
“አብርሃ ደስታ ሆይ!”
ጃዋር በኦነግ የፊደል መማርያ ማደጉን እና አንተም በወያኔ የጥላቻ መማርያ ደብተር ማደግህን ለዛሬ የተበረዘ አስተሳሰባችሁ አስተዋጽኦ ቦኖረውም (ለዛወም ይሆናል “ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦሮሚያ” ብሎ ጃዋር ሲል ፖለቲካው ይመቸኛል ያልከው) ትንሽ ስታድግ አክራሪ ብሔረተኛነትክን ትንሽም ቢሆን ማሻሻል ነበረብህ። ሆኖም ፈቀቅ አላልክም። አፈር በል! በፖለቲካው እየሸበትክ ስትመጣ “ሰከን ስትል” የኋለ ኋላ የምትናገራቸው ነገሮች መልሰው ይከነክኑሃል።
አብርሃ ደስታ ዞሮ ዞሮ የወያኔ ጀሌ ነው እያልን ስንናገር፤ ብዙ ሰዎች አላመኑም ነበር። ጀሌ ማለት የግድ አባል መሆን ማለት አይደለም። ድሮ የተከናነበበትን ማጃጃያ ነጠላውን ጥሎ ዛሬ በግልጽ ስለወያኔዎች ወንጀለኞች ጥብቅና ቆሞ እየተከራከረ ነው። ድሮም ዛሬም ከወያኔ የተደመረ እንጂ ከወያኔ የተለየ ሰው አልነበረም ብለናል።
ዛሬ አብርሃ ደስታ ጀሌነቱን ለማሳየት በግልጽ በሚጽፋቸው ጽሑፎቹ የወያኔ ወንጀለኞች ሲከላከልላቸው ታያላችሁ። ወያኔ በፋሺዝም ርዕዮት የተመራ የፋሺስት ድርጅት ነው ብለን ብዙ ጩኸናል። ያውም አንዳንዶቹ የስድብ ደብዳቤ ሁሉ ጽፈውልኛል። አንዳንዶቹ የነፃ ሚዲያ ብለው ራሳቸውን በከንቱ የሚያወድሱ “የሚዲያ አምባገነኖች እና ቡድንተኞች” ሳይቀሩ ስለ አብርሃ የምንጽፈውን አፍነውታል። ሓፍረት አያውቁም እንጂ ማፈር በተገባቸው፤ ይቀርታም በጠየቁን ነበር። ከነፈሰው ጋር ስለሚነፍሱ ለይቅርታ አልታደሉም። ዛሬ እነ አብርሃ በፋሺስቶች የፖለቲካ ጡጦ እየጠቡ በማደጋቸው ዛሬም የፋሺስቶቹን ቁንጮ መለስ ዜናዊን እንደ … እንደ ወንድም… እንደ…. ያከብረዋል። በሂትለር የተጎዱ አይሁዶች አንድ አይሁድ አሂትለርን እንደ ወንድሜ እንደ..አከብረዋለሁ የሚል ሲሰሙ የሚሰማቸው ስሜት ምን እንሚመስል እናንተው ፍረዱ። አብርሃ ደስታ ድሮም አክራሪ ብሔረተኛ ነበር፡ ዛሬም ስለ ወያኔዎች ጥብቅና በመቆም እንዲህ ይለናል፤ ልጥቀስ፦
“…(ህወሓት) ወደ ድሮ መጥፎ ማንነቷ ተመልሳ በትግራይ ህዝብ ስም እየነገደች የባለስልጣናትን ኪስ መሙላት ነው። ህወሓት አሁንም ለትግራይ ህዝብ ጥቅም ሳይሆን ለስልጣኗ እንደምትቆም እያስመሰከረች ነው” ይላል።
ህወሓት በሕገ ወጥ የባለሥልጣናቶቿን ኪስ ስትሞላ እንደነበረች እየነገረን፤ ዛሬም ለሥልጣኗ እንደምትቆም እየነገረን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በሕዝብ የሚፈለጉ ወንጀል የፈጸሙ ፥ ሲገርፉ፥ ሲገድሉ፥ ሲዘርፉ፥ ሕዝብ ከሕዝብ ሲያባሉ እና ሲጨፈጭፉ የነበሩ የህወሓት ባለሥልጣኖች እና ተባባሪዎቻቸው፥ እንዲሁም ሥልጣን ተጠቅመው የባለሥልጣኖቹን ኪስ ሲሞሉ የነበሩ የህወሓት ባለሥልጣናትን ለጥያቄ ሕግ ሲፈልጋቸው (የሚፈልጋቸው ከሆነ) አብርሃ ደስታ እየነገረን ያለው በትግርኛው ጽሑፉ አሕሊፍና አይክንህቦምን፤ ክገዝኡና ግን አይክነፍቅደሎምን (አሳልፈን አንሰጣቸውም ሊገዙን ግን አንፈቅድላቸውም) ይላል። ይህ ምን ማለት ነው? የህወሓት መሪዎች በሕግ ከተፈለጉ ወደ ሕግ እንዳይቀርቡ እንከላከልላቸዋለን። አሳልፈን ለሕግ አንሰጣቸውም ማለት ነው።
ይህንን በሕግ ትንታኔ የወንጀለኞች /ተፈላጊዎች አባሪ/ደባቂ/ተባባሪ/ተከላካይ ነው በሚል ይተረጎማል (ሌላ ጋር ቢሆን ኖሮ ‘ሕግን በማደናቀፍ/በኢንተርፈራንስ/ ያስከስሳል)። ይህንን በስነ ልቦና ብንመለከተውም፤ አብርሃ ደስታ አክራሪ ብሔረተኛ መሆኑን በግልጽ ማየት እንችላልን። አክራሪ ብሄረተኛነት ደግሞ በሰዎች ላይ የሚያስከትለው ስነልቦናዊ ለውጥና የሚፈጥረው ተፅዕኖ እጅግ ክፉ ስለሆነ የተማረም ያልተማረም በአክራሪ የጎሳ ልክፍት ወይንም በአክራሪ የሃይሞኖት ልክፍት የተለከፈ ሁሉ ምንም ቢሆን የገዛ የጎሳ አለቆቹ/የሃይማኖት መሪዎቹ በሌሎች ላይ ለፈጸሙዋቸው ወንጀሎች ሌላ አካል በሕግ ሊጠይቅ የሚመጣውን ክፍል አሳልፈው ሊሰጡዋቸው አይፈልጉም። “ምክንያቱም ሕሊናቸው የተቀረጸው “በባዕድ እና በወገን” ወይንም ‘በኛ እና በእነሱ’ የሚል ክፍተት/አጥር ስለሚፈጥሩ ነው።
ትግሬው አብርሃ ደስታ በዚያ በጎሳ አጥር ተንጠልጥሎ እየነገረን ያለው ወያኔዎች “የፈለገው ወንጀል ቢፈጽሙም በኔ ላይም ድብዳበ እና እስራት ቢፈጽሙም የህወሓት መሪዎች “የኛ” ስለሆኑ ለሌሎች አሳልፈን አንሰጣቸውም” ነው እያለን ያለው። የአብርሃ ደስታ ቀጥተኛ ትርጉም *ምንም ቢሆን ቢደበድበኝም፤ ሌላ ሰው ደብድበሃል ተብሎ በሕግ ቢጠየቅም “አባቴ ነውና አሳልፌ አልሰጠውም”። ምንም ብትበድለኝም “እህቴ ናት እና ለሌላ አሳልፌ አልሰጣትም።” የሚለው ቀጥተኛ ትርጉም ተያያዥነት አለው። “በሰብኣዊ መብት ረጋጣ እና በሥልጣን መማገጥ” የኢትዮጵያን ሕዝብ ያስለቀሱ (አብርሃንም ጭምር ያስለቀሱ) ወንጀለኞችን ለጥያቄ ሲፈለጉም አሳልፈን አንሰጥም ብሎ ለወንጀለኞች ‘መከላከል’ የምሁርነቱን ብስለት ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ቢሆንም፤ በዋናነት ግን አክራሪ የጎሳ ባሕሪው ጎልቶ የሚያሳይ አባባል ነው። “አሳልፈን አንሰጣቸውም እንዲገዙን ግን አንፈቅድላቸውም” ማለት የአብርሃ ደስታ አክራሪ ብሔረተኛነት አስቀድማችሁ ስትጠራጡ ለነበራችሁ ሁሉ ዛሬ የዚህ ልጅ ብልሹ ሕሊና ኮለል ያለ ስዕል እንድታዩ የረዳችሁ ይመስለኛል። የትግራይ ብሔረተኞች ማፈሪያዎች ናቸው ብየ የምከራከረውም ለዚህ ነው።
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
አብርሃ ደስታ በወያኔ የታገተ፤ቤቱ የተበረበረ፤ እቃው የተዘረፈ፤ የሌሎች ወገኖቹን ስቃይ በዓይኑ የመሰከረ ሰው ነው። አሁን እንሆ አዲስ ጭንቅላትና ሳንባ ተገጥሞለት የወያኔን ከበሮ መደለቁ እንግዳ አይሆንም። በፊትም ተዳፍኖ የነበረ እይታው ሊሆን ይችላልና! የዘር ተሰላፊዎች ዋናው ችግር ከአፍንጫቸው ራቅ ያለ አስተሳሰብ የሌላቸው ጠባብ ጎጠኞች መሆናቸው ነው። ትውልድ የትውልድን ሃሳብ ይሽራል። የተመሪ ተመሪ መሆን ግን እንዴት ያሳዝናል። “አሳልፈን አንሰጣቸውም፡ እንዲገዙን ግን አንፈቅድላቸውም” ማለት በራስ ላይ መቀለድ ይመስለኛል። አንተና የኢትዮጵያ ህዝብ ፈቅዶ አይደለም ወያኔ 27 ዓመት ስልጣን ላይ ያለው። በጠበንጃ ሃይል እንጂ! ዛሬም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ገዢው ወያኔ ነው። አብርሃ ደስታ መቀሌ ላይ ተቀምጦ እንዲገዙን አንፈቅድላቸውም ማለቱ ተንጋለው ቢተፉ ተመልሶ ታፉ እንደማለት ነው። አብርሃ ደስታ ስለትግራይ የቴሌቪዝን አስተዳዳሪ በቅጥፈት ከሥራ መባረር ምን ይላል? የትግራይ ፓሊሶች ተፈላጊውን የቀድሞ የስለላ ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋን ወደ ሱዳን ማሻገራቸውንስ ምን ይላል? በቅርቡ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ከቀናት መታገት በህዋላ ስለተመለሱት ልዮ ወታደራዊ ሃይል ምን የሚለው አለ? ጌታቸው አሰፋን ለመያዝ የተላኩ ይሆን? መቀሌ የወያኔ የዘራፊዎችና የደም አፍሳሾች ምሽግ መሆኗ እየታወቀ ተምሬአለሁ የሚለው አብርሃ ደስታ ዛሬም በዘሩ ዙሪያ መሰለፉ ምን ያህል የዘር ፓለቲካ በሃገራችን መሰረት እንደጣለ አመላካች ነው። ኢትዮጵያዊ ሆኖ ኢትዮጵያዊነትን መዘከር ወያኔ እርም የሆነበት የጥቁር ሃገር የሆነችውን ኢትዮጵያን የቅኝ ገዢነት ባለጸጋ ከሰጣት የጫካ የፓለቲካ ፍልስፍና ጀመሮ ነው። ስለሆነም በአማራም፤ በትግሬም፤ በኦሮሞና በሌሎችም ክልሎች (ክልል የሚለውን ስም እጅግ እጠላዋለሁ) ዘርን ቋንቋን ሌላውንም ጥቃቅን ነገር ተገን በማድረግ ሃተፍተፍ ከማለት ይልቅ ለአንዲትና ሁሉም በኩልነት ለሚኖርባት ሃገር በህብረት እንስራ። አቶ አብርሃ ደስታም በዚሁ ሂሳብ ቢደመሩ ከልምዳቸው ለመላው የሃገራችን ህዝብ የሚጠቅም ሃሳብ ይኖራቸዋል። ይደመሩ!!
ትንሽ ስለ ‘መለሲ-ዝም’: ከኢህአዴጎች የምስማማበት ነጥብ
August 25, 2013 | Abraha Desta from Mekele, Tigrai
ሳስበው ሳስበው ስለ ‘መለሲዝም’ ሰበካ የተጀመረ ይመስለኛል። በመለስ ማመናቸው ችግር የለብኝም። ግን መለስ ፈጣሪያቸው መሆኑ እየነገሩን ነው። ብዙ ነገሮች በሱ ስም እየተሰየሙ ናቸው። እነሱ እንደሚነግሩን ከሆነ የኢህአዴግ ፖሊሲ የመለስ ነው፣ መለስ ወታደራዊ መሃንዲሳቸው ነበር፣ መለስ አንቀሳቃሽ ሞተራቸው ነበር፣ የኢህአዴግ ሓሳብና ተግባር የመነጨው ከመለስ ነበር፣ ባጠቃላይ መለስ ሁለመናቸው ነበር።
ለዚህም ነው የኢህአዴግ አባላት አውቀውም ሳያውቁም መለስ የተናገረውን እንደ ፓሮት የሚደግሙት። በራሳቸው ማየት ሳይችሉ መለስ በመራቸው ይጓዛሉ። ለዚህም ነው መለስ ያወጣውን ፖሊሲ መተግበር የማይችሉ። ፖሊሲው መተግበር ያልቻሉበት መንገድ ማየት ስለሚሳናቸው ፖሊሲው ጥሩ መሆኑ ተናዘው ችግሩ ያለው ግን አፈፃፀሙ ላይ መሆኑ ይለፍፋሉ።
ግን አንድ ትክክል ወይ ጥሩ የሆነ ፖሊሲ እንዴት ላይፈፀም ይችላል? ፖሊሲ’ኮ አፈፃፀም ነው። ፖሊሲ ከህልም የሚለይበት ዋነኛው መስፈርት ስለሚፈፀም ነው። ስለዚህ አንድ ፖሊሲ አፈፃፀም ላይ ችግር ካጋጠመው ፖሊሲው ትክክል አይደለም ማለት ነው። ግን የመለስ ልጆች ‘ፖሊሲው ስህተት ነው’ ብለው የማጋለጥ ዓቅሙና ድፍረቱስ አላቸው? አይመስለኝም። ምክንያቱም ፖሊሲው የመለስ ነው። ፖሊሲው ስህተት እንደሆነ መናገር ማለት መለስ እንደሚሳሳት መመስከር ነው። መለስ ደግሞ ፈጣሪያቸው ነው። ለዚህም ነው ከነ ስህተቱ ‘የመለስ ሌጋሲ ወይ ራእይ’ እያሉ የመለስን የተሳሳተ የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅጣጫ ለማስቀጠል የሚባዝኑ።
ከኢህአዴግ አባላት የምስማማበት ነጥብ አለኝ፤ መለስ ሁለመናቸው ነው። እሱ የተናገረውን ያደርጋሉ፣ ይፈፅማሉ። ከነሱ ጋር የምስማማበት ነጥብ ይሄ ነው። ይሄንን ነጥብ ትርጓሜ እንስጠው።
የኢህአዴግ አባላት (እነሱ ራሳቸው እንደሚነግሩን) መለስ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ዕይታ ምንጫቸው ነው። አዎ! ነው። ይህ ማለት አባላቱ ምን መስራት እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው መለስ ይነግራቸው ነበር ማለት ነው። እነሱም ‘የታላቁ ባለራእይ መሪ’ ትእዛዞች ተቀብለው ይተገብሩ ነበር ማለት ነው።
የመለስና የአባላቱ ግንኙነት እንዲህ ከነበረ መለስ dictate ያደርጋቸው ነበር ማለት ነው። በእንግሊዝኛው አጠራር ሌሎችን dictate የሚያደርግ መሪ Dictator ይባላል። ስለዚህ ከተግባራዊ ትርጓሜው ተነስተን መለስን ስንገልፀው Dictator ነበር ማለት ነው። “Dictator’ ወደ አማርኛ ስንመልሰው ‘አምባገነን’ (ብትግርኛ ‘ዉልቀ መላኺ’) የሚል ትርጓሜ ይይዛል። ስለዚህ ‘ሁሉም ወይም አብዛኞቹ የፓርቲው ስራዎች የመለስ ነበሩ’ በሚል ከተስማማን ‘መለስ አምባገነን ነበር’ በሚልም መስማማት ይኖርብናል።
እኔ ‘መለስ አምባገነን ነበር’ ሲል ‘የሁሉንም አድራጊ እሱ ነበር’ እያልኩኝ ነው። እናንተም በራሳቹሁ ሚድያና አንደበት ተመሳሳይ ነገር እየነገራችሁን ነው። ስለዚህ ሓሳባችን አንድ ነው። ተስማምተናል። በመለስ ስራና ስያሜ ላይ ልዩነት የለንም።
(ስለ መለስ ላለመፃፍ ዕቅድ የነበረኝ ቢሆንም የመንግስት ሚድያዎች ግን ስለሱ እያስታወሱ አስቸገሩኝ)
ለመሆኑ ኣቶ ኣብራሃ ደስታ እሥርቤት ውስጥ የቆየው እውነተኛ እሥረኛ ሆኖ ነው ወይስ ለይምሰል ያህል ነው? ብዙ የይምሰል እሥረኞች መዕከላዊ ውስጥ እንኩዋ እንደነበሩ እውነተኞቹ እሥረኞች ኣረጋግጠው ሲናገሩ እንደነበር ኣይዘነጋም።
እንደሚመስለኝ ሰውዬው ለመሰለል የታሰረ ሊሆን ይችላል ነገር ግን የዘረኝነት ጥንካሬና የጥላቻው ጣራ ለሌሎች ዘሮች ያለው ወያኔ እግሩን ቢቆርጠው እንኳን ኣሳልፎ አይሰጥም ይህ አይነቱ ዲሲፕሊን በኢሕአፓ ኣባላቶች ውስጠሰ የነበረ ቃል ኪዳን ሲሆን ብዙዎቹ አናውቅም ብለው ሞተዋል ። የወያኔም ኣባላት ያላቸው ተመሳሳይ ቃል ኪዳን ነው። ወያኔዎች ሁሉም ወታደርና እራሳቸውን Comrade ብሐው ስለሚጠሩ ኣሳልፈን አነሸሰጥም ቢል ሊደንቀን አይገባም ። የሚያሳዝነው ግን ምንም አይነት ሰብዓዊ ርዕራሄ የሌላቸው ፍጡራን መሆናቸው እየገረመኝ ነው። ከማን ጋር ነው ነኖርነው ለመሆኑ? ከሰው ጋር ወይስ ከወደቁት ጨካኝ መላዕክት ጋር? መልሱን ለአንባቢያን ትቼዋለሁ።
TPLF leaders to much negative thinking is eating into leaders minds. Thry are living in emotional dungeon they don’t even knows what life all about. They are failed and frustrated people. I don’t blame this guy b/c this failure-type symptoms is characterized by indecisivness.