
በማህበረሰባችን መካከል ወልደህ ሳም የሚባል የተለመደ ምርቃን ነበር፤ ከአንደበት የሚወጣ ቃል ደግሞ በረከትን ወይም መርገምን ሊያስከትል እንደሚችል ይገመታል፤ በምድራችን ውስጥ ልጆች በጤና ተወልደው እንዲያድጉ ወላጆች የልጆቻቸውን የጤና ስጋት ለመቀነስ ሲሉ ገና ከእርግዝና በፊት ጀምሮ ገድል ከማሳዘልና እትፍ እትፍ ከሚሉ ሰዎች እስከ የቡና ስኒ ገልባጭ መናፍስት ጠሪዎች ድረስ በልጁ የማደግና የወደፊት የሕይወት እጣፋንታ ላይ ትንቢት መሰል ሟርት እያውጁበት እንዲያድግ ይደረጋል፤ በዚህ ሁሉ ግን ሁላችንም ምንም ዓይነት የጤና ድጋፍ በሌለበትና የመናፍስት ጠሪዎች ቁጥር በርካታ በሆነባት ምድር ውስጥ ተወልደን ማደጋችን ገብቶን በማወቅ ባናከብረውም የፈጣሪ ጥበቃና ምህረት እንደሆነ አምናለሁ።
ከዚህ ችግር ስፋትና ጥልቀት የተነሳ በርካታ ልጆች ተወልደው የማደግ እድል ሳያገኙ ከእናታቸው ጋር ሕይወታቸውን ያጡ ብዙ ናቸው፤ ሆኖም ግን ይህ ሁሉ ስጋት ታልፎ ተወልዶ፣ አድጎና ተምሮ ሃገር የሚረከብ ትውልድ በዘመናት ሁሉ ታጥቶ አለመታወቁ ምድርን ሙሏትና ግዟት የሚለው መለኮታዊ ትእዛዝ እስከ ፍጻሜው ድረስ የማያቋርጥ ለመሆኑ ምልክት ነው፤ ጥያቄ የሚሆነው ግን የዘመኑ ባላደራ ትውልድ ለተገኘበት ማህበረሰብ የሚበጅ ሥራ እያበረከተ ነውን? ወይስ ወላጆቹን በማስመረር ባልተወለድክ ወይም የወላድ መካን እያስባለ ነው? መልሱን ለአንባቢ ኀሊና ልተወው።
ይህ ጥያቄ ወደ እኔ አእምሮ የመጣው በድንገት አይደለም፤ ሁላችንም የተገኘንበት ማህበረሰብ በኑሮው እየደረሰበት ያለው መከራ ሳያንሰው ሰሞኑን መንፈሳዊ አስተማሪ የሆነው መምህር ምህረትአብ አሰፋ በፌስ ቡክና በዩቲዩብ የለቀቀው የጦርነት አዋጅ ነው፤ በመልካም አስተዳደር እጦት ለዘመናት እየተሰቃየ ባለ ሕዝብ ላይ ሌላ የሃይማኖት ጦርነት! ያውም ያገር እንደራሴ ሆና በቆየችው በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተወልደው ባደጉና ለሕዝቡ የፍቅር ምሳሌ ሊሆኑ በሚችሉ አገልጋዮች መካከል ሊፈጸም የታሰበ የወንድማማቾች የጦርነት አዋጅ! (እባክዎ የሚከተለውን ሊንክ በማስተዋል ይመልከቱና በመጽሐፍ ቅዱስ ይመዝኑት)
ለዚህ ነው በአንድ እጅ የፍቅር ምንጭ የሆነውን ወንጌለ ክርስቶስን፣ በሌላው እጅ ደግሞ ወንድምን ለመግደል የሚያስችል መሳሪያ አንግቦ በወገኖች መካከል የጦርነትን አዋጅ ለሚጎስሙ ለእነ ምህረተአብ አሰፋና መሰሎቹ በአውደ ምህረቱ ላይ እንደፈለጉ መፋነን የፈቀደች እናት ቤተ ክርስቲያናችንን እራሷን በእጇ ላይ ባለው መጽሐፍ ቅዱስ መዝና ወደ ቀደመ ማንነቷ ትመለስ/ትታደስ በማለት የምንጮኸው ይላሉ የዚችው ቤተ ክርስቲያን ካህናት፤ እዚህ ላይ እውነቱን ለይቶ የራስ ለማድረግ ግን የሁላችን ሃላፊነት መሆኑንና ሁሉንም ቆም ብለን በማስተዋል መዝነን የሚበጀንን መያዝ እንጂ በሃይማኖትና በባንዲራ ስም ለሚደረግ ጮኸት ሁሉ ሳይገባን ማጨብጨ የሌለብን።
እስቲ ተመልከቱ! ፍቅርና ጥል፣ ሐጢአትና ጽድቅ፣ ክርስቶስና ዲያብሎስ፣ ሞትና ሕይወት፣ ሥጋና መንፈስ፣ ጦርነትና የሰላም ወንጌል መቼ ነው አብረው የሚሄዱት? ምናልባት ለምህረተአብ አዲስ ግኝት ወይም መገለጥ መስሎት ይሆን? ግን እኮ ሰይጣንም የብርሃን መልአክ መስሎ አይደል የሚመጣው? ስለዚህ ሁሉን መፈተን አምልጦ ማስመለጥ ስለሚሆን እናንተ ከእውነት የተወለዳችሁ ወገኖች በሙሉ እባካችሁ! ይህ የጠመጠመና መስቀል የጨበጠ ሁሉ እውነተኛ የመንፈስ አባት የሚመስለው የዋህ ወገናችን የጮሌዎች መጫዎቻ ሲሆን እያየን ዝም አንበል? የማህበረ ቅዱሳንና የተሐድሶ ጉዳይ ወደ አደባባይ ወጥቶና ሕዝብ በሙሉ አውቆት የራሱን ውሳኔ እንዲሰጥበት መድረኮች ይዘጋጁና ውይይት ይደረግበት፤ በውጭም በአገር ቤትም ያላችሁ የቤተ ክርስቲያኒቷ መሪ የሆናችሁ ጳጳሳትም ደግሞ እባካችሁ ዝምታውን ሰብራችሁ በመውጣት ይህ እግዚአብሔርን ፈልጎ ለማግኘ ከደብር ደብር በዚህ ጡንቸኛ ማህበር ስም የሚንከራተተው ምእመን እንዲያርፍና ከአሳራፊው ጋር እንዲገናኝ ሃላፊነታችሁን ተወጡ፤ እረፉ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ ያለው ጌታ ቃሉን እንደ ሰው ለውጦ ከገዳም ገዳም ባዝኑ አላለምና።
በፖለቲካው መስክ የሚተራመሰው የህብረተሰብ ክፍል በዘር በሽታ ተልክፎ ለፖለቲካው ፍጆታ ሲል በዚህ አብሮ በኖረ ሕዝብ መካከል ይህን የዘር በሽታ መርዝ በማሰራጨቱ ምክንያት ወገናችን በሙሉ በማያባራ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ገብቶ እየተሰቃየ ባለበት በዚህ ሁኔታ ላይ ይህን የመሰለ የሃይማኖት ጦርነት ማወጁ ለማን ጥቅም ነው? በእውነትስ የኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን እውነተኛ ተቆርቋሪና ወዳጅ ማነው? ወዘተ ለመሳሰሉት ጥያቄዎች በመረጃ የተደገፈ መልስ ሁላችንም በመስጠትና ሚናችንን በመለየት ለሃገርና ለወገን ዘለቄታ ጥቅም በእውነት ለእውነት መነሳት አለብን እላለሁ፤ ሁላችንንም ሊበላ ያለ እሳት በዚህ መልኩ በየዋሁ ወገናችን መካከል ያውም በመንፈሳዊ አስተማሪዎች ነን ባዮች ሲጫር እያየን ቸል ልንለው አይገባምና በአለንበት አካባቢ ጉዳዩን አንስተን በመወያየት አቋም መውሰድ ይገባናል እላለሁ። እስቲ በዚህ ጉዳይ ላይ አቋም ከመውሰዳችን በፊት ማን? ማነው? ምንስ እየሠራ ነው? የሚሉትን ዋና ዋና ጥያቄዎች ለመመለስ የምህረትአብ አሰፋን ቡድን አስተምህሮና የተከሳሹን የተሃድሶን ወገን አስተምህሮ የሁለቱም መንፈሳዊ የክርስትና ትምህርት መሰረት ዋና መመሪያ በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ሚዛንነት አብረን እንየው፡
1/ ጦርነትን ያወጀው የምህረትአብና የመሰል ጓደኞቹ አስተምህሮ፡
- እኛ ሃይማኖታችን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እንጂ ክርስቲያን አይደለንም፣ (ዩቲዩብ ላይ የምህረተአብ ትምህርትን ያዳምጡ)
- የአዳም ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ነበር ይላሉ፣
- የአባታችን የአዳም አባት አፈር ስለሆነ አፈር አያታችን ነው፣
- ስለዚህ ኦርቶዶክስ ቀጥተኛና እውነተኛ ሃይማኖት ስለሆነች ተሃድሶ ጨርሶ አያስፈልጋትም (ቃሉ ብቻ ይሰበክ=ተሃድሶ)
- ልብሳችንን ለብሰው ተሃድሶ ብለው የተነሱት የአባቶቻችንን ሃይማኖት ለማጥፋት የተነሱ ናቸው ይላሉ (ቤተ ክርስቲያኒቱ ወልዳና አስተምራ ያሳደገችን ልጆቿ ስለሆን እንደ ፊተኛ ወገኖቻችን አኩርፈን ወይም እነ ምህረተአብ ባርከው ባልተረዳው ወገናችን እጅ የሚወርድብንን የድንጋይ በረዶ ፈርተን በመውጣት ወደ ሌላ ቤተ እምነት በመኮብለል እናት ቤተ ክርስቲያናችንን የወላድ መካን አናደርጋትምና የሚወጣው ይውጣ እንጂ እኛ አንወጣም፤ ልብሱና ቆቡም ቢሆን የምንወዳት እናታችን ያለበሰችን እንጂ እነምህረተአ ሲፈልጉ የሚቸሩን ካልፈለጉ ደግሞ የሚገፉን እርጥባን አይደለም ይላሉ ተሃድሶዎች) ወዘተ
2/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ማህበር፡
- ቤተ ክርስቲያናችን ከተመሰረተችበት የወንጌል ተልእኮ ወጥታለችና ወደ ቀደመ የወንጌል ቃል ትመለስ ይላሉ
- የተሐድሶ ጥያቄ የቀደሙ የቤተ ክርስቲያኒቷ ሊቃውንትና መነኮሳት የጀመሩትና የሞቱለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ እንጂ ዛሬ የተጀመረ ጉዳይ አለመሆኑን ይናገራሉ
- ሕዝባችን ሊማርና ሊሰበከው የሚገባው ሕይወት፣ ፍቅርና ሰላም ሰጪ የሆነው የክርስቶስ ወንጌል ብቻ እንጂ መርገምን የሚያስከትል ልዩ ወንጌል መሆን የለበትም በማለት ይሟገታሉ፣
- ቤተ ክስቲያኒቷ ከመናፍስት ጠሪዎችና ከልዩ ወንጌል ሰባኪዎች በቃሉ ብርሃን ትጽዳ፣
- ቤተ ክርስቲያኒቷ ንጹህ ወንጌል ባለመስበኳ ምክንያት የቃሉ ራሃብተኛ የሆኑት በርካታ ልጆቿ ወደ ሌላ ቤተ እምነት በመኮብለል የወላድ መካን የሆነችበትን ችግር የተመለከተ አምላካችን በመንፈሱ ያመጣውንና በራሷ ልጆች ትከሻ ላይ የጣለውን ሰማያዊ አደራ እስከ ነፍስ ህቅታ ድረስ ዋጋ በመክፈል ቤ/ክርስቲያናችን የሚገሰጸውን እየገሰጸች የሚባረከውን ደግሞ እየባረከች በምድራችን ላይ የጽድቅ ተጽእኖ የምታመጣ ታማኝ የሰማይና ያገር እንደራሴ እንድትሆን ሳንታክት እንሠራለን ይላሉ፣
- በምድሪቱ ውስጥ ያለው ሁለንተናዊ የሕይወት ችግራችን ምንጩ መንፈሳዊ ሕይወታችን ከእግዚአብሔር ህያው ቃል በመራቃችን ስለሆነ ክርስቲያናዊ ታሪካችን ከማንም ሃገርና ሕዝብ በፊት እጃችን በገባው መጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ይመዘን ይላሉ፣
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ወዳጅና ጠላት ማን እንደሆነ በሲኖዶሱ፣ በሊቃውንት ጉባኤውና በምእመኑ ፊት በግልጽነት ታውቆ ሁሉም አቋም እንዲኖረው ለማድረግ የሚያስችል መድረክ እንዲዘጋጅ ይፈልጋሉ፣
- ባለው ሕግ መሰረት ፈቃድ አግኝተን ታሪክ የጣለብንን አደራ አሳድጎ ላስተማረን ወገናችን ለማበርከት በግልጽ በመንቀሳቀስ ላይ ሳለን የሥጋ ጉልበትና አቅም ያለው ሁሉ በተገኘው አጋጣሚ የበሬ ወለደ መርዝ በየዋህ ወገናችን መካከል በመርጨት ለጦርነት የማነሳሳቱን ኢሕጋዊ ሥራ መንግሥት ተከታትሎ ሕጋዊ እርምጃ ካልወሰደ አደጋው ለሁሉም ስለሚሆን የሰላም ሰዎች ሁሉ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡት የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ በአጽንዖት ያሳስባል!!! (የሚከተለውን ሊንክ ለመረጃ ይመልከቱ፡)
ጥብቅ ማሳሰቢያ
ይህን ጽሑፍ የምታነቡ ወገኖች እባካችሁ ለዚህ እውነተኛ መነፈሳዊ መሪና አስተማሪ ለሌለውና በአስመሳዮች ትክሻው ለጎበጠው ሕዝባችን መትረፍና ማረፍ ለእውነት በእውነት በዚህ ጉዳይ ላይ ላልሰማ እያሰማን በጋራ እንነሳ???
የእውነት አምላክ የሆነው እግዚአብሔር ሃገራችንን/ሕዝባችንን ይጠብቅ
እውነቱ ይነገር: eunethiwot@gmail.com
ከዝግጅት ክፍሉ፣ ይህ ጽሁፍ ሃይማኖታዊ ይዘት ያለውና የግለሰብን ስም የሚጠቅስ በመሆኑ ጎልጉል የየትኛውንም ወገን የሚደግፍ ወይም የሚቃወም አለመሆኑ እንዲታወቅ ይሁን። በጠየቅነው መሠረት የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ይህንን ጽሁፋቸውን ለመምህር ምህረተአብ በፌስቡክ ገጻቸው በኩል መላካቸውን ለጎልጉል አረጋግጠዋል። መምህር ምህረተአብ ለዚህ ጽሁፍ ምላሽ ካላቸው የምናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን።
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
የአርዮስ ፍሬዎች
መልስ
“ለሌላ አደገኛ የጦርነት አዋጅ በወገናችን ላይ ታወጀ”
ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ በጎልጉል ድረገጽ ላይ እራሳቸውን ተሃድሶ ብለው በሚጠሩ ነገር ግን እውነተኛ ማንነታቸው ለሰወሩት ወይንም በማንነታቸው ለሚያፍሩት ፣ የምንፍቅና አቀንቃኞች መልስ ይሆን ዘንድ ነው ። በመምህር ምህረተአብ ላይ ላቀረቡት ትችት ከሞላ ጎደል መልስ ይሆናቸዋል ብዬ አምናለሁ ።
ጸሃፊው ፤ አቤቱታውን ሲያሰማ እንዲህ ይላል ፤ ተወልደን ባደግንበት ኦርቶዶክስ በቴ ክርስትያን “የፍቅር ምሳሌ ሊሆኑ በሚችሉ አገልጋዮች ላይ የጦርነት አዋጅ ታወጀብን” ተወልደን ያደግንበት ከማለት ፤ ተዘርተን የበቀልንበት ቢል ማንነቱን ይበልጥ ይገልጸዋል ብዬ አምናለሁ ። የመወለድና የመዘራት ትርጉሙ ካልገባቸው ለማለት ነው ። ሲጀመር ይህች ቤተ ክርስቲያን ባጎረሰች የተነከሰች ለመሆኗ ጸሃፊው እራሱ ይክደዋል ብዬ አላምንም ። የሉተር ፍልፍሎችና ቅፍቅፎች ፤ እንዲሁም የመለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ በመባል የሚታወቅ ዘላንና ሰካራም ወያኔ በለስ ቀንቶአቸው ኢትዮጵያን ከተቆጣተሩበት ጊዜ ጀምሮ አማራንና ኦርቶዶክስን አከርካሪውን ሰበርነው ፤ እያሉ ያወጁትንና የፎከሩበትን ተግባራዊ ለማድረግ ምኞታቸውን ከግብ ለማድረስ የሰሩት የስራ ውጤት ነው ። ምንም እንኳን ቢማርና ቢያውቅም ሆዱ ጭንቅላት የሆነበት አለማዊ ንዋይና ዝና ያሰከረውን ሟቹን አባ ዲያቢሎስን በቤተ ክህነት አናት ላይ አስቀምጠው አገር ማፍረስ ብቻ ሳይሆን አምነታችንንም ከስር መንግሎ ለመጣል እራሳቸውን ተሃድሶ ብለው በሚጠሩ አፍቅሮተ ንዋይ ያሸነፋቸውንና ሆድ አደር ወፍ ዘራሾችን በማሰባሰብና በማደራጀት ከምን ግዜውም በላይ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ እንደተነሳሱ ይስተዋላል ።
የምእራባውያን ንዋይ በገፍ በሚፈስላቸው ፤ የበግ ለምድ የለበሱ አሳዊ መሲሆች ፤ መጽሃፍ ቅዱስን በመሰረዝ ፤ በመደለዝ ፤ የሌለ በመጨመር ፤ ቀላል አማርኛ በሚል ቅጥ አንባሩ በጠፋ መጽሃፍ ቅዱስ ተብዬ በማወናበድ ፤ አዲሱን ትውልድ በየመድረኩ በሚወራጩ ፤ በሚደንሱ ፤ በሚንፈራገጡ ፤ ትያትረኞች ትርጉም የለሽ የአጋንንት ልሳን ትርኪ ምርኪ እየዘላበዱ ብዙዎችን ይዘው እንደጠፉ ቢታመንም ፤ “የፈሲታ ተቆጢታ” ሲሆኑ ግን ሊነገራቸው ይገባል ።
ሲጀምር ቀና የሚያደርግ መንፈስ ቅዱስ እንጂ በየመድረኩ የሚዘርርና አረፋ የሚያስደፍቅ መንፈስ የጨለማው መንፈስ ካልሆነ ሌላ ሊሆን አይችልም ። ልሳኑም ቢሆን የሻምፓራራ ድግግሞሽ እራሱ ተናጋሪው የተናገረውን የማያውቀው ፤ የማይሰማ ፤ የማይተረጎም ፤ ቢተረጎመምም በየጊዜው አንድ የተለመደ ቃል እየቀባጠሩ ዛሬ የሚተረጉመው ሌላ ፤ ነገ የሚተረጉመው ሌላ ፤ ስለሆነ ምንጩ ማን እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ የልጆች ጨዋታ ስለሆነ በግድ እኛን ካልመሰላችሁ ካልወረዳችሁ ብሎ ሙግት አብረን እንውደቅ ካልሆነ በቀር ሌላ ምንም ሊሆን ስለማይችል እዚያው በጸበላችሁ ።
በመጨመር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ባሉበት ለመከራከርም ጥያቄ ያነሳል ጸሃፊው ፣ በውነት እነዚህ አዋቂ ነን ባዮች የያዙትን ወንጌል በርግጥ አንብበውት ያውቃሉ? አይመስለኝም! ከሆነ ግን እምነት ለመከራከሪያ እንዳልሆነ ተጽፏል የተጻፈን እንኳን አንብቦ መረዳት የተሳናቸው ፤ የዞረባቸው እንደሆነ ከጽሁፉ በቀላሉ መረዳት ይቻላል ። ብታምን ታምናለህ ፣ ባታምን ወደመሰለህ ትሄዳለህ እንጂ ካንተ ጋር ተቀምጦ የሚከራከር የሚሟገት አይኖርም ። እምነት መከራከሪያ አለመሆኑን ስታውቁ ፤ ያኔ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትክክለኛ እምነት እንደሆነች ትማራላችሁ ብዬ አምናለሁ ።
ጸሃፊውም ሆነ መሰሎቹ አንድ ሊያውቁት የሚገባ ነገር ቢኖር ኢትዮጵያ መላው ዓለም በተለይም የመናፍቃኑ መሪዎችና አቀንቃኝ የሆኑት ምዕራባውያኑ ድንጋይ እየቀረጹና እንጨት እየፈለጡ በሺ የሚቆጠሩ ጣኦታትን በሚያመልኩበት ዘመን ኢትዮጵያ አንድ አምላክ ብላ በስነ ልቦና ፈጣሪን የተቀበለች ፤ ከዚያም በኦሪት ዘመን ብሉይ ኪዳንን የተቀበለች ፤ ከጌታችን ከመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ በኋላም አዲስ ኪዳንን በመቀበል በትክክለኛው እምነትና መንገድ ጸንታ የኖረች ወደፊትም እስከ ምፅዓት በዚሁ በጸናው እምነቷ ጸንታ እንደምትኖር እነ ፍራሽ አዳሽ ሳይሆኑ ዓለም የሚመሰክርላት እና ሊያውቀው የሚገባ የማይታበል ሃቅ ነው ። የመናፍቁ አባትና መሪ እንኳን ከክህደቱ በፊት ለ 1,500 ዓመታት ኦርቶዶክስ ስታስተምረው እንደቆየችና በማናቸውም ነገር እንደምትቀድመው ፤ እንደምትበልጠው እንዴት ሊሰወርባቸው እንደቻለ ግልጽ አይደለም ። ዛሬ ዛሬ “ከኋላ የመጣ አይን አወጣ” ወይንም “ምጥ ለናቷ አስተማረች” ሆነና ውሃው ሽቅብ ካልፈሰስኩ ብሎ ይሞግታል ።
ሌላው የቤት ክህንትን ልብሰ ተክህኖን መዝረፍን በተመለከተ ይሆናል ። ይህም ምንም ከእውነት የራቀ አይደለም ፤ እርግጥ የቤተ ክህነትን ልብሰ ተክህኖና የቀሳውስቱን አለባበስ ይሄው አራሱን ተሃድሶ ብሎ የሚጠራው የጴንጤው አቀንቃኝ አለአግባብ ሲጠቀሙበት ይስተዋላል ። ከመደበኛው ጴንጤ ምንም የሚለያቸው ነገር ሳይኖር ለምን እራሳቸውንም ኦርቶዶክስ ብለው እንደሚጠሩ ከማንም የተሰወረ ባይሆንም ዋና አላማው ምዕመኑን ለማሳሳትና ለማወናበድ ቀላል ዘዴ ሆኖ ስለተገኘ ነው ። ስብከታቸውም ሆነ እምነታቸው እንዳለ የጴንጤው እንደሆነና ውሎና አዳራቸውም ከነሱ ፓስተሮችና ተከታዮቻቸው ጋር እንደሆነ ያደባባይ ሚስጥር ነው ። አለባበሳቸውንም እንደ መሰል ፓስተር ጓዶቻቸው ሱፍና ከረባት እንዳይለብሱ የኦርቶዶክን ቆብና ቀሚስ ያስፈለገበት አብዩ ምክንያት አሳቹ ተኩላ በግ መስሎ መምጣቱ የግድ ስለሆነ ነው ። አላማውን ለመገንዘብ እምብዛም ምርምር አያሻም ። በማናቸውም መንገድ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን አስመስሎ መቅረቡ ተቀባይነትን ሊያስገኝላቸው ስለሚችል የተኩላው መመሳሰል ግድ ይላል ። እሱ ብቻም ሳይሆን ተኩላው አስመስሎ ሊመጣና ብዙዎችን እንደሚያስት የተነገረውም ትንቢት ይፈጸው ዘንድ የግድ ነውና ።
ተኩላው በሚገርም ሁኔታ የጌታችን የመድሃኒታችን እናት የሆነችውን የድንግል ማርያምን ምስል ከሚሰበሰቡበት መጋዘን ከሰባኪያቸው ጀርባ ለምዕመናን በግላጭ እንዲታይ አድርጎ ማስቀመጥ አንዱ የማሳቻ ዘዴያቸው ሲሆን ፤ እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን ነገር ቢኖር ግን ስዕሏን ያስቀምጡ እንጂ ስለእመቤታችን ድንግል ማርያም በድንግልና መውለድና ፤ በድንግልና ለዘለዓለም የጸናች መሆኗን ፤ አማላጃችን መሆኗን ፤ የማይተነፍሱ ነገር ግን ስዕሏን አላግባብ በማስቀመጥ ፤ የዋሃንን ለማሳት ፤ አይነተኛ ዘዴ አድርገው ሲጠቀሙበት ይታያል ። ከዚህ ቀደም እንደምናውቃቸው መናፍቃን በግላጭ ድንግልን ፤ መላይክትንና ጻድቃንን ከመስደብ ተቆጥበው ዋና ጨዋታ አድርገው የያዙት ፤ ጭራሽ ስማቸውን ባለማንሳት ምስላቸውን ብቻ እያሳዩ ኦርቶዶክሳዊ መስሎ በመቅረብ ፤ ገድላቸውን በማዳፈን ፤ አማላጅነታቸውን ባለመመስከር ፤ የማስረሳትና የማዘናጋት ጨዋታ እየተጫወቱ እንደሆነ ለብዙሃኑ አስተዋይ እና ብሩህ አይምሮ ላለው ኢትዮጵያዊ የማይሰራ ተራ የመንደር ትያትር እየተገበሩ እንደሆነ ነጋሪ ቢያገኙና ቢነገራቸው አካሄዳቸውን ለማስተካከል ይረዳቸው ይሆናል ።
በጣም አሳዛኙ ተግባራቸው ግን እየገረፉ ለምን እንደሚያለቃቅሱ ሊገባኝ አልቻለም ። እንደሚታወቀው ተሃድሶ ተባለ ጴንጤ ያንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች እንደሆኑ ጸሃፊው እራሱ እንደማይክደው አምናለሁ ። ታዲያ ለምን ኦርቶዶክስ ተዋህዶን መስሎ መቅረብ አስፈለገ? ሁለተኛ መቼም አንድ ሰው ወይንም ቡድን በማይመስለው እምነት አዳራሽ ገብቶ የራሱን የእምነት አመለካከት እንዲሰብክ በማናቸውም የእምነት ተቋም እንደማይፈቀድ የማያውቅ ይኖራል ብዬ አልገምትም ። ታዲያ የኛ ፍራሽ አዳሾች ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤት ምን ይሰራሉ? ድርሽ እንዳይሉ ተከልክለውም ከሆነ አግባብ ነው እላለሁ ። በሶስተኛ ደረጃ ይሄው የበግ ለምድ ለባሽ ለምን በየጴንጤው መጋዘን ይሰብካል? ተጋባዥ እንግዳ ሆኖ ይቀርባል? ለምንስ መደበኛው ጴንጤ ተሃድሶ ተብዬውን ሊያጠናክረው የገንዘንና የቁሳቁስ እርዳታ ያደርግለታል? ይሄንን እውነታ ፈጥሬ ሳይሆን በትንሹ አኔ በማውቀው ቅዳሜ ቅዳሜ (8:00AM to 11AM eastern US standard time) በምስራቃዊ አሜሪካ ሰዓት አቆጣጠር ጠኋት ስምንት ሰዓት ላይ የጀመረ አስከረፋዱ አስራ አንድ ስዓት ድረስ (Ethiopian christian plus all) በሚባል የጴንጤዎች የፓል ቶክ ክፍል ውስጥ ፕሮግራም ተይዞላቸው ኦርቶዶክስን ሲሰድቡና ሲያሰድቡ ፤ ድንግልንም ሆነ መላይክትን እንዲሁም ጻድቃንን ሲያንጓጥጡ እንደሚውሉ ማንም ኢትዮጵያዊ የሆነ እዚህ የመናፍቃን የፓል ቶክ ክፍል በመምጣት የፍራሽ አዳሹን እውነተኛ ማንንነት ማወቅ ይችላል ።
ታዲያ ይህ ሁሉ እውነታ ስለናንተ እየታወቀና እያለ ሁለት ቦታ መረጋገጡ ምን ለማምጣት ነው እነ ተሃድሶ? እስቲ ጥያቄያችሁን በጥያቄ ልቅረበው ። ለምን ሁሉ አማረሽ ሆናችሁ? ስለምንስ አንድ ቦታ መርጋት አቃታችሁ? ስለምንስ የኦርቶዶክስን ስም መዋስ አስፈለጋችሁ? እውነተኛ ማንነታችሁን የማያውቅ ያለ ይመስላችሁ ይሆን? ከሆነ በርግጥ በጣም የዋሆች ናችሁ ።
አምነት የመዳን ጉዳይ እንጂ ፣ የቲፎዞ ወይንም የደጋፊ መብዛት ጉዳይ ከመሰላችሁ እጅግ በጣም ተሳስታችኋል ። መንግስተ ሰማይ በቲፎዞ ብዛት ሳይሆን የምትወረሰው በእምነትና በተግባር አንደሆነ የያዛችሁትን ወንጌል መመርመር ያሻል ። ስለሆነ በየጴንጤው መጋዘን ደጋፊ ፍለጋ መንጦዝጦዝና ደጅ መጥናት የመንግስተ ሰማይን ደጃፍ አያስከፍትም ምድራዊ አንቱታን ከሆነ ይቻል ይሆናል ያውም የከንቱ አንቱታ ።
ታዛቢው
መቼም ይህ ድረገጽ በዚህ አቋሙ በመጽናት የኔንም አስተያየት ለንባብ ያበቃልኝል ብዬ አምናለሁ ።
ከዝግጅት ክፍሉ፣ ይህ ጽሁፍ ሃይማኖታዊ ይዘት ያለውና የግለሰብን ስም የሚጠቅስ በመሆኑ ጎልጉል የየትኛውንም ወገን የሚደግፍ ወይም የሚቃወም አለመሆኑ እንዲታወቅ ይሁን። በጠየቅነው መሠረት የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ይህንን ጽሁፋቸውን ለመምህር ምህረተአብ በፌስቡክ ገጻቸው በኩል መላካቸውን ለጎልጉል አረጋግጠዋል። መምህር ምህረተአብ ለዚህ ጽሁፍ ምላሽ ካላቸው የምናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን ።
»> አርዕስቱና ትንታኔው የነገሩ ጭብጥ ተበታተነ!
“በመልካም አስተዳደር እጦት ለዘመናት እየተሰቃየ ባለ ሕዝብ ላይ ሌላ የሃይማኖት ጦርነት! ያ አዳሜ በሰይጣን ኮከብ በሃይማኖት ነጻነት እንዲህ እየተቆላህ!?
https://youtu.be/tJc80tgJnBg
“እስቲ ተመልከቱ! ፍቅርና ጥል፣ ሐጢአትና ጽድቅ፣ ክርስቶስና ዲያብሎስ፣ ሞትና ሕይወት፣ ሥጋና መንፈስ፣ ጦርነትና የሰላም ወንጌል መቼ ነው አብረው የሚሄዱት? ምናልባት ለምህረተአብ አዲስ ግኝት ወይም መገለጥ መስሎት ይሆን? ግን እኮ ሰይጣንም የብርሃን መልአክ መስሎ አይደል የሚመጣው?
‘ጥብቅ ማሳሰቢያ
“ይህን ጽሑፍ የምታነቡ ወገኖች እባካችሁ ለዚህ እውነተኛ መነፈሳዊ መሪና አስተማሪ ለሌለውና በአስመሳዮች ትክሻው ለጎበጠው ሕዝባችን መትረፍና ማረፍ ለእውነት በእውነት በዚህ ጉዳይ ላይ ላልሰማ እያሰማን በጋራ እንነሳ???
የእውነት አምላክ የሆነው እግዚአብሔር ሃገራችንን/ሕዝባችንን ይጠብቅ። አሜን!
ጎልጉሎች በተደጋጋሜ የኦርቶዶክስ ተዋህዶን የሚያረክስ ጽሁፍ ለምን እንደምታወጡ አይገባኝም?ይህ የሚያሳየው ሙሉ ለሙሉ ፀረ-ኦርቶዶክስ መሆናችሁን ነው።ለምን?ከዚህ በፊት በመረጃ ስለ ግንቦት7 እና ኢሳት ሰዎች በስም በመጥቀስ ስልክላችሁ የግለሰቦችን ስም ማውጣ ትክክል እንዳልሆነ በመግለፅ የላኩላችሁን ጽሁፎች ውድቅ ማድረጋችሁ የማትክዱት ነው።ዛሬ ግን በዲያቆን ምርእተአብ ላይ ፀያፍ አባባሎች እንደወረደ ስታቀርቡ በውጭ የምትኖሮ ጋዜጠኛ ተብየዎች ህሊና የሚባል ነገር እንዳልፈጠረባችሁ ይህ ተጨባጭ መረጃ ነው።እንዲህ ያለ ነግር ተልኮ ያለው “ከእናት ጡት ነካሾች” የሚጠበቅ በመሆኑ የሚገርመን አይደለም።
አንተነህ ጌትነት ሙላቱ
“አትንኩኝ ባይነት” ካልሆነ በስተቀር ስለ ጎልጉል የጻፉት የተሳሳተ ሃሳብ ነው። “ጸረ-ኦርቶዶክስ” የሚለው አባባልዎ ቢያንስ በየጊዜው እየተላከልን የምናትመውን የቀሲስ አስተርአየን እና የወንድሙ መኰንን ጽሁፍ ያላነበቡ መሆንዎን ነው።
በጽህፉ ላይ ስለ መምህር ምህረተአብ የሠፈረ ምንም “ጸያፍ” ቃል አላገኘንም። ሌላው ጸሃፊው ይህንን ጽሁፋቸውን ለመምህር ምህረተአብ ልከውላቸው እንዲደርሳቸው ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪ ይህንን ብለናል:
ከዝግጅት ክፍሉ፣ ይህ ጽሁፍ ሃይማኖታዊ ይዘት ያለውና የግለሰብን ስም የሚጠቅስ በመሆኑ ጎልጉል የየትኛውንም ወገን የሚደግፍ ወይም የሚቃወም አለመሆኑ እንዲታወቅ ይሁን። በጠየቅነው መሠረት የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ይህንን ጽሁፋቸውን ለመምህር ምህረተአብ በፌስቡክ ገጻቸው በኩል መላካቸውን ለጎልጉል አረጋግጠዋል። መምህር ምህረተአብ ለዚህ ጽሁፍ ምላሽ ካላቸው የምናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን።
ከዚህ ሌላ እርስዎ ስለጠቀሱት ጽሁፍ አሁን የምናስታውሰው ባይኖርም የግለሰቦች ስም እየተዘለፈ ወይም እየተከሰሰ የሚጻፍ ጽሁፍን አናትምም። ነገር ግን የሰዎችን ርዕዮት (አስተሳሰብ) ትክክል አይደለም በማለት ሃሳባቸውን በጨዋነት የሚገልጹ ጽሁፎችን እንደ አጻጻፋቸውና ሃሳብ አገላለጻቸው እየገመገምን እናትማለን። የተጻፈባቸው ሰዎች ፅሁፉን የሚያነቡበትንና ከቻሉም ምላሽ የሚሰጡበትን መንገድ እናመቻቻለን። ለዚህ ደግሞ ሥራችን ምሥክር ነውና ሌላ ምስክር ወይም ዋስትና አንፈልግም።
መርሳት የሌለብዎ ይህ በነጻ ለሕዝባችን የምንሠጠው አገልግሎት ነው እንጂ ተቀጥረን በትዕዛዝ የምንሠራው አይደለም።
አሁንም ጽሁፍ ካለዎት ያቅርቡ – ሃሳብን በሃሳብ ይሞግቱ። የሰውን ስብዕና ሳይነካ ሃሳብን አብጠጥሮ መቃወምን በጣም እንደግፋለን።
ከሰላምታ ጋር
የጎልጉል አርታኢ
መንግስት፣ ህዝብን ለእልቂት በማነሳሳት
ላይ ነህ በማለት በአገሩቱ ህግ መሰረት
ለምን አይጠይቅም ወይስ
በቄስ ላይ ሕጉ አይሠራም ማለት ነው
ሣይቃጠል በቅጠል ይባላል ።
አጨር ቃል ተሐድሶ የሚባል ነገር የለም መናፍቃን ናቸው። ሰርገው የገቡ የተደበቁ መናፍቃን። ይህንንም ወያኔ ውስጥ ያሉ መናፍቃን ጠቅላይ ሚኒስትር ተብዬ እና ሌሎቹም መናፍቃን የሚደግፉት በጎጥ ምክንያትም በቤተክህንት ያሉ ጳጳሳት የሆኑና ለዚሁ ስራ ሰርገው የገቡ የቤተክህንት ሰራተኞች የሚደግፉት ኢትዮጵያን እና የ ኦርቶዶክስ እምነትን ለማዳከም የታቀና እየተሰራ ያለ የመናፍቃን እንቅስቃሴ ነው። መ. ምህረተ አብያወጀው ቤተክርስቲያን ማወጅ የነበረባትን ነው። የፈለጋችሁተን እዛው ውጡና አምልኩ። እኛ የምናመልከውን እናውቀዋለን። ድንግል ማርያም ቅዱሳን መላእክት አማላጆች ናቸው። ስለ እነርሱም ይሰበካል። እኛ በተሰቀለው አምላክ በሆነው በሚፈርደው አማላጅ ባልሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን። እናንተ በሃሳዊ መሲህ እመኑ።
የሥጋ ወንድሞቼ፡
1) ታዛቢው፣
2) በለው፣
3) አንተነህና
4) እውነት
ምነው ”የምጣዱ ቀርቶ የእንቅቡ ተንጣጣ” እንደሚባለው የጦርነቱን አዋጅ በየዋሁ ወገናችን መካከል በይፋ ያወጀው መምህር ምህረታብ ደብዳቤው በፌስቡክ ደርሶት አንዳች ነገር ትንፍሽ ሳይል እናንተ ያልተወከላችሁ ጠበቆች ብቻ መድረኩን የቅቤ ገበያ አስመሰላችሁት?
እስቲ ለራሳችሁ ላልተበከለ ህሊና የሚከተሉትን ጥያቄዎች በፍቅር ላቅርብላችሁ፡
1) ይህን በወገናችን ላይ በመረጃ የተደገፈ የጦርነት አዋጅ ስትደግፉ በኦሮሞና በአማራ ላይ የተደረገውንና እየተደረገ ያለውን ጦርነት መቃዎም የምትችሉበት ሌላ ተለዋጭ ህሊና አላችሁ ማለት ነው? ወይስ የጠመጠመና መስቀል የያዘ ሰው ካወጀው ዓይናችሁን ጨፍናችሁ ቢሆን አሜን በሉ ነው የምትሉን? ይህን ደግሞ እግዜር እራሱ ቃሉን ባስተላለፈልን በመጽሐፍ ቅዱስ ዮሐ 13፡17 በማወቅና በማድረግ እንድንከተለው በመንፈሱ ስላስተማረን ለእኛ ጨርሶ አይመቸንም፤
2) ወንጌለ ክርስቶስ፡
”በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም”/ዘካ 4:6/፣ ”ሰይፍ የሚያነሱ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ” /ማቴ 26፡52/ እና ”ሰላምን እተውላችኋለሁ፣ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም”/የሐ 14፡27/ የሜል የፍቅርና የሰላም ወንጌል ሆኖ ሳለ ሰውንና ቅርስን የሚበላ ጦርነትን ማወጅና መደገፍ ከየት ተማራችሁት? ምናልባት ታዛቢው በስም አባ ዲያብሎስ ብለው በጽሁፋቸው እንደጠቀሱት በዮሐ 10፡10 ላይ ”ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ፣ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም” የተባለለትን የሰውና የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ምናልባት እየደገፋችሁ እንዳይሆን እሰጋለሁ??? እግዜር ነጻ ፈቃድ በመስጠት ውብ አድርጎ ቢፈጥረንም የመሰላችሁን መደገፍና መቃወም ግን መብታችሁ ነው!!! /ሞት ወይም ሕይወት?/
3) እራሳችሁን የኦርቶዶክስ ዋና ወዳጅና ተቆርቋሪ! ሌላውን ኦርቶዶክስ ሃይማኖትንና ቅርስን አውዳሚ አድርጋችሁ የፈረጃችሁበትን ስልጣን ማን ሰጥቷችሁ ነው? በቤተ ክርስቲያኒቷ ውስጥ ተወለደው ያደጉትን ሊቃውንት ውጡና ግቡ የምትሉት? እንደ እነ አለቃ ታየ ያሉ አባቶቻችን የወንጌል ቃል ብቻ ይብቃ! ካስፈለገም በበሬ ወለደ ወሬ ሕዝቡን የእንጀራ መበያና ከብር ማስጠበቂያ ከማድረግ የራሷ የቤተ ክርስቲያኒቷ መጽሐፍት በአትሮንሱ ላይ ተዘርግተው ዓይናማ በሆኑ የድጓ፣ የቅኔ፣ የዜማ፣ የመጻሕፍት፣ የአቋቋም ወዘተ መምህራን ፊት በሰከነ መንፋስ ነገሩን እንወያይበት ማለታችንን ታዛቢው ክርክር ሃጤአት ነውና አይቻልም የሚል መሸፈኛ አቅርበዋል! ማን ምን እንደሆነ ሕዝቡ ይወቅና የራሱን ምርጫ እንዲወስን እድል ይሰጠው የሚለውን ጥያቄ ለምን ፈራችሁት???
4) እስከ መቼ ነው ጮሌዎች አንድ እውነትን ፈላጊና በራሱ የሚተማመን ኢትዮጵያዊ ለሃገሩና ለወገኑ ባለው ፍቅር ተቃዋሚዎች በሚደረጉት ስብሰባ ተሳትፎ ሲወጣ የተመለከተው የመንግስት ካድሬ በሚያቀርበው መረጃ ተመስርቶ መንግሥት ተቃዋሚ ነው ብሎ በመፈረጅ በወጣበት በገባበት እየተከታተለ መከራውን ሲያሳየው ተቃዋሚዎችም መንግሥት በሚያደርገው ስብሰባ የተካፈለን ሰው በዚያው መልኩ ጠልተው ሲያስጠሉና ስም ሲያጎድፉ ማየት የተለመደ ቆሻሻ የፖለቲካ ሥራ ሆኗል!!! ታዲያ እናንተ ወገኖቼ የኦንሊ ጅሰስ ተከታይ ከሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር እኛን በስላሴ የምናምንን የኦርቶዶክስ ተሃድሶን አማኞች አንድ አድርጋችሁ በመፈረጅ ለጥላቻችሁ መጠቀሚያ ስታደርጉት: ሀ/ የእምነት ልዩነቱን ጭራሺ የማታውቁ ”ጨዋ” ናችሁ ማለት ነው ? ለ/ ነው ወይስ ይህን ጉሉህ የእምነት ልዩነት ሕዝቡ ፈጽሞ አያውቅም በማለት ንቃችሁት? ሐ/ ወይስ ”ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ይሏታል ጅግራ” ከሆነ ነገራችሁ፡ ለመንስቱ ሥራ በመንፈሱ በእውነት ለእውነት የጠራንና የሚጠብቀን የአባቶቻችን አምላክ አይተኛም አያንቀላፋምና እስከ ነፍሳችን ህቅታ በዚህ ጉዳይ ላይ ፍቅር ብቻ ሳይሆን የሚባላ እሳት ጭምር የሆነው ጨካኙ ያስጨከነን መሆኑን ዛሬ ላይ ሆነን በሰማይ ፍቅር ስም እናረጋግጥላችኋለን!!!
5) በመጨረሻም በጎልጉሎች አሠራር ላይ ትችት ላቀረበከው አቶ ጌትነት ጎልጉሎች ከሰጡህ መረጃ በተጨማሪ የጋዜጣው ኤዲተር ስህተት ላለመሥራት ያደረገውን ሙያዊ ጥረትና ብቃት /professional ethics/ በማስረጃ ለማወቅ ከፈለጉ ከእኔ ጋር ያደረግናቸውን የኢሜል ሙግቶች ልልክልዎ እችላለሁና ኢሜልዎን ቢልኩልኝ ደስ ይለኛል!
ከዚህ በተረፈ ለሁለንተናዊ ችግሮቻችን በስነ ሥርዓትና በሰከነ መንፈስ ተወያይተን መፍታት የምንችልበትን ጊዜ እናፍቃለሁ!
አባቶቻችን አደዋ ላይ እየፎከሩ ቆመው ይተኩሱ የነበረው የወቅቱ የወንድነት መለኪያ ንቃተ ህሊና ስለነበረ ነውና፣
ወገኖቼ እባካችሁ እባካችሁ ዛሬ ላይ ቆመን ትናንትን ሚዛን አድርገን በመጠቀም:
ወደቀ ሲባል ተሰበረ!በማለት አትንኩኝ ወይም አትድፈሩኝ! ካልሆነ ያዙኝ ልቀቁኝ!በለው!አሳደው!ውገረው!
ለሚል የጦርነት አዋጅ በባለጉዳዩ ሳንጠየቅ ጥብቅና መቆም ሰውየው ንስሃ ገብቶ ከተመለሰ መቼ ጠየኳችሁ ሊል ይችላልና
ማስተዋሉና የራስ ህሊና ባለቤት መሆኑ ብልህነት ነው እላለሁ!!!!
ሊላው አፍ የሚጎርሰውን እጅ ይመጥነዋል እንዲሉ
አንደበታችሁን ስድብ ሳይሆን መልካም የሆነ ቃል!
የሚያስተምርና የሚያንጽ ቃል ተናገሩበት!
የሳተ ካለ መልሱበት !!!
***የጠ/ሚ/ሩንና የእኛን እምነት አንድ አድርጎ ያቀረበውን ሰው አስተያየት ጎልጉሎች መረጃ ቢጠይቁ ኖሮ አያወጡትም ነበር፤
እኔ ግን ባለማወቅ ከተነገረ መማማር ስለምንችል ማውጣችሁን ደግፊዋለሁ።
በተረፈ ወደዳችሁም ጠላችሁም እኛ ተሃድሶዎች እንደ እናንተው በኢትዮጵያ ምድር ያውም በኦርቶዶክስ ቤ/ክ ቅኔውን ከነሰሙና ወርቁ ጋር ቆጥረን የምናስቆጥር ተቀኝተን የምናስቀኝ ያገር ተወላጆች እንጂ ከሰማይ የመጣን ዩፎ በራሪዎች /ልዩ ፍጥረቶች/ አለመሆናችንና እንደ እናንተው ለሃገርና ለወገን የምናስብና የምንጨነቅ መሆናችንን ማሳወቅ እንሻለን!!! ካልተዋጠላችሁ ከእናንተ በተሻለ መለኩ ሰው ሁሉ በልቶት በሚረካበት ፍሬ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለምድራችን ቃል በገባልን ጌታ ስም በጸጋው በሆነ እምነት ስንገለጥ ታዩናላችሁ!!!! ለሁላችንም እድሜ ይስጠን???አሜን።
ዛሬም :
የእናንተው ወገን!
እውነቱ ይነገር ነኝ
ካለሁበት
አቶ ውነቱ ይነገር ባለፈው ትችቴ ተወልደን ባደግንበት ባልከው ጽሁፍህ ላይ ተዘርተን በበቀልንበት ብለህ ጽሁፍህን እንድታስተካክል ማሳሰቢያ አቅርቤ ነበር ነገር ግን አልሆነም ፣ አሁንም ስምህን እውነቱ ይነገር የሚለውን ቀይረህ ሃሰቱ ይለፈፍ ብትለው የተሻለ ማንነትህን ይገልጸዋል ብዬ አምናለኡና እባክህ ተመከር ። ነገር በጭራሽ የማይገባህ ግለሰብ እንደሆንክ በደንብ ተረድቻለሁ ፣ እራስን መቆለልና አንቱ በሉኝ የመናፍቅ ዋና መለያ ታፔላ እንደሆነ ይገባኛል ፣ አንተ መምህር ምህረተአብንም ሆነ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን ተንጠራርተህ ስትዘረጥጥ አንተን ማን ባለ መብትና ባለስልጣን እንዳረገህ የታወቀህ አትመስልም ሲጀመር ነገር የሚገባህ እንዳልሆንክ ነግሬሃለሁ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ለመምህር ምህረተ አብ ብቻ የተሰጠች ሌላውን የማያገባው አድርገህ ለመግለጽ መሞከርህ በራሱ ትንሽ አይምሮ እንዳለህ ፍንትው አድርጎ ያሳብቅብሃል ። ሲጀመር አሁንም እንደማይገባህ ባውቅም በድጋሚ እነግርሃለሁ ሃይማኖት መከራከሪያ ሳይሆን ግለሰብ በፈቀደበት የሚሄድበት ጉዳይ ነው እሳትና ውሃ ቀርቦልሃል እጅህን ወደፈቀድከው መስደድ መብትህ ነው ። መምህር ምህረተ አብም መልስ ያልሰጠህ ወይንም የማይሰጥህ ከዚህ በመነጨ አስተሳሰብ ሊሆን ይችላል ካልሆነም የምትናቅ ስለሆንክ ንቆል ሊሆን ይችላል ብዬ እገምታለሁ ።
አባ ዲያቢሎስ እንኳን ማንን እንደሚያመለክት ያልገባህ ሌላ ጠለቅ ያለ ሚስጥር ይገባሃል ብዬ ባልገምትም ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ኢትዮጵያዊ ወገኔ ነህና ላቀናህና ልደግፍህ እሞክራለሁ የለም አሻፈረኝ እንደ ርያ ከጭቃዬ ላይ ልንከባለል ተወኝ ካልክ ምርጫው አሁንም ያንተው ነው ። ነገር አይገባህም የምልህ እንዲያው ከመሬት ተነስቼ ሳይሆን እውነታው እሱና እሱ ብቻ ስለሆነ ነው ። ወንድሜ ሃሰቱ ይለፈፍ የዞረብህ እንደሆንክ ሃይማኖትንና ፖለቲካን ባንድ ላይ እየገመድክ ማቅረብህ ምን ያክል አርቆ የማያይ አይምሮ እንዳለህ አሁንም በድጋሚ ያሳብቅብሃል “ይህን በወገናችን ላይ በመረጃ የተደገፈ የጦርነት አዋጅ ስትደግፉ በኦሮሞና በአማራ ላይ የተደረገውንና እየተደረገ ያለውን ጦርነት መቃዎም የምትችሉበት ሌላ ተለዋጭ ህሊና አላችሁ ማለት ነው።” ስትል ትችትህን አቅርበሃል ፣ አየህ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ማለት ይሄ ነው ። እየተነጋገርን ያለነው ስለሰማያዊ እምነት እንጂ ስለ ምድራዊ ፖለቲካ እንኳን እንዳልሆነ አልገባህም በጣም ዞሮብሃል ፣ አማራ ኦሮሞ እያልክ በቅሎን ይመስል “አባትሽ ማነው ስትባል ፈረስ አጎቴ ነው” ያለችው አይነት አቀራረብ መቅረብህ የምታሳዝን ሳትሆን ሊታዘንልህ የሚገባ እንደሆንክ ምስክር ነው ። ይሄንን ላንተ ለማብራራት አልደክምም ነገር ግን የዘባረቅከውን መዘባረቅ ዝም ብዬ ባልፍም ባለማወቅህ ላይ ጭል ጭል የምትለውን የብርሃን ሻማ ከናካቴው ማጥፋት ስለሚሆንብኝ ለዘባረቅከው መዘባረቅ ባጭሩ አንድ ጥያቄ ብጠይቅህ ጥያቄው በራሱ መልስ ሊሆንህ ይችላል ብዬ አምናለሁ ጥያቄው ካልገባህ ያውቃሉ ያልካቸው አለቃ ማንትስ ያልካቸው ያንተ ሊቅ ዘንድ ሄደህ ይሄ ምን ማለት ነው ያብራሩልኝ በላቸው እሺ? ሲጀመር የአማራም ሆነ የኦሮሞ እንዲሁም የሌላው ብሄር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ እንዳለ ታምናለህ? በተመሳሳይ ሁኔታ አንዲሁ ከነዚህ ብሄር ብሄረሰቦች መካከል እንዳንተው መናፍቅ እንዳለ ታምናለህ? እኔስ አማራ ልሁን ኦሮሞ የምታውቀው ነገር አለህ? አየህ ለዚህ ነው አባትህን ስትጠየቅ ፈረስ አጎቴ ነው አትበል ያልኩህ ፣ የዚህን ጥያቄ መልስ ካገኘህ ነገሮች ገብተውሃል ማለት ነው ለጥያቀዬ መልስ ከሌለህ ግን ውሃ አልወቅጥም እያዘንኩ አሰናብትሃለሁ ። ውሃና ዘይትን ለመቀላቀል አትሞክር ሚስጥሩ ከረቀቀብህ አሁንም አለቃ ማንትስዬን ጠይቀህ ሚስጥሩን ለመረዳት ሞክር ።
አሁንም በድጋሚ አንተም በመጋዘንህ እኛም በቤተ መቅደሳችን ቃለ እግዚአብሄርን ሰምተን በልቦናችን ጽላት እንዲጽፍልን እንጸልይ እንጂ ክርክር የተፈቀደ አይደለም የያዝከውን ወንጌል (ወንጀል)አንብብ ፣ ሁሉም በያለበት የገባውን ያስተምራል ምዕመኑ የመሰለውን ይከተላል ። አንተ በያዝከው ወንጌል(ወንጀል)ላይ ባይኖርም እኛ በምንቀበለውና በምናምነው ወንጌል ላይ በይሁዳ መልዕክት ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፫ ላይ እንዲህ ይላል፣ “ወዳጆች ሆይ ስለምከፍለው ስለመዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ ለቅዱሳን አንድ ግዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ” ይላል አየህ ለእምነት ተጋደል ሲል አማኙን ሁሉ እንጂ ያልጠመጠመ ወይንም መምህር ምህረተአብ ካልሆነ ሌሎቻችሁ አያገባችሁም አላለም ለነገሩ የይሁዳ መልክት አንተ ላይ ስለሌለ ከየት አምጥተህ ታውቀዋለህ? ድከም ብሎኝ እንጂ ።
አንተ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሰበከችው ፣ አስተማረችው ፣ ወየው ብለህ ጭርጭር ያረገህ ከብዙ በጥቂቱ ከዚህ በታች ያለው እንደሆነ ይገባኛል ። አዎ በቀላል አማርኛ ተብሎ አረም ብቻ በሆነው ወንጀል ውስጥ የለም አታገኘውም ግን እውነታውና ሃቁ ያሳበደህ ይሄ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው ። ባለፈውም ጴንጤዎች ናችሁ እራሳችሁን አትደብቁ በራሳችሁ ተማመኑ የኦርቶዶክስን ልብሰ ተክህኖም ሆነ ስሟን አትጠቀሙ እዚያው ፓስተሮቻችሁን ስም አውጡልን በሏቸው ዳቦው ባይቆረስም ስም ይውጣላችሁ መናፍቃን የስም ችግር የለባቸው ይሄው ዛሬ በዓለማችን ላይ ከ33,000 በላይ ደርሰዋል ስለሆነም እናንተን 33,001 ያርጓችሁ ከሰው ትከሻ ውረዱ ።
በል እውነተኛውን ወንጌል ፈልገህ እነዚህን ጥቅሶች ተመልከት ቢያምህም ቢመርህም ቻለው መድሃኒት ጣፍጦም አያውቅ መረር ማለቱ አይቀርምና ተዳፍረህ ተቀበለው ።
ኦሪት ዘጽአት ፳፫፣ ፳ , ኦሪት ዘጽአት ፳፩ ፣ ፳፫ , ኦሪት ዘጽአት ፲፱፣ ፲፬ , ትንቢተ ዳንኤል ፲፪ ፣፲፮ , ትንቢተ ዘካርያስ ፩፣፲፪ , መዝሙር ፴፫ ፣ ፮ , መዝሙር ፴፫ ፣ ፳፩ መዝሙር ፴፫፣ ፲፭-፲፮ , መዝሙር ፻፩፩ ፣ ፮ , መጽሃፈ ምሳሌ ፲፣ ፮ , ማቲዮስ ፲፣ ፵-፵፪ , ወደ እብራውያን ፩፣ ፲፫-፲፬
ወንድሜ ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል ፣ ሆኖም ግን አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም ነውና በዚሁ ላይ አበቃለሁ ፣ እወቅ ያለው ባርባ ቀኑ ያውቃል አትወቅ ያለው ደግሞ ባርባ ዘመኑን ደንቁሮ ያደናቁራልና ድጋሚ አንተንና መሰሎችህን በተመለከተ አልመለስም ።
ታዛቢው
እውነቱ ይነገር ካልከንማ! ተመልከት ስማ ላልሰማም አሰማ!
https://youtu.be/xd3eZ2VtWR0
“የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ!”
፩) በኦሮሞና በአማራ ላይ የተደረገውንና እየተደረገ ያለውን ጦርነት መቃዎም የምትችሉበት ሌላ ተለዋጭ ህሊና አላችሁ ማለት ነው?
__ የፖለቲካ ሽቀላ ይቁም!ይህ በድሃ እሬሳና እንባ መሞላፈጥ ጀግና አያደርግም! “እኛ በምንኖርበት አካባቢ ፺፰ ከመቶ ሙስሊም ስለሆነ ቀና ብሎ የተናገረውን አንገቱን በሜንጫ(በቡጢ) ነው የምንለው ሲሉ የጀዋሪያን አብዮተኞች አብራችሁ በእየአዳራሹ ታሽቋልጣላችሁ እንጂ አርባ ጉጉ፡ በደኖን የታረደ ክእነነፍሱ ታስሮ ገደል የተወረወረውን ኦርቶዶክስ..ቤተክርስቲያን በላያቸው ላይ የተቃጠለባቸውንም ክርስቲያን ኦሮሞዎች አላዳናችሁም!?።
፪) የፍቅርና የሰላም ወንጌል ሆኖ ሳለ ሰውንና ቅርስን የሚበላ ጦርነትን ማወጅና መደገፍ ከየት ተማራችሁት?
___ ተነስ! ንቃ! እራስህን ከሰው በላ ጠብቅ ማለት..ከላይ በቪዲዎቹ ማስረጃ እንዳስቀመጠኩልህ.. በርህን አፍክን ከፍተህ ሀገርና ሕዝብህን አስበላ የሚል ትምህርትና ቡራኬ አንተ ከየት ተማረክ? የፖለቲካና ሃይማኖት ወቀጣውን እንዴት እውነት ብለህ ትቅጥፋክለህ!?
፫) እራሳችሁን የኦርቶዶክስ ዋና ወዳጅና ተቆርቋሪ! ሌላውን ኦርቶዶክስ ሃይማኖትንና ቅርስን አውዳሚ አድርጋችሁ የፈረጃችሁበትን ስልጣን ማን ሰጥቷችሁ ነው?
___ ከጥንትም ሃይማኖት የግል ሀገር የጋራ ነው።አሁንም ምንም የሃይማኖት ነጻነት ቢባዛ ሃይማኖተኛ አንሷል..አስመሳይ ሸቃይ በዝቷል እያልን ነው ይሰማል? የሌላውን ሥርዓት ከመጋፋት ትውልዱን ከማወናበድ ወደሥራ እንዲሰማራ ጭንቀላቱን ባታናውጡት አወርቶ በል ጀዝባ እንዳይሆን ባትጠልፉትስ?
፬) “የኦንሊ ጅሰስ ተከታይ ከሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር እኛን በስላሴ የምናምንን የኦርቶዶክስ ተሃድሶን አማኞች አንድ አድርጋችሁ በመፈረጅ ለጥላቻችሁ መጠቀሚያ ስታደርጉት: ሀ/ የእምነት ልዩነቱን ጭራሺ የማታውቁ ”ጨዋ” ናችሁ ማለት ነው ?
__ ይህ እራሱን የቻለ ዝባዝንኬ ነው…ማንነትና ምንነት እነሱው የሰጡህ መብት ነው(ጥልቅ (ተሃደሶ/ታድሶ)…አይመሳሰልም!? አዳሜ እርስ በእርስ እየተላፋሽ እንታገላለን ትያለሽ አደለም አደል?ዋሸሁ እንዴ? ”ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ይሏታል ጅግራ” ሰውን ጨርሳችኋል ጅግራስ ቢተርፋችሁ አደለም?
፭) “አባቶቻችን አደዋ ላይ እየፎከሩ ቆመው ይተኩሱ የነበረው የወቅቱ የወንድነት መለኪያ ንቃተ ህሊና ስለነበረ ነውና፣
ወገኖቼ እባካችሁ እባካችሁ ዛሬ ላይ ቆመን ትናንትን ሚዛን አድርገን በመጠቀም:
___ በአድዋ ድል ሰሞን ነጋሪት ይጎሰም የሚመስላቸው ፈሪዎች እንጂ ‘ፈርሃ እግዝሕብሔር’ ያላቸው አያሰኝም። ለግልሰቡ የተጻፈን ደብዳቤ እንደ ዓለም መጨረሻ አድርጎ ጉልጉል ጋዜጣ ላይ መለጠፍ ትክክለኛነትን አያጎናጽፍም፡ ጭራሽም ጭር ሲል አልወድም የሚል አርዕስት ፈጠራ፡ የተጯጯሁና የጉልጎል ባለቤቶች ሰዓትና መልካም ሥራቸውን ለመበከል ሆን ተብሎ የተጣደ ነገር መሰለኝ!? የራሳችሁ ድረ ገፅና ጋዜጣ የላችሁም!?እዚህ ላይ የረጅም ግዜ ተጠቃሚ ነኝ እንዲህ ያለ የጸብ አጫሪ ጽሁፍ አላየሁም።ለማንኛውም ግን ይህን የጅምላ ቱማታ አልቀበልም በግሌ ህሳብ ላይ ግን ሐሳብ መስጠት ችግር የለብኝም ።
እየተከባበርን…
የዘወትር የጎልጉል ወዳጅ በለው፥
በዚህ ጽሁፍ ምክንያት ብዙ ተብለናል። ነገር ግን እንደ እርስዎ ያለ ስለ እኛ አቋም ምስክርነት መስጠት የሚችል ሰው በመኖሩና ይህንንም በገሃድ በመናገሩ ለሌሎች ትምህርት የሚሰጥ ይመስለናልና ምስጋናችን ይድረስዎ።
የማሰብ፥ የመናገር፥ የመጻፍ ወዘተ መብቶችን በማክበር ነበር ይህንን ጽሁፍ ፈቃድ ሰጥተን የለጠፍነው። ሆኖም በርካታው ምላሽ ሰጪ ሃሳብን በሃሳብ ከመሞገት ይልቅ ወደ ዘለፋ መሄዱም አማራጭ አድርጎ ስናይ ገና ብዙ ይቀረናል እንድንል ያደርገናል። ከዚህ ሌላ የሃይማኖት ጽንፈኝነት በርካታዎችን “አትንኩኝ ባይ” እንዳደረገው ምስክር ሆኗል ለማለት አስደፍሮናል።
ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምረን እጅግ ሥልጡን ሕዝብ ነን። ንግግራችንም ሆነ ሙግታችን ጨዋና ሃሳብን የሚሞግት እንደነበር የእሠጥ አገባ እና ሌሎች ተሞክሮአችን ምስክር ናቸው። ከዚያ ወርደን ዘለፋና ስድብ ውስጥ መግባታችን ያሳዝናል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ሃይማኖተኛ ነን የሚሉ ሰዎች በዚህ ረድፍ ተሰልፈው ማየት እጅግ ያሳፍራል።
በቅኔ፥ በዘዬ፥ በሰምና ወርቅ፥ ወዘተ የከረረ ሙግት መግጠም የሚችሉት አባቶቻችን የኛን እዚህ ደረጃ መዝቀጥ ሳያዩ ማለፋቸው ዕድለኛ የሚያደርጋቸው ይመስለናል።
የጎልጉል አርታኢ
“ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምረን እጅግ ሥልጡን ሕዝብ ነን። ንግግራችንም ሆነ ሙግታችን ጨዋና ሃሳብን የሚሞግት እንደነበር የእሠጥ አገባ እና ሌሎች ተሞክሮአችን ምስክር ናቸው። ከዚያ ወርደን ዘለፋና ስድብ ውስጥ መግባታችን ያሳዝናል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ሃይማኖተኛ ነን የሚሉ ሰዎች በዚህ ረድፍ ተሰልፈው ማየት እጅግ ያሳፍራል።”…. “ዋናው የውድቀታችን ምንጭ ተማሪና አስተማሪው እኩል ማወራታቸው ነው።”
__ይህ መንግስት ያወረሰን ራዕይ..’ትውልድ ማምከንና ማባከን’ ሥርዓቱን ብንቀይር እንኳ ያጠፉትን ሀገርና ትውልድ ደግሞ ለመገንባት ቢያንስ አንድ ዓርባ ይፈጅብናል።…ተፈወስ ያላለው ሕዝብ ዓርባ ዓመት ይባላል….(ቅድስት ሀገረ ኢትዮጵያ ብዙም ጫጫታ አትወድም ታስለቅሰናለች!)
__ አዎን! “በቅኔ፥ በዘዬ፥ በሰምና ወርቅ፥ ወዘተ የከረረ ሙግት መግጠም የሚችሉት አባቶቻችን የኛን እዚህ ደረጃ መዝቀጥ ሳያዩ ማለፋቸው ዕድለኛ የሚያደርጋቸው ይመስለናል።” ፈላስፋ በዛ ልበል? አዋቂ በዛ ልበል? አውቆ አበድ ጨመረ ይሆን? ጥፋታዊ አውርቶ አደር በረከተ?
‘ይብላኝ ለቋሚው የሞተ ዓረፈ በለው!’ በመፈቃቀደና በመፈቃቀር ሀገሩን በክልል ለውጦ ማንነቱ የጣላ ጠፋብኝ ብሎ ይጮሃል!? ምግብ፡ውሃ፡ ጤና፡ ትምህርት ለተቸገረ የዋህ ቅን ሕዝብ ‘ፖለቲካና ሃይማኖት አብኩተው ጋግረው” ጥጋብኛ ይሉታል። ዘይገርምዩ !ሠላም ለለሁሉም ይሁን።
ከምሥጋና ጋር!
https://youtu.be/n90ThLH1w3M
https://youtu.be/U8tiLCN1BNI
ጉግሎች – የድህረ-ገፅ ጋዜጣ ከመክፈታችሁ በፊት፣ ጉግል ተብሎ የሚታተም ጋዜጣ ነበራችሁ እንዴ ?
ጎልጉል ፀረ ኦርቶዶክስ መሆኑ ተረጋገጠ
ለታዛቢው
በመጀመሪያ ጤና ይስጥልኝ! የእግዚአብሔር ቸርነትና ምህረት ይብዛልዎ እያልኩ ከዚህ በመቀጠል እኔም እንደ እርስዎ የኦርቶዶክስ ቤተ እምነት ተከታይ ወይም ምእመን በመሆኔ የኦርቶዶክስ ትርጉም ቀጥተኛና እውነተኛ ማለት ስለሆነ እንደ ስማችን ሆነን መገኘት አለብን ብዬ አምናለሁ።
በመጀመሪያ ሲጀምሩ “ማንነታቸውን ለሰወሩት ወይም በማንነታቸው ለሚያፍሩት” ብለው ጀመሩ፤ ጸሐፊው እውነቱ ይነገር ብለው ስማቸውን አስቀምጠዋል፤ ነገር ግን እርስዎ እራስዎ ታዛቢው ብለው ነው ስምዎትን ያስቀመጡት፤ ታዲያ የራስዎን ስም ደብቀው የሰውን ማንነት መጠየቅዎ እርስዎ ያልሆኑትን ሌላው እንዲሆን መፈለግዎ ትንሽ ግራ የሚያጋባ አይመስልዎትም? እንደ እኔ መረዳት ቁምነገሩ ያለው ስማቸው ወይም ማንነታቸዉ ላይ ሳይሆን የጻፉት ጽሑፍ ይዘት ላይ ሊሆን ይገባ ነበር። በዚህ መሰረት ጸሐፊው ባስቀመጡዋቸው ነጥቦች ላይ አስተያየትዎን ይሰጣሉ ብዬ ስጠብቅ ምንም ተጨባጭነት የሌላቸው ሃሳቦች (Unsubstantiated argument)፣ የራስዎን ግምት ወይም ውስን እውቀት ነው ሊያሳዩን የሞከሩት። እኔ በጣም የሚገርመኝ እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ለምን መጸሐፍ ቅዱስን ገልጠን መነጋገር እንደማንችል ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስን ጠቅሰን በተነሱት ነጥቦች ላይ ከመነጋገር ይልቅ ስድብና ምንም ፋይዳ በማይሰጥ እሰጥ አገባ ውድ የሆነውን ጊዜአችንን ማቃጠላችን ያሳዝነኛል። ኢትዮጵያዊ ነን እንላለን ግን ኢትዮጵያዊ ስነ ምግባር አይታይብንም፤ ክርስትያን ነን እንላለን ክርስቲያናዊ ስነምግባር እርሱም ወንድምህን እንደ ራስህ ውደድ የሚለውን ቃል ከነጭራሹ የምናውቀው አይመስለኝም፤ ለነገሩ የክርስትና መነሻና ዋና ማእከል የሆነውን ክርስቶስን ትተን በብዙ አማልክትና ከእውነት በራቁ ትምህርቶች ተጠምቀን እንዴት ክርስቲያን ተብለን ልንጠራ እንችላለን??? ራሳችንን በቃሉ መስተዋት ብናይ ጥሩ ነበር ብዬ አምናለሁ፤ መጽሐፍ “የጠቢብ አይን ወደ ራሱ ነው” እንደሚል ራሳችንን ብንፈትሽ ባልተፈረደብን ነበር። ሰለዚህ አቶ ታዛቢው የሌላውን እምነት ከመንቀፍዎ በፊት የራስዎን እምነት ጠንቅቀው ይወቁ እላለሁ፤ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችን ስድብንና ወንድምን መጥላትን አላስተማረችንም፤ ስለዚህ እርስዎም ሆኑ ሌሎች የሚሳደቡ ሁሉ እኛን ኦርቶዶክሳዊያንን አትወክሉንምና ቤተ ክርስቲያኒቱ በስርዓቷ መሰረት መድባ ሳትልካችሁ በስሟ ባትናገሩና ባታስንቋት መልካም ነው እላለሁ።
ከዚህ በተጨማሪ ጸሐፊው ቁጭ ብሎ በጠረጴዛ ዙሪያ ስለመነጋገር ያቀረቡትን ሃሳብ እርስዎ ሲመልሱ፡ “እምነት ለመከራከሪያ አይደለም፣ ካንተ ጋር ቁጭ ብሎ የሚነጋገር የለም” ብለው ሲኖዶሱን ወክለው መልስ የሰጡ ነው ያስመሰለብዎት! ለምንድነው ተሃድሶ የሚባሉት ከኦርቶዶክስ አባቶች (ከሲኖዶሱ) ጋርቁጭ ብለው መነጋገር መፈለጋቸውን የሚቃወሙት??? ምክንያቱም በመነጋገር ወደ አንድ ከፍ ያለ ደረጃ ይደረሳል ብዬ ስለማምን ነው። እርስዎ ራስዎ በርዕስዎ ላይ ያስቀመጡት (የአርዮስ ፍሬዎች) የሚለው ታሪካዊ አመጣጡና አስተምህሮቱ እንዴት እንደ ተወገዘ አላነበቡምን??? ታሪኩን ካላወቁ ባጭሩ፦ ወደ 350 የሚሆኑ አባቶች ተቀምጠው አሪዮስ በሚያስተምረው ትምህርት ላይ ለ3 አመት ያህል ከተነጋገሩና ከተከራከሩ በኋላ ነበር 350 ከሚደርሱ አባቶች መካከል 318ቱ በአንድ ሃሳብ በመስማማታቸው ምክንያት አሪዮስንና ትምህርቱን ሊያወግዙ የቻሉት፤ መጸሃፍ ቅዱስ (በሐዋርያት ሥራ 17:10-11) ላይ ስለ ቤሪያ ሰዎች አስተዋይነት ዛሬ ላይ ያለን ሰዎች ከነሱ እንድንማር የሚከተለውን ይለናል፡ “ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፥ በደረሱም ጊዜ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ፤ እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና። ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።”
ከዚህ የምንማረው ምንድነው? እነዚህ የቤርያ ሰዎች በጣም አስተዋዮችና ልበ ሰፊዎች እንደነበሩ ነው፤ ሐዋሪያ የሆነው ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ስለሰበከላቸው ብቻ ሳይሆን የተቀበሉት (ያመኑት)፥ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን??? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን ይመረምሩ ስለነበረ ነው። ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊያን አባቶቼ፣ እናቶቼ፣ ወንድሞቼና እህቶቼ አንድን ነገር ከመቀበላችንም ሆነ ከማውገዛችን በፊት የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸውንና የእምነት አባቶች ተስማምተው ያጸደቋቸውን ቅዱሳት መጽሐፍቶችን በደንብ በመመርመርና በማጥናት ተርፈን ቤተ ክርስቲያናችንን ማስጠበቅ ይኖርብናል፤ ለዚህም የእግዚአብሔር መንፈስ እንዲገልጥልን በጾም በጸሎት እየተጋን እውነትን ማወቅና ማደግ እንችላለን እንጂ መንፈሳዊ ነገር እንዲሁ ባካኪ ዘራፍ ፉከራ ጭራሺ የሚሆን አይመስለኝም፤ በስጋ ጉልበት የሚከናወን ሥራ ስላልሆነ!!! ዛሬም ቢሆን በኦርቶዶክስ ስርአትና ደንብ መሠረት ሊቃውንት አባቶች (ሲኖዶሱ) አንድን ሰው ወይም ማህበር ስለሚያስተምረው ትምህርት ጠርተው ከማነጋገራቸው በፊት ግለሰቡንም ሆነ አስተምህሮቱን ወይንም የዛን ትምህርት ተከታይ የሆኑትን ምዕመናኑን የማውገዝም ሆነ የመገዘት ስልጣን የላቸውም ስለሚል፤ አቶ ታዛቢው ከማን ሰምተው ወይም ተምረው ነው መናፍቅ፣ የሉተር ፍልፍሎች፣ ፍራሽ አዳሾች ወዘተ. እያሉ ሲኖዶሱ ያላወገዛቸውን እንደውም ገና ያላነጋገራቸውን ሰዎች እርስዎና መሰሎችዎ እንዴት ባለ ድፍረት ነው የምታወግዙት???? “አወቅሽ አወቅሽ ቢሉዋት የባልዋን መጽሐፍ አጠበችው” እንዲሉ፤ ይልቁንስ ይሄን አዲሱን ትውልድ ከሌሎች ቤተ እምነቶች ማትረፍ የምንችለው የቀደመችውን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እውነተኛ የወንጌል አስተምህሮና ክርስቲያን የተሰኘንበትን መሠረት (1ኛ ቆሮ 3:10-11) ጠንቅቆ እንዲያውቅና እንዲመረምር ስንፈቅድለት ብቻ ነው። በተጨማሪም እርስዎ መጋዘን ብለው የጠሩትም ስፍራ ሆነ እኛ ቤተክርስቲያን ብለን ስለምናስቀድስበት ስፍራ መጽሐፍ ቅዱስን ካነበቡ ሲናገር፦ በአዲስ ኪዳን ቤተመቅደስ የሚለው በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑትን ሰዎች እንጂ ህንጻውን አይደለም። (1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 3:16)ን ይመልከቱ።
በመጨረሻም በጣም ልቤን ያሳዘነኝ ነገር ቢኖር ስለ አለቃ ታዬ በንቀት የተናገሩት ነገር ነው፤ ይኼውም “ሂድና ለዛ ለአለቃህ ንገረው፣ ጠይቀው፣ወዘተ.” ያሉትን ቃላቶች ሳነባቸው በጣም ደንግጪ ተገርሜያለሁ፤ ምክንያቱም እኚህ በዘመናቸው ታዋቂ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቅ የነበሩ፣ በቤተክህነት ዋና አገልጋይ የነበሩ፣ ኢትዮጵያን ወክለው በጀርመን ሀገር የግዕዝን ቋንቋ በ (University Level) እንዲሰጥና እስከዛሬ ድረስ ስማችንን እያስጠሩ ያሉ የቤተክርስቲያናችንን አይናማ ሊቅ ከመሬት አንስተው ሲያፈርጧቸው ሳይ ኢትዮጵያዊ ስነምግባር ይጎድልዎታል እንድል አስገድዶኛል። በባህላችን እንኳ ሙታንን መውቀስ እንደ ነውር ይቆጠራል (ሙት ወቃሽ አያርገኝ ይባላል)፤ እንኳን ጥሩ ቅርስ ጥለውልን ያለፉትን አባቶች ይቅርና ክፉዎችንም እንኳ ቢሆን በክፉ አናነሳም፤ ስለዚህ አለቃ ታዬን ፈጽመው የሚያውቋቸው አልመሰለኝምና ስለእሳቸው ማወቅ ከፈለጉ የኢትዮጵያን ክርስትናና የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ታሪክ ጠንቅቀው እንዲያጠኑ በትህትና እጋብዝዎታለሁ።
ብዙ የምለው ነገር ነበረኝ፤ ነገር ግን የልቤን ሁሉ አውጥቼ በአንዴ መዘርገፍ ስለማልችል ለዛሬ ይብቃኝ! በማስተዋል ሰምቶ ለሚጠቀምበት ይህ በቂ ከበቂም በላይ ነው እላለሁ።
ቸር ያቆየን!!!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ጥበቡ ሞላልኝ
ጥበቡ ሞላልኝ ፣ በቅድሚያ ምንም የሞላልህ ጥበብ እንደለሌ ልነግርህ እወዳለሁ ፣ አንተም ሆንክ እውነቱ ይነገር ነኝ ባዩ ሁለታችሁም ስማችሁ እንዳልሆነ አንተም ታውቃለህ እኔም አበጥሬ አውቃለሁ ። ነገር አይገባችሁም የምለው ከመሬት ተነስቼ አይደለም ። አንተም ስታነብ ነገሩ በደንብ እንዲገባህ አድርገህ አንብብ ተነካሁ በሚል በግንፍለኝነት አትናገር ፣ ማንነታችሁን አትደብቁ ነው ያልኩት ጮኬ መጻፍ አልችል ጮኬ መናገር እንጂ ። ጥበቡ ተባለ እውነቱ ከናንተ የብዕር ስም አይደለም ጉዳዬ ጴንጤ ስትሆኑ አንዴ ተሃድሶ አንዴ ኦርቶዶክስ አትበሉሉሉሉሉ……….. አማርኛ ይገባችኋል? ወይንስ የማደናቆር ጨዋታ ነው የያዛች ሁት? ማስረጃ አንዲሆን https://www.youtube.com/watch?v=Hd78BCB37t0 ይሄንን ማስፈንጠሪያ ተመልከትና እራስህንና ጓደኛህን እዚያ በተንቀሳቃሽ ቪዲዮ ስለምታይ ያኔ የምናገረው ይገባህ ይሆናል ። እዚህም ናቸው እዚያም ናቸው ይላል ፓስተራችሁ ፣ አየህ ለዚህ ነው አንዴ ተሃድሶ ፣ አንዴ ኦርቶዶክስ ገለመሌ ብላችሁ እራሳችሁን እየደበቃችሁ አትምጡ የምለው ። ሁለትና ሶስት ቦታ አትረጋግጡ አንድ ቦታ እረግታችሁ ጽኑ አታታክተኝ ። እኛ የቀድሞ ኦርቶዶክሶች ዛሬ ግን ተገንጥለን ጴንጤ የሆነው ካላችሁ ያኔ በቁም ነገር ልናወራ እንችል ይሆናል ። እንዲያው ጻድቅና የተባረከ ለመምስለል እየተለሳለሳችሁ ሌላውን ምግባረ ብልሹ ለማስመሰል እራሳችሁን አጽድቃችሁ የምትለሳለሱበትን ሊቀበልህ ወደሚችለው ውሰደው እንጂ እኔጋ አይሰራም ። አሁንም በድጋሚ እንደማይገባችሁ እያወቅኩ ግን እደግመዋለሁ “ሃይማኖት መከራከሪያ አይደለም” አትከራከሩ ይላል የያዝከውን ወንጌል ተብዬ ተመልከተው ። ያንን ማለቴ ሲኖዶስን ወክለህ ተናገርክ አልክ ሲኖዶስ ነው እንዴ ወንጌልን የጻፈው? እንደናንተ ወንጌል ተብዬ ማንም ያሻውን የሚጨምርበትና ያሻውን የሚያስወጣበት መስሎህ ይሆን ወንጌሉ? መልስ ከመስጠትህ በፊት ይሄ ሰው ስለምንድነው የሚያወራው ብለህ ነገሩን ለመረዳት ሞክር ። አንተን ያስደነገጠህ ሊቃችንን ተናገርክ ነው የናንተ መሪና አቀንቃኝ የነበረውንም ሟቹን አባ ዲያቢሎስንም እኮ አባ ዲያቢሎስ ብዬዋለሁ የክህደት መሪና አቀንቃኝን የማክበር ግዴታ የለብኝም አንተ ከፈለክ ይሁዳንም ማክበር ማንገስ ትችላለህ ፣ ሲጀመር እኔ ለናንተ መልስ አልሰጥም ብዬ ነበር ነገር ግን ስሜን ጠቅሰህ ስለመጣህ ግድ ሆነብኝ እንጂ ያንተ ቢጤ መናፍቅ በየ ጉራንጉሩና በየ ስርቻው እንዳሸን ፈልቶ የለ እንዴ ፣ ልክ ሌሎች የኦርቶዶክስ መምህራን ንቀው እንደተዋችሁ ሁሉ እኔም ንቄ መተው እችል ነበር ግን እናንተ ሲንቋችሁ የተፈራችሁ ስለሚመስላችሁ እኔንም በግል ስሜን ስለጠቀስክ ያ እንዳልሆነ እንድታውቁት እንጂ የውሃ መውቀጥ አባዜ የለኝም ።
ለዝብርቅርቅ(ለታዛቢው)
ሰላም ጤና ይስጥልኝ እያልኩ በመቀጠልም አስተያየትዎን ሳይ ምንም እንኳ መመላለሱን ባልፈልገውም በድጋሚ መልስ እንድሰጥዎ ተገድጃለሁ፤
እርስዎ እየደጋገሙ ማንነት ማንነት ማንነት ይላሉ ማንነቴን እኮ እርስዎ የሰጡኝ ወይም የሚሰጡኝ ሳይሆን ልዑል አምላክ ገና ሲፈጥረኝ በራሱ አምሳል አርጎ የሰራኝ፣ ማንነቱን በውስጤ አስቀምጦ የፈጠረኝ ስለሆንኩ ስለማንነቴ እርስዎ እንዲነግሩኝ አያስፈልገኝም፤ ምክርም አልጠየኮትምና በመጀመሪያ እራስዎን ጠንቅቀው ይወቁ እላለሁ፤
ሌላው ደግሞ አይገባችሁም አይገባችሁም እያሉ ብዙ ጊዜ ይጮሃሉ “ያብዬን ወደ እምዬ” አሉ፤ የማይገባኝ እኔ ወይስ እርስዎ??? ይመስለኛል የማይገባቹህ የሚለው ቃል እንደ ገደል ማሚቶ እየነጠረ ወደ እርስዎ እየተመላለሰ ሳይሆን አይቀርም እየደጋገሙ ያንኑ ጩኽትዎን በሃይል የሚያስተጋቡብን፤ መጽሐፍ “ሰው እንደ ሚያስበው እንደዛው ነው”፤ እንደሚል! ከጹሁፎ እንደተረዳሁት ምን አይነት ሰው ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት አያቅተኝም፤ ሰው ያለውን ነውና የሚሰጠው ያሎት ይሄ ብቻ ስለሆነ የሚሉትም ያንኑ ነው፤ በተጨማሪም ለኔ መልስ መስጠት የሰለቸዎት ነው የሚመስሉት ልክ ብዙ ጊዜ እንደጻፍኩልዎ ያህል፣ እኔ ብዙ የ(Social Media) ተጠቃሚ አይደለሁም፤ ይህም ሶሻል ሚድያ ጥሩ ስላልሆነ ሳይሆን እኔ ካለብኝ ብዙ ሃላፊነትና ጫና የተነሳ ጊዜ ስለሚያጥረኝ ነው፤ እናም በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ አሁን ደግሞ ለሁለተኝ ጊዜ አስተያየት መስጠቴ ነው አመኑም አላመኑም አንዳችሁንም አላውቅም እርስዎም እኔን አያውቁኝም፤ ይሄንንም ቢሆን አንድ ወዳጄ ነው ሊንኩን ልኮልኝ እስቲ ግባና ተመልከት ብሎ ጎልጉሎችን ያስተዋወቀኝ፤ ጎልጉሎችን በዚህ አጋጣሚ ለማመስገን እወዳለሁ፤ ጥሩ ጥሩ ጹሑፉችን አይቻለሁ ደንበኛችሁ ሳልሆን አልቀርም፤ እናም በሊንኩ መሠረት ገብቼ ሲዘባርቁ ሳይ አላስችል ብሎኝ ነው የጻፍኩልዎ፣ በመሠረቱ በመጽሐፈ ምሳሌ ላይ “ሰነፍን አትገስጸው ይሰድብሃል፣ ጠቢብን ግን ምከረው ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል” እንደሚል እያወኩ ነበር እስቲ ምንአልባት ከሰሙ በሚል ቅን ሃሳብ ተነስቼ ምክሬን የለገስኩዎት፤ እናም አቶ ዝብርቅርቅ በግድ ጻፉ ያለዎት ደግሞ የለም፤ “ሲጀመር ለናንተ መልስ አልሰጥም ነበር” ላሉት ደግሞ መልስዎንማ አየነው እኮ!ምንም ፍሬ ነገር የሌለበት ከንቱ ጩኽት! ውስጡ የሞላው ሰው ጻፍ ባይባልም እንኳ ውስጡ ጭራሽ አያስቀምጠውምና መጻፉን አይተውም፤ ሰለዚህ ላለመጻፍዎ እንኔ ወይም ሌላውን ምክንያት ማድረግ አይችሉም፤
በተጨማሪ ደግሞ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረውን ሰውን አይናቁ፤ “እናንተን ሲንቋቹህ የተፈራቹህ ይመስላችሗል፣ ምናምን ብለዋል” ለመከበር መርሁ (The Principle) ሌላውን መናቅ ሳይሆን ራስን ዝቅ ማድረግ ነው፤ እኔ ጨርሻለሁ ከእርስዎ ጋር እሰጥ አገባ ሙግት የምገባበት ጊዜ የለኝም፤ ባለፈው እንዳልኩዎ ቢያስተውሉ ኖሮ ያለፈው አስተያየቴ ብቻ ይበቃዎት ነበር፤ ነገር ግን ከእርስዎ ጋር መነጋገር ማለት ድንጋይ ላይ ውሃ እንደማፍሰስ መስሎ ነው የታየኝ፤ ውድ ጊዜዬን በንትርክ አላጠፋም።
በመጨረሻም ያሳቀኝ ነገር ቢኖር እኔ እያወራሁ የነበርኩት ስለ አለቃ ታዬ፣ እርስዎ የሚያወሩት ስለ አባ ዲያብሎስ ምናምን ነበር፤ ምንም የማይገናኝ ነገር፡ “ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ” አሉ! ይሄ መቼም ጤነኝነት አይመስለኝም፤ ከዚህ በላይ የምልዎ የለኝም እግዚአብሔር ንፁህ ልብና ተሳዳቢ ያልሆነ አንደበት ይስጥዎ ከማለት በስተቀር፣ እኔ ጨርሻለሁ፤ እርስዎ እንደለመዱት መዘባረቁን መቀጠል ይችላሉ።
“ስምን መልአክ ያወጣዋል” እንዲሉ፣ እውነትም ዝብርቅርቅ!!!
ጥበቡ ሞላልኝ
ይድረስ ለ….
ለያንዳንዷ አረፍተ ነገር እንዲህ ስትል እንዲህ ብዬ መልስ ሰጥቻለሁ ካላልኩ የሚገባህ ስላልመሰለኝ የግድ ያንተን አባባሎች በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ እያስገባሁ ላነሳኸው ጉዳይ መልስ በመስጠት የዚህን ምዕራፍ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይቋጨዋል ብዬ አምናለሁ ።
“እርስዎ እየደጋገሙ ማንነት ማንነት ማንነት ይላሉ ማንነቴን እኮ እርስዎ የሰጡኝ ወይም የሚሰጡኝ ሳይሆን ልዑል አምላክ ገና ሲፈጥረኝ በራሱ አምሳል አርጎ የሰራኝ፣ ማንነቱን በውስጤ አስቀምጦ የፈጠረኝ ስለሆንኩ ስለማንነቴ እርስዎ እንዲነግሩኝ አያስፈልገኝም፤ ምክርም አልጠየኮትምና በመጀመሪያ እራስዎን ጠንቅቀው ይወቁ እላለሁ “
ግብራዊ ማንነትህን እንጂ በአረያ ስላሴ ስለመፈጠርህ እንዳልጠየቅኩህ እንኳን አልገባህም ፤ ለዚህ ነው ጠንቅቃችሁና አስተውላችሁ አንብቡ የነገሩ ጭብጥ ሳይገባችሁ መልስ ለመስጠት አትጣደፉ የምለው አሁንስ ተግባባን ?
“ሌላው ደግሞ አይገባችሁም አይገባችሁም እያሉ ብዙ ጊዜ ይጮሃሉ “ያብዬን ወደ እምዬ” አሉ፤ የማይገባኝ እኔ ወይስ እርስዎ???”
ትክክል ! ቢገባህማ ካንዴም ሁለት ሶስቴ ጥያቄ ጠይቄ መልስ አላገኘሁም ስለዚህ አሁንም አይገባህም ወይንም አይገባችሁም በሚለው አቋሜ እንደጸናሁ ነኝ ።
ጥያቄ 1) ጴንጤ ስትሆኑ ለምን አንዴ ተሃድሶ አንዴ ኦርቶዶክስ እያላችሁ ሰው ለማሳት ትሞክራላችሁ? በራሳችሁ ማንነት ቅረቡ እንጂ ጭንብል እያጠለቃችሁ አትምጡ ላልኩት እስካሁን መቼ መልስ አገኘሁ ? እንኪያ ሰላንቲያ እንጂ!
ጥያቄ 2) ወንጌል በሃይማኖት ጉዳይ አትከራከሩ ይላልና ክርክር አላስፈላጊ ነው ስለሆነም ውሃና እሳት ቀርቦልሃል እጅህን ወዳሻህ መስደድ መብትህ ነው ስለዚህ ሁሉም በያለበት ያመነውን ያስተምር እንጂ ክርክር አያስፈልግም ያልኩትን አዎ ልክ ነህ ወይንም አይደለህም አላላችሁም ታዲያ እንዴት አድርጌ ነገር ይገባችኋል ብዬ ልቀበል? በማስረጃ በቪዲዮ ከነ ጥምጥማችሁ በየጴንጤው መጋዘን ስትፏልሉ አየታያችሁ አይናችሁን በጨው ታጥቦ የሰው ልብ ማውለቅ ለምን አስፈለገ?
ጥያቄ 3) በገሃድ በማስረጃ ተይዛችሁ እንኳን ሰው ለማስካድ የምትጥሩ እስቲ ማን ይሙት እናንተ ናችሁ ስለ ሰማያዊው ህይወት ሰውን ልታስተምሩ የምትችሉት እስቲ እራሳችሁን ዞር በሉና ፈትሹ ባዶ ናችሁ እኮ ። አየህ እኔ አፌን ሞልቼ በድፍረት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ መሆኔን እናገራለሁ እመሰክራለሁ ፤ አንተን ግን እንግዲህ በወላዲት አምላክ ስትል አልልህ አታውቃት ስለዚህ በምታምነው ይዤሃለሁ አዎ ጰንጤ ነኝ ብለህ እመን በማንነትህ አትፈር በየመጋዘኑ ከነጥምጥምህ ስትፏልል እጅ ከፍንጅ ተይዘሃልና እባክህ ተለመን ፤ ጴንጤ ነኝ ስትል እመን ። ተኩላው ግን ተኩላ ሲሆን ለምን በግ ነኝ ማለት አስፈለገው ? ትርጉም … ተሃድሶው ጴንጤ ሲሆን ለምን ኦርቶዶክስ ነኝ ብሎ ማጃጃሉን መረጠ ?
“ይመስለኛል የማይገባቹህ የሚለው ቃል እንደ ገደል ማሚቶ እየነጠረ ወደ እርስዎ እየተመላለሰ ሳይሆን አይቀርም እየደጋገሙ ያንኑ ጩኽትዎን በሃይል የሚያስተጋቡብን፤ መጽሐፍ “ሰው እንደ ሚያስበው እንደዛው ነው” ፤ እንደሚል! ከጹሁፎ እንደተረዳሁት ምን አይነት ሰው ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት አያቅተኝም፤ ሰው ያለውን ነውና የሚሰጠው ያሎት ይሄ ብቻ ስለሆነ የሚሉትም ያንኑ ነው”
አሁንም በድጋሚ ወደ መሰረታዊው ጥያቄ ወደዚህ ወደሳበን ጉዳይ ልመለስና የቀደመው ጸሃፊ ከኦርቶዶክስ መምህራን ወይንም ከእምነቱ መሪዎች ጋር ክርክር ፈለገ እኔም በመጽሃፋችን ስለ ሃይማኖት መከራከር አስፈላጊ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ መልስ ሰጠሁ ። ታዲያ አሁን ባንተ አባባል የገድል ማሚቶው እኔ ወይንስ አንተ? እየነጠረ የመጣውስ ወዳንተ ነው ወይንስ ወደኔ? ያልገባውስ እኔ ነኝ አንተ ? አንብብ አንጂ! አየህ ሳታነብና ሳይገባህ አትመልስ የምለው ለዚህ ነው አሁን እንደገባኝ ከሆነም ወንጌሉንም ልክ ለኔን መልስ ለመስጠት በጥድፊያ እንደምታነቡት እንደ ድርሰት በግልቢያ እያነበባችሁ ትርጓሜውና ፍቺው ሳይገባችሁ ነው አውቀናል! ያዙን! ልቀቁን! እያላችሁ አገር የምታምሱት ። ለዚች ለትንሿ በኔና በናንተ መሃከል ላለችው መመላለሳችን በራሷ መልስ ለመስጠት ምን ያክል የተጣደፋችሁ እንደሆናችሁ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ አይመስልህም? የወንጌሉን ጉዳይ ወደጎን እንተወውና ። አንተኑ ልጠይቅ እንጂ እኔስ ጠንቅቄ አውቃችኋለሁ ።
“በመጨረሻም ያሳቀኝ ነገር ቢኖር እኔ እያወራሁ የነበርኩት ስለ አለቃ ታዬ፣ እርስዎ የሚያወሩት ስለ አባ ዲያብሎስ ምናምን ነበር፤ ምንም የማይገናኝ ነገር፡ “ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ” አሉ!”
ሳታነብ መልስ አትስጥ ፣ ያልገባህ ነገር ካለ ጠይቅ ፣ ስለ አለቃህም ሆነ ስለ አባ ዲያቢሎስህ መልስ ሰጥቻለሁ ፣ ተመልሰህ አንብበው ። ሁሌም በንዴትና በግለፍተኝነት ለኔ መልስ ለመስጠት ስትጣደፉ እየተናገርኩ ያለውን ከምን ግዜም በላይ እያጠናከራችሁልኝ እንደሆነ ይገባሃል? ቢገባህ ይሻላል!
“ሰነፍን አትገስጸው ይሰድብሃል ፣ ጠቢብን ግን ምከረው ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል”
አየህ እራስ ህን ምን ያክልል እንደቆለልክ ? ማንነት ህን እንኳን ማመን ሳትችል ሰውን እንዴት ዝቅ አርገህ እንደምታይ ያስተዋልክ አይመስለኝም ፣ ሆኖም ግን ለዚህ ማቃለልህ እዚያው ጥቅሱን ካመጣህበት ደግሞ እንዲህ ይላል “እውቀትን ጠልተዋልና ፥ እግዚአብሔርንም መፍራት አልመረጡምና ፤ ምክሬን አልፈቀዱምና ፥ ዘለፋዬንም ሁሉ ንቀዋልና ፤ ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ ፥ ከራሳቸው ምክር ይጠግባሉ ።” ከናንተ ከመመፃደቅና ከኛ በላይ አዋቂ ላሳር ከማለት በቀር ምንም እንደማይገኝ ስለምንተዋወቅ ነገሩን በፈላስፎች አባባል ብዘጋው እመርጣለሁ ። “I know that I am intelligent, because I know that I know nothing”.( Socrates) እኔ ግን “ አለማወቄን ስለማውቅ ከሌሎች እበልጣለሁ”
“ስምን መልአክ ያወጣዋል” እንዲሉ፣ እውነትም ዝብርቅርቅ!!!
እዚህ ላይ ግን ያንተንም ስም መልዓክ ነው ያወጣው እንዳትለኝ እና በሳቅ እንዳልሞትብህ አደራ ? ይህ በዚህ እንዳለ ፣ ስሙን ማንም ያውጣው ማን የኔ መዘባረቅ በጸበል ፣ እናንተ ባታምኑትም ይሄ ይሰመርልኝ እና ፣ ወይም በህክምና ፣ ካልሆነም በጥሩ አስተማሪ ይቃና ይሆናል ፣ ጥበቡ ሳይሞላላቸው ፣ እውቀታችን ሞልቶ ተረፈ ፣ ከከረጢቱ ሞልቶ ፈሰሰ ፣ እያሉ በጉድለታቸው የሚመፃደቁትን የበግ ለምድ የለበሱትን መፃጉዎችሽ የሚፈውሳቸው ምን ይሆን ?
እንግዲህ ለያንዳዱ ላነሳችሁት አተካሮ መልስ ሰጥቻለሁ ፣ ሃራምባና ቆቦ እንዳትረግጡ ደግሞ የራሳች ሁን አባባል በቅደም ተከተሉ መሰረት እያስቀመጥኩ መልስ ይሆናል ያልኩትን ከስር ከስሩ አስቀምጫለሁ ፣ እናንተም ለጠየቅኩት ጥያቄ ባትመልሱም መልሱን ስለማውቀው መድከም አያስፈልግም ፣ ነገሩ ጉንጭ አልፋ ነው የሆነው ፣ እሰጣ ገባው እዚህ ላይ ያብቃ ።
ታዛቢው
ሰላም ወዳጆቼ እንደምን አላችሁልኝ ከዚህ በመቀጠል እኔ አስተያየቴን አክዬ መስጠት የምፈልገው እውነቱ ይናገር ባቀረበው ትክክለኛና ተገቢ የሆነው ሃሳብ ላይ ነው ቤተክርስቲያኒቱ ዛሬ ላይ ጠባቂ ያጣ እረኛ ሆና የገድሉንና የድርሳኑን ተረት የሰዎች አስተምህሮ የሆነውን የሥህተት ትምህርት ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ የሆኑ ልዩ ልዩ ግብስባሶ ነገሮች የተጠራቀሙባትና የታጨቁባት ብትሖንም ቤትዋን በመጥረግ የጠፋውን ድሪምዋን እንደፈለገች ሴት እኛም ይህንን ሁሉ የሥህተት የትምህርት አቡዋራ ጠርገንና አራግፈን በቃሉ ውስጥ ሰፍረው የተጻፉትን እውነት ከዚህች ቤት ስንፈልግ የከበሩና አይደለም ለሀገር ለዓለም የሚተርፉ ብዙ መልካም ነገሮች አግኝተንባታል ስለዚህ የሰው ወርቅ አያደምቅ እንደሚባለው በዚህች ቤት ውስጥ ተወልደን ጥርሳችንን ነቅለን ያደግን ነንና ከዚህ ሁሉ መልስ የትም መሄድ ሳያስፈልገን ወይም የትም ሳንሄድ ፣ አጊጠንና እንደ ሣራም በውስጥ ሰውነታችን ሳይቀር ተሸልመን ያለነው በዚህች ቤት ውስጥ ባለ መንፈሳዊ እውነትና እውቀት ነው 1ኛ ጴጥሮስ 3 ፥ 1 _ 6 ፣ ቆላስያስ 2 ፥ 6 እና 7 ፣ ኤፌሶን 3 ፥ 14 _ 19 ፣ 2ኛ ጴጥሮስ 3 ፥ 16 _ 18 ስለዚህ በቤትዋ ውስጥ የተወለዱትን ፣ በድንገት እና በስሕተትም ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ የተገኙትን ቤተክርስቲያኒቱንም ሲፈልጉ ለባርነት የሚዳርጓት አለበለዚያም ደግሞ የጨዋይቱ ልጅ የሚያደርጓትን የሣራ፣ የአጋር ፍሬ የሆኑትን እስማኤልና ይስሐቅን እንዲሁም ዘሮቻቸውንም ጭምር አውቀናል ስለዚህ ማን ከማን ተለይቶ መውጣትና መውረስ እንዳለበት ፣ እንደሌለበት ያወቅን ደግሞም የተረዳን ስለሆንን አንዱን ከሌላው ለይተንና ነጥለን ለማስወጣት የተቸገርን አንሆንም ስለዚህ ለባርነት የሚዳርገው የአጋር ዘር የሆነው እስማኤልና ዘሩ በቅርብ ቀን አብቅቶለት ፣ ተለይቶና ለይቶለትም መውጣቱ አይቀርም ከዚያ በኋላ ነው እንግዲህ ይህቺ እናት ቤተክርስቲያናችን የጨዋይቱ ልጆች የሞሉባት የሰማይቱ ሀገር የጽዮን ምሳሌ ሆና የምትቀጥለው ገላትያ 4 ፥ 21 _ 31 ይህ እስኪሆን ድረስ ግን ከወዴት እንደሆኑ የማይታወቁ አመልካችነታቸውም ለማን እንደሆነ በውል የማይታወቅ ፣ የት በቅለው በማን ተኮትኩተውና አድገው እዚህ እንደደረሱ በውል ያልተለዩ የቤተክርስቲያኒቱ ተቆርቋሪ ለመምሠል በየመድረኮችዋ ይንጫጫሉ እነርሱም ዛሬ ላይ በክተት ሠራዊት አዋጅ የተገለጡ ምሕረተ አብና ባልንጀሮቹ ብቻ ሳይሆኑ ከእነርሱም በፊት በዚሁ በእነርሱ ዓይነት መንገድ ተገልጠው ዓላማቸውን ያሳኩና በጊዜያዊ ገንዘብ የካበቱ ሰዎች ናቸው ታድያ እነዚህ ሰዎች ግን ከዚህ በኋላ በዚህች ቤት ውስጥ የማይፈነጩባት ይሆናሉ ለምን ስንል ይህን የሚያደርጉት ኃላፊነት ተሰምቶት ምርቱን ከግርዱ በመለየት እውነቱን የሚያውቅና ለእውነትም የሚቆረቆር አንድ መልካም የሆነ ሰው ስላጡ ነው ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ እንደሚባለው ይህቺ ቤተክርስቲያን የእውነት ቃል በሆነው በእግዚአብሔር ቃል የተመሠረተች ባለቤት ያላትና ባለቤቷም ክርስቶስ የሆነ ሲሆን አጥር ድንበርዋና መሠረትዋም እርሱ ክርስቶስ ነው ነገር ግን ቀን ስላልመጣና እውነቱም ስላልተገለጠ ሊጠበቁና ሊታገዱ የሚገባቸው የተጠባቂ ጠባቂዎች የታጋጅ አጋጆች ማኅበረቅዱሳን ፣ ምሕረተአብና ምሕረተአብን የመሰሉ ሰዎች ቤተክርስቲያኒቱን የዶሮ እርሻ አድርገዋት አሉ ይኖራሉም ይሁን እንጂ በዚሁ በቅርብ ቀን እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና የሚያጠራው የእግዚአብሔር ነገር በመጨረሻም የኋላኛውና የመጨረሻው ዝናብ ሊያጠራ ሊያስተካክል በዚህች ቤተክርስቲያን መምጣቱ አይቀርም
ከጸሐፊው
ምዕራፉ ይገለጥ
»» ምዕራፉ ተግለጦ እውነቱ ሲነገር ያገኘነው ጥበብ !?…
https://youtu.be/JShoxLbEjxg
https://youtu.be/I3javBPBkgI
….. ለዚህ ነበር ይህ ጽሑፍ ሲጀምር በአዋጅ፡ በፖለቲካ፡ ዘር ነክ አጠቃቀስኩ የጀመረው!?
” በጎልጉል ድረገጽ አዘጋጅ አባላት እንዳሰፈሩት “የማሰብ፥ የመናገር፥ የመጻፍ ወዘተ መብቶችን በማክበር ነበር ይህንን ጽሁፍ ፈቃድ ሰጥተን የለጠፍነው። ሆኖም በርካታው ምላሽ ሰጪ ሃሳብን በሃሳብ ከመሞገት ይልቅ ወደ ዘለፋ መሄዱም አማራጭ አድርጎ ስናይ ገና ብዙ ይቀረናል እንድንል ያደርገናል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ሃይማኖተኛ ነን የሚሉ ሰዎች በዚህ ረድፍ ተሰልፈው ማየት እጅግ ያሳፍራል።”….
በሚለው አቋምና ሃሳባቸው እስማማለሁ። ለሁሉም ግዜ ብቻ ሳይሆን ቦታ አለው። ከምሥጋና ጋር! ያዢ ያጣች ሀገር።
ታሪክ እራሱን ይደግማል
ሺ ዓመት የኖረውን ፤ ጎጆውን አፍርሶ
ያበላ ያጠጣውን ፤ የናቱን እጅ ነክሶ
የእምነቱን መለያ ፤ ማተቡን በጥሶ
የጉያ ውስጥ እሳት ፤ ጴንጤው ተሃድሶ
ሲሸረሽር ኖሮ ፤ አብሮ ተለሳልሶ
ወደ ጴንጤው ገባ ፣ እሮጠ ገስግሶ
ከረከሱት ጋራ ፤ ለመኖር እረክሶ ።
በቤተ ክህነት ፤ ያስተማሩት አባ
ቆቡን ያጠለቀ ፤ ዘይት የተቀባ
ገንዘብ አማለለው ፤ ጣሉት በጠረባ
ታድሻለሁ ብሎ ፤ ወደ ጴንጤው ገባ
ፍየል ሆነ በጉ ፤ ከእንግዲህ አይልም ባ
እዘኑ አልቅሱለት ፤ አፍሱለት እንባ ።
አልታይ ቢለው ፤ እሳት የነደደ
ለስጋው አደላ ፤ በክህደት ነጎደ
ቅዱሳንን ሁሉ ፤ ሰደበ አዋረደ
አይን እያለው ላያይ ፤ ሆኖ ተጋረደ
ቤቱን ጥሎ ጠፋ ፤ ሄደ ተሰደደ
ለሃሰተኛ አምላክ ፤ በእንብርክክ ሰገደ
ከብርሃን ይልቅ ፤ ጨለማን ወደደ
የሌጊዮን መስዋይት ፤ ሆነና ታረደ
ሳይፈረድበት ፤ በራሱ ፈረደ ።
አይምሮ እያለው ፤ ሰው ሆኖ ተፈጥሮ
መለየት ካልቻለ ፤ እውነትን መርምሮ
ቀልቡን ከሰረቀው ፤ ኑፋቄ አስተምህሮ
ልቡ ከፈቀደ ፤ መንተባተብ አብሮ
አቲዮ ባቲዮ ፤ ቅጥ አልባ ተናግሮ
ከዲያቢሎስ በቀር ፤ የማይሰማው ጆሮ
ትርጉም የለሽ ቋንቋ ፤ ያድነው ቀባጥሮ
ለሞት የተጠራ ፤ አይሰማም ተመክሮ
ይግባ ወደ እሳቱ ፤ ይጣል ተሽቀንጥሮ ።
እምነትም ፤ እንደ ጨርቅ ፤ ከሆነች ቡቱቱ
አውጥቶ ከጣላት ፤ በጥሶ ካንገቱ
ቀሚሱን አውልቆ ፣ ሱፉን መጎተቱ
መታደስ ከሆኑ ፤ ሱሪውና ኮቱ
ያድነኛል ካለ ፤ ያንገት ከረባቱ
ዳንኪራና ልሳን ፤ ከሆነ ድህነቱ
ተሃድሶው ጴንጤ ፤ ሁለቴ ናት ሞቱ
ሲዖል ልግባ ካለ ፤ ይሙላለት ምኞቱ ።
በገናም ካስጠላው ፤ ከበሮ ማሲንቆ
ዘበናይ ከሆነ ፤ ጽናጽሉን ንቆ
መንፈስ ከተሞላ ፤ ከመድረክ ላይ ወድቆ
ሲንደፋደፍ ውሎ ፤ አረፋውን ደፍቆ
ኩራቴ ናት ካለ ፤ ከረባት ሸምቀቆ
የፈቀደው ይሁን ፤ ይሙትባት ታንቆ ።
ቁሳቁስ ይመስል ፤ እምነት ላትታደስ
ተሃድሶ እያሉ ፤ መሯሯጥ መታመስ
የሞት ሃዋርያ ፤ ሆኖ ከመቀደስ
ደም የጠማው ሰይጣን ፤ ሄዶ በመቀስቀስ
ጴንጤው ተሃድሶ ፤ ስሙን በማድበስበስ
ምክንያት ከማብዛት ፤ ገብቶ ለመደነስ
እንቅልፍ አጥቶ ማደር ፤ የሰው ቤት ለማፍረስ
ደጅ መጥኛ አረገው ፤ ተዋህዶን መውቀስ ።
በነ ሉተር ሸንጎ ፤ ገብቶ መለሳለስ
ሳይጠራ አቤት ባይ ፤ የዲያቢሎስ ፈረስ
ምን ያደባብቃል ፤ ከረከሱ መርከስ
መታደሱን ትቶ ፤ ጴንጤነቱን መልበስ
ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ፤ ጉልበትን መጨረስ
እውነትን ኮንኖ ፤ ሃሰትን ማወደስ
ኦርቶዶክስ እንደሆን ፤ አትፈርስ አትቀመስ
እንኳንስ ልትጠፋ ፤ ይብስ ልትሞገስ
ታብባለች ገና ፤ በዓለም ላይ ልትነግስ ።
እነ ሱሪ ባንገት ፤ ካልወለቀ ባዮች
ምግባረ ይሁዳ ፤ የናት ጡት ነካሾች
ሆድ የሚገዛቸው ፤ ላበላ ሰጋጆች
ሞትን የሚጠሩ ፤ የሲኦል ወዳጆች
የጨለማው ልኡል ፤ የሳጥናኤል ልጆች
ትንቢት መፈጸሚያ ፤ የገሃነም ደጆች ።
ባለ ቃልኪዳኗ ፤ ለታመኗት ጋሻ
የጌታችን እናት ፤ ባዘለን ትከሻ
ሊያውም ሃጢያተኞች ፤ የሌለን መድረሻ
አለኝታ መጠጊያ ፤ በሆነችን ዋሻ
እሷን ጥሎ ሄዶ ፤ የት ይሆን መድረሻ፧
ያውም በማለቂያው ፤ በስተመጨረሻ
አልጋ ሲሉት መሬት፤ ዘበናይ አበሻ
ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ፤ ምርጫው ሆነ ውሻ፧
ባልታደሉ ሰዎች ፤ ሰይጣን በልብ አድሮ
ልክ እንደ ይሁዳ ፤ በሹክሹክታ መክሮ
በኑፋቄ ትምህርት ፤ ልብን አሳውሮ
ከቤተ መቅደሷ ፤ ደጃፍ ተገትሮ
ሊገባ ይዳዳል ፤ ቅጥሯን ተሻግሮ
መቼ ይደፈርና ፤ በመቤቴ ታጥሮ ።
ቅዳሴ እረዘመ ፤ ማርያም አትመስገን
ከፃድቃንም ቢሆን ፤ ከመላይክት ወገን
ምን አማላጅ ያሻል ፤ ጌታ ልጅ ካረገን ፤
እያለ አስተማሪ ፤ ጴንጤው ተሃድሶ
እንዳባቱ ክዶ ፤ ጠፋ ተልከስክሶ
ጉዞ እያደረገ ፣ ለዋይታና ለቅሶ
አብረን እንሙት ይላል ፣ መልሶ መላልሶ ።
ቆባቸውን ጥለው ፤ ከመቅደስ የወጡ
በየ ጴንጤው ደጃፍ ፤ የሚቀላውጡ
ከላይ ታች ቢሉ ፤ ዙሪያውን ቢሮጡ
ጺዮን ላይ ቢነሱ ፤ ሰው ቢበጠብጡ
አስሩን ቢጭሩ ፤ ሺውን ቢቧጥጡ
መጣላቸው ላይቀር ፣ ከጨለማው ማጡ
ከኦርቶዶክስ ደጃፍ ፣ ምናለ ባይመጡ ።
የገሃነም ደጆች ፤ ሊያጠፏት ቢያልሙ
በሚችሉት ሁሉ ፤ ቢለፉ ቢደክሙ
ለመውደቅ ካልሆነ ፤ ለመግባት ከፍሙ
ጌታ በመስቀሉ ፤ ያቆማት በደሙ
ቃሉ ቃል ናትና ፤ አይፋቅ ማህተሙ
ተሃድሶው ጴንጤ ፤ ይነገረው እርሙ
ተዋህዶ አትጠፋም ፤ እስከ ዘላለሙ ።
ያብረሃም ልጆች ነን ፤ ብለው የሚኩራሩ
ስለ ነቢያቶች ፤ ቆመው ያስተማሩ
መጻህፍት አዋቂ ፤ የተመራመሩ
በሃሰት ወንጅለው ፤ ጌታን ያሳሰሩ
ማን አለ ከነዚህ ፤ የከፋ በግብሩ
ድንጋይ ያቀበሉ ፤ ሰቅለው ያስወገሩ
እነ ተሃድሶም ፤ ሃቅን ያልተማሩ
በነ ሉተር ትምህርት ፤ ፊጢኝ የታሰሩ
በዲያቢሎስ ቋንቋ ፤ የሚቀባጥሩ
እንቆቅልሽ የለም ፤ ግልጽ ነው ሚስጥሩ
በሰላሳ ዲናር ፤ ተገዝተው በብሩ
አልታይ ቢላቸው ፤ ጥልቁ መቃብሩ
አፋቸውን ሞልተው ፣ በክህደት ተኩራሩ ።
የለጊዮን ሎሌ ፣ የማያይ አርቆ
በሉተር ኑፋቄ ፣ ልቦናው ተሰርቆ
ወላዲት አምላክን ፣ ከልቦናው ፍቆ
ቅዱሳን መላእክት ፣ ፃድቃንን አዋድቆ
በሃይማኖት ሽፋን ፣ እራሱን ደብቆ
ሰይጣናዊ ቋንቋ ፣ ልሳኑን ዘባርቆ
አብረን እንሙት ይላል ፣ በሞት ተጨማልቆ ።
ለትንሹ ያደረ ፣ ትንሹ አይምሮ
ለራሱ የሚዋሽ ፣ እውነትን ሰውሮ
አበውን ዘላፊ ፣ ስሩን አግተርትሮ
ድንግልን አዋራጅ ፣ የሰይጣን እንኩሮ
መቼም አያመልጥም ፣ ከዋይታና እሮሮ ።
ትንንሽ ጭንቅላት ፣ ክህደት የተሞላ
ወንጌል የሚያጣምም ፣ ቃላት እየከላ
ኑፋቄ አስተማሪ ፣ ካምላኩ የተጣላ
የፉኝት ልጅ እባብ ፣ የእምነት አሜኬላ
ሰው የተመሰለ ፣ ከሰው መሃል ያለ ፣ የዲያቢሎስ ጥላ ።
ትንንሽ ጭንቅላት ፣ አፈ ሰፋፊዎች
እሾህ ኩርንችቶች ፣ የገሃነም ደጆች
በጫጫታ አምላኪ ፣ የመድረክ ደናሾች
እንዳበደ ውሻ ፣ ያዩትን ነካሾች
የጨለማው ንጉስ ፣ ደቀመዝመዛሙርቶች
የዘመኑ አርዮስ ፣ ታድሰናል ባዮች ።
አእላፍ ቢነሱ ፤ ለመሆን ትኩሳት
ጆሮ አለመስጠት ነው ፤ እንዲሁም ፈት መንሳት
ከኛ የሚጠበቀው ፤ በአላማ መጽናት
የቀደመ እምነትን ፤ ጨርሶ አለመርሳት
ያለ የነበረ ነው ፤ ፈሪሳዊ መሳት ።
ሰው አያስተውልም ፤ እጅጉን ይገርማል
እምነት አትታደስ ፤ በከንቱ ይደክማል
ኑፋቄ እንደ ሞገድ ፤ ዙሪያውን ይተማል
ከድህነት ይልቅ ፤ ለመሞት ይፈጥናል
ታሪክ እንደገና ፤ እራሱን ይደግማል ።
የአምናው ፣ መምሩ
ዘንድሮ ፣ ፓስተሩ
ከነ ቀሚሳችሁ ፣ ከምትጨፍሩ
እስቲ ልብ ይግዙና ፣ ይሄን ይመርምሩ ።
https://www.youtube.com/watch?v=Hd78BCB37t0
https://www.youtube.com/watch?v=oh97_rC3czw
ታዛቢው
አንተም ተው፣ አንተም ተው!
በምንወደው ገልጉል ድረ-ገፅ ላይ በቅርቡ ከወጡት አምዶች “ሌላ የጦርነት አዋጅ በወገኖቻችን ላይ ታወጀ” የሚለው ሃይማኖታዊ ይዘት ያለው ነበር፡፡ ጽሑፉን ያቀረበው አቶ እውነቱ ይነገር፣ የኦርቶዶክስ ተሐድሶ የእምነት ጎራ ውስጥ መሆኑ እንዲታወቅ አድርጎ የተሰማውን ስጋት አስቀምጧል፡፡
ስጋቱንም “የጦርነት አዋጅ ታውጇል” በሚለው ጽሁፍ ውስጥ በትክክልና በማስረጃ አቅርቧል፡፡ ጽሑፉን ያነበቡ ሁሉ እንዳስተዋሉት ማስረጃዊ የሆኑ ነጥቦችንና የጦርነት አዋጅ ቀረበበት የተባለውን የቪዲዮ ማስፈንጠሪያ ተሰጥቶበታል፡፡ ከጽሑፈ ውስጥ በጣም ግልፅ እንደሆነው ከሆነ፣ የጽሑፉ አቅራቢ ሐሳብ የሚመስለው ለምን ተቻችለን አንኖርም? ለምን ብጥብጥ ውስጥ መግባት ያስፈልጋል? ችግር እንኳን ቢኖር ለምን በውይይት አንፈታውም? የሚል ነበር፡፡
በማህበረሰቡ ውስጥ ችግር ይፈጥራሉ የሚባሉ ስጋቶችን አይቶ ይሄ ነገር ያሰጋል፣ “ሳይቃጠል በቅጠል እንበለው” የሚል ሰው መገኘቱ የሚያስመሰግን ነው፣ የጽሑፉ አቅራቢ አቶ እውነቱ ይነገር (ይሄ ስም የብዕር ይሁን አይሁን እኔ አይደንቀኝም)፣ ማስረጃዎቹን ከስጋቱ ጋር አቅርቦ በመሪነት ላይ ለተቀመጡትና ያገባኛል ለሚሉት እንዲሁም ለሕዝቡ ሁሉ “የአንተም ተው የአንተም ተው” ሽምግልና ውስጥ እንዲገቡ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
እንዲህ ዓይነት አስጊ የሆኑ ነገሮችን ገልጦ አንድን የሕዝብ ቡድን በሌላው ቡድን እንዳይጠቃ ችግሩን ሰምተውና አይተው የሚጠቁሙ ሰዎች መኖራቸው ለአንድ አገር እድገትና ማህበረሰባዊ መቻቻል በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የነፃ ጋዜጠኞች ጋዜጣዊ ሚናና ሙያ፣ የጎልጉልና ሌሎች የድረ-ገፅ መድረኮችም ሚናና የተቋቋሙትም ለዚህ ነው፣ ምነው፣ ምነው እንደ አቶ እውነቱና እንደነጎልጉል ሚዲያዎቹ ያሉት ቢበዙልን!
የአቶ እውነቱ ይነገርን ጽሑፍ ብዙዎች እንዳነበቡት እገምታለሁ፣ ነገር ግን ከብዙዎች አንባቢዎች መካከል እንዲህም ዓይነት ስጋት አለ እንዴ? ብለው ጥንቃቄ የሚያደርጉ ሊኖሩ ሲችሉ፣ አንዳንዶች ደግሞ ይሄ አይነት ስጋት በጭራሽ የለም የሚሉ ይገኛሉ፣ አንዳንዶች ደግሞ ነቀፋ የመስጠትና የማጣጣል እርምጃዎችን ይወስዳሉ፡፡
ጎልጉሎች ሐሳብን በሐሳብ የመሞገት ባህልን እንደሚያራምዱ አውቃለሁ፣ በዚህ ግልፅነታቸው ተጠቅሜያለሁ፣ ደስም ይለኛል፣ ስለዚህ የማጣጣል ዘመቻ ካካሄዱት ጋር ጥቂት የሐሳብ ሙግት ውስጥ ለመግባት እፈልጋለሁ፡፡
ታዲያም የአቶ እውነቱን ጽሑፍ አንብቤ፣ የተሰጡትን አስተያየቶች በዝርዝር ተመልክቻለሁ፣ አስተያየቶቹ ከላይ እንደጠቆሙኩት ደጋፊ፣ ሚዛን ሰፋሪ እና ተቃዋሚ ወይንም ነቃፉ ተብለው ሊፈረጁ ይችላሉ፡፡ ይህን ጽሑፍ በተመለከተ ከቀረቡት ውስጥ ደጋፊዎቹና መሐል ሰፋሪዎቹ ጥቂቶች ሲሆኑ ነቃፊ ወይንም ተቃዋሚዎቹ ጽሑፎች ያመዝናሉ፡፡ ከነቃፊዎቹ መካከል አራት ጊዜ በስድ ጽሑፍ አንድ ጊዜ በግጥም የቀረበው በአንድ ነቃፊ በኩል ነው፡፡ ከግጥሙ ጭምር አምስቱን ጽሑፎች ያቀረበውን ነቃፊ ትንሽ መሞገት እፈልጋለሁ፣ መብቴም ነው፡፡
የአቶ ታዛቢው ጽሑፎች
ነቃፊው አቶ ታዛቢ በመጀመሪያው የነቀፋ ጽሑፉ ውስጥ የብዕር ስም አጠቃቀምን አውግዞ ጸሐፊው ማንነቱን ግልፅ ቢያደርግ መልስ ለመስጠት ይመቸው እንደነበረ ገልጧል፣ ጥሩ ነበር ነገር ግን አቶ ታዛቢው እራሱ የብዕር ስም እየተጠቀመ አለማወቁ ቢያንስ ቢያንስ እኔን አስገርሞኛል፣ ሚዛን ያጣ አካሄድ መሆኑንም ጠቁሞኛል፣ አቶ ታዛቢው አንት እራስህ ለመንቀፍ እንዲያመችህ የራስህን ስም ለምን አልጠቀስከው?
ነቃፊው አቶ ታዛቢ ብዙ ጽሑፎችን ሲያስነብበን ስለኖረ የእርሱ ማንነት ለሁሉም ግልፅ ነው፣ በእርግጥ እንደዛሬው አይሁንና አቶ ታዛቢው ድሮ ድሮ በትክክል ስሙ ያስቀምጣቸው የነበሩት ጽሑፎቹ ጥሩና ትምህርታዊነት የነበራቸው ነበሩ፡፡ አቶ ታዛቢው በድሮ ጽሑፎቹ ምን ያህል ለአገር ተቆርቋሪ መሆኑ እያስደነቀን ለትልቅ ማዕረግ እንዲበቃ ምኞታችንን ብቻ ሳይሆን ድጋፋችንንም ሁሉ ለመስጠት ወደ ኋላ የማንል እንደነበረ ማንም አይስተውም፡፡
የአቶ ታዛቢው ጽሑፎች በየጊዜው መልካቸው እየተለወጠ መምጣት ከጀመረ ታዲያ ሰነባብቷል፣ እንደዚያ ብዙ እውነቶችን ይፈነጥቁ የነበሩና፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ እውቀት ክምችት ከነበረበት የዩኒቨርስቲ መምህር አዕምሮ ውስጥ ይወጡ የነበሩት አስተማሪ ጽሑፎች በድንገር በስድብ ውርጅብኞች ተለወጡ፡፡ ፖለቲከኞችንም ሆነ ሃይማኖተኞችን መስደብና ማዋረድ የአቶ ታዛቢው የዋና መጠሪያ ስምና መታወቂያም ከሆነ ሰነባበተ፡፡ ያ ሰው ሁሉ ይጠብውና ይወደው የነበረ ጽሑፍ ቁም ነገር ሰጪነቱ አልፎ ወደ ስድብና ስርጠጣ ማስተማሪያነት ተለወጠ፣ ስለዚህም አቶ ታዛቢው በብዕር ስም መምጣቱ ምንም አያስደነቅም፣ ቢያንስ እኔን አያስደንቀኝም፣ የምሁራዊ በሳል አስተያየት አሰጣጡ ገና ድሮ እንደጥላ ጥሎት ስለሄደ መለያ ታርጋው ስድብ ብቻ ሆኗል፡፡
በእርግጥ አቶ ታዛቢው ወደ ስድብ ውስጥ ዘልቆ የወረደው፣ ነገሮች እንደሚፈልገው ባለመሄዳቸው ሊሆን ይችላል፣ ምናልባትም ኢህአዴግ ስልጣን ባለመልቀቁ ተበሳጭቶ ይሆናል፣ ቢሆንም ግን አንዳንዴም ስድብ አልባ የሆነ ጽሑፍ መጻፍም እኮ ያስፈልጋል፣ አቶ ታዛቢው በሁሉ ነገር ሰዎችን ሁሉ የሚሳደበው መካሪ ስላጣ ይሆን! ጽሑፍህ ስድብ ይበዛበታል የሚል ወዳጅ ስለሌለው ይሆን? ከሆነ ደግሞ በጣም አዝንለታለሁ!
አቶ ታዛቢው በሃይማኖት ውስጥ መግባት የጀመረው አሁን አይደለም፣ የለንደኑ ቤተክርስትያን ብጥብጥ ውስጥ አንዱን ደግፎ ሌላውን ይነቅፍ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ነው፣ ይህም ምንም አይደለም ግን ስድብ ምን አመጣው? አስተያየትን ያለስድብ ማስቀመጥ አይቻልም እንዴ? ስድብ አልባ ጽሑፍና አባባል የኛ አገር የጨዋነት ምልክት አይደለም እንዴ? ደግሞስ አቶ ታዛቢው ያላመነውን ነገር ያመኑ ሰዎች እርሱ ያላመነውን ባለማመናቸው መሰደብ አለባቸው እንዴ?
በአቶ እውነቱ የተጻፈውን ጽሑፍ አንብቤ አቶ ታዛቢው አምስት ጊዜ የተሰጠውን መልስ ስመለከት የአቶ ታዛቢውን ሚዛናዊነት ተጠራጥሬዋለሁ፡፡
የአርዮ ፍሬዎች በሚል ርዕስ በአቶ ታዛቢው የቀረበው ሃሳብ ከመጀመሪያው አረፍተ ነገር ጀምሮ እስከ መደምደሚያው የተቀመጠው በስድብ ቃላትና ሐረጎች ነው፣ ምነው አቶ ታዛቢው ሐሳብህን ያለስድብ ማቅረብ አትችልም ማለት ነው፡፡ አየህ የስድብ ውርጅብኝ የሆነው ይህ ጽሑፍህ የብዕር ያልሆነውን እውነተኛውን መጠሪያ ስምህን ማንነት አሳብቆብሃል፣ እኔ ያንን ስምህን ስለምታውቅና ስድብህን የሚያውቁ ስለሚያውቁት መናገር አልፈልግም፣ ሆኖም ለዚህም ጽሑፍ የስድም መልስ ስትሰጥ ያን ጊዜ እገልገጠዋለሁ፡፡
አቶ እውነቱ ለአንተና ለሌሎች መልስ የሰጠው ቁጣም ስድብም ሳይኖርበት ነበር፣ ለአቶ እውነቱ የመልስ መልስ ስትጽፍ ያስቀመጥካቸው ስድቦች አሁንም የሚገርሙ ናቸው፡፡ መሆን የነበረበት ጥያቄ፣ የጦርነት አዋጅ አስግቶኛል ብሎ አቶ እውነቱ ያቀረበው ሃሳብና ማስረጃ ተጨባጭ ነው አይደለም፣ ተገቢ ነው አይደለም? የሚሉትን ጠቅሶ ተጨባጭና ተገቢ ካልሆነ በማስረጃ ማስረዳት፣ በማስረጃ የተጨበጠ ከሆነ ደግሞ እንደ አዋቂና ምሁር መፍትሔ ለመፈለግ መነሳት ይገባ ነበር፡፡ አቶ ታዛቢው ያሳየኸው ነገር ግን ቁጣ ንዴት እና ስድብ የተሞላው ውርጅብኝ ነበር፣ አንተን እንደዚህ ናላህ እስኪዞር ድረስ እንድትሳደብ ያደረገህ ምክንያቱ አልገባኝም! አንድ ሰው ስጋቱን ለምን ገለፀ ነው፣ ወይንስ ጭፍን ጥላቻ ነው?
ከአቶ እውነቱ ስጋት ጋር የተቀራረበ ወይንም የአቶ እውነቱን ስጋት የተጋራ ሊሆን የሚችለው ጽሑፍ የአቶ ጥበቡ ነበር፡፡ የአቶ ጥበቡንም ጽሑፍ በተበመለከተ የሰጠኸው መልስ ሙሉውን ስድብ ነው፣ አሁንም ለምን መሳደብ አስፈለገ፣ የኢትዮጵያዊነት መቻቻልና በስነ ስርዓትና በወግ መነጋገር አልተማርክም ነበር ማለት ነው? ወይንስ ንዴትህን በስድብ መናገር ለውጥ ያመጣል ብለህ አስበህ ይሆን? መልሱን ለአንተ ልተወው፡፡
አቶ ጥበቡ መጠነኛ መልስ ሰጥቷል የሰጠውም በጨዋነት ደንብ ነው፣ ስድብም ንቀትም አልነበረበትም፣ እኔም ስድብና ንቀት አይወጣኝም፣ የዩኒቨርስቲ አስተማሪና ለትልቅ ደረጃ እጠብቅህ የነበርከውን ምሁር አልሳደብም፣ ስድብ አስፀያፊና ነውር ነው፣ ከባህላችን ጋር አይሄድም፡፡ አንተ ግን ከአንድ ምሁር የማይጠበቅ ከጽሑፋዊ ጨዋነት መስመር የወጣ ስድብን ደረደርክ፣ ለዚህ እንደ አጭርና ስለአንድ ስጋት የተጻፈ ነገር ግን ስድብ በሌለበት ጽሑፍ ላይ ጽሑፍ አራት ጊዜ በስድ ንባብ አንድ ጊዜ በድምሩ አምስት ጊዜ የሰጠኸው መልስ ሙሉውን ስድብ ነበር፡፡
በእርግት የአንተ ስድብ ከአቶ ጥበቡ ጋር በነበረህ እስጥ አገባ ያበቃ ይሆናል ብዬ ገምቼ ነበር፡፡ ነገር ግን በስድ ንባብ ያቀረብከውን በስነ ግጥምም ደግመህ አቀረብከው፣ ግጥምህን እየሳቅሁ አንብቤዋለሁ፣ ለነገሩ ጥሩ ትገጥማለህ፣ ስለግጥምህና ስለእያንዳንዱ ስንኝ ስድብህ ሳስብ ተሳዳቢም፣ ለስድብ ግጥም መግጠም ይችላል! በማለት ደንቆኛል፣ ለነገሩ ከተሳዳቢው አዕምሮ ስድ ንባብ ከወጣ ግጥምም የማይወጣበት ምክንያት የለውም፣ ምንጫቸው አንድ ነውና፡፡ አቶ ታዛቢው (ተሳስቼ ዋናውን ስምህን እዚህ ላይ ልጠቅሰው ነበር) ለመሆኑ ሐሳብህን ያለስድብ ማቅረብ አትችልም ማለት ነው?
የአቶ ታዛቢው የስድብ ቃላትና ሐረጎች
በአቶ ታዛቢው አራት ጽሑፎችና ግጥም ውስጥ ያሉትን ስድቦች መዘርዘር በእርግጥ ስራ መፍታት ነው፡፡ ነገር ግን ለአቶ ታዛቢው የወደፊት ጽሑፎች ስድብ አልባና ገንቢ እንዲሆኑለት ማስተዋልና እንዲችል፣ አንባቢዎችም ስድቦቹ በማንኛውም መልኩ (ሃይማኖታዊም ሆነ ፖለቲካዊ) ስነምግባር የጎደላቸው መሆኑን ለማሳየት ጥቂቶቹን ብቻ ልጥቀሳቸው፡
1. በመጀመሪያው ጽሑፍ ውስጥ ካሉት ስድቦች በከፊል፡
“የሉተር ቅፍቅፎችና ፍልፍሎች”፣ “የመለስና የስብሃት ነጋ ውጤት”፣ “ሆድ አደር ወፍ ዘራሾች”፣ “ዝርዝር ስድብና “”የፈሲታ ተቆጢታዎች””፣ “የተጻፈ አንብቦ መረዳት ያቃታቸው”፣ “የዞረባቸው”፣ “እየገረፉ የሚያለቃቅሱ”፣ “የኛ ፍራሽ አዳሾች”፤ ወዘተ፣
2. በሁለተኛው ጽሑፍ ውስጥ ካሉት ስድቦች በከፊል፡
“ስምህን ሐሰቱ ይለፈፍ ብለህ ቀይረው”፣ “የማይገባህ”፣ “እራስን መቆለል”፣ “በራስህ ትንሽ አዕምሮ ውስጥ አለህ”፣ “የምትናቅ ነህ”፣ “የዞረብህ”፣ “ዞሮብሃል”፣ “የምታሳዝን፤ ሊታዘንልህ የሚገባ”፣ ወዘተ፣
3. በሦስተኛው ጽሑፍ ውስጥ ካሉት ስድቦች በከፊል፡
“የማደናቆር ጨዋታ ነው የያዛችሁት”፣ “እንደማይገባችሁ አውቃለሁ”፣ “አባ ዲያቢሎስ”፣ “ያንተ ቢጤ መናፍቅ”፣ “ሲንቋችሁ የተፈራችሁ ይመስላችኋል”፣ ወዘተ፣
4. በአራተኛው ጽሑፍ ውስጥ ካሉት ስድቦች በከፊል፡
“የነገሩ ጭብጥ አይገባችሁም”፣ “ባዶ ናችሁ”፣ “ሳይገባችሁ ያዘን ልቀቀን ብላችሁ አገር ታምሳላችሁ”፣ “በጉድለታቸው የሚመፃደቁ፣ የበግ ለምድ የለበሱ”፣ “መፃጉዎች”፣ ወዘተ፣
5. በአምስተኛውና በግጥሙ ውስጥ
በግጥሙ ውስጥ ያሉትንና ክብረ ስብዕናን የሚያዋርዱትን፣ ከአንድ ምሁርና የሃይማኖት ሰው ጭራሽ የማይጠበቁትን ስድቦች አንባቢ እንዲመለከት እጋብዛለሁ፡፡
ድሮ ድሮ ጴንጤዎችን ስለ እምነቱ የማያውቁ ሰዎች፣ ለልብስ ብላችሁ ነው፣ ለዘይት ብላችሁ ነው፣ ለገንዘብ ብላችሁ ነው፣ እንላቸው ነበር፣ ብዙ ሰዎች ገንዘብና ዱቄት ጴንጤ እንደማያስደርግ፣ እንደዚያ ማለት ባዶ ወሬ መሆኑን አውቀዋል፣ እንደዚያ የሚባልበትም ጊዜ አልፏል፣ የአቶ ታዛቢው ግጥም ግን የዛሬ አርባ ዓመቱን ያስታውሰናል፣ መማር ከሚሰጠው ጥቅም አልታደሉም አልልም፣ የጥላቻ ሽምጠጣ አሳውሯቸዋል እንጂ፡፡
ወደሚቀጥለው ነጥቤ ከማለፌ በፊት አቶ ታዛቢውን ጥቂት ጥያቄዎችን ላቀርብለት እወዳለሁ፣ አቶ ታዛቢው፡ እንደዚህ ተሳዳቢ ያደረገህ ምንድነው? እውቀትህና ትምህርትህ ነው? ሃይማኖትህ ነው? የምትፈልገው ነገር አልሳካ ስላለህ ውስጣዊ ብስጭትህን ለመወጣት ነው? ወይንስ አስተዳደግህ ነው? አስተዳደግህ ከሆነ ትምህርትህ እንዴት አልቀየረህም? ትምህርትህ ተሳዳቢ አድርጎህ ከሆነ ደግሞ ሃይማኖትህና ባህልህ ለምን አልቀየረህም? ያንተ ስድብ ለሁሉ ሰው ጥያቄ ነው፡፡ የአቶ ታዛቢው ስድብ፣ “አፍ ሲያመልጥ እራስ ሲመለጥ አይታወቅም” እንደሚባለው ኣባባል ቢሆን ኖሮ የአንድ ጊዜ ስህተት ነው ብለን እናልፈው ነበር፣ የአንተ ስድብ ግን “አፍና ቂጥ እንዳስለመዱት ነው” የሚባለው አባባል ዓይነት ነው፣ ምነው ልምድህን ብትተወው?! እንዳንተ ከተማረም ሰው ይሁን ከማንም አዕምሮ ካለው ሰብዓዊ ፍጡር ስድብ በጭራሽ አይጠበቅም፡፡
የሚገርም ተስፋ
አቶ ታዛቢው ካደረጋቸው የጽሑፍ ምልልስ ውስጥ ስድቡን ትቶ ወደ ትክክለኛው መንገድ የመመለስ ተስፋ እንዳለው መመልከቴን ሳልጠቅስ ለማለፍ አልፈልግ፡፡ ከአቶ ጥበቡ ጋር በተደረገው እስጥ አገባ፣ (እሰጥ አገባ ልበል!)፣ አቶ ጥበቡ፣ ለጽሑፉ መልስ አቶ ታዛቢውን እንደተደራሲ በአድራሻው ላይ ሲጠቅስ፣ የአቶ ታዛቢን ርዕሰ መለያውን ማለትም(Zebirkrik) የሚለውን በአማርኛ ጠቅሶ፣ ለዝብርዝቅ ብሎ በቅንፍ ደግ ለታዛቢው በማለት አስቀምጦ ነበር፣ ከዚያን ሰዓት ጀምሮ በእንግሊዝኛ ዝብርቅርቅ የሚለውን አቶ ታዛበኒው አጥፍቶታል፡፡ ለዚህ እርምጃው የአቶ ታዛቢ ምክንያት ምንም ይሁን ምን፣ እኔ ግን ለካ ይህም ሰውዬ ከስድብ ሕይወቱ ሊመለስ ይችል ይሆናል፣ የሚል የሚገርም ተስፋ አድሮብኛል፣ ስለዚህም ተሳዳቢ የሚለው መታወቂያ ተለውጦ ስድበ አልባ ጠቃሚ ጽሑፎች ወደ መጻፍና እንደ ድሮው ወደ አስተማሪነቱ ይመጣል የሚል ተስፋ አድሮብኛል፣ የሚገርም ተስፋ ትሉት ይሆን? እኔ ብየውለሁ፡፡ የአቶ ጥበቡ ድርጊት ቢያንስ ይህንን አስቀይሯልና፣ አቶ ጥበቡን ሳላመሰግንና መልካም ውጤት አምጥተህልናል ሳልል አላልፍም፡፡
ይህን ሁሉ ማለት ያስፈለገው ለመማማርና ለመገነባባት ነው እንጂ ለማፍረስና ለማጥፋት እንዳይደለ አቶ ታዛቢው እንደሚረዳልኝ ተስፋ አለኝ፣ አቶ ታዛቢውም ሆነ ማንም አስተያየትና ጥያቄ ካላችሁ በኤሜል ልትገኛኙኝ ትችላላችሁ፡፡
አሁንም እኔ ይጠቅማል የምለው ችግር ሲነሳ፣ ወይንም ስጋት ሲሰማን፣ ሽምግልና ገብቶ አንተም ተው፣ አንተም ተው፣ ማለትና መሸምገል ነው፣ ያሳደጉን አባቶች ያስተማሩን መቻቻል ለምን ይጥፋ፣ አንተም ተው፣ እባክህ አንተም ተው!
ቸር ይግጠመን
አክባሪያችሁ
ሐሰን
hasen.jafar2@gmail.com
“አንተም ተው አንተም ተው” ጥሩ አባባል ነው ።ሆኖም ግን አርእስቱና በውስጡ ያዘለው ወገናዊ የሆነ አመለካከት “አንተም ተው አንተም ተው” ሳይሆን ወገንተኝነትን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ እንደሆነ ልነግርህ እወዳለሁ ። እንግዲህ ወደ መልስ መስጠቱ ከመግባቴ በፊት ያንተን የብዕር ስም ይሁን እውነተኛ ስምህ እንደሆነ ባላውቅም በግምት ግን እውነተኛ ስምህ ይመስለኛል ። እዚህ ላይ በግምት የሚለው አባባል ይሰመርልኝ ። ስለሆነም አንተ እምነትህ እስልምና እንደሆነ ሰው አድርጌ ለሰጠኸው ትችት ፣ አስተያየት ፣ ዘለፋ መልሱን በዚያ አይነት አቀራረብ እንደምቀርበው ከወዲሁ ላሳውቅህ እወዳለሁ ።
በመጀመሪያ ስለሁለቱ ግለሰቦች ስም ልሂድና በዚያ ላይ ያለኝን አመለካከት ቢዋጥልህም ባይዋጥልህም ለማስረዳት እሞክራለሁ ፣ የመጀመረያው ጸሃፊ ስሙን “እውነቱ ይነገር” ብሎ መጥቷል ያን እኔም ሆንኩ አንተ እውነተኛ ስሙ እንዳልሆነ በሚገባ የምናውቅ ይመስለኛል ፣ በሁለተኛ ደረጃ የመጣው ጸሃፊ ደግሞ ስሙን “ጥበቡ ሞላልኝ” ብሏል አየህ የሁለቱንም ስም ልብ አርገህ ብትመረምረው ምናልባት ላንተ ላይገለጽልህ ይችላል እንጂ ፣ እውነቱ ይነገር ሲል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዋሾ ጴንጤው ግን ሃቀኛ ነው ለማለት ነው ። ሁለተኛውም ጸሃፊ ጥበቡ ሞላልኝ ያለው ፣ እኛ ጴንጤዎች ጥበቡ ወይንም እውቀቱ የሞላልን አዋቂዎች ነን ። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግን ጥበቡ የጎደላቸው እምነትም የጎደላቸው ለማለት ነው ። አሽሙር ባህል በሆነበት አገር አድገን እቺ እቺ ትጠፋን ይመስልሃል ? ልትቀበለው ላትቀበለው ትችላለህ ፣ እውነታውና ሃቁ ግን ይሄው ነው ።
በመቀጠልም አቶ ሐሰን አንዲህ ብለሃል “ነቃፊው አቶ ታዛቢ በመጀመሪያው የነቀፋ ጽሑፉ ውስጥ የብዕር ስም አጠቃቀምን አውግዞ ጸሐፊው ማንነቱን ግልፅ ቢያደርግ መልስ ለመስጠት ይመቸው እንደነበረ ገልጧል ።” ስትል ተችተሃል ይሀንን አባባል የት እንዳገኘኸው ብታሳውቀኝ ደስ ባለኝ ነበር ፣ እኔ እራሴ የጻፍኳቸውን መልሶች ዘወር ብዬ ባገላብጥ እንኳ ላገኛቸው አልቻልኩምና ብትረዳኝ እወዳለሁ ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ ጥበቡ ሞላልኝ በመጀመሪያ ሲጀምሩ “ማንነታቸውን ለሰወሩት ወይም በማንነታቸው ለሚያፍሩት” ብለው ጀመሩ ፤ ጸሐፊው እውነቱ ይነገር ብለው ስማቸውን አስቀምጠዋል ፤ ነገር ግን እርስዎ እራስዎ ታዛቢው ብለው ነው ስምዎትን ያስቀመጡት ፤ ታዲያ የራስዎን ስም ደብቀው የሰውን ማንነት መጠየቅዎ እርስዎ ያልሆኑትን ሌላው እንዲሆን መፈለግዎ ትንሽ ግራ የሚያጋባ አይመስልዎትም ? እንደ እኔ መረዳት ቁምነገሩ ያለው ስማቸው ወይም ማንነታቸዉ ላይ ሳይሆን የጻፉት ጽሑፍ ይዘት ላይ ሊሆን ይገባ ነበር ።” ብለው ለጻፉት መልሰጥ እንዲህ በማለት መልስ ሰጥቻለሁ ። “በቅድሚያ ምንም የሞላልህ ጥበብ እንደለሌ ልነግርህ እወዳለሁ ፣ አንተም ሆንክ እውነቱ ይነገር ነኝ ባዩ ሁለታችሁም ስማችሁ እንዳልሆነ አንተም ታውቃለህ እኔም አበጥሬ አውቃለሁ ። ነገር አይገባችሁም የምለው ከመሬት ተነስቼ አይደለም ። አንተም ስታነብ ነገሩ በደንብ እንዲገባህ አድርገህ አንብብ ተነካሁ በሚል በግንፍለኝነት አትናገር ፣ ማንነታችሁን አትደብቁ ነው ያልኩት ጮኬ መጻፍ አልችል ጮኬ መናገር እንጂ ። ጥበቡ ተባለ እውነቱ ከናንተ የብዕር ስም አይደለም ጉዳዬ ጴንጤ ስትሆኑ አንዴ ተሃድሶ አንዴ ኦርቶዶክስ አትበሉሉሉሉሉ………። አማርኛ ይገባችኋል? “በማለት መልስ ሰጥቻለሁ ። ጉዳዬ ከነሱ የብዕር ስም አልነበረማ! አየህ አንተም ሳታነብ ነገሩን ሳትረዳ ወደትችቱ ነጎድክ ። ማንነታችሁን የሚያመለክተው የብዕር ስማቸውን ሳይሆን የእምነት ጎራቸውን ነበር ፣ አንተ ግን “ታዛቢ በመጀመሪያው የነቀፋ ጽሑፉ ውስጥ የብዕር ስም አጠቃቀምን አውግዞ ጸሐፊው ማንነቱን ግልፅ ቢያደርግ መልስ ለመስጠት ይመቸው እንደነበረ ገልጧል ።” ብለህ ያልተባለን እንደተባለ አድርገህ አስቀምጠሃል ይሄ አንዱ ስተትህ ሲሆን በመቀጠል “ነገር ግን አቶ ታዛቢው እራሱ የብዕር ስም እየተጠቀመ አለማወቁ ቢያንስ ቢያንስ እኔን አስገርሞኛል፣ ሚዛን ያጣ አካሄድ መሆኑንም ጠቁሞኛል፣ አቶ ታዛቢው አንት እራስህ ለመንቀፍ እንዲያመችህ የራስህን ስም ለምን አልጠቀስከው?” ስትል በትችት መልክ አስቀምጠሃል ለዚህ መልስ ለመስጠት በመጀመሪያ እኔ የብዕር ስም አልተጠቀምኩም አላልኩም ፣ ስለራሴም የብዕር ስሜ አይደለም የሚል አንድም ቦታ በማከላከያነት አልጠቀስኩም ። አንተ ግን ባጠቃላይ ወገንተኛ ስለሆንክና የኔ አጻጻፍና አቀራረብ አልጥም ስላለህ በሩጫ አንብበህ በሩጫ ትችትህን አቅርበሃል ። አሁን በዋናነት ያነሳኸውና ያንገበገበህ ነገር ቢኖር ጽሁፍህ ውስጥ እንዳለ ስድብ ይበዛዋል ብለህ የቻልከውን ያክል ከጻፍኳቸው ውስጥ ከብዙው በጥቂቱ መርጠህ አነዚህን አቅርበሃል ። “የሉተር ቅፍቅፎችና ፍልፍሎች”፣ “የመለስና የስብሃት ነጋ ውጤት”፣ “ሆድ አደርወፍ ዘራሾች”፣ “ዝርዝር ስድብና “”የፈሲታ ተቆጢታዎች””፣ “የተጻፈ አንብቦ መረዳት ያቃታቸው”፣ “የዞረባቸው”፣ “እየገረፉ የሚያለቃቅሱ”፣ “የኛ ፍራሽ አዳሾች” ሲጀመር ያልኳቸው ቃላቶች በሙሉ ስድቦች ሳይሆኑ ማንነትን አመልካች ናቸው ። ላንተም ሆነ ለጴንጤዎቹ ግን ስድብ መስሎ ሊታያችሁ እንደሚችል በደንብ እረዳለሁ ። በምሳሌ ላስረዳህ በጦር ሜዳ ጀግናን ሰው ለማወደስ አንበሳው ፣ ሳተናው ፣ አጅሬ ወዘተ… ይባላል እንዲሁም ባንጻሩ ለፈሪው በተመሳሳይ ሁኔታ ቡከን ፣ ቦቅቧቃ ወዘተ … ይባላል ያ ግለሰቦችን በግብራቸው ገላጭ ነው ፣ አኩሪ ተግባር ያለው እንደ ጀግናው ያለ አጅሬ ፣ አንበሶ ቢባል ደስ ይለዋል እንጂ አይከፋውም ፣ እንዲሁም ባንጻሩ ፈሪው ቡከን ፣ ቦቅቧቃ ሲባል ሊከፋው ይችላል ። ስለሆነም አሳፋሪ ተግባር የሰራ ሰው በዚያ አሳፋሪ ተግባሩ ሲጠራ ተሰደብኩ ማለቱ አይቀሬ ነው ። ስለዚህ ላንተም ለሌሎችም ስድብ ከመሰላችሁ አዝናለሁ ። እንደዚህ አይነት አገላለጽ ለኔ የግለሰቦቹን ወይንም የቡድኑን ማንነት ጥሩ ገላጭ ስለሆነልኝ ወደፊትም በዚሁ ሁኔታ እንደምቀጥል ነው ።
በጣም የገረመኝ ነገር ግን ቢኖር ስለ መለስ ዜናዊ ፣ ስብሃት ነጋ እንዲሁም ስለ ሟቹ አባ ዲያቢሎስም የተነሳው ነገር አንገብግቦሃል ። አሁንም ስብሃት ነጋንና መልስ ዜናዊን ባንዳ የባንዳ ልጆች ብዬ ብናገር ተሳደብክ ትለኝ ይሆናል ። አየህ ሰውን በግብሩ መጥራት የተለመደ ነው ስለሆነም ተነኩብኝ የምትላቸው ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች በግብራቸው ሊጠሩ የግድ ነው ። መለስ ዜናዊ ፣ ስብሃት ነጋ ፣ አባ ዲያቢሎስ እንዲሁም ጠቅላላ ወያኔዎችና የወያኔ ደጋፊዎች ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ለማጥፋት እንደተነሱ እነሱ አፋቸውን ሞልተው የተናገሩትን ልታስክዱን ባትሞክሩ እንዴት ደስ ባለን ። ስለሆነም በሉተር ቅፍቅፎችም ሆነ ወፍ ዘራሾች ዛሬም ሆነ መቼም ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ማጥፋት እንደማይቻል ላበስርልህ እወዳለሁ ።
ወያኔንና ባንዳውንም ሁሉ ሆድ አደር ፣ ባንዳ ብዬ እጣራለሁ ፣ ተሰደብን ካሉ ያ የነሱ ችግር ነው ። አይ እኔም እዚያ ውስጥ አለሁበት ካሉ አቶ ሐሰንም ቢያሳውቁን ደስ ይለናን ። የማይረባን ነገር አይረባም እላለሁ እንጂ ፣ አላወድስም ። እንዲህ ያለ ሽንገላ በጭራሽ አይመቸኝም ። እስቲ አቶ ሐሰን እዚህ ላይ አንወሻሽና በኔና ባንተ መሃከል ብቻ እቺ ጽሁፍ ከኢንባሲ አካባቢ ነው እነዴ የወጣችው ?
በመቀጠልም “አቶ እውነቱ ይነገር ስጋቱንም “የጦርነት አዋጅ ታውጇል” በሚለው ጽሁፍ ውስጥ በትክክልና በማስረጃ አቅርቧል፡” ብለሃል አዎ ያ ተባለ የተባለው እኮ በዩ ትዩብ ላይ ያለ ማንም ሊያየው የሚችል ነው ። በተመሳሳይ ሁኔታም በየ አብያተ ክርስቲያኑ የሚነገር ሸርሻሪዎች ፣ የበግ ለምድ ለብሰው እንደመጡ ዘወትር ማሳሰቢያ ይሰጣል ፣ ታዲያ ማስረጃነቱ ምኑ ላይ ነው ፣ ይልቁን እኔ በተደጋጋሚ እነሱ ኦርቶዶክስ ተሃድሶ ነን ብለው ሲመጡ የሚታደስ ሃይማኖት የለም ተሃድሶም የሚባል ነገር የለም ሁሉም የጴንጤ ልዑካን አፍራሾች ናቸው በሚል ተደጋጋሚ የተንቀሳቃሽ ቪዲዮ የሚያሳይ ቄስ ተብዬዎቹ እራሳቸውን ተሃድሶ ብለው የሚጠሩ በተጨባጭ ከነ ቀሚሳቸው ፣ ከነ መቋሚያቸው ፣ ከነ ጥምጥማቸው በየ ጴንጤው መጋዘን ሲደንሱና ሲጨፍሩ ያቀረብኩትን ማስረጃ እንዴት ሳታይ ልትስተው ቻልክ? እስቲ ቢዋጥልህም ባይዋጥልህም ፣ አሁን ሽንጥህን ገትረህ ተሰደቡብኝ በህግ አምላክ ያዙኝ ልቀቁኝ ያልከው ይሀንንም ተመልከትና እነዚህ መናፍቃን በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ በየመጋዘኑ እየሄዱ የሚያደርጉት ተግባር አግባብነት አለው ፣ እሰየው ፣አበጁ በለኝ እስቲ ።
እስቲ የሌሎቹን ማስረጃ እንዳየኸው ሁሉ አቅሙ ይኑርህና ይሄንንም አይተህ ፍረድ ።
https://www.youtube.com/watch?v=I3javBPBkgI&feature=youtu.be
https://www.youtube.com/watch?v=Hd78BCB37t0
https://www.youtube.com/watch?v=oh97_rC3czw
https://www.youtube.com/watch?v=iUt4yGEBdG8
https://www.youtube.com/watch?v=iUt4yGEBdG8
ሲጀምር ከስምህ ብነሳ ትክክለኛ ሊሆን እንደሚችል በማመን እንዲሁም ያንን እምነቴን በማጽናት ፣ አንተኑ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ፣ እኔ ባቀረብኩት ጽሁፍ ላይ ቅሬታ እንዳለህ አይቻለሁ ፣ ቅሬታህም ምን እንደሆነ ተረድቻለሁ ፣ ለዚያም ቅሬታህ በጥቂቱ መልስ ለመስጠት ሞክሪያለሁ ፣ ይህ በንዲህ እንዳለ አንተው በጻፍከው ጽሁፍ ላይ እንዲህ ብለሃል ። “ይህን ጽሑፍ በተመለከተ ከቀረቡት ውስጥ ደጋፊዎቹና መሐል ሰፋሪዎቹ ጥቂቶች ሲሆኑ ነቃፊ ወይንም ተቃዋሚዎቹ ጽሑፎች ያመዝናሉ ፡፡” ብለሃል ታዲያ የተቃዋሚው ማመዘን ምንን ያመለክትህ ይሆን ?
ባገራችን “ያልተነካ ግልግል ያውቃል” እንዲሉ አንተም ምንህም ስላልተነካ የምንለው ባይገባህ አይገርመኝም ። “በሰው ቁስል እንጨት መስደድ” የሚወዱ ብዙዎች ናቸውና አይገርመኝም ። አንተ ስለ ክርስትና እምነት ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ሊኖርህ ይችል ይሆናል እኔ ግን ስለ እስልምና ምንም አይነት ግንዛቤ የለኝም ፡፡ አሁንም አንተን ከስምህ ተነስቼ እንጂ የእስልምና እምነት ተከታይ ልትሆንም ላትሆንም ትችላለህ ፣ እንደኔ ግን የእምነቱ ተከታይ ትመስለኛለህ ፣ አሁንም ትመስለኛለህ የሚለው ቃል ይሰመርልኝ እና ፣ ታዲያ ይህንን ያንተን እምነት በተመለከተ ምን ያክል ትክክል እንደሆንኩ ባላውቅም ፣እንዲሁ በእስልምናውም ውስጥ የተለያዩ የእስልምና አስተምህሮዎች እንዳሉ ይነገራል ፣ በተለይ አሁን በብዛት በየዜና ማሰራጫው እንደምንሰማው ሱኒ እና ሺያት የተባሉ ሁለት የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዳሉ ይዘገባል ፣ እርስ በርሳቸውም በመለያየታቸው የተነሳ ይገዳደላሉ ። ከነዚ ውስጥ በተለይ ሺያት በመባል የሚታወቁት ክርስቲያንን ማጥቃታቸው ብቻ ሳይሆን የእስልምና ተከታዩን ሱኒ የሆነውንም ለሰው ልጅ በሚገርምና በሚዘገንን ሁኔታ ሲያጠቁ ይታያል ፣ ያም ሆኖ ግን አንተም ከነዚህ ከሁለቱ ወዴትኛው እንደምትመደብ ባላውቅም ፣ ወይንም ሌላም ተጨማሪ ዘርፍ እንዳለ እና ከዚያኛው ጎራ ትመደብም እንደሆን ባላውቅም ፣ ባጠቃላይ ከስልምና አማኙ ወገን ልትሆን ትችላለህ በሚል አመለካከት ፣ ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ስለ እምነቱ ምንም እውቀት ስለሌለኝ ሁለትም ይሁኑ ከዚያም በላይ በእስልምናው እምነት ውስጥ በመግባት አስተያየቴን አልሰጥም ። ከላይ እንደገለጽኩት ስለ እምነቱም ምንም አይነት እውቀት የለኝምና ። ስለዚህ አንተም በማታምነው እምነት ውስጥ በሚደረግ አለመግባባት ውስጥ ገብተህ የራስህን ወገንተኛነት በማንጸባረቅ ያደረከው ትችት አግባብ ባይሆንም እኔ ግን ያንተን እምነት አልነካም ፣ አንተ የምታምነውን ማንኛውም አይነት ቁራን ይሁን ሌላ ከቁራን ውጪ ያለ በእስልምናው አማኝ ክፍል ተቀባይነት ያለውን ጽሁፍ ወይንም መጽሐፍ አጉድዬ ፣ሰርዤ ፣ ቀንሼ ወይንም ጨምሬ ፣ ባበላሽብህና ትክክለኛው እኔ የሰረዝኩት የደለዝኩት ነው ብዬ ብልህ ምን ሊሰማህ እንደሚችል ከወዲሁ መገመት አያቅተኝም ። ስለሆነም በምታውቀውና በሚያገባህ እንጂ በማታውቀውና በማያገባህ ባትገባ ምንኛ ደስ ባለኝ ።
ታዲያ አንተን ባልበላህ ቦታ ገብተህ ማከኩን ምን አመጣው ። ለመሆኑ እራሱን ተሃድሶ ብሎ በሚጠራው የጴንጤዎች ጎራ ቤተ ክርስትያናችንን ምን ያክል እንደተጎዳትና የእምነቱንም ተከታይ ምዕመን ምን ያክል እንዳሳዘኑ ታውቅ ይሆን ? አይመስለኝም! ምክንያት ቢባል ምንህም አልተነካማ ። ምናልባትም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጥቃት የሚያስደስትህ ስው ልትሆን እንደምትችል በሙሉ ልብ መናገር እችላለሁ ፣ ሂደትህ ጅማሮህ ያሳብቅብሃልና ። ባይሆንማ የርጎ ዝንብ በመሆን ከሌላ እምነት መጥተህ ወገንተኛነት ባላሳየህ ነበር ።
ባጠቃላይ በኔ ግማጋሜ ከእስልምና እምነት መጥተህ በማያገባህ የክርስትና እምነት ውስጥ አንዱን ደግፈህ ትክክል ነው ስትል ፣ ሌላውን ነቅፈህ ተሳዳቢ ስትል ያንተን ማንነነት ቁልጭ አድርጎ አሳይቶኛል ። የፈለከውን በል እንጂ መምጫህ ከወያኔው ጎራ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው ። ወያኔ ነህ! እንዴት ቢባል? መልስ ተሰደበ ፣ ስብሃት ተሰደበ ፣ አባ ዲያቢሎስ ተሰደበ እርር ድብን አርጎሃል ፣ ባይገርምህ አልተሰደቡም ፣ እውነተኛ ማንነታቸው ተነገራቸው እንጂ ። ያንተን ማንነት ለማወቅ የሮኬት ሳይንቲስት መሆን አይጠበቅብኝም ። “ኢሃዴግ” እያልክ ደብረኸኛል ። አፍህን ሞልተህ እራሳቸውን ወያኔ ብለው የሚጠሩትን አንኳን ወያኔ ማለት አልቻልክም ። በማታምነው እምነት እጅህን ሰደህ ፣ ታዛቢው ተሳደበ ፣ ፖለቲካው አልሆን ሲለው ወደ እምነቱ ጎራ ተቀላቀለ ትላለህ ፣ አንተ ፖለቲካው ጎራ ከነበርክ አሁን ወደ እምነቱ ምን አመጣህ ? ወይስ ወደ ፖለቲካውም ወደ እምነቱም ለመሄድ መብቱ ያናንተ የወያኔዎች ብቻ ይሆን? መቼም አያልቅባችሁ ። ሁሉን ሰፍረን እንስጣችሁ ሆናችሁ እኮ ።
በማሳረጊያው ከተቸሃቸው ብዙ ትችቶች መሃከል “በእርግጥ አቶ ታዛቢው ወደ ስድብ ውስጥ ዘልቆ የወረደው፣ ነገሮች እንደሚፈልገው ባለመሄዳቸው ሊሆንይችላል፣ ምናልባትም ኢህአዴግ ስልጣን ባለመልቀቁ ተበሳጭቶ ይሆናል ።” አዎ እሱን ልክ ብለሃል እዚህ ላይ ግን “ኢሃዴግነቱ” ላንተ እንጂ ለኔ አይደለም ወደፊት ኢሃዴግ እያልክ አትጻፍ “ወያኔ” በል ይበልጥ ልታናድደኝና ደስ የማይልህን ማንነትህን ላበራየው እችላለሁና አስብበት ። ታዲያ እንዳልከው ወያኔ ባለመውደቁ ብበሳጭ ያ የኔ ብቻ ብስጭት ሳይሆን የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ብስጭት መሰለኝ ፣ አዎ በወያኔ አለመውደቅ ተበሳጭቻለሁ አንተ ደስተኛ ነህ መሰለኝ? ስትጠራቸውም ታሳምራቸዋለህ ። በማያገባህ እምነት ትተቻለህ ፣ ዘለህ ደግሞ ፖለቲካ ውስጥ ገብተህ ትፈተፍታለህ ፣ ይገርማል አዎ! በወያኔ አለመውደቅ እርር ድብን ብያለሁ! ደስ አለህ አሁን? የምትገርም ሰው ነህ ። አንድ ነገር ልንገርህ ሆዳም ሳይ ሆዳም የምል እንጂ አንጀቱ ታጥፎ መች ይበላና አልልም ፣ ለምን ብትለኝ የሰውን ማንነት ደብቆ መሸንገል አልወድምና ነው ። ወያኔም ሳይ ባንዳ ፣ አገር ሻጭ ፣ ዘረኛ ጠባብ ፣ እላለሁ ፣ ሰደብክብኝ እሪ የምትልም ከሆነ ያ ያንተ ችግር እንጂ የኔ አይደለም ። እንዳንተም አያገባው ገብቶ የሚዘባርቅ ሳይ የርጎ ዝንብ ፣ ያልበላውን የሚያክ ፣ ስውር ተልዕኮ ያለው ፣በማያምነው እምነት ውስጥ እየገባ የሚዘላብድ ከማለት ወደኋላ አልልም ። ይህ ባህሪዬ ደግሞ በጽሑፍ ብቻ ሳይሆን በተግባርም በየአደባባዩ የምተገብረው ነውና ሐሰን አባክህ ካሁን ወዲያ ስትጽፍ ታዛቢው ብለህ አትጻፍ እውነተኛ ስሜን ስለምታውቀው በእውነተኛ ስሜ እንድትመልስልኝ እማጸንሃለሁ ። አባቴ ባወጣልኝ ስም የምኮራ እንጂ የማፍር አይምሰልህ ዘርግፈው ያበጠው ይፈንዳ ።
በማንነታችሁ ስትጠሩ ተሰደብን ከማለት ማንነትን ማደስ አይቀልም ይልቅዬ?
ታዛቢው
የግጥም ርዕስ
በአንድ እግር ቆመህ
የግጥም መነባንብ ዝግጅት
የግጥም ርዕስ
በአንድ እግር ቆመህ
በአንድ እግር ቆመህ
ገድል አነብንበህ
የሰኔ ጐልጐታ ራዕየ ማርያም ብለህ
ታምረ ማርያሙ ድርሳኑ ሳይቀርህ
ሕዝብን ወደ ገደል ልትጨምር ተነሳህ !
ጉድ አይሰማም በል መስከረም ሲጠባ
ተብሎም ቢተረት በእሰጣገባ
ሆኖ ቢነገርም በረባም ባልረባ
ተስማምቶ ቀረልህ ለአንተም የተገባ
በተረትህ ስትኖር እያልክ ፈራ ተባ
ሕዝቡም ወደ እውነት ፍጹም እንዳይመጣ
በልብ ወለድ ድርሰት ሆነህ በለበጣ
ስትተርክ ውለህ ተርከህ ታድራለህ
ቁም ነገርን ማውራት አታውቅም ጨርሰህ
ዋዛና ፈዛዛ የአሮጊቶች ስላቅ
ስታውቅ ስትችል ስቀህ ልታሳስቅ
ምነው ግራ ገባህ መጽሐፉን ለመስማት
የእግዚአብሔር ቃል ሆኖ ተነግሮህ ለሕይወት
አልሰማ ብለህም አምጸህ ቆመሃል
ለስድብ ለጡጫ ልብህ ተነሳስቷል
ዓይንህን አፍጥጠህ ካራ ትመዛለህ
የአባቶቼ እምነት ሃይማኖቴ ብለህ
አባቶች እንደዚህ አላስተማሩህም
ብልሃትና ዘዴን ቀላውጠህ ከዓለም
ሾተልህን መዝዘህ ልትወጋ የተነሣህ
አባቶች አይደሉም አንተው እራስህ ነህ
የቆጡን የባጡን አወራለሁ ብለህ
እንዲህ ልትናገር ማን አደፋፈረህ ?
ነገር ግን በፍጹም የሚሰማህ የለም
ትውልዱም ንቆሃል ሰልችቶህ ታክቶትም
ከዚህ ሁሉ ውርደት ምነው ቢቀርብህ
ለመማር ብትመርጥ እንደ ማርያም ሆነህ
ከጌታ እግር ሥር ዝቅ ብለህ ተቀምጠህ
ተምረህ ስትገኝ በማስተማር ተራህ
ይማር አልተማረም አያውቅም እያለህ
አቅልህን አሳጥቶ ይዞ የሚሞግትህ
ፍጹም አይገኝም ወንድሜ ልንገርህ
አሁን ግን መምህር ልትሆን ልታስተምር
ካልተሰማሁ ስትል ቆመህ በመገተር
የሚሰማህ የለም ብትፈጥርም ግርግር
ደግሞም አንድ ነገር ብትሰማ ልንገርህ
መራራውን ሕይወት እንዲያጣፍጥልህ
ኢየሱስ የሚባል የሕይወት ጌታ አለ
አምነህ ብትቀበል ሊፈውስህ ያለ
ሳትጠራጠረው እመነው በቶሎ
ፍጹም ያድንሃል ችግርህን አቅልሎ
መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና የሐዋርያት ሥራ 4 : 12
ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም የዮሐንስ ወንጌል 14 : 6
ከጸሐፊው ፦ ምዕራፉ ይገለጥ
የግጥም መነባንብ ዝግጅት
የግጥሙ ርዕስ ፦ የከተሜው ፓስተር የበጐች እረኛው
ከእጅ አይሻል ዶማ
ፓስተር የከተማ
ለምቾትህ ስትል ቢሮ ተከራይተህ
ለኑሮ የመጣውን የዳነ ሕዝብ ይዘህ
ያልደከምክበትን መንጋዬ ነው ስትል
ምነው መጣራትህ እንዲሁ በቀላል
አረ ትንሽ ፍራው እግዚአብሔሩን
ራስህን ተመልከት ደግሞም ማንነትህን
ከአገልግሎት በፊት መጠራት ይቀድማል
የኢየሱስን ሕይወት ማጣጣም እንዲቻል
ይህንንም እውነት ያወቀው ጌታችን
ከአገልግሎት በፊት የእርሱ እንድትሆን
ከአልባሌ ሥፍራ ከተራ ሜዳ ላይ
አንስቶ ሸላልሞ ሊያኖርህ በሰማይ
የጠራህን ጌታ እስቲ ተመልከተው
አገልግሎት ለእኔ ሕይወቴ ነው ያልከው
የከተሜው ፓስተር የበጐች እረኛው
መኪና ቀያይሮ መንዳቱን ታውቃለህ
አመልካች ጠቋሚ ማንም ሳያሳይህ
በከተማው ኑሮ በተደላደለው
ተመቻችቶ መኖር ጥማትህ የሆነው
አሁንማ ወሬህ እርሱ ብቻ ሆኗል
መጽሐፉም ተረስቶ ጥቅሱም ጠፍቶብሃል
ሰንበታት ሲመጡ ሆነው በየተራ
ለዚህ ለዳነ ሕዝብ ምን ብዬ ምን ላውራ
ብለህ ስታጣጥር ስትቆጥር ጣራ
መሽቶ ይነጋና ማለዳው ሲመጣ
አገልግሎት ሽክም ሆኖብህ ፈጣጣ
ያለዝግጅትህ መድረክ ላይ ስትወጣ
ትንሽም አታፍር ሕዝቡን ለአንድ አፍታ
ደግሞስ ምን ይደረግ መድረክ በይሉኝታ
ለአንተ ሆነው መጥተው ተሰጥተው በተርታ
ያወናጭፉሃል ያለዝግጅትህ
ሥልጣን ያንተ እያሉ ከልካይ የሌለብህ
ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2 : 15 — 16
ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2 : 17
ከጸሐፊው ፦ ምዕራፉ ይገለጥ