ተወልደው ያደጉት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሲሆን የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት በሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት ነው። አራት ሴት ልጆች ለነበሯቸው ወላጆቻቸው የመጀመሪያ ልጅ የሆኑት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገና በ17 ዓመታቸው ነጻ የትምህርት ዕደል አግኝተው ወደ ፈረንሳይ በማቅናት ሞንትፔልየር (Montpellier) በምትባለው የፈረንሳይ ከተማ በሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሞንትፔልየር (University of Montpellier) የተፈጥሮ ሳይንስን አጥንተዋል።
በሀገረ ፈረንሳይ ለዘጠኝ ዓመታት ከቆዩ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ የሕዝብ ግንኙነት ክፍልን ማገልገል ጀመሩ። ቆይተውም የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉን በበላይነት መርተዋል። ከዚያም ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመዘዋወር በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች አገልግለዋል።
ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በአምባሳደርነት ለመሾም ከአምባሳደር ዮዲት እምሩ ቀጥሎ ሁለተኛዋ እንስት ናቸው። በመጀመሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙትም ሴኔጋል ሲሆን የአምባሳደርነት ስልጣናቸውም ሴኔጋልን ጨምሮ ማሊን፣ ኬፕ ቨርዴን፣ ጊኒ ቢሳውን፣ ጋምቢያን እና ጊኒን (እ.ኤ.አ 1989–1993) ያጠቃልል ነበር።
ቀጥሎም እ.ኤ.አ 1983–2002 በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደርና በኢጋድ (IGAD) የኢትዮጵያ ተጠሪ ሆነው አገልግለዋል። እ.ኤ.አ ከ2002 ጀምሮ እስከ 2006 ድረሰ በፈረንሳይ (ሞሮኮን ጨምሮ) የኢትዮጵያ አምባሳደርና በዩኔስኮ (UNESCO) የኢትዮጵያ ተጠሪ ሆነው አገልግለዋል። እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ እስከ 2009 ድረስ በአፍሪካ ህብረት (AU) እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የኢትዮጵያ ተጠሪ ሆነው ሀገራቸውን አገልግለዋል።
ከሀያ ዓመታት በላይ በተለያዩ ሀገራትና ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች የኢትዮጵያ አምባሳደርና ተጠሪ በመሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤትን ያገለገሉት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ እ.ኤ.አ በ2009 የተበባሩት መንግስታት ድርጅትን (ተመድ) በመቀላቀል የድርጅቱ በመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ የተቀናጀ ሰላም ግንባታ መሪ (Head BINUCA) በመሆን ማገልገል ጀመሩ።
ይህ አገልግሎታቸውም ወደ ሚቀጥለው ኃላፊነት አሸጋግሯቸው እ.ኤ.አ በ2011 ዓም የዚያን ጊዜ የተመድ ጠቅላይ-ጸሀፊ ባን ኪ-ሙን አዲስ ለተቋቃመው በናይሮቢ የተመድ ጽህፈት ቤት (UNON) የመጀመሪያዋ ጠቅላይ-መሪ አድርገው ሾማቸው። በዚያም ለሰባት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ እ.ኤ.አ በሰኔ ወር 2010 የአሁኑ የተመድ ጠቅላይ-ጸሀፊ አንቶንዮ ጉቴሬስ አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴን በተመድ ጠቅላይ-መሪ ስር (Under-Secretary-General) የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተጠሪ (UN’s Special Representative to the AU) እና በአፍሪካ ህብረት ውስጥ የተመድ ጽህፈት ቤት ዋና ኃላፊ (Head of UNOAU) አድርገው ሾሟቸው፤ ፕሬዚዳንት እስከሆኑበት ቀን ድረስ በዚሁ ሹመታቸው እያገለገሉ ነበር።
አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ባለትዳርና የሁለት ወንድ ልጆች እናት ናቸው።
gi Haile says
የአንድ ታላቀሰ መሪ መለኪያዎች በየትኛውም የሥልጣን እርከን ይሁን ታመኝና ታታሪ ሰራተኛ ሆኖ መገኘትና የተሰጠውን ኃለፊነት በብቃት የሚወጣ ማለት ነው ። የአዲሱ ፕሬዝዳንት የመሪነት ልምድ ያካበቱት የተሰጣቸውን ኃለፊነት በብቃት መወጣት ነው። ኢትዮጵያ ብዙ ታማኝ መራዎች በዘመናት መካከል ነበሩኣት። እነዚህን መሪዎች ልናመሰግን እንወዳለን። በለፉት 27 አመት ውስጥ ደግሞ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ብልሹ መሪዎች የተፈጠሩበት ጊዜም ነው። ስለነዚህ ብልሹ መሪዎች ደገሰሞ በጣም እናዝናለን እናፈራለን። እንደ ፕሬዘዳንት ሳዕለወርቅ ዘውዴ ያሉ መሪዎች አገራችን በጣም ያስፈልጓታል። ኢትዮጵያ በመልካም ሕዝቦቿና መሪዎቿ ጋር ለዘለዓለም ትኑር ።
በለው ! says
ጋዜጠኛ ለታሪክ ጀርባውን ሲሰጥ አስፈሪም አሳፋሪም ይሆናል!!!
አቻምየለህ ታምሩ
* አገራችን ከወይዘሮ ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ በፊት ንግስተ-ነገስታት ዘውዲቱ ምኒልክ፣ ሕንደኬ፣ ማክዳና ዮዲት የሚባሉ ሴት ርዕሳነ ብሔራት ነበሯት!
የኢትዮጵያን እድሜ ከወያኔ የአገዛዝ ዘመን ጀምረው የሚቆጥሩ እንደ BBC News Amharic አይነት ጋዜጠኞች ወይዘሮ ሣሕለ ወርቅ ዘውዴን የመጀመሪያዋ ሴት የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር እያደረጓቸው ይገኛሉ። ከዛሬ 98 ዓመታት በፊት ወይዘሮ ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ ዛሬ በገቡበት የኢትዮጵያ ቤተ መንግሥት ውስጥ የኢትዮጵያ መሪ ሆነው የገቡ ሌላ ሴት ርዕሰ ብሔር ነበሩ። ስማቸው ወይዘሮ ዘውዲቱ ምኒልክ ይባላል!
* ወይዘሮ ሣሕለ ወርቅ ዘውዴን ርዕሰ ብሔር አድርጎ የሾመው ኦሮሞው ዐቢይ አሕመድ ነው።
* ወይዘሮ ዘውዲቱ ምኒልክንም ርዕሰ ብሔር አድርገው የሾሟቸው የዘመኑ አንጋሽና የጦር መሪ የነበሩት ኦሮሞው ፊታውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ ዲኔግዴ (አባ መላ) ናቸው።
ከወይዘሮ ዘውዲቱ ምኒልክ በፊት ሕንደኬ፣ ማክዳና ዮዲት የሚባሉ ሴት የኢትዮጵያ ርዕሳነ ብሔራት ነበሩ። ወይዘሮ ዘውዲቱ ምኒልክን ጨምሮ ከወይዘሮ ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ በፊት የነበሩት የኢትዮጵያ ሴት ርዕሳነ ብሔራት ሁሉ በሥልጣን ረገድ ከዛሬዋ ርዕሰ ብሔር እጅግ የገዘፈ የሙሉ ሥልጣን ባለቤቶች ነበሩ።
የዛሬዋ ርዕሰ ብሔር የፖለቲካ ሥልጣናቸው የይስሙላ ወይንም cermonial ነው። ከወይዘሮ ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ በፊት የነበሩት የኢትዮጵያ ሴት ርዕሳነ ብሔራት ግን ዘውድ እየጫኑ የሚያነሱ፣ ሹም ሽር የሚያደርጉ፣ ጦር የሚያዝዙ፣ ብቸኛ የአገር መሪዎችና አባወራዎች ነበሩ! የዛሬዋ ርዕሰ ብሔር ወይዘሮ ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ ግን ሌላው ቢቀር ከተሰጣቸው ሥልጣን መካከል ዋና የሆነው ሕግ የማጽደቅ ሥልጣን እንኳ ረቂቁ ቀርቦላቸው በ15 ቀናት ውስጥ ካልፈረሙት የርሳቸውን ይሁንታ ሳያገኝ ሕግ መሆን የሚችልበት ትርጉም የሌለው ሥልጣን ነው ያላቸው!
F