የተካደ ትውልድ
አይዞህ ባይ የሌለው
ታዳጊ የሌለው
ወይ ጠባቂ መላክ፤ ወይ አበጀ በለው
ደርሶ ከቀንበሩ የማይገላግለው
የተካደ ትውልድ፤
አብዝቶ የጾመ፤ ተግቶ የጸለየ
ጥቂት መና ሳይሆን፤ ጥይት ሲዘንብ ያየ
እድሜ ይፍታህ ተብሎ፤ የተወለደ’ለት
አምባሩ ካቴና፤ ማተቡ ሠንሠለት፡፡
ምቾትን የማያውቅ፤ ረፍት የተቀማ
አልጋው ያጋም እሾህ፤ ምኝታው የሣማ
የተካደ ትውልድ፤
ሞቶ እንኳ ሬሳው፤ አይላላለት ቀንበር
በዘብ እጅ ተገድሎ፤ በሹም የሚቀበር
ከጡት አስጥል በላይ፤ ኑሮ የመረረው
እንዳይሄድ፤ ጎዳናው፤ የተደናገረው
ድል ያልሰመረለት ትግል ሳይቸግረው
የተካደ ትውልድ
በሥጋ በነፍሱ
በቀልቡ በገላው
ኧረ ምንድን ይሆን ፤ ምንድን ይሆን መላው?
(በዕውቀቱ ሥዩም)
Ezira says
በእዉቀቱ ሥዩም እጥር ምጥን ያለችውን የግጥም ስንኝህን አነበብኳት። የግጥምህ የመጨረሻ መደምደሚያ በጥያቄ የተቋጨ መሆኑን ሳይ ለጥያቄህ መልስ ይሆን ዘንድ ይሄንን ለመፃፍ ወደድኩ።
መላው እንደ አያያዙና እንደ አመጣጡ ቆርጦ መታገል ብቻ ነው። የነጻነት ዋጋ ውድ ነው ። በ ዉድ ዋጋ የሚገኝ ነገር ደግሞ ዉድ ህይወትን ሁሉ ይጠይቃል። ዓለማችንን ከጥፋት ማዕበል ተመልሳ እንደትቆም ያደረገው ልዩ ተምሳሌችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውድ ህይወቱን ከፍሏል። ኢየሱስ ክርስቶስ ለስው ልጆች መዳን ሲል ዉድ ህይወቱን ሁሉ ከፍሎልናል ብለው የሚያምኑና የሚከተሉት ምዕመናን ዛሬ በዓለማችን ላይ ብዙሃን እና ለቁጥር የሚያታክቱ ናቸው። የስው ልጅም እንዳለከው በተፈጥሮው ሰው በመሆኑ ብቻ ሊያገኘው የሚገባውን መብቱን የተነጠቀ ሲመስለውና መነጠቁን ካወቀ ለነጻነቱ ሲል “በሥጋ በነፍሱ በቀልቡ በገላው” መስዋትንነትን ክፍሎ የነፃነቱ የመብቱ ባለቤት መሆኑ አይቀሬ ነው። ይሄንን አይቀሬነት እስኪያረጋግጥና የነፃነቱ ባለቤት እስኪሆን ድረስ እያንዳንዱ ትዉልድ (በየትዉልድ ዘመኑ) ከፊቱ የሚጋረጥበትን ወይም የሚያደናቅፈዉን እንቅፋት ታግሎ ማሸነፍ ተፍጥሯዊ ግዴታው ነው። በመሆኑም በተፈጥሮ ህግ እንደሚናጋ ስለምናውቅ ነው ጨለማን የማንፈራው ለማለት ነው። በእዉቀቱ ሥዩም ጠፈተህ፤ ጠፍተህ ከረመህ አሁን በዚች እጥር ምጥን ባለች ግጥምህ ብቅ ስላልክ ዴግሞ እንኳን ደህና መጣህ ለማለትም ጭምር ነው።
አትንኩት መላኩ says
እውንትህን እግዚአብሔር። ይስ
ጥህ እንዴት ትርድህው ባክህ