ቅዳሜ ምሽት በድሬዳዋ ከተማ በተለምዶ ገንደ ቦዬ ተብሎ በሚጠራው መንደር በተቀሰቀሰው ግጭት የአንድ ወጣት ህይወት ማለፉ ተሰምቷል። ምሽቱ በጥይት እሩምታና በአስለቃሽ ጭስ ተኩስ ነዋሪዎችን ጭንቀት ውስጥ ከቶ ያለፈ ነበር። በምሽቱ ግጭት ህይወቱን ያጣው ወጣት አብዱረዛቅ ሪቫቶ ከፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰበት ጥይት ለአካል መቁሰል ተዳርጎ ወደ ድል ጮራ ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱን ለማትረፍ አልተቻለም። ፍፁም መከሰት የሌለበትና በቀላሉ ሊፈታ የሚገባው ችግር ማመዛዘን በጎደለውና በቸኮለ እርምጃ የሰው ህይወት በድሬዳዋ ተቀጥፏል ብሏል ዜናውን ያሰራጨው ድሬ ትዩብ። ጨምሮም የህግ አስከባሪዎች ለሚወስዱት ማንኛውም እርምጃ ሞያዊ ክህሎት የተላበሰና ማስተዋል የተጨመረበት መሆን አለበት፤ ኮሽ ባለ ቁጥር አፈ ሙዝ የሚደቅን የፀጥታ ሀይል አላግባብ በሆነ መልኩ ህይወትን ያሳጣል ብሏል። በድሬዳዋ … [Read more...] about በድሬዳዋ ከተማ የሰው ህይወት አለፈ
Archives for October 2018
ኮ/ል ጎሹ ወልዴ አዲስ አበባ ገቡ
በደርግ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ኮ/ል ጎሹ ወልዴ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመንና እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ነብያት ጌታቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርግውላቸዋል። የቀድሞው ሚኒስትር በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የደርግን አገዛዝ በመቃወም ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ከለቀቁና ኑሯቸውን በአሜሪካ ካደረጉ ጀምሮ ላለፉት 32 አመታት የአገራቸውን መሬት ሲረግጡ የመጀመሪያቸው መሆኑን ገልፀዋል። ኮ/ል ጎሹ ወልዴ አመጣጣቸው የአገሪቱን አጠቃላይ የለውጥ ሂደት ለማየት፣ ለረጅም ጊዜ የናፈቋቸውን ዘመድ ወዳጆች ለማግኘትና የተጀመረውን የሰላም፣ የፍቅርና የመደመር ሂደት በሚችሉት መጠን … [Read more...] about ኮ/ል ጎሹ ወልዴ አዲስ አበባ ገቡ
ሕገወጥ የመሣሪያ ዝውውር የአገር ስጋት ሆኗል ተባለ
ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በአገር ደረጃ ስጋት ሆኗል ተባለ። ከተለያዩ አገራት በድንበር በኩል የሚገባውን ሕገወጥ የጦር መሳሪያ አስመልክቶ ጠንከር ያለ ሕጋዊ አሰራር ሊኖር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተናግሯል። በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የኢንዶክትሪኔሽንና ሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በከተማዋ በስፋት እየተስተዋለ ያለውን ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ለመግታት ጠንካራ የቁጥጥር ህግ ያስፈልጋል ብለዋል። 412 ሽጉጦችን፣ ከ12 ሺ በላይ የሽጉጥ ጥይቶችንና ከ9 ሺ በላይ የክላሽ ጥይቶችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የተገኙ 5 ተጠርጣሪዎችን ፍ/ቤት በዋስ መልቀቁ ጥብቅ የሆነ አሰራር ላለመኖሩ ማሳያ መሆኑን ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል። ከህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በተጨማሪ በጦር መሳሪያ የታገዘ ዘረፋና ቤት ሰብሮ ስርቆት … [Read more...] about ሕገወጥ የመሣሪያ ዝውውር የአገር ስጋት ሆኗል ተባለ
በሐሰት ውንጀላ ተመራማሪ ተማሪዎች በግፍ ተገደሉ
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለዶክትሬት ማጠናቀቂያ ጥናታቸው ወደ ምዕራብ ጎጃም ዞን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ወደ አዲስ አለም ከተማ ተጉዘው የነበሩ ግለሰቦች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሁለቱ ሲገደሉ አንዱ መቁሰሉን የዞኑ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። አጥኒዎቹ በከተማው ባለው አንድ ትምሕርት ቤት ውስጥ ለምርምር የሚሆን የሽንትና የዐይነ ምድር ናሙና እየሰበሰቡ ባሉበት ወቅት፤ “ሦስት ተማሪዎች ሞቱ” የሚል ወሬ በመሰራጨቱ ተቆጥተው በመጡ የአካባቢው ወጣቶች በደረሰባቸው ከፍተኛ ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉን የምዕራብ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ አንማው ዳኛቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። በተጨማሪም ለቤተ ክርስቲያን ህንፃ ግንባታ ግልጋሎት የሚውል ሲሚንቶ በራሳቸው መኪና ጭነው ወደ አካባቢው ተጉዘው የነበሩ ጥንዶች ንብረትም መቃጠሉ … [Read more...] about በሐሰት ውንጀላ ተመራማሪ ተማሪዎች በግፍ ተገደሉ
ሳህለወርቅ ዘውዴ – የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት
ተወልደው ያደጉት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሲሆን የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት በሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት ነው። አራት ሴት ልጆች ለነበሯቸው ወላጆቻቸው የመጀመሪያ ልጅ የሆኑት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገና በ17 ዓመታቸው ነጻ የትምህርት ዕደል አግኝተው ወደ ፈረንሳይ በማቅናት ሞንትፔልየር (Montpellier) በምትባለው የፈረንሳይ ከተማ በሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሞንትፔልየር (University of Montpellier) የተፈጥሮ ሳይንስን አጥንተዋል። በሀገረ ፈረንሳይ ለዘጠኝ ዓመታት ከቆዩ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ የሕዝብ ግንኙነት ክፍልን ማገልገል ጀመሩ። ቆይተውም የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉን በበላይነት መርተዋል። ከዚያም ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመዘዋወር በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች አገልግለዋል። ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ … [Read more...] about ሳህለወርቅ ዘውዴ – የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት
የለማ መገርሣ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ትርክትና የመሐመድ አዴሞ ሹመት
የኦሮሚያ ክልላዊ ምክርቤት ሰኞ መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም. የበርካታ አዲስ የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች አደረጃጀትን ሲያጸድቅ የአዳዲስ ተሿሚዎችን ሹመትም አጽድቋል። ከእነዚህ መካከል የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) ዋና ዳይሬክተር እንዲሆን የተሾመው መሐመድ አዴሞ ነው። የአቶ ለማ መገርሣ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” የሚለው ልብ የሚያረካ አባባል ከመሐመድ አዴሞ ለዓመታት የዘለቀ ፀረ ኢትዮጵያዊነት አቋም ጋር የሚጋጭባቸው ወገኖች የሹመቱ ጉዳይ ትልቅ ጥያቄ ፈጥሮባቸዋል። በአንጻሩ ደግሞ መሐመድን ብቃት ካለው ባለሙያ አንጻር የሚመለከቱት ሹመቱ ትክክለኛ ብቻ ሳይሆን ገጣሚም ነው ይላሉ። ለሃያ ሰባት ዓመታት በግፍ ቀንበር ሥር የነበረውን ሕዝብ በለውጥ ማዕበል ውስጥ በማስገባት “እንቁላሉን ከውስጥ የሰበሩት” የለማ ቡድን (ቲምለማ) አባላት በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ … [Read more...] about የለማ መገርሣ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ትርክትና የመሐመድ አዴሞ ሹመት
“እርካብና መንበር” – ሙሴ እና ዐብይ*
ሳይታሰብ ብልጭ ብላ እንደገና ድርግም ያለችው የለውጥ ጭላንጭል፣ በእያንዳንዱ ልብ ውስጥ ተቋጥራ የነበረች የተስፋ ስንቅንም ይዛ ጭልጥ ያለች ይመስላል። አዕምሯችን ይህንን ቅጽበታዊ ለውጥ ለመቀበል ቢቸግረውም፣ በሌላኛው መነጽር ስንመለከተው ግን ይህ ሊሆን ግድ ይላል። በተዓምር የቆመች የዚህች የደም ምድር እጣ ፈንታን መጽሃፉ በአንዲት ምዕራፍ ውስጥ እንደቋጫት እንገነዘባለን። አይናችንን በደንብ ካልገለጥን ግን ነገሩን ላናየው እንችላለን። ስለዚህ መፅሐፉን ማንበብ ብቻ በቂ አይደለም። መረዳትንም ይጠይቃል። በደንብ የተረዳው ሰው፣ በለሆሳስ የተላለፈ መልዕክቱን ያገኘዋል። መልዕክቱም ግልጽ ነው። የነጻነት ተጋድሎ። በዚህ ፍልሚያ ውስጥ ሶስት ተዋንያን ይኖራሉ። ተሻጋሪ ሕዝብ፣ አሻጋሪ ሰው እና አሳዳጅ ሃይል። ከብዙ ትንቅንቅ እና ተጋድሎ በኋላ የአሳዳጁ ገቢር ከትዕይንቱ ይወጣና ሁለቱ … [Read more...] about “እርካብና መንበር” – ሙሴ እና ዐብይ*