• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ምኒልክነትን የጠየቀው” የአድዋ ድል!

March 2, 2017 08:01 am by Editor 4 Comments

“ … ወታደር ባለመሆኔ የጦርነቱን ውሎ ማተት አያምርብኝም፡፡ ያም ሆኖ የአድዋ ድል ዛሬ ብርቅ በሆኑብን ሁለት እሴቶች ረድኤት የተገኘ ይመስለኛል፡፡ እኒህ ሁለት እሴቶች መተባበርና መደማመጥ ናቸው፡፡ ጣልያኖቹ በጊዜው ወደ ጦርነት ሲገቡ ተስፋቸውን የጣሉት በመድፍና በጠመንጃቸው ሳይሆን ኢትዮጵያውያን ዝነኛ በነበሩበት የውስጥ መቆራቆስ ላይ ነው፡፡ የትግራይ ቅልጥም ሲመታ ሸዋ ያነክሳል ብለው አላሰቡም፡፡ በርግጥም በክፍለ ሀገሮች ውስጥ የተለያዩ ሽኩቻዎች ነበሩ፡፡ እኒህን ሽኩቻዎች አስረስቶ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ለአንድ አላማ ማሠለፍ ምኒልክነትን ይጠይቃል፡፡

“መደማመጥ ያልሁትን ላሳይ፡፡ አባ ዳኘው ከዛሬው የይስሙላ ፓርላማችን በተሻለ ሁኔታ ለልዩነቶች ቦታ የሚሰጥ ተንቀሳቃሽ ምክር ቤት በጦርነቱ ወቅት መፍጠር ችለዋል፡፡ ፀሐፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ በውጊያው ዋዜማ የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ይገልፁታል

‘… አፄ ሚኒልክም በበነጋው ሰራዊቱን የቀኙን በቀኝ፣ የግራውን በግራ አሰልፈው ነጋሪትዋን እያስመቱ ወደሱ ተጓዙ፡፡ ኢጣሊያኖችም ዘበኛው ሲመጣ ባዩ ጊዜ ተመልሰው ወደ እርዳቸው ገብተው ተኙ፡፡

ከዚህ በኋላ ሰራዊቱም እንደ ኤሊ ስንመጣበት ከድንጋይ ይገባል፤ ስንመለስ ይወጣል፤ እንዲህ አርጐ ሊጫወትብን ነውን? ብሎ እጅግ አጥብቆ ተናደደ፡፡ መኳንንቶቹም ተሰብስበው ከዚህ ሰፍረን አድረን በማለዳ እዚያው ካሉበት ከርዱ ድረስ ሄደን እንዋጋለን ብለው መከሩ፡፡ ንጉሠ ነገሥቱም እሺ ብለው ድንኳኑን ለማስመጣት አዘዙ፡፡

ይህ ምክር ካለቀ በኋላ የትግሬው ገዢ ራስ መንገሻ ተሰልፎ በፈረስ ሆኖ መጣ፡፡ እሱም ይህ ምክር እንዳለቀ ባዬ ጊዜ አንድ ነገር ልናገር ይፍቀዱልኝ ብሎ ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ቀርቦ እንዲህ አለ፡፡ እንደ ተርታ ነገር ካልሆነ ስፍራ ሄደን ልናስፈጀው ነውን? አለ፡፡ ይህ ምክር የተስማማ ምክር ሆነ፡፡ አፄ ምኒልክም ተመልሰው ከድንኳንዋ ከገቡ በኋላ እንዲህ አሉ፡፡ እንግዲህ ከሰፈሬ ወጥቶ ተኩስ አልጀመረ ባይኔ ካላየሁት ተሰልፌ አልወጣም፡፡’

“ፀሐፌ ትእዛዝ ያቀረቡትን ዘገባ ወደ ዘመናዊ አማርኛ አሳጥሬ ሳዛውረው የሚከተለውን ይመስላል፡፡

“ርዕሰ-ብሔር ምኒልክ ሰራዊታቸውን እየመሩ ወደፊት ሲገሰግሱ የጣልያን ሰራዊት ስልታዊ ማፈግፈግ አድርጎ ወደ ምሽጉ ገባ፡፡ ምኒልክ በቀጣዩ ስትራቴጂ ላይ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ ጠሩ፡፡ በስብሰባው ላይ ወደ ጠላት ምሽግ ሄደን እንዋጋ የሚል ሐሳብ ቀርቦ ባብላጫ ድምፅ ፀደቀ፡፡ ምኒልክም በብዙሃኑ ተሰብሳቢ የቀረበውን ሐሳብ ለማስፈፀም ተዘጋጁ፡፡ ይሁን እንጂ ጄኔራል መንገሻ ዮሐንስ ዘግይቶ ስብሰባውን ከተቀላቀለ በኋላ “ምሽግ ድረስ ሄዶ መዋጋት በወገን ጦር ላይ ጉዳት ያስከትላል” ብሎ መከራከር ጀመረ፡፡ ምኒልክም “እኔ አንዴ ወስኛለሁ፤ ውሳኔዬ ካልጣመህ በሊማሊሞ በኩል ማቋረጥ ትችላለህ” ብለው ሳያሸማቅቁት ሐሳቡ እንዲጤን አደረጉለት፡፡ ሐሳቡ በድምፅ ብልጫ ፀደቀ፡፡ በድምፅ ብልጫ ያልሁት “ይህ ምክር የተስማማ ምክር ሆነ” የሚለውን የፅሐፌ ትዕዛዙን አማርኛ ተርጉሜ ነው፡፡”

“እንደተመለከተው አጤ ምኒልክ ልዩ ልዩ ሐሳቦችን ለማዳመጥና አወዳድረው የነጠረውን ሐሳብ ለማስፈፀም ዝግጁ ነበሩ፡፡ በአራት ነጥብ የታጠረ ግትርነት አልነበረባቸውም፡፡

“ሾፐናወር የተባለ የጀርመን አገር ፈላስፋ ከአድዋ ሠላሳ አምስት አመት አስቀድሞ “ከጥንት ግብፃውያንና ከህንዶች ውጭ ያለው ታላቅ የስልጣኔ ፍሬ ሁሉ በነጮች ጥረት ውጤት ነው፡፡ ከጥቁር ህዝቦች መካከል እንኳ የገዢነትን ስልጣን የሚይዙት በቀለም ፈካ ያሉት ናቸው” ብሎ ነበር፡፡ ያጤ ምኒልክ ፊት ይህንን ንድፈ ሐሳብ በይፋ ለማስተባበል የተፈጠረ አይመስልም?”

በዕውቀቱ ስዩም፤

ምንጭ፡ ፍትህ፤ ቅጽ 5፣ ቁጥር 177፤ የካቲት 23፤2004ዓም

ጊዜ በማያደበዘዝው የአድዋ ድል ማግስት…

የዓለም ህዝብ ሁሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጭን ድል ያደረገውን የጥቁር ጦር መሪ አጤ ምኒልክን ለማወቅ እጅግ ጓጓ፡፡

ምስላቸውን ለማየት ተቁነጠነጠ፡፡

ሙሉ ታሪካቸውን ለመስማት ተንሰፈሰፈ፡፡

ይህንኑ ተከትሎም፤ “እንኳንም ደስ አለዎት” ለማለት ከቁጥር የበዙ ደብዳቤዎች ይጎርፉላቸው ነበር፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ በፖስታ ቤት በኩል የኢትዮጵያ ቴምብር የተለጠፈበት መልስ እንዲላክላቸው ይጠይቁ ነበር፡፡

ለምን… ?

ቴምብሩ ላይ ያለውን የምኒልክን መልክ ለማየት፡፡

ባለ ብዙ ዝናና ክብር ባለቤት የሆኑትን የምኒልክን ጥቁር ፊት ለማየት፡፡

የሰው ሀገር ሰው ሁሉ፤ “ዝናውን እንደሰማሁ መቼ ሄጄ ባየሁት”፣ “በጀግንነቱ እንደ ተማረኩ መች ተጉዤ ባገኘሁት”፣ “ካሁን ካሁን ፈቅዶልኝ ወታደር ሆኜ ባገለገልኩት” ያለላቸው አጤ ምኒልክ የኛ ናቸው፡፡

በዓለም ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጭን ያንበረከከ የጥቁር ጦርን የመሩት ንጉስ የኛ ናቸው፡፡

መወድስ የማይበዛበት የአድዋ ድልም የኛ ነውና፣

እንኳን ትላንትም፣ ዛሬም፣ ነገም ለምንኮራበት በዓላችን በጤንነት አደረሰን! (ምንጭ: ነቆራ እና ሌሎችም ወጎች ከሕይወት እምሻው ጋር – Hiwot Emishaw)

ዝክረ አድዋ!!

(የጥቁር ሕዝብ ኩራት!!)

ልክ የዛሬ 121 ዓመት እብሪተኛውን ጣልያን አድዋ ላይ ገጥሞ አይቀጡ ቅጣት የቀጣው የኢትዮጵያ ጦር በእምዬ ምኒሊክ ፊታውራሪነት በድል ተመልሶ አዲስ አበባ ሲገባ ህዝቡ በታላቅ እልልታና ጭፈራ ተቀበላቸው፤ ወዲያውም ግዳይ ሲጣልና ሲፎከር ለጀግኖቹ ክብር የሚከተለው ተገጠመለታቸው፡-

ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡
***************
ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ፡፡
በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ
ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡
ምኒሊክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ
ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ፡፡
አባተ በመድፉ አምሳውን ሲገድል
ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል
የጎጃሙ ንጉስ ግፋ በለው ሲል
እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሀን
ዳዊቱዋን ዘርግታ ስምዓኒ ስትል፡፡
ተማራኪው ባዙቅ ውሃ ውሃ ሲል
ዳኛው ስጠው አለ ሠላሳ በርሜል፡፡
እንደ በላኤ ሰብዕ እንደመቤታችን
ሲቻለው ይምራል የኛማ ጌታችን
መድፉን መትረየሱን ባድዋ መሬት ዘርቶ
እንክርዳዱን ነቅሎ ስንዴውን ለይቶ
የተዘራውን ውል አጭዶና ወቅቶ
ላንቶኔሊ አሳየው ፍሬውን አምርቶ
እንፋቀር ብሎ ለምኖ መሬት
ንግድ ሊያሰፋበት ሊዘራ አታክልት
እያመጣ ሊሰጥ ግብሩን ለመንግስት
ለጉዋዙ ማረፊያ አገር ቢሰጡት
ተጠማኝ ሰንብቶ ሆኖ ባለ ርስት
ወሰን እየገፋ ጥቂት በጥቂት
እውነት ርስት ሆነው ተቀበረበት
ባሕር ዘሎ መምጣት ለማንም አትበጅ
እንደተልባ ስፍር ትከዳለች እንጅ
አትረጋምና ያለ ተወላጅ፡፡
የዳኛው አሽከሮች እየተባባሉ
ብልት መቆራረጥ አድነት ያውቃሉ
አድዋ ከከተማው ሥጋ ቆርጠው ጣሉ፡፡
የእስክንድር ፈረስ መቸ ተወለደ
የሚኒሊክ ፈረስ በክንፎቹ ሄደ
ደንገላባ ሲዘል እየተጓደደ የሮማውን ኩራት በእግሩ አሰገደ
አገርህን ሚኒሊክ እንዳሁን ፈትሻት ባያይህ ነውና ጠላትህ የሚሻት
እጁን ቀምሼ አላውቅ እያለ ሲያማህ
ቀመሰና እጅህን መጥቶ ጠላትህ
ሮም ላይ ተሰማ ለጋስ መሆንህ፡፡

(ምንጭ: This day in Ethiopian History facebook page)

አድዋ! 121 ዓመት!

“… የተተከለው ድንኳን ሲታይ ከብዛቱ የተነሳ አፍሪካ ኤሮጳን ለመጠራረግ የተነሳች ይመስላል፡፡ የጦርነቱ ዕለት ኢትዮጵያውያኑ ደማቅ ቀለም ያለው ካባ ለብሰው፤ ጠመንጃና ጦር ይዘው፤ ጎራዴ ታጥቀው፤ የነብር ያንበሳ ቆዳ ለብሰው፤ አዝማሪዎቹ እየዘፈኑ፤ ቄሶች፤ ልጆች፤ ሴቶች ሳይቀሩ ፀሐይዋ ፈንጠቅ ስትል በተራራው ላይ በታዩ ጊዜ የኢጣሊያን ክፍል አሸበሩት” የበርክለይ ምስክርነት፤ አጤ ምኒልክ በጳውሎስ ኞኞ፤ ገጽ 195

eth at adwaጽሁፎቹ ከዚህ በፊት ካተምናቸው የተቀናበሩ ናቸው፡፡


ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Politics, Social Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Tariku says

    March 2, 2017 11:05 am at 11:05 am

    It is an object lesson for this generation that is under brutal foreign-installed Tigre occupation. United, Ethiopians could obliterate this loathsome enemy in a day.

    The wayward Oromo opposition, has every opportunity to redress its grave errors of the past. Its alliance with the TPLF fascists to carry out a spate of systematic massacre of innocent, unarmed and unsuspecting Amaras rea,l or imagined cannot be forgotten.

    The existential threat staring our country, can be removed with or without any intervention as the extremely wicked and corrupt Tigre regime is imploding.
    However, a coordinated armed struggle of Amaras and Oromos would make the effort decisively a brief affair, That Amaras in the north have started the war of liberation in earnest, is encouraging.

    Reply
  2. Tesfa says

    March 3, 2017 12:36 am at 12:36 am

    መቸውንም ቢሆን የወያኔን እይታ ለይቶ ማወቅ ጭራሽ አይቻልም። Tigrai online የተሰኘው አፍቃሪ ወያኔ ድህረ-ገጽ “አዲሱ ትውልድ ውሽት የሆነውን ምኒልክ ነክ ታሪክ በመተው ወደ አዲሱ የታሪክ ምዕራፍ እንዲሸጋገር በማተተ፤ አጼ ምኒሊክን ያጣጥላል። ያው ውሻ በበላበት ይጮሃልና በመሆኑ ከዘረኛ አስተሳሰብ ሃረግ አይመዘዝም። በአንጻሩ የመቀሌው አለቃ አቶ አባይ ወልድ ስለአድዋ የተናገሩትን (በአማርኛ) ላዳመጠ ግራ ያጋባል። ግን እሳቸው ናቸው ሌላ የሚናገረው አስብሎኛል። አላመንኩምና! አቶ አባይ ወልድ እውነቱን ከአለፈ ታሪክ ጋር በማገጣጠም ያስተላለፉት መልዕክት ለእኔ ተስማምቶኛል። አንዲት ሃገር የሚገነባና የሚያስተዳድር የህዝብ ድልን ማናናቅ የለበትም። በመሆኑም አድዋ የጥቁር ህዝቦች ኩራት፤ የኢትዮጵያዊያን ዘርና ወገን ሳይለይ የተገኘ የድል ውጤት ናት! በአምባዋና በተራሮቿ ሥር ደማቸው የፈሰሰው የሃገራችን ህዝቦች ለዘርና ለጎሳ ስልፈኞች አልነበሩም። የውጭ ጠላትን የመከቱት በአንድነት አብረው ነበር። አሁን ከ121 ዓመታት በህዋላ እኔ አማራ አንተ ኦሮሞ ሌላው ሌላ እያልን እንደ እንስሳት የዘር ስርቻችንን ስንፈልግ አለም ጥሎን ተመነጠቀ።
    አሁን ወያኔ በአመቻቸው የዘር አጥር ውስጥ ሆነን የውጭ ወራሪ እንደገና አድዋን ቢወር ዝም እንል ይሆን? የእኔ ክልል ሰላም ነውና አድዋ የትግሬ ናት በማለት የወያኔን የሙታን የማላዘኛ ፓለቲካ ተቀብለን የትግራይ ህዝብ በጠላት ሲወረር እኔ ምን አገባኝ እንል ይሆን? ፈጣሪ ይህን አስተሳሰብ ከልባችን ያርቀው። ትግራይ ሃገራችን ምድራችን፡ ህዝቡም ወገናችን! ዛሬም እንደጥንቱ ስንቅ ቋጥረን በየቦታው እንሞታለን እንጂ!! ወያኔ ቀን እያለ ቢነቃ ይሻለዋል። ይህ በዘር ሰውን የማሰልፍ ነገር ሁላችንንም አይነስውር ያደርጋል። በየበረሃው ላመኑበት ነገር የተሰውትን፤ የቆሰሉትንና ዛሬም በህይወት ያሉትን የትግራይ ልጆች ደም ያረክሳል። ሰው ላመነበት ሲሞት ክብር ነው። በመጨረሻም ከዶ/ር አረጋዊ በርሄ መጽሃፍ “A political history of the Tigray people’s liberation front (1975-1991) መጽሃፉን ለማስታወሻነት “Dedication” ላይ የጻፉትን በመጥቀስ ስለአድዋ ከጻፉኩት አጭር ግጥም ጋር እሰናበታቹሃለሁ። “To the memory of Ato Gessesew Ayele (Sihul) and all those who died struggling for the cause of social justice, equality and a brighter future for Ethiopia”. Thank you Dr. Berhe – Indeed, a bright future is what we seek for our people and country!

    አድዋ ዝምታሽ ይብቃ
    ተራሮችሽ ይናገሩ
    ሰማይ አጥናፉ መለከትን ይንፉ
    ሜዳው ዳገቱና ቁልቁለቱ አፍ ይሁኑሽ
    እማኝ ሆነው ለዛሬው ትውልድ
    ይመስክሩ
    እጅና እግር አውጥተው ይሩጡ
    የምስራችን ይናገሩ
    አድዋ የጀግኖች አምባ
    የወራሪ የመቃብር ስፍራ
    አድዋ የጥቁር ህዝቦች መኩሪያ
    ሰሜናዊቷ ኮከብ የሃገር ሃብት አድዋ
    አፍ አውጥተሽ ተናገሪ
    የዛሬውን ዘረኛ አሳፍሪ
    ያኔ የሞቱልሽን አወድሺ
    አድዋ የጥቁር ህዝቦች የደል አርማ!!
    ተስፋ በጊዜው
    ነሃሴ 23 2009

    Reply
  3. Tadesse says

    March 4, 2017 01:37 am at 1:37 am

    Through out the struggle,I have believed and stayed Ethiopian,what we have been reading directed us to think so,I didn’t even believe in separation.Cry Freedom/Steven Biko.

    Reply
  4. Mulugeta Andargie says

    March 6, 2017 01:38 am at 1:38 am

    Guys!!! Some people are bluffing out of article. Adwa is in Tigrai. Without Tigrai talking about Adwa is just simply, would be odd. But those who wrote about that event are left argumentative or additional or important things missed and erased. Those things led us to tribal or hidden reasons to the current generation. Adwa is a historical place!!! The writers are left a bitter or a scar points with their pen and taught the youth. It has to be corrected!!! The cause of the war, the outcome, the useful and the disadvantageous and so on, and so on. Let it be revised.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule