰብለ ህይወትዋ አልፏል።  የሶስት ልጆችዋ አባት የነበረው ጀርመናዊው ስቴፋን ዲትሪች ገድሎ እዚያው መኖርያ ቤታቸው እንደቀበራት ፖሊስ ጠቁሟል።  በፖሊስ እና በሰለጠኑ ውሾች ጥቆማ የተገኘው የሰብለ አስከሬን በቶሮንቶ ኮርነርስ ኮምፕለክስ ለጥናት ተልኮ የተገኘው ውጤት ሰብለ በሰው እንደተገደለች ተረጋግጧል። ዋናው ተጠርጣሪም ጀርመናዊው ባለበትዋ ነው።

በመጀመርያ ደረጃ የግድያ ወንጀል የተከሰሰው የሚሚ ባለቤት ስቴፋን  ዲትሪች ፍርድ ቤት ቀርቦ በሰጠው ቃል ጉዳዩ በጀርመን ሃገር እንዲታይለት ጠይቋል። በእለቱ ኢትዮጵያውያን ፍርድ ቤቱን አጥለቅልቀውት ነበር።

ሰብለ ዲትሪች ተገድላ ከተሰወረች ከአመት በኋላ የቀብር ስርዓትዋ እለተ አርብ (ጁላይ 18) በካናዳ ቅዱስ ፓውሎስ ቤተ ክርስትያን ተፈጽሟል። በቀብሩ ላይ ወላጅ እናትዋን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል።

seble funeralስቴፋን  ዲትሪች የአዞ እንባ እያነባ ምስጢሩን ለአመት ከደበቀው በኋላ መኖርያ ቤቱን ለመሸጥ ማስታወቅያ አውጥቶ ነበር። ይህ ድርጊቱ የፖሊስን ጥርጣሬ እንዳጎላው ግልጽ ነው።

ሰብለ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነበረች። የቤተ ክርስትያኑ ዘማሪም ናት። ባልዋ ዲትሪችም እንደዚሁ። ከጀርመን ሃገር ወደ ካናዳ ከተዘዋወሩ በሁዋላ እጅግ በጣም የተደላደለ ኑሮ እንደነበራቸው ይነገራል።  ሰብለ ከኢትዮጵያውያን የቤተ-ክርስትያን ሰዎች በተለይ ከፓስተሮች ጋር የምታደርገው የአገልግሎት ግንኙነት ግን ለስቴፋን ዲትሪች እንዳልተመቸው የሚመሰክሩ አሉ።  ይህም ቢሆን ክቡር ነብስን ለማጥፋት ምክንያት ሊሆን አይችልም። …. ስቴፋን ዲትሪች ሰብለን ለምን ገደላት? ገድሎስ ለምን ቤቱ ቀበራት? ይህንን ከፍርድ ቤቱ ሂደት የምናየው ይሆናል።

የሰብለ እናት የካናዳ የመኖርያ ፈቃድ አግኝተው የመጡ ሲሆን ሶስት ልጆቹን እሳቸው እንደሚንከባከቧቸው ከካናዳ መንግስት መረጃ አግኝቻለሁ።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእምዬ ምኒልክ አዳራሽ October 30, 2023 10:27 am
  • የኢትዮጵያ መከላከያ መሥራች አጼ ምኒልክ መሆናቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናገሩ October 26, 2023 01:30 pm
  • ጥቅምት 15 ለምን? October 26, 2023 01:29 am
  • “በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት” October 26, 2023 12:57 am
  • “ውትድርና ሕይወቴ ነው” October 26, 2023 12:13 am
  • መከላከያ በሁሉም መስክ ኢትዮጵያን የሚመጥን ኃይል እየገነባ ነው October 20, 2023 05:07 pm
  • “ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትምህርት ቤት እኩል ነው በችሎታው ነው እንጂ የሚመዘነው” ፕ/ር ብርሃኑ October 20, 2023 04:47 pm
  • 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች ታሰሩ October 18, 2023 04:29 pm
  • በተማሪዎች ፈተና ውጤት ለታየው ውድቀት ትምህርት ሚ/ር ኃላፊ መሆን አለበት ተባለ October 18, 2023 04:00 pm
  • ቀይ ባሕር እና ዓባይ “የኅልውና ጉዳይ ናቸው”፤ “መተንፈሻ ወደብ ያስፈልገናል” October 13, 2023 10:04 pm
  • ከ3,106 ትምህርት ቤቶች 1,328ቱ (44%) አንድም ተማሪ አላሳለፉም October 10, 2023 01:51 pm
  • “አቋጥሬ” በአማራ ክልል እያጫረሰ ነው፤ ” ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም ” ነዋሪዎች October 10, 2023 09:07 am
  • እሸቴ አሸባሪ፤ ቲዲኤፍ/ትሕነግ “ሰማዕት” – የዘመናችን ጉድ! October 7, 2023 06:47 am
  • በወልቃይት 1.1ሚሊዮን ኩንታል ሰሊጥ ለመሰብሰብ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሠራተኛ ይፈለጋል September 27, 2023 10:42 am
  • በአማራ ክልል ሰላም ዕጦት ከ90.5 ቢሊዮን ብር በላይ ፕሮጀክቶች ቆመዋል September 27, 2023 08:41 am
  • ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው September 21, 2023 02:38 pm
  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule