• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አዲስ አበባ ተቆላልፋለች

October 6, 2016 08:23 am by Editor 3 Comments

ወቅታዊ ሪፖርታዥ

በሳምንቱ መግቢያ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ብሄራዊ እርቅ እና ድርድር እንዲደረግ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። አምስቱ የሕወሃት ቁንጮዎች ትእቢት የተሞላበት ምላሽ ነው የሰጡት። ከድርድር ይልቅ ከሕዝብ ጋር ጦርነት መግጠምን መርጠዋል።

አብዛኛው የፖሊስ እና የሃገር መከላከያ ሰራዊቱ “ሕዝብ ላይ አልተኩስም” ማለታቸው የህወሃት አመራርን ጭንቅ ውስጥ አስገብተውታል።

አዲስ አበባ ተቆላልፋለች። በአራቱም አቅጣጫ በኩል የሚገባም የሚወጣም የለም። መንገዶች በሙሉ ተዘጋግተዋል። ስልክ እና ኢንተርኔት ጠፍቷል።enat-bank

በአዲስ አበባ ዙርያ ባሉ ከተሞች ሰኞ መስከረም 23 ቀን የተጀመረውን ሕዝባዊ አመጽ ለማዳፈን በህወሃት የተወሰደው የአፈሳ እርምጃ አመጹን አላቆመውም። ሰኞ ማምሻውን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ታፍሰው ወዳልታወቀ ስፍራ በመወሰዳቸው ሳብያ አመጹ በዛሬው እለት ተባብሶ ቀጥሏል። የአካባቢ ፖሊሶችም ከሕዝብ ጋር በመሆን በአመጹ እየተሳተፉ በመሆኑ የስራአቱን ቁንጮዎች ጭንቀት ውስጥ ከቷቸዋል።

ሰበታ ላይ የነበረው የቱርክ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ እና የሃይል ማመንጫ ኩባንያ በትናንትናው እለት መውደሙን ሮይተርስ ከስፍራው ዘግቧል። በሆለታ በነበረው አመጽ ሚስ ሻሮን ሬይ የተባለች አሜሪካው የግብርና ኤክፐርት መገደልዋንም ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቦ ነበር። ይህ ዜና በአለም የመገናኛ ብዙሃን ከተሰማ በኋላ ህወሃት የስልክ እና የኢንተርነት አገልሎት እንዲቋረጥ አድርጓል። የአመጹ ዜና ወደ ሌሎች እንዳይሰራጭ ታቅዶ የተደረገው  ይህ ድርጊታቸው የህዝብን ቁጣ እያበረታው መጥቶ ካድሬዎችን እየለቀሙ መምታት እንዲጀመር አስተዋጽኦ አድርጓል።

ሕዝብ በጋራ ተነስቶ የህወሃት ተላላኪዎችን እያስጠነቀቀ ሲሆን እንቢ ያሉት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገናል። የወንጂ ስኳር ፍብሪካ ከፉተኛ ቃጠሎ የደረሰበት ሲሆን፣ ኩሪፉቱ የሼክ አላዓሙዲን የከብት ማድለቢያ ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። በቀርሳ ወረዳ አንድ የህወሃት ተላላኪ alem-genaበህዝብ ተገድሏል፣ በሆሮ ጉድሩ እና በጉጂም የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ላይ ሕዝብ እርምጃ ወስዶባቸዋል። በድሬ ዳዋ ዲፖ ጋዝ ስቴሽን በእሳት ጋይቷል።

የናይጄሪያዊው ኪሎ ዲንጎቴ ንብረት የነበረው ዲንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ  ሙሉ በሙሉ በህዝባዊ አመጽ መውደሙን የአፍሪካ ሜድያ ኔትወርክ ዘግቧል። ጉጂ ዞን ያለው የሼክ አላሙዲን የወርቅ ማእድን በትላንትናው እለት መውደሙን ማህበራዊ ድረ-ገጾች ዘግበዋል።

ባዶ እጁን እየወጣ ሲገደል የነበረው የኦሮሞ ሕዝብ አሁን ራሱን ራሱን የሚከላከልበት መሳርያ እየያዘ  መውጣቱን የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ። በአለም ገና ዳሽን ባንክ እና ከገዥው ፓርቲ ጋር ንክኪ ያላቸው መኪናዎች ተቃጥለዋል።

በአርሲ፣ በመቱ እና በጂማ በተማሪዎች የተቀሰቀሰው አመጽ እንደቀጠለ ነው። የጅማ ወህኒ ቤት ተቃጥሎ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ እንዲፈቱ የተደረገው ትላንት ምሽት ላይ ነበር።

አዲስ አበባ ከእሬቻው እልቂት በኋላ የሙት ከተማ መስላለች። የንግድ እንቀስቃሴ በሙሉ ቆሟል። ሱቆች ዝግ ናቸው፣ የህዝብ ትራንስፖርትም የለም። መርካቶም ጸጥ-ረጭ እንዳለች ነው። በዛሬው እለት ታክሲ በከተማዋ ባለመኖሩ አብዛኛው ሰው ስራdangote-cement አልገባም። ከተወሰኑ የግል ትምህርት ቤቶች  በስተቀር የመንግስት ትምህርት ቤቶች አሁንም ዝግ ሆነው እንዲቆዩ ተወስኗል። አንዳንድ የግል ት/ቤቶች ወላጆችንን  ልጆቻቸውን ወደ ት/ቤት  እንዳይልኩ እየመከሩ ይገኛሉ።

ለአዲስ ተማሪዎች ጥሪ ያደረገው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ነው። ሌላዎቹ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ተማሪ ገብቶ የመማሩ ጉዳይ የሚታሰብ አይደለም።

በደቡብ ወደ ሻሸመኔ እና ወደ አዋሳ የሚወስደው መንገድ እሁድ ጀምሮ ዝግ ነው። በሰሜን ሱልልታ፣ ለገዳዲ፣ ቦሌ ቡልቡላ፤ በም እራብ በአስኮ፣  በቡራዩ፣  ሰበታ፣ አለምገና፣ ብስራተ-ገብሬል፣ አየር ጤና፣ ወሊሶ፣ ወደ ሆሳዕና እና ጅማ የሚወስዱ መንገዶች በሙሉ ተዘግተዋል። በዚያ የሚተላለፍ ተሽከርካሪ ቢገኝ የድንጋይ ናዳ ይወርድበታል።

አጋዚ ይህ ሕዝባዊ አመጽ ከቁጥጥር ውጪ ስለሆነበት አዲስ አበባን ብቻ ከብቦ እየጠበቀ፣ ንጹሃን ዜጋን በማፈስ ስራ ላይ ተጠምዷል።

agaziህወሃት በአማራው ሕዝብ ላይ በይፋ ያወጀው ጦርነት አልተሳካም። ራሱን ከመከላከል አልፎ አካባቢውን ከአጋዚ ነጻ እይደረገ ይገኛል። በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ከእስር ነጻ ወጥተዋል። የባህርዳር ዩንቨርስቲ እስካሁን እንደተከበበ ነው። የኮሶበር ህዝብ የዳሽን ቢራን ጭኖ የነበረ ከባድ መኪና ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል።

በባህር ዳር ወጣቶችን ሲያሰቃይ የነበረ የማንኩሳ ተወላጅ ማንነቱ ባልታወቀ አካል ተገድሎ መገኘቱ በማህበራዊ ድረ-ገጽ ተዘግቧል።

የህወሃት ባለስልጣናት አሸንዳን በርችት፣ እሬቻን በጥይት ካስተናገዱ በኋላ በወገን ላይ በደረሰው አሰቃቂ እልቂት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ብሄራዊ ሃዘን ላይ ነበር።

ብሄራው ሃዘን ላይ የነበረው ህዝብ ወደ ብሄራዊ አመጽ የገባ ይመስላል። ሰላማዊ ሕዝብን እንደ ግራዚያኒ፣ እንደ ሞሶሎኒ በጥይት እና በመርዝ ጭስ ከጨረሱ በኋላ በቴሌቭዥን ወጥተው አዝነናል እያሉ፣ ቁስልን የባሰ ሲነካኩበት ከዚህ ውጭ አማራጭ የለም። ሕወሃቶች ይልቁንም ለራሳቸው ይዘኑ። ሰላማዊውን ህዝብ እየጨረሱ ያሉት ሁሉ በተራቸው የሚያለቅሱበት ግዜ ሩቅ አይደለም። በደም የታጠበ እጃቸው ገና ሳታደርቅ በቴሌቭዥን ወጥተው በሟች አጽም ላይ መቀለዳቸው ሳያንስ በተለመደ የሽብርተኞች ዲስኩር ህዝብ ላይ እጅ መቀሰር ድፍረት ነው።hawassa

ግዜ ሊወስድ ይችል ይሆናል እንጂ  እነዚህ ነብሰ-ገዳዮች የእያንዳንዱ ነብስ ዋጋ መክፈላቸው አይቀሬ ነው።

የቢሾፍቱው ግድያ የህወሃት “ጥልቅ ተሃድሶ” ጅማሬ መሆኑ ነው። ግን ህዝብን እየረገጡ ብዙ ሊዘልቁ አይችሉም። ፍም እሳት የሆነ የአመጽ ትውልድ ተፈጥሯል። እነሱ ባሰሩ እና በገደሉ ቁጥር ሚሊዮን ሆኖ የሚነሳ ትውልድ። ምንም ነገር ሳይዝ በድምጹ ብቻ የሚያስፈራ ትውልድ። ህዝብን ጠላት አድርጎ ለመግዛት የሚሞክር ስርዓት ይህንን ሁሉ ህዝብ ከቶውንም ገድሎ ሊጨርስ አይችልም።

ክንፉ አሰፋ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Politics Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Lemma says

    October 6, 2016 06:06 pm at 6:06 pm

    ፍም እሳት የሆነ የአመጽ ትውልድ ተፈጥሯል። እነዚህ ነብሰ-ገዳዮች የእያንዳንዱn ነብስ ዋጋ መክፈላቸው አይቀሬ ነው!!!!

    Reply
  2. Admasu Dua says

    October 6, 2016 10:33 pm at 10:33 pm

    Nice!

    Reply
  3. Tesfa says

    October 7, 2016 03:26 pm at 3:26 pm

    ብየ ነበር…
    አይመችም ሰውን በዘር ማሰለፍ
    አሸንዳን በርችት
    እሬቻን በጥይት መቀበል
    በጎሳና በዘር እየለዩ እሳትን መለኮስ
    ብየ ነበር
    ሃገር ሃገር አትሆንም ተሰምራ በክልል
    መስሎን እንጂ የመጠቅን የሰለጠን
    የክልላችን አለቆች፤ እኛው በእኛው ተዳዳሪዎች
    የራሳችን እድል በራሳችን ወሳኞች
    ያፈራነውን ፍሬ ቀማሾች
    በቋንቋችን የኮራን
    የክልል ሰንደቃችን ከፍ ያረግን
    በልተን ለበላተኛ የምናካፍል
    በእጃችን የቀረውን ስናይ
    የተቸረን ፍርፋሪ እንጂ
    ያመረትነው ምርት አይደለም።
    እፎይ ብለን በዘራችን በቋንቋንች ስንኩራራ
    ቀኑ መሽቶ ነግቶልን ብንነቃ
    አገኘነው የዘር አሰላለፋችንን
    ሆኖ የልጆች ጫዋታ
    ያደረ እንጀራ ቁርስርስ
    የቆመ ነገር ፍርስርስ።
    እኔስ ብየ ነበር አይጠቅመንም
    ብሄራዊነት የለሌው ሰልፋችን
    ካለፈ ታሪክ ለማይማር
    እንደ ወያኔ ላለ ግራዚያኒ
    መጠቀሚያ መገልገያ
    የግዛት ዘመናቸው ማራዘሚያ
    ብልሃታቸው እኛኑ መከፋፈል በዘር በጎሳ ማሰለፍ
    ማተራመስ፤ የዘር ቁማር መጫወት።
    ሲጨንቃቸው ጊዜ ሲጨልምባቸው
    አሁን ደግሞ ይሉናል
    ጥልቅ ተሃድሶ ያሻናል
    የህዝብ ድምጽ ሰምተናል
    እስራቱ፤ ግድያው፤ አፈናና ዘርፊያው ይቀጥላል
    በማለት ቁማር ይጫወቱብናል።
    ግን በየ ነበር…. ሲፈራርሱ
    ሃገሪቱን ከላይ እስከ ታች በእሳት ሲለኩሱ
    ያለ የሌለውን ይዘው ሲኮበልሉ
    እኛም እንደ እነርሱ ያዘው ጥለፈው
    ከማለት እንድንቆጠብ፤
    የርስ በርስ ደም ማፋሰስ እንዲቆም
    አሁን ነው ጊዜው ህዝባችን የምንመክረው
    ራሱን እንዲከላከል፤ ወዳጅ ጠላቱን ለይቶ
    እሳትን በእሳት ፈትኖ
    ደም አፍሳሽን ተጋፍጦ
    የዛሬውን ገራፊ
    ህዝባችንን አስለቃሽ
    በተራው እንዲያለቅስ
    የቢሾፍቱው ብሄራዊ ሃዘናችን
    ህቡእና ግልጽ የሆነ አመጻችን
    አመድ እንዲያደርግ የዘርና የጎሳ አሰላለፋችን
    ብየ ነበር አይጠቅመንም የተናጠል ሩጫ
    ህብር ያልሆነ ፍርጥጫ፤
    ያደርገናል መሳቂያ
    ለጠላቶቻችን ማላገጫ
    ለስልጣን ጥመኞች መሰንበቻ።
    ተስፋ በወቅቱ
    መስከረም 26 2009
    አሜሪካ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule