• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጅብ በማያውቁት ሃገር ሄዶ ቁርበት አንጥፍሉኝ አለ

October 2, 2016 07:45 pm by Editor 3 Comments

ኢትዮሚዲያ በ26/09/2016 ከግደይ ዘርአፅዮን ጋር ያካሄደውን ቃለ ምልልስ አንብቤዋለሁ። ግደይ ዘርአፅዮንን የማውቀው ገና ትግሉ ሳይጀመር በፊት ነው። ግደይ በጥሩ ቤተሰብ ያደገ ግለሰብ ነው። ትግሉ ሳይጀመር በመስከረም 1967 አዲስ አባባ ውስጥ (ማኅበረ ገስግስቲ ብሔረ ትግራይ) ማገበትን መሰረቱ። የመሰረቱትም አረጋዊ በርሄ፣ ገደይ ዘርአፅዮን፣ አባይ ፀሃየ፣ ሥዩም መስፍን፣ ዘርኡ ገሰሰ፣ ሃይሉ መንገሻና አስፍሃ ሃጎስ ናቸው። ከዚያ በኋላ እነ መለስና ስብሃት ወዘተ ተቀላቀሉ።

ግደይ ስለእኔ፤ ገብረመድህን፤ መስራች አልነበረም ብሎ ነው የተናገረው። ያለው ትክክል ነው፤ እኔ የማገበት – ተሓህት መስራች አልነበርኩም። ማገበት እንደተመሰረተ በተራ አባልነት ተመልምዬ ከማገበት ጀመሮ ትግሉን ለማጠናከር ስንቀሳቀስ የነበርኩ ተራ አባል ነበርኩኝ እንጂ መስራች አይደለሁም። ስለ (ተጋዳሊ ሕዝቢ ሓርነት ትግራይ) ተሕሓት – ህወሓት ማንነትን ግን ከግደይ ዘርአፅዮን ያላነሰ እውቀት አለኝ። ልክ እንደ እኔ፣ በወቅቱ የነበርው ታጋይ የህወሓትን እኩይ ሥራ ያውቃል። የህወሓት አመራር ፀረ-ኢትዮጵያ፣ ዘረኛ፣ የአማራውን ዘር ለማጥፋት የተነሳ ወዘተ መሆኑን አስምሮበት ያለፈ ታጋይ ነው።

በትግርኛ አንድ ተረት አለ። እሱም “መባእያእንዳ አባገሪማ ዝበለእስ ባእሉ ይለፋለፍ” ይባላል። ይህ ማለት፣ የአባ ገሪማ መባእ፣ የሰረቀ ሌባ ራሱ ይናዘዛል እንደማለት ነው።

gebremedhin-araya
አቶ ገብረመድኅን አርአያ

ግደይ ዘርአፅዮን ትልቅ ትኩረት የሰጠው ከኢሳት ሰብአዊ መብት ተሟጋች ESAT Human Rights, May 13, 2016 –May 15, 2016 ባካሄድኩት በሁለት ክፍል ኢሳት ባስተላለፈው ቃለ ምልልስ፣ ስለ 06 ሓለዋ ወያኔ ሁኔታ ነበር። 06 ሓለዋ ወያኔ የገዳይ ማእከል ነው። በዚሁ ቃለ ምልልስ ላይ እኔ ገብረመድህን አርአያ፣ የነበሩ ሓለዋ ወያኔ ብዛት ከመሬት በታች ሁለት ሜትር ተቆፍሮ፣ ነፋስ መግቢያ የሌለው ማጎሪያ ውስጥ ስለተገደሉት፣ ትግሬና አማራ መሆናቸውን በዝርዝር የገለጽኩበት ቃለ ምልልስ ነው። ግደይ ዘርአፅዮን ከኢቲዮ ሚዲያ ጋር ባካሄደው ቃለ ምልልስና በጽሁፍም የተዘረጋው በጣም አናድዶታል፣ ከንክኖታልም። በዚህም ምክንያት ይመስላል ብዙ ስድቦችን አውርዶብኛል።

ግደይ የተናደደበት ዋናው ምክንያት፣ ምስጢራችንን በዝርዝር አውጥቶ አጋለጠን ብሎ ነው። ይህም ይመስላል ወደ ተራ ስድብና ውሸት የከተተው። የትግራይን ሕዝብ አጸያፊ ስድብ ተሳደበ ብሎም ወንጅሎኛል። እኔ ማን ሆኜ ነው የትግራይን ወላጆችና ወንድሞቼን የምሰድበው? ሃቅ ነው ካለስ፣ የተሳደብኩትን ስድብስ ለምን አልተናገረም? ግደይና ግብረአበሮቹ የህወሓት አመራር የትግራይ ሕዝብ ፊውዳል፣ ሸዋዊ አማራ ትግሬ፣ ፀረ-ህወሓት ወዘተ እያላችሁ የገደላችሁት አንተና ጓደኞችህ አልነበራችሁም? እኔ የነበሩትን፣ 06 ሓለዋ ወያነ፣ በነሱ ውስጥም ስንት የሰው ፍጡር፣ አማራና ትግሬ – አማራው በዝቶ የተገደለበት – ቦታዎች መሆናቸውን ነው በትክክል የገለጽኩት። ቅንጣት ውሸት አልጨመርኩበትም። ግደይ ከፈጸመው ወንጀል ነፃ የሚወጣ መስሎታል። እውነት በውሸትና በማስመሰል አትታጠፍም።

ግደይ ዘርአፅዮን ሲናገር፣ 06 ሓለዋ ወያኔ ከመሬት በታች ሁለት ሜትር መሆኑን በቃሉ አምኖበታል። ማመኑ ጥሩ ነው። ነገር ግን ዋሻም እንጠቀማለን ያለው ውሸት ነው። ይህንንም የምናደርገው የጦር ቀጠና ስለሆነ ነው ብሏል። ይህም ትክክል አይደለም። የህወሓት አመራር ሰውን ነፋስ በማይገባበት ጉድጓድ ውስጥ እያሸጉ የስንት ንጹሃን ኢትዮጵያዊያኖችን፣ ህፃን፣ ሽማግሌ፣ ወጣት፣ ወንድ፣ ሴት፣ እርጉዞችን ጭምር አጥፍተዋል፣ ግድለዋል። ሲፈጸም የነበረውንም ቶርቸር አንተ ራስህ፣ ግደይ ዘርአፅዮን፣ ቡምበትና ሱር ሓለዋ ወያኔ የፈጸምከውን ዘግናኝ ግድያ አምነህ መቀበል ይኖርብሃል። ኢትዮጵያን ለችግር የዳረጋችኋት አንተና አረጋዊ በርሄ ናችሁ። በአማራው ላይ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተሰማራችሁት አንተና ጓደኞችህ መሆናቸውን አምነህ ተቀበል።

ስለምርኮኛዎችም  ተናግረሃል። መናገርህ ጥሩ ነው። የነበሩት ምርኮኞች ከሻእቢያ የመጡ ናቸው እንጂ ተሓህት – ህወሓት የማረካቸው አልነበሩም። አሻግራችሁ ወደየመጡበት ሸኙአቸው እየተባለ ተሓህት – ህወሓት እየተቀበላችሁ ትገድሏቸው ነበር። ይህንንም ሁሉም የድርጅቱ ታጋይ በወቅቱ የሚያውቀው ሃቅ ነበር። ግደይ፤ ታጋዮች በአይናቸው ያዩትን እና የተናገሩትን ሃቅ በአንተ በኩል በዚያ ወቅት የፈጸምከውን ላንሳልህ፡፡ 300 (ሶስት መቶ) ከሻእቢያ በህዳር 1971 የተላኩትን ምርኮኞች ምን ፈረድክባቸው? በጥይት ተረሽነው እንዲገደሉ አደርገሃቸው። ለዚህም በውጭ ሃገር የሚኖሩ በርካታ የቀድሞ ታጋዮች የዓይን ምስክሮች አሉ። የተረሸኑትም ሌላ ሃጢያት ሳይኖራቸው አማራ በመሆናቸው ብቻ ነው።

እናንተ የህወሓት አመራሮች የፈጸማችሁት ስንት ከባድ ወንጀል ተሸፋፍኖ እያለ፣ ይፋ ከሆነ የሚገጥማችሁ እስራት ብሎም ግድያ ይጠብቀናል በሚል ፍርሃቻ አካላችሁ ስለተወረረ፣ ከዚያ ለመላቀቅ ጥፋታችሁን ለሕዝብ ተናዛችሁ ይቅርታ ብትጠይቁ ይሻላችሁ ነበር። ግደይ፣ እኔ ፖሊት ቢሮ ስለነበርኩኝ የምናገረው ሁሉ ተአማኒነት አለው ብለህ ታስባለህ፣ ግን ስተሳስተሃል። ህወሓት ለምርኮኞች ብዙ እንክብካቤ ሲያደርግ እንደ ነበርም ተናግረሃል። የተናገርከው ግን ሙልጭ ያለ ውሸት ነው። ህወሓት የዚህ ዓይነት ባህሪ የለውም።

ግደይ ሲናገርም ገብረመድህን የትግራይ ሕዝብ አማራን ይጠላል ይላል ብሏላ። እኔ የምናገረውን አውቃለሁ። ግደይ የዘነጋው ነገር ግን አለ። ተሓህት – ህወሕት ገና ከጅምሩ በየቦታው እየተንቀሳቀሰ አማራ የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ነው እያላችሁ ስትሰብኩ እንደነበር የማይካድ ሃቅ ነው። ለዚህም የትግራይ ሕዝብ የሰጣችሁን መልስ አትዘነጋውም። ላስታውስህና፣ የትግራይ ሕዝብ ያለው አማራ ጠላታችን አይደለም፣ ወንድማችን፣ ደማችን፣ አጥንታችን፣ ኢትዮጵያዊ እንጂ ነው ያለው። ለትግራይ ሕዝብ የውሸት ስም እየሰጣችሁ፣ ትግራዋይ ሸዋዊ ብላችሁ፣ በምክንያት ስንት ሺዎች የትግራይን ሕዝብ ገድላችኋል፣ ንብረቱን ዘርፋችኋል።

በየካቲት 1968፣ ተሓህት – ህወሓት፣ ፕሮግራሙን ሲያሰራጭ የትግራይ ሕዝብ አንቀበልም በማለቱ በተከታታይ እያሳደዳችሁ በመግደል ወንጀል ፈጽማችሁበታል። በሓለዋ ወያኔ 06 እያሰራችሁ ፍዳውን አሳይታችሁታል። ፈዳያን አጥፍቶ ጠፊ አሰማርታችሁ የከተማውን ሕዝብ እየገደላችሁ ደሙ በየፒያሳው መጠጥ ቤት እንዲፈስ አድርጋችኋል። ይህንን የፈጸማችሁት ደግሞ፣ አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርአፅዮን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስብሃት ነጋ፣ ሥዩም መስፍን እና መለስ ዜናዊ ናችሁ። ምስክሬ የትግራይ ሕዝብ ነው።

ይህንን ሁሉ ግፍ ሲያስፈጽም የነበርረው ግደይ ዘርአፅዮን ለትግራይ ሕዝብ ተቆርቋሪ መስሎ የትግራይን ሕዝብ ሰደበ የሚለኝ፣ ስሰድብ የተቀረጸ የድምጽ ምስክርነት ካለው ያቅርብ። ኢሳትም ይህን ብለህ ነበር ብሎ በማለት ለሕዝብ ያጋልጠኝ። የትግራይን ሕዝብ የጨፈጨፈ ግደይ እንጂ እኔ አይደለሁም። ግደይ ዘርአፅዮን በኢሳት ላይ ባለው ጥላቻ ኢሳትን ውሽታም እያለ በሰው ሕዝብ ያሰድባል ማለቱ በጣም አስገራሚ ነው። ኢሳት ሕዝብን የሚሳደቡ ማሰባሰቢያ የመገናኛ ብዙሃን አይደለም። ግደይ ኢሳት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቆመ ሚዲያ መሆኑም አልተረዳውም። ኢሳትን መስደብና ማንቋሸሽ የኢትዮጵያን ሕዝብ መስደብና ማንቋሸሽ ነው። አሁንም እንደዱሮው በሕዝብ ላይ ያለው ንቀት አልለቀቀውም።

ግደይ ዘርአፅዮን ስለ ወልቃይት ሲናገር እንዲህ ብሏል፣ “ትግሉን ስንጀምር ትግራይ የሚባለው ያኔ የትግራይ ጠቅላይ ግዛት የነበረው ከአለወሃ መለስና ወልቃይት ያለው ትግርኛ ተናጋሪ የሚኖርበትን ያጠቃለለ ነው” ይላል። (ሰረዙ የኔ ነው)። እንዲህ ብሎ መናገሩ ከእውነት የራቀ ነው። ያልነበረውን ነበረ ማለት ያልተላቀቀውና ያደገበት የህወሓት መርህ ነው።

ግደይና ጓደኞቹ በረሃ ከመውጣታቸው በጣም ቀደም ብሎ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ስቲት ሁመራ፣ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት፣ በተከዜ ወንዝ ድንበርነት አማራ መሆናቸው በታሪክ የተረጋገጠ ነው። አለወሃ መለስ ወልዲያ፣ ራያና ቆቦ፣ አፍላደራ ወዘተ በወሎ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ መሆናቸው ታሪክ ያረጋግጣል። ግደይ ዘርአፅዮን የወልቃይት አማራን በሁለት ከፍሎታል። ትግርኛ ተናጋሪ ወልቃይትና አማርኛ ተናጋሪ ወልቃይት በማለት ሰንጥቆታል። በታሪክም ሆን በአፈ ታሪክ ይህ አይነቱ አነጋገር ተሰምቶም አያውቅም። የወልቃይት ሕዝብ አማራ እንጂ ትግሬ አይደለም። ግደይ ስለ ሬፈረንደምም ለመዘባረቅ ሞክሯል። ጠገዴ አንተና የወያኔ መሪዎች በጉልበት ነጥቃችሁ ዘሩን እያጠፋችሁት እያለ፣ አንተ በምትቀባጥረው አይነት ሳይሆን ነገ ሕዝቡ በፈለገውና በመረጠው ዘዴ ማንነቱን ያስከብራል፣ መሬቱንም ወደ ቀድሞው ይዞታው ያስመልሳል።

ግደይ ይህን ሃሳብ ያነሳው የወልቃይት ሕዝብ ለጥቃት ከፋፍሎ እየሰጠው ነው። የአንድን አውራጃ ሕዝብ ለሁለት ከፍሎ ትግርኛ ተናጋሪና አማርኛ ተናጋሪ ብሎ ሕዝብ ለማጋጨትና አለመተማመን እና ጥርጣሬን ለመፍጠር አልሞ የተነሳ ነው። ይህ ደግሞ ወያኔ አሁን የሚጠቀምበት ዘዴ ነው። ታዲያ ግደይና ወያኔ ምን ልዩነት አላቸው? በታህሳስ 1972፣ ህወሓት መሬት ለመውረር በተነሳበት ጊዜ የህወሓት ፖሊት ቢሮ እየተመራ በሕዝቡ ላይ ጦርነት አወጀ። የግል ንብረታቸው በሕወሓት ተወረሰ፣ ተዘረፈ። በዚህም የተነሳ በርካቶች ለስደት ተዳረጉ። በሺዎች የሚቆጠሩም ወደ 06 ሓለዋ ወያነ እየተጋዙ ተገደሉ። የዚህ ሁሉ እልቂትና ዘር ማጥፋት ዋናው ተዋናይ ግደይ ዘርአፅዮን ነበር። አሁንም በአማራው የሚካሄደው የዘር ማጥፋት እንደቀጠለ ነው። የመሬት ወረራ በተጀመረበት ወቅት ግደይ ዘርአፅዮን የመጀመሪውያው ፖሊት ቢሮ ም/ሊቀመንበር ነበር። የሓለዋ ወያኔ እስር ቤቶች ሁለት ሜትር ወደ መሬት ጠልቀው እንዲሠሩ ትእዛዙን ያስተላለፈ መሪ ነበር። በትእዛዙም መሠረት ተፈጸመ። ነፋስ መግቢያ የሌለው፣ እርጥብ እንጨት “ዓየ” ተብሎ የሚታወቅ ዛፍ እየተቆራረጠ በማቃጠል ጪስ እየተለቀቀ የአማራውና የትግሬው ሕዝብ በአየር እጦት እየታፈነ አልቋል። የዚህም ፈላስፋ ግደይ ዘርአፅዮን ነበር።

ግደይ ወልቃይት ስንገባ ሕዝቡ አልተቃወመንም ብሏል። ይህ አነጋገር ቅንጣት ያህልም ሃቅነት የለውም። የወልቃይት ጠለምት ጠገዴ ሕዝብ ወራሪ መጣብን ብሎ እልህ አስጨራሽ በሆነ መልክ መሳሪያ አንስተው ፀረ ወያኔ ትግል ማቀጣጠላቸው በገሃድ ይታወቃል። ከፋኝ የሚባለውና ህወሓትን ያስጭነቀው ፀረ-ወያኔ ድርጅት የተፈጠረውም በዚያ ጊዜ ነበር።

ግደይ ዘርአፅዮን የፖሊት ቢሮ አባል ሆኜ እንኳን ስለ 06 ብዙም የማላውቀው ነገር አለ ብሏል። ታዲያ የህወሓት ፖሊት ቢሮ ም/ሊቀመንበር ሆኖ ሳለ ድርጅቱን በሞግዚትነት ነበር የሚያስተዳድረው?  (ይቀጥላል)

የመሪዎቹ ስም ዝርዝርና ገበናቸው ቀጥሎ ይቀርባል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

ገብረመድህን አርአያ
02 ኦክቶበር 2016
02 October 2016


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Tadesse says

    October 3, 2016 09:31 am at 9:31 am

    Esaten alankuasheshem but I have no interest to listen to them except may be one,the dark skinned interviewer/wise yemaiadala atleast in such a narrow minded media.

    Reply
  2. Tadesse says

    October 3, 2016 09:51 am at 9:51 am

    We’re kemawrat Ethiopiawianen mastbaber jegnenet new.

    Reply
  3. Alem says

    October 3, 2016 04:12 pm at 4:12 pm

    “the dark skinned” interviewer?

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule