• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አብርሃ ደስታ ስለ ህወሓቶች፤ “አሳልፈን አንሰጣቸውም”

August 22, 2018 04:54 pm by Editor 5 Comments

“አብርሃ ደስታ ሆይ!”

ጃዋር  በኦነግ የፊደል መማርያ ማደጉን እና አንተም በወያኔ የጥላቻ መማርያ ደብተር ማደግህን ለዛሬ የተበረዘ አስተሳሰባችሁ አስተዋጽኦ ቦኖረውም (ለዛወም ይሆናል “ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦሮሚያ” ብሎ ጃዋር ሲል ፖለቲካው ይመቸኛል ያልከው) ትንሽ ስታድግ አክራሪ ብሔረተኛነትክን ትንሽም ቢሆን ማሻሻል ነበረብህ። ሆኖም ፈቀቅ አላልክም። አፈር በል! በፖለቲካው እየሸበትክ ስትመጣ “ሰከን ስትል” የኋለ ኋላ የምትናገራቸው ነገሮች መልሰው ይከነክኑሃል።

አብርሃ ደስታ ዞሮ ዞሮ የወያኔ ጀሌ ነው እያልን ስንናገር፤ ብዙ ሰዎች አላመኑም ነበር። ጀሌ ማለት የግድ አባል መሆን ማለት አይደለም። ድሮ የተከናነበበትን ማጃጃያ ነጠላውን ጥሎ ዛሬ በግልጽ ስለወያኔዎች ወንጀለኞች ጥብቅና ቆሞ እየተከራከረ ነው። ድሮም ዛሬም ከወያኔ የተደመረ እንጂ ከወያኔ የተለየ ሰው አልነበረም ብለናል።

ዛሬ አብርሃ ደስታ ጀሌነቱን ለማሳየት በግልጽ በሚጽፋቸው ጽሑፎቹ የወያኔ ወንጀለኞች ሲከላከልላቸው ታያላችሁ። ወያኔ በፋሺዝም ርዕዮት የተመራ የፋሺስት ድርጅት ነው ብለን ብዙ ጩኸናል። ያውም አንዳንዶቹ የስድብ ደብዳቤ ሁሉ ጽፈውልኛል። አንዳንዶቹ የነፃ ሚዲያ ብለው ራሳቸውን በከንቱ የሚያወድሱ “የሚዲያ አምባገነኖች እና ቡድንተኞች” ሳይቀሩ ስለ አብርሃ የምንጽፈውን አፍነውታል። ሓፍረት አያውቁም እንጂ ማፈር በተገባቸው፤ ይቀርታም በጠየቁን ነበር። ከነፈሰው ጋር ስለሚነፍሱ ለይቅርታ  አልታደሉም።  ዛሬ እነ አብርሃ በፋሺስቶች የፖለቲካ ጡጦ እየጠቡ በማደጋቸው ዛሬም የፋሺስቶቹን ቁንጮ መለስ ዜናዊን እንደ … እንደ ወንድም… እንደ…. ያከብረዋል። በሂትለር የተጎዱ አይሁዶች አንድ አይሁድ አሂትለርን እንደ ወንድሜ እንደ..አከብረዋለሁ የሚል ሲሰሙ የሚሰማቸው ስሜት ምን እንሚመስል እናንተው ፍረዱ። አብርሃ ደስታ ድሮም አክራሪ ብሔረተኛ ነበር፡ ዛሬም ስለ ወያኔዎች ጥብቅና በመቆም እንዲህ ይለናል፤ ልጥቀስ፦

“…(ህወሓት) ወደ ድሮ መጥፎ ማንነቷ ተመልሳ በትግራይ ህዝብ ስም እየነገደች የባለስልጣናትን ኪስ መሙላት ነው። ህወሓት አሁንም ለትግራይ ህዝብ ጥቅም ሳይሆን ለስልጣኗ እንደምትቆም እያስመሰከረች ነው” ይላል።

ህወሓት በሕገ ወጥ የባለሥልጣናቶቿን ኪስ ስትሞላ እንደነበረች እየነገረን፤ ዛሬም ለሥልጣኗ እንደምትቆም እየነገረን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በሕዝብ የሚፈለጉ ወንጀል የፈጸሙ ፥ ሲገርፉ፥ ሲገድሉ፥ ሲዘርፉ፥ ሕዝብ ከሕዝብ ሲያባሉ እና ሲጨፈጭፉ የነበሩ የህወሓት ባለሥልጣኖች እና ተባባሪዎቻቸው፥ እንዲሁም ሥልጣን ተጠቅመው የባለሥልጣኖቹን ኪስ ሲሞሉ የነበሩ የህወሓት ባለሥልጣናትን ለጥያቄ ሕግ ሲፈልጋቸው (የሚፈልጋቸው ከሆነ) አብርሃ ደስታ እየነገረን ያለው በትግርኛው ጽሑፉ አሕሊፍና አይክንህቦምን፤ ክገዝኡና ግን አይክነፍቅደሎምን (አሳልፈን አንሰጣቸውም ሊገዙን ግን አንፈቅድላቸውም) ይላል። ይህ ምን ማለት ነው? የህወሓት መሪዎች በሕግ ከተፈለጉ ወደ ሕግ እንዳይቀርቡ እንከላከልላቸዋለን። አሳልፈን ለሕግ አንሰጣቸውም ማለት ነው።

ይህንን በሕግ ትንታኔ የወንጀለኞች /ተፈላጊዎች አባሪ/ደባቂ/ተባባሪ/ተከላካይ ነው በሚል ይተረጎማል (ሌላ ጋር ቢሆን ኖሮ ‘ሕግን በማደናቀፍ/በኢንተርፈራንስ/ ያስከስሳል)። ይህንን በስነ ልቦና ብንመለከተውም፤ አብርሃ ደስታ አክራሪ ብሔረተኛ መሆኑን በግልጽ ማየት እንችላልን። አክራሪ ብሄረተኛነት ደግሞ በሰዎች ላይ የሚያስከትለው ስነልቦናዊ ለውጥና የሚፈጥረው ተፅዕኖ እጅግ ክፉ ስለሆነ የተማረም ያልተማረም በአክራሪ የጎሳ ልክፍት ወይንም በአክራሪ የሃይሞኖት ልክፍት የተለከፈ ሁሉ ምንም ቢሆን የገዛ የጎሳ አለቆቹ/የሃይማኖት መሪዎቹ በሌሎች ላይ ለፈጸሙዋቸው ወንጀሎች ሌላ አካል በሕግ ሊጠይቅ የሚመጣውን ክፍል አሳልፈው ሊሰጡዋቸው አይፈልጉም። “ምክንያቱም ሕሊናቸው የተቀረጸው “በባዕድ እና በወገን” ወይንም ‘በኛ እና በእነሱ’ የሚል ክፍተት/አጥር ስለሚፈጥሩ ነው።

ትግሬው አብርሃ ደስታ በዚያ በጎሳ አጥር ተንጠልጥሎ እየነገረን ያለው ወያኔዎች “የፈለገው ወንጀል ቢፈጽሙም በኔ ላይም ድብዳበ እና እስራት ቢፈጽሙም የህወሓት መሪዎች “የኛ” ስለሆኑ ለሌሎች አሳልፈን አንሰጣቸውም” ነው እያለን ያለው። የአብርሃ ደስታ ቀጥተኛ ትርጉም *ምንም ቢሆን ቢደበድበኝም፤ ሌላ ሰው ደብድበሃል ተብሎ በሕግ ቢጠየቅም “አባቴ ነውና አሳልፌ አልሰጠውም”። ምንም ብትበድለኝም “እህቴ ናት እና ለሌላ አሳልፌ አልሰጣትም።” የሚለው ቀጥተኛ ትርጉም ተያያዥነት አለው። “በሰብኣዊ መብት ረጋጣ እና በሥልጣን መማገጥ” የኢትዮጵያን ሕዝብ ያስለቀሱ (አብርሃንም ጭምር ያስለቀሱ) ወንጀለኞችን ለጥያቄ ሲፈለጉም አሳልፈን አንሰጥም ብሎ  ለወንጀለኞች ‘መከላከል’ የምሁርነቱን ብስለት ጥያቄ ውስጥ  የሚገባ ቢሆንም፤ በዋናነት ግን አክራሪ የጎሳ ባሕሪው ጎልቶ የሚያሳይ አባባል ነው። “አሳልፈን አንሰጣቸውም እንዲገዙን ግን አንፈቅድላቸውም” ማለት የአብርሃ ደስታ አክራሪ ብሔረተኛነት አስቀድማችሁ ስትጠራጡ ለነበራችሁ ሁሉ ዛሬ የዚህ ልጅ ብልሹ ሕሊና ኮለል ያለ ስዕል እንድታዩ የረዳችሁ ይመስለኛል። የትግራይ ብሔረተኞች ማፈሪያዎች ናቸው ብየ የምከራከረውም ለዚህ ነው።

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    August 23, 2018 01:26 pm at 1:26 pm

    አብርሃ ደስታ በወያኔ የታገተ፤ቤቱ የተበረበረ፤ እቃው የተዘረፈ፤ የሌሎች ወገኖቹን ስቃይ በዓይኑ የመሰከረ ሰው ነው። አሁን እንሆ አዲስ ጭንቅላትና ሳንባ ተገጥሞለት የወያኔን ከበሮ መደለቁ እንግዳ አይሆንም። በፊትም ተዳፍኖ የነበረ እይታው ሊሆን ይችላልና! የዘር ተሰላፊዎች ዋናው ችግር ከአፍንጫቸው ራቅ ያለ አስተሳሰብ የሌላቸው ጠባብ ጎጠኞች መሆናቸው ነው። ትውልድ የትውልድን ሃሳብ ይሽራል። የተመሪ ተመሪ መሆን ግን እንዴት ያሳዝናል። “አሳልፈን አንሰጣቸውም፡ እንዲገዙን ግን አንፈቅድላቸውም” ማለት በራስ ላይ መቀለድ ይመስለኛል። አንተና የኢትዮጵያ ህዝብ ፈቅዶ አይደለም ወያኔ 27 ዓመት ስልጣን ላይ ያለው። በጠበንጃ ሃይል እንጂ! ዛሬም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ገዢው ወያኔ ነው። አብርሃ ደስታ መቀሌ ላይ ተቀምጦ እንዲገዙን አንፈቅድላቸውም ማለቱ ተንጋለው ቢተፉ ተመልሶ ታፉ እንደማለት ነው። አብርሃ ደስታ ስለትግራይ የቴሌቪዝን አስተዳዳሪ በቅጥፈት ከሥራ መባረር ምን ይላል? የትግራይ ፓሊሶች ተፈላጊውን የቀድሞ የስለላ ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋን ወደ ሱዳን ማሻገራቸውንስ ምን ይላል? በቅርቡ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ከቀናት መታገት በህዋላ ስለተመለሱት ልዮ ወታደራዊ ሃይል ምን የሚለው አለ? ጌታቸው አሰፋን ለመያዝ የተላኩ ይሆን? መቀሌ የወያኔ የዘራፊዎችና የደም አፍሳሾች ምሽግ መሆኗ እየታወቀ ተምሬአለሁ የሚለው አብርሃ ደስታ ዛሬም በዘሩ ዙሪያ መሰለፉ ምን ያህል የዘር ፓለቲካ በሃገራችን መሰረት እንደጣለ አመላካች ነው። ኢትዮጵያዊ ሆኖ ኢትዮጵያዊነትን መዘከር ወያኔ እርም የሆነበት የጥቁር ሃገር የሆነችውን ኢትዮጵያን የቅኝ ገዢነት ባለጸጋ ከሰጣት የጫካ የፓለቲካ ፍልስፍና ጀመሮ ነው። ስለሆነም በአማራም፤ በትግሬም፤ በኦሮሞና በሌሎችም ክልሎች (ክልል የሚለውን ስም እጅግ እጠላዋለሁ) ዘርን ቋንቋን ሌላውንም ጥቃቅን ነገር ተገን በማድረግ ሃተፍተፍ ከማለት ይልቅ ለአንዲትና ሁሉም በኩልነት ለሚኖርባት ሃገር በህብረት እንስራ። አቶ አብርሃ ደስታም በዚሁ ሂሳብ ቢደመሩ ከልምዳቸው ለመላው የሃገራችን ህዝብ የሚጠቅም ሃሳብ ይኖራቸዋል። ይደመሩ!!

    Reply
  2. በለው ! says

    August 24, 2018 11:51 pm at 11:51 pm

    ትንሽ ስለ ‘መለሲ-ዝም’: ከኢህአዴጎች የምስማማበት ነጥብ
    August 25, 2013 | Abraha Desta from Mekele, Tigrai
    ሳስበው ሳስበው ስለ ‘መለሲዝም’ ሰበካ የተጀመረ ይመስለኛል። በመለስ ማመናቸው ችግር የለብኝም። ግን መለስ ፈጣሪያቸው መሆኑ እየነገሩን ነው። ብዙ ነገሮች በሱ ስም እየተሰየሙ ናቸው። እነሱ እንደሚነግሩን ከሆነ የኢህአዴግ ፖሊሲ የመለስ ነው፣ መለስ ወታደራዊ መሃንዲሳቸው ነበር፣ መለስ አንቀሳቃሽ ሞተራቸው ነበር፣ የኢህአዴግ ሓሳብና ተግባር የመነጨው ከመለስ ነበር፣ ባጠቃላይ መለስ ሁለመናቸው ነበር።

    ለዚህም ነው የኢህአዴግ አባላት አውቀውም ሳያውቁም መለስ የተናገረውን እንደ ፓሮት የሚደግሙት። በራሳቸው ማየት ሳይችሉ መለስ በመራቸው ይጓዛሉ። ለዚህም ነው መለስ ያወጣውን ፖሊሲ መተግበር የማይችሉ። ፖሊሲው መተግበር ያልቻሉበት መንገድ ማየት ስለሚሳናቸው ፖሊሲው ጥሩ መሆኑ ተናዘው ችግሩ ያለው ግን አፈፃፀሙ ላይ መሆኑ ይለፍፋሉ።

    ግን አንድ ትክክል ወይ ጥሩ የሆነ ፖሊሲ እንዴት ላይፈፀም ይችላል? ፖሊሲ’ኮ አፈፃፀም ነው። ፖሊሲ ከህልም የሚለይበት ዋነኛው መስፈርት ስለሚፈፀም ነው። ስለዚህ አንድ ፖሊሲ አፈፃፀም ላይ ችግር ካጋጠመው ፖሊሲው ትክክል አይደለም ማለት ነው። ግን የመለስ ልጆች ‘ፖሊሲው ስህተት ነው’ ብለው የማጋለጥ ዓቅሙና ድፍረቱስ አላቸው? አይመስለኝም። ምክንያቱም ፖሊሲው የመለስ ነው። ፖሊሲው ስህተት እንደሆነ መናገር ማለት መለስ እንደሚሳሳት መመስከር ነው። መለስ ደግሞ ፈጣሪያቸው ነው። ለዚህም ነው ከነ ስህተቱ ‘የመለስ ሌጋሲ ወይ ራእይ’ እያሉ የመለስን የተሳሳተ የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅጣጫ ለማስቀጠል የሚባዝኑ።

    ከኢህአዴግ አባላት የምስማማበት ነጥብ አለኝ፤ መለስ ሁለመናቸው ነው። እሱ የተናገረውን ያደርጋሉ፣ ይፈፅማሉ። ከነሱ ጋር የምስማማበት ነጥብ ይሄ ነው። ይሄንን ነጥብ ትርጓሜ እንስጠው።

    የኢህአዴግ አባላት (እነሱ ራሳቸው እንደሚነግሩን) መለስ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ዕይታ ምንጫቸው ነው። አዎ! ነው። ይህ ማለት አባላቱ ምን መስራት እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው መለስ ይነግራቸው ነበር ማለት ነው። እነሱም ‘የታላቁ ባለራእይ መሪ’ ትእዛዞች ተቀብለው ይተገብሩ ነበር ማለት ነው።

    የመለስና የአባላቱ ግንኙነት እንዲህ ከነበረ መለስ dictate ያደርጋቸው ነበር ማለት ነው። በእንግሊዝኛው አጠራር ሌሎችን dictate የሚያደርግ መሪ Dictator ይባላል። ስለዚህ ከተግባራዊ ትርጓሜው ተነስተን መለስን ስንገልፀው Dictator ነበር ማለት ነው። “Dictator’ ወደ አማርኛ ስንመልሰው ‘አምባገነን’ (ብትግርኛ ‘ዉልቀ መላኺ’) የሚል ትርጓሜ ይይዛል። ስለዚህ ‘ሁሉም ወይም አብዛኞቹ የፓርቲው ስራዎች የመለስ ነበሩ’ በሚል ከተስማማን ‘መለስ አምባገነን ነበር’ በሚልም መስማማት ይኖርብናል።

    እኔ ‘መለስ አምባገነን ነበር’ ሲል ‘የሁሉንም አድራጊ እሱ ነበር’ እያልኩኝ ነው። እናንተም በራሳቹሁ ሚድያና አንደበት ተመሳሳይ ነገር እየነገራችሁን ነው። ስለዚህ ሓሳባችን አንድ ነው። ተስማምተናል። በመለስ ስራና ስያሜ ላይ ልዩነት የለንም።

    (ስለ መለስ ላለመፃፍ ዕቅድ የነበረኝ ቢሆንም የመንግስት ሚድያዎች ግን ስለሱ እያስታወሱ አስቸገሩኝ)

    Reply
  3. Mertcha D-Tabor says

    August 31, 2018 12:43 am at 12:43 am

    ለመሆኑ ኣቶ ኣብራሃ ደስታ እሥርቤት ውስጥ የቆየው እውነተኛ እሥረኛ ሆኖ ነው ወይስ ለይምሰል ያህል ነው? ብዙ የይምሰል እሥረኞች መዕከላዊ ውስጥ እንኩዋ እንደነበሩ እውነተኞቹ እሥረኞች ኣረጋግጠው ሲናገሩ እንደነበር ኣይዘነጋም።

    Reply
    • gi Haile says

      November 1, 2018 06:42 pm at 6:42 pm

      እንደሚመስለኝ ሰውዬው ለመሰለል የታሰረ ሊሆን ይችላል ነገር ግን የዘረኝነት ጥንካሬና የጥላቻው ጣራ ለሌሎች ዘሮች ያለው ወያኔ እግሩን ቢቆርጠው እንኳን ኣሳልፎ አይሰጥም ይህ አይነቱ ዲሲፕሊን በኢሕአፓ ኣባላቶች ውስጠሰ የነበረ ቃል ኪዳን ሲሆን ብዙዎቹ አናውቅም ብለው ሞተዋል ። የወያኔም ኣባላት ያላቸው ተመሳሳይ ቃል ኪዳን ነው። ወያኔዎች ሁሉም ወታደርና እራሳቸውን Comrade ብሐው ስለሚጠሩ ኣሳልፈን አነሸሰጥም ቢል ሊደንቀን አይገባም ። የሚያሳዝነው ግን ምንም አይነት ሰብዓዊ ርዕራሄ የሌላቸው ፍጡራን መሆናቸው እየገረመኝ ነው። ከማን ጋር ነው ነኖርነው ለመሆኑ? ከሰው ጋር ወይስ ከወደቁት ጨካኝ መላዕክት ጋር? መልሱን ለአንባቢያን ትቼዋለሁ።

      Reply
  4. gi Haile says

    November 1, 2018 06:30 pm at 6:30 pm

    TPLF leaders to much negative thinking is eating into leaders minds. Thry are living in emotional dungeon they don’t even knows what life all about. They are failed and frustrated people. I don’t blame this guy b/c this failure-type symptoms is characterized by indecisivness.

    Reply

Leave a Reply to gi Haile Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule