"አሁን ማንም ሰው ነው አግቶ የሚወስድህ፤ የሚጠብቅ የፀጥታ አካል የለም" ትህነግ በእብሪት ተሞልቶ መቀሌ መሽጎ በነበረበት ወቅት አገሪቱ በግጭት ስትታመስ፤ ዜጎች ሲፈናቀሉ፣ ለውጡ ነውጥ ሆኖ ኢትዮጵያ በመፍረስ አደጋ ውስጥ ሆና ሳለ የሰላም ጉዳይ ያሳሰባቸው እናቶች ወደተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተጉዘው ነበር። በሁሉም ቦታዎች የክብር አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ የተጓዙት ወደ መቀሌ ነበር። የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው፣ የሰላም ሠንደቅ በማውለብለብ እያለቀሱ መሬት ላይ ተደፍተው “ሰላም ላገራችን” ብለው ልመናቸውን ሲያቀርቡ የወንበዴው ቡድን መሪና በወቅቱ የክልሉ አስተዳዳሪ የነበረው ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እያላገጠ “እኛ ክልል ሰላም ነው፤ ይልቅ ሌላ ክልል ነው ሰላም የጠፋው፤ ስለዚህ እዚያ ብትሔዱ ይሻላል፤ እኛ ጋር ለምን እንደመጣችሁ አናውቀም?” በማለት ነበር … [Read more...] about ትግራይ እየፈረሰች ነው – ሐይቲ በኢትዮጵያ