ባለፈው ሳምንት በፓኪስታን ላሆር ከሌሎች ቤተሰቦቹ ጋር የ9 ወር ህጻን በመግደል ሙከራ ተከስሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡ ህጻኑ ከነጡጦው በፍርድ ቤት መዝገብ ላይ በአያቱ እርዳታ ጣቱን በቀለም አጥቅሶ ከፈረመ በኋላ ዳኛው ጊዜያዊ የዋስትና መብቱ እንዲጠበቅ በማድረግ ለሚያዚያ 4 ቀጠሮ ሰጥተውታል፡፡
ህጻኑና ወደ25 የሚጠጉት ቤተሰቦቹ የተከሰሱት በፖሊስ ላይ ድንጋይ በመወርወርና የፖሊስ ኃይሎችን ለመግደል ሞክረዋል በሚል ነው፡፡ በላሆር የሚገኙ ነዋሪዎች የጋዝና የኤሌክትሪክ ክፍያ ባለመፈጸማቸው ውዝፍ ዕዳ ስለተጠራቀመባቸው የጋዝና የኤሌክትሪክ መስመሮቹን ለመቁረጥ የፖሊስ ኃይል ወደሥፍራው የዛሬ ሁለት ወር አካባቢ ተንቀሳቅሶ ነበር፡፡ በሁኔታው የተናደዱ የአካባቢው ነዋሪዎች በፖሊስ ቡድኑ ላይ ድንጋይ በመወርወር ጥቃት ከማድረስ አልፎ የተወሰኑት ላይ ጉዳት አድርሰው ነበር፡፡
ክስተቱን ለፍርድቤት በማቅረብ ክስ የመሰረተው የፖሊስ ኃይል በወቅቱ በጥቃቱ ላይ ተሳትፈዋል ያላቸውን 25 ግለሰቦችን ሲከስ ህጻኑን እና ቤተሰቦቹ አብሮ ለክስ አቅርቧል፡፡
ህጻኑም በአያቱ ታቅፎ ፍርድቤት በቀረበበት ወቅት በፍርድቤቱ መዝገብ ላይ በጣቱ ፈርሟል፡፡ ክሱን የተቃወመው የቤተሰቡ ጠበቃ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተናገረው ፍርድቤቱ በተለይ በህጻኑ ላይ የተመሰረተውን ክስ ወዲያውኑ ውድቅ ማድረግ ነበረበት ብሏል፡፡ ይህንን አለማድረጉ በራሱ የፖሊስ ኃይላችንና የፍትህ አካላቶች ምን ያል ብቃት እንደሌላቸው የሚያጋልጥ ነው በማለት ተቃውሞውን ገልጾዋል፡፡
አብሮ ለፍርድ የቀረበው የህጻኑ አባት ፖሊስ የሃሰት ክስ እንደመሠረተባቸው በመጥቀስ የልጁን መከሰስ አጥብቆ ተቃውሟል፡፡ “እኛ በወቅቱ አንከፍልም ብለን የተቃወምነው ኤሌክትሪክ በሰፈራች ሳይኖር ወርሃዊ ክፍያ ፈጽሙ በመባላችን” ነው በማለት የክሱን ኢፍትሃዊነት አስረድቷል፡፡
ህጻኑ ከሌሎቹ ተከሳሾች ጋር በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ፍርድቤት እንዲቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶታል፡፡ ዜናው ይፋ ከሆነ በኋላ በተለይ ህጻኑ ላይ ክስ እንዲመሠረት ያደረገው የፖሊስ አባል ከሥራው እንዲገለል ተደርጓል፡፡
ባለፈው ዓመት በተሻሻለው የፓኪስታን ሕግ መሠረት በወንጀል የሚከሰሱ የመነሻ ዕድሜ ከ7 ዓመት ወደ 12ዓመት ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡ ይህንን ሕግ በመጻረር ዳኛው በህጻኑ ላይ ክሱ እንዲመሠረት መፍቀዳቸው የበርካታ ሚዲያዎች መወያያ ርዕስ ሆኗል፡፡
(ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ዜናውን ከተለያዩ ዓለምአቀፍ ምንጮች እንደዘገበው)
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
jarso says
What is the big deal here ? we have witnessed in our very eyes while the woyane butchers killing thousands of children in Ethiopia and several of them thrown in jungle to be eaten by hungry hyenas .