ሁለትም ናቸው። በግብ ግን የሚለያቸው የለም። ያን ጊዜ በአካል ላይተዋወቁ ይችሉ ይሆናል። በመንፈስ ግን የአንድ እናት ልጆች ናቸው። ትላንት ገጽ ለገጽ ሳይገናኙ፡ በስምም ሳይተዋወቁ በአንድ ካምፕ ለአንድ ሰፈር ሲጫወቱ ነበር። በመሃል መንገዳቸው ተለያየና በየፊናቸው ህይወትን ቀጠሉ። አንደኛው የህወሀት ቃለቀባይ ስጋጃ አንጣፊ ሆኖ ተከሰተ። ሌላኛው በኪነጥበብና መዝናኛ መድረኮች የጭቃ ውስጥ እሾህ ባህርይ ተላብሶ ብቅ አለ። ነገ እንደሚገናኙ ላያውቁ ይችሉ ይሆናል። አንድ ቀን የመንፈስ ጥምረታቸውን በአካል ተገናኝተው የሚያጠናክሩበት ጊዜ እንደሚኖር ሀገር ቤት ሳሉ ላያውቁት ይችሉም ይሆናል። የባህርይ አምላክ፡ በመንፈስ ያጣመራቸው ጌታ ፍቃድ ሆኖ ግን ሳያውቁት በባህር ማዶ ተገናኙ። በአካልም በመንፈስም ተቀራረቡ። በየግል በልባቸው የተከመረውን የጥላቻና የእኩይ መንፈስ በጋራ … [Read more...] about ካድሬውና ገጣሚው
Archives for February 2020
“የህዳሴ ግድብ ስምምነት ፊርማ እንዲዘገይ አመራር ሰጥቻለሁ” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተገዙ ሌት ከቀን እየደከሙ ነው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ ከአደራዳሪዎቹ ጋር በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ የህዳሴ ግድብ ስምምነት ፊርማ እንዲዘገይ አመራር መስጠታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ። ዐቢይ ከትራምፕ ጋር በስልክ መነጋገራቸው ይፋ ከሆነ በኋላ ራሳቸውን ተንታኝ ያደረጉ ወገኖች የስምምነት ፊርማው እንዲፈረም በተደራዳሪዎች ላይ ጫና እንደፈጠሩ በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲያጠልሹዋቸው ከርመው ነበር። ዶ/ር ዐቢይ ሰኞ በተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ባደረጉት ጥያቄና መልስ እንደገለጹት የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ መስጠትን በተመለከተ የሚደረግ አንድም ዓይነት ስምምነት እንደማይኖር አረጋግጠዋል። ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ከአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስትር ስቴፈን ሙኑሺን እና ከዓለም ባንኩ ፕሬዚዳንት … [Read more...] about “የህዳሴ ግድብ ስምምነት ፊርማ እንዲዘገይ አመራር ሰጥቻለሁ” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ