
“ለሌላ አደገኛ የጦርነት አዋጅ በወገናችን ላይ ታወጀ” በሚል ለተጻፈው መልስ
ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ በጎልጉል ድረገጽ ላይ እራሳቸውን ተሃድሶ ብለው በሚጠሩ ነገር ግን እውነተኛ ማንነታቸው ለሰወሩት ወይንም በማንነታቸው ለሚያፍሩት፣ የምንፍቅና አቀንቃኞች መልስ ይሆን ዘንድ ነው። በመምህር ምህረተአብ ላይ ላቀረቡት ትችት ከሞላ ጎደል መልስ ይሆናቸዋል ብዬ አምናለሁ።
ጸሃፊው፤ አቤቱታውን ሲያሰማ እንዲህ ይላል፤ ተወልደን ባደግንበት ኦርቶዶክስ በቴ ክርስትያን “የፍቅር ምሳሌ ሊሆኑ በሚችሉ አገልጋዮች ላይ የጦርነት አዋጅ ታወጀብን” ተወልደን ያደግንበት ከማለት፤ ተዘርተን የበቀልንበት ቢል ማንነቱን ይበልጥ ይገልጸዋል ብዬ አምናለሁ። የመወለድና የመዘራት ትርጉሙ ካልገባቸው ለማለት ነው። ሲጀመር ይህች ቤተ ክርስቲያን ባጎረሰች የተነከሰች ለመሆኗ ጸሃፊው እራሱ ይክደዋል ብዬ አላምንም። የሉተር ፍልፍሎችና ቅፍቅፎች፤ እንዲሁም የመለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ በመባል የሚታወቅ ዘላንና ሰካራም ወያኔ በለስ ቀንቶአቸው ኢትዮጵያን ከተቆጣጠሩበት ጊዜ ጀምሮ አማራንና ኦርቶዶክስን አከርካሪውን ሰበርነው፤ እያሉ ያወጁትንና የፎከሩበትን ተግባራዊ ለማድረግ ምኞታቸውን ከግብ ለማድረስ የሰሩት የስራ ውጤት ነው። ምንም እንኳን ቢማርና ቢያውቅም ሆዱ ጭንቅላት የሆነበት አለማዊ ንዋይና ዝና ያሰከረውን ሟቹን አባ ዲያቢሎስን በቤተ ክህነት አናት ላይ አስቀምጠው አገር ማፍረስ ብቻ ሳይሆን አምነታችንንም ከስር መንግሎ ለመጣል እራሳቸውን ተሃድሶ ብለው በሚጠሩ አፍቅሮተ ንዋይ ያሸነፋቸውንና ሆድ አደር ወፍ ዘራሾችን በማሰባሰብና በማደራጀት ከምን ግዜውም በላይ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ እንደተነሳሱ ይስተዋላል።
የምእራባውያን ንዋይ በገፍ በሚፈስላቸው፤ የበግ ለምድ የለበሱ አሳዊ መሲሆች ፤ መጽሃፍ ቅዱስን በመሰረዝ፤ በመደለዝ፤ የሌለ በመጨመር፤ ቀላል አማርኛ በሚል ቅጥ አንባሩ በጠፋ መጽሃፍ ቅዱስ ተብዬ በማወናበድ፤ አዲሱን ትውልድ በየመድረኩ በሚወራጩ ፤ በሚደንሱ፤ በሚንፈራገጡ፤ ትያትረኞች ትርጉም የለሽ የአጋንንት ልሳን ትርኪ ምርኪ እየዘላበዱ ብዙዎችን ይዘው እንደጠፉ ቢታመንም፤ “የፈሲታ ተቆጢታ” ሲሆኑ ግን ሊነገራቸው ይገባል።
ሲጀምር ቀና የሚያደርግ መንፈስ ቅዱስ እንጂ በየመድረኩ የሚዘርርና አረፋ የሚያስደፍቅ መንፈስ የጨለማው መንፈስ ካልሆነ ሌላ ሊሆን አይችልም። ልሳኑም ቢሆን የሻምፓራራ ድግግሞሽ እራሱ ተናጋሪው የተናገረውን የማያውቀው፤ የማይሰማ፤ የማይተረጎም፤ ቢተረጎመምም በየጊዜው አንድ የተለመደ ቃል እየቀባጠሩ ዛሬ የሚተረጉመው ሌላ፤ ነገ የሚተረጉመው ሌላ፤ ስለሆነ ምንጩ ማን እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ የልጆች ጨዋታ ስለሆነ በግድ እኛን ካልመሰላችሁ ካልወረዳችሁ ብሎ ሙግት አብረን እንውደቅ ካልሆነ በቀር ሌላ
ምንም ሊሆን ስለማይችል እዚያው በጸበላችሁ።
በመጨመር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ባሉበት ለመከራከርም ጥያቄ ያነሳል ጸሃፊው፣ በውነት እነዚህ አዋቂ ነን ባዮች የያዙትን ወንጌል በርግጥ አንብበውት ያውቃሉ? አይመስለኝም! ከሆነ ግን እምነት ለመከራከሪያ እንዳልሆነ ተጽፏል የተጻፈን እንኳን አንብቦ መረዳት የተሳናቸው ፤ የዞረባቸው እንደሆነ ከጽሁፉ በቀላሉ መረዳት ይቻላል።
ብታምን ታምናለህ፣ ባታምን ወደመሰለህ ትሄዳለህ እንጂ ካንተ ጋር ተቀምጦ የሚከራከር የሚሟገት አይኖርም። እምነት መከራከሪያ አለመሆኑን ስታውቁ ፤ ያኔ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትክክለኛ እምነት እንደሆነች ትማራላችሁ ብዬ አምናለሁ።
ጸሃፊውም ሆነ መሰሎቹ አንድ ሊያውቁት የሚገባ ነገር ቢኖር ኢትዮጵያ መላው ዓለም በተለይም የመናፍቃኑ መሪዎችና አቀንቃኝ የሆኑት ምዕራባውያኑ ድንጋይ እየቀረጹና እንጨት እየፈለጡ በሺ የሚቆጠሩ ጣኦታትን በሚያመልኩበት ዘመን ኢትዮጵያ አንድ አምላክ ብላ በስነ ልቦና ፈጣሪን የተቀበለች፤ ከዚያም በኦሪት ዘመን ብሉይ ኪዳንን የተቀበለች፤ ከጌታችን ከመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ በኋላም አዲስ ኪዳንን በመቀበል በትክክለኛው እምነትና መንገድ ጸንታ የኖረች ወደፊትም እስከ ምፅዓት በዚሁ በጸናው እምነቷ ጸንታ እንደምትኖር እነ ፍራሽ አዳሽ ሳይሆኑ ዓለም የሚመሰክርላት እና ሊያውቀው የሚገባ የማይታበል ሃቅ ነው። የመናፍቁ አባትና መሪ እንኳን ከክህደቱ በፊት ለ1,500 ዓመታት ኦርቶዶክስ ስታስተምረው እንደቆየችና በማናቸውም ነገር እንደምትቀድመው፤ እንደምትበልጠው እንዴት ሊሰወርባቸው እንደቻለ ግልጽ አይደለም። ዛሬ ዛሬ “ከኋላ የመጣ
አይን አወጣ” ወይንም “ምጥ ለናቷ አስተማረች” ሆነና ውሃው ሽቅብ ካልፈሰስኩ ብሎ ይሞግታል።
ሌላው የቤት ክህንትን ልብሰ ተክህኖን መዝረፍን በተመለከተ ይሆናል። ይህም ምንም ከእውነት የራቀ አይደለም፤ እርግጥ የቤተ ክህነትን ልብሰ ተክህኖና የቀሳውስቱን አለባበስ ይሄው አራሱን ተሃድሶ ብሎ የሚጠራው የጴንጤው አቀንቃኝ አለአግባብ ሲጠቀሙበት ይስተዋላል። ከመደበኛው ጴንጤ ምንም የሚለያቸው ነገር ሳይኖር ለምን እራሳቸውንም ኦርቶዶክስ ብለው እንደሚጠሩ ከማንም የተሰወረ ባይሆንም ዋና አላማው ምዕመኑን ለማሳሳትና ለማወናበድ ቀላል ዘዴ ሆኖ ስለተገኘ ነው ። ስብከታቸውም ሆነ እምነታቸው እንዳለ የጴንጤው እንደሆነና ውሎና አዳራቸውም ከነሱ ፓስተሮችና ተከታዮቻቸው ጋር እንደሆነ ያደባባይ ሚስጥር ነው። አለባበሳቸውንም እንደ መሰል ፓስተር ጓዶቻቸው ሱፍና ከረባት እንዳይለብሱ የኦርቶዶክን ቆብና ቀሚስ ያስፈለገበት አብዩ ምክንያት አሳቹ ተኩላ በግ መስሎ መምጣቱ የግድ ስለሆነ ነው። አላማውን ለመገንዘብ እምብዛም ምርምር አያሻም።
በማናቸውም መንገድ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን አስመስሎ መቅረቡ ተቀባይነትን ሊያስገኝላቸው ስለሚችል የተኩላው መመሳሰል ግድ ይላል። እሱ ብቻም ሳይሆን ተኩላው አስመስሎ ሊመጣና ብዙዎችን እንደሚያስት የተነገረውም ትንቢት ይፈጸው ዘንድ የግድ ነውና። ተኩላው በሚገርም ሁኔታ የጌታችን የመድሃኒታችን እናት የሆነችውን የድንግል ማርያምን ምስል ከሚሰበሰቡበት መጋዘን ከሰባኪያቸው ጀርባ ለምዕመናን በግላጭ እንዲታይ አድርጎ ማስቀመጥ አንዱ የማሳቻ ዘዴያቸው ሲሆን፤ እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን ነገር ቢኖር ግን ስዕሏን ያስቀምጡ እንጂ ስለእመቤታችን ድንግል ማርያም በድንግልና መውለድና፤ በድንግልና ለዘለዓለም የጸናች መሆኗን፤ አማላጃችን መሆኗን ፤ የማይተነፍሱ ነገር ግን ስዕሏን አላግባብ በማስቀመጥ፤ የዋሃንን ለማሳት ፤ አይነተኛ ዘዴ አድርገው ሲጠቀሙበት ይታያል።
ከዚህ ቀደም እንደምናውቃቸው መናፍቃን በግላጭ ድንግልን፤ መላይክትንና ጻድቃንን ከመስደብ ተቆጥበው ዋና ጨዋታ አድርገው የያዙት፤ ጭራሽ ስማቸውን ባለማንሳት ምስላቸውን ብቻ እያሳዩ ኦርቶዶክሳዊ መስሎ በመቅረብ፤ ገድላቸውን በማዳፈን፤ አማላጅነታቸውን ባለመመስከር፤ የማስረሳትና የማዘናጋት ጨዋታ እየተጫወቱ እንደሆነ ለብዙሃኑ አስተዋይ እና ብሩህ አይምሮ ላለው ኢትዮጵያዊ የማይሰራ ተራ የመንደር ትያትር እየተገበሩ እንደሆነ ነጋሪ ቢያገኙና ቢነገራቸው አካሄዳቸውን ለማስተካከል ይረዳቸው ይሆናል።
በጣም አሳዛኙ ተግባራቸው ግን እየገረፉ ለምን እንደሚያለቃቅሱ ሊገባኝ አልቻለም። እንደሚታወቀው ተሃድሶ ተባለ ጴንጤ ያንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች እንደሆኑ ጸሃፊው እራሱ እንደማይክደው አምናለሁ። ታዲያ ለምን ኦርቶዶክስ ተዋህዶን መስሎ መቅረብ አስፈለገ?
ሁለተኛ መቼም አንድ ሰው ወይንም ቡድን በማይመስለው እምነት አዳራሽ ገብቶ የራሱን የእምነት አመለካከት እንዲሰብክ በማናቸውም የእምነት ተቋም እንደማይፈቀድ የማያውቅ ይኖራል ብዬ አልገምትም። ታዲያ የኛ ፍራሽ አዳሾች ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤት ምን ይሰራሉ?
ድርሽ እንዳይሉ ተከልክለውም ከሆነ አግባብ ነው እላለሁ። በሶስተኛ ደረጃ ይሄው የበግ ለምድ ለባሽ ለምን በየጴንጤው መጋዘን ይሰብካል? ተጋባዥ እንግዳ ሆኖ ይቀርባል? ለምንስ መደበኛው ጴንጤ ተሃድሶ ተብዬውን ሊያጠናክረው የገንዘንና የቁሳቁስ እርዳታ ያደርግለታል?
ይሄንን እውነታ ፈጥሬ ሳይሆን በትንሹ አኔ በማውቀው ቅዳሜ ቅዳሜ (8:00AM to 11AM eastern US standard time) በምስራቃዊ አሜሪካ ሰዓት አቆጣጠር ጠኋት ስምንት ሰዓት ላይ የጀመረ አስከረፋዱ አስራ አንድ ስዓት ድረስ (Ethiopian christian plus all) በሚባል የጴንጤዎች የፓል ቶክ ክፍል ውስጥ ፕሮግራም ተይዞላቸው ኦርቶዶክስን ሲሰድቡና ሲያሰድቡ ፤ ድንግልንም ሆነ መላይክትን እንዲሁም ጻድቃንን ሲያንጓጥጡ እንደሚውሉ ማንም ኢትዮጵያዊ የሆነ እዚህ የመናፍቃን የፓል ቶክ ክፍል በመምጣት የፍራሽ አዳሹን እውነተኛ ማንንነት ማወቅ ይችላል።
ታዲያ ይህ ሁሉ እውነታ ስለናንተ እየታወቀና እያለ ሁለት ቦታ መረጋገጡ ምን ለማምጣት ነው እነ ተሃድሶ? እስቲ ጥያቄያችሁን በጥያቄ ልቅረበው ። ለምን ሁሉ አማረሽ ሆናችሁ? ስለምንስ አንድ ቦታ መርጋት አቃታችሁ? ስለምንስ የኦርቶዶክስን ስም መዋስ አስፈለጋችሁ? እውነተኛ ማንነታችሁን የማያውቅ ያለ ይመስላችሁ ይሆን? ከሆነ በርግጥ በጣም የዋሆች ናችሁ።
አምነት የመዳን ጉዳይ እንጂ፣ የቲፎዞ ወይንም የደጋፊ መብዛት ጉዳይ ከመሰላችሁ እጅግ በጣም ተሳስታችኋል። መንግስተ ሰማይ በቲፎዞ ብዛት ሳይሆን የምትወረሰው በእምነትና በተግባር አንደሆነ የያዛችሁትን ወንጌል መመርመር ያሻል። ስለሆነ በየጴንጤው መጋዘን ደጋፊ ፍለጋ መንጦዝጦዝና ደጅ መጥናት የመንግስተ ሰማይን ደጃፍ አያስከፍትም ምድራዊ አንቱታን ከሆነ ይቻል ይሆናል ያውም የከንቱ አንቱታ።
ታዛቢው (kaleab2k@gmail.com)
ከዝግጅት ክፍሉ፣ የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ መምህር ምሕረተአብ ሳይሆኑ “ጉዳዩ የሚመለከተኝ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ነኝ” ብለዋል። ከዚህ በኋላ በዚህ “ለሌላ አደገኛ የጦርነት አዋጅ በወገናችን ላይ ታወጀ” ጽሁፍ ዙሪያ ከመምህር ምሕረተአብ በስተቀር ከማንኛውም ሰው የሚላኩልንን ማናቸውንም ጽሁፎች አናትምም። አስተያየት ያላችሁ ለጸሐፊዎቹ በኢሜይል አድራሻቸው መላክ ወይም እዚሁ ሥር በአስተያየት መስጪያው (Comments) ሃሳባችሁን መግለጽ ትችላላችሁ።
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
ለአቶ ታዛቢውና
ፍንክች የማይል ተመሳሳይ
ባህሪ ላላችሁ አበሾች በሙሉ:
አንድ በመረጃ ተደግፎ የቀረበን ሃሳብ በሌላ በተሻለና በሚያሳምን ሃሳብ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ማቅረብና የሳተ ካለ ማሳመንና ማረም ሲገባችሁ ተራ ዘለፋና ስድብ በዚህ ማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ ማቅረቡ እራሳችሁን ትልቅ ትዝብት ላይ ከመጣሉ ባሻገር አስተዋይ የኦርቶዶክስ አማኞችን ጭምር የሚያሳፍር ይመስለኛልና የእናንተን ሃሳብ የተቃወመውን ሁሉ ቃላትን እየለቃቀመን ካለበቂ መረጃ እንዲህ ነው ወይም ናችው በማለት የተነሳችሁለትን ዓላማ (ካላችሁ) በቂ ደጋፊ አግኝታችሁ ከግብ ማድረስ የምትችሉ አይመስለኝም፤ ለዚህ መሰለኝ በእኛ በኢትዮጵያውያን መካከል ብዙ ነገር ጀምረን መጨረስ እያቃተን መሀል ላይ የሚበተንብን። ስለዚህ አቶ ታዛቢውና ሌሎች የሚቃማችሁ ሁሉ ጠላት የሚደግፋችሁን ደግሞ ወዳጅ አድርጋችሁ በመቁጠር በቅደም ተከተል አስጠልቶ ለማስወደድ የሚያስችለውን የፊት ወንበር መቀመጫ ወንበሩን በመያዝ ይህን የመሰለ የሁልጊዜ እኔ አለሁ ባይነታችሁ በያላችሁበት ብቻችሁን ያለ አንባቢ እንዳያስቀራችሁ እፈራለሁ!!!
Hi Golguloch,
Why my comment is late to be posted on your web???
Yours,
Chewa Ethiopiawi
እርስዎ ምንም እንኳን እንደተለያየ ሰው በተለያየ ስም የሚጽፉ ቢሆንም እስካሁን ያላተምነው የለም።
አንድ ስድብ “አስተያየት” ነው ብሎ የላከልንን አላተምንም፥ አናትምም።
ከዚህ በቀር ቀረብኝ የሚሉት አስተያየት ካለ እንደተለመደው ስምዎን ቀየር አድርገው ደግመው ሊጽፉት ይችላሉ።
ከዚህ በተረፈ ከሰዓታት ወይም ከአንድ ቀን በፊት ጽፈው ለምን አልታተመልኝም የሚሉ ከሆነ ተሳስተዋል።
ጉዳዩን ግልጽ ያደረግን ይመስለናል።
የጎልጉል አርታኢ
ጎልጉሎች,
የእናንተ ሥራ ማህበረ ሰቡ ገንቢና አፍራሽ ሃሳቡን አቅርቦ
የሚወያይበት መድርክ በመሆናችሁ ጠቃሚና ገንቢ በሆነ የጋራ
ሃሳብ ላይ ብቻ ብታተኩሩ ይሻላል፤
በግለሰብ ማንነት ላይ እንዲህና እንዲያ ነህ ማለቱ ለችግራችን
መፍትሄ ስለሌለው ለአላችሁኝ ጉዳይ ተገቢ መልስ ቢኖረኝም
ቆብ ቀዶ መስፋት ውስጥ መግባት አልፈለኩም፤
ደግሞም ለእናንተ ሥራ ያለኝን ክብር በዚህ ጠቃሚ ባልሆነ
ነገር ምክንያት ማበላሽት አልፈለኩምና ለጋራ ጉዳያችን
ድርሻችንን በመግባባት እንወጣ? የላኩትን ጽሑፍ ለምን ቶሎ
አላወጣችሁትም ለሚለው የችኮላ ጥያቄዬ ግን ካባቶቻችን
በተማርኩት ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ጎንበስ ብዬ ይቅርታ
እጠይቃለሁ???
ስለሁሉም ሰፊ የይቅርታ ልብ ይኑረን
ደህና ሁኑልኝ
በሰጠነው አስተያየት ላይ የተሳሳትነው ነገር የለም። እርስዎም ይቅርታ መጠየቅ አያስፈልግዎትም ነበር። ነገር ግን በጨዋነት ላቀረቡት ይቅርታ በትህትና መቀበል የኛ ኃላፊነት ነውና ተቀብለናል።
ከሰላምታ ጋር
የጎልጉል አርታኢ
I am commenting on the title of this article. I am not interested on the content of the article as I am not into religion. I do not believe in a sky god or something like that.
Back to the topic, which is the topic of the article that refers to Arius.
Arius was an Alexandrian priest who argued against Athanathius on the nature of Christ. Arius argued that there was a time when Christ was not, meaning that Christ was born at some time and therefore he could not have been with God from the start. Athenathius argued that Christ was part of the God head as a son and that he was there all along from the begining of time.
However, though Arius had a huge followers, he lost the debate and was beaten up and forced into exile.
Finally Emperor Constantine advised for compromise and the nature of Christ was to be called “consubstantial”, meaning that Christ was part of God and also human. This I believe is what the Orthodox “Tewahido” emerged from.
Respected Seifu,
I really appreciate your timely comment for the writer of this article.
This can be a good lesson if and only if he is a good listener!
I would, therefore, like to add the following statement so that we all
Can use our ears properly:
”He who has an ear, let him hear what
the Spirit says to the redeemed”