ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለዶክትሬት ማጠናቀቂያ ጥናታቸው ወደ ምዕራብ ጎጃም ዞን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ወደ አዲስ አለም ከተማ ተጉዘው የነበሩ ግለሰቦች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሁለቱ ሲገደሉ አንዱ መቁሰሉን የዞኑ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
አጥኒዎቹ በከተማው ባለው አንድ ትምሕርት ቤት ውስጥ ለምርምር የሚሆን የሽንትና የዐይነ ምድር ናሙና እየሰበሰቡ ባሉበት ወቅት፤ “ሦስት ተማሪዎች ሞቱ” የሚል ወሬ በመሰራጨቱ ተቆጥተው በመጡ የአካባቢው ወጣቶች በደረሰባቸው ከፍተኛ ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉን የምዕራብ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ አንማው ዳኛቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ለቤተ ክርስቲያን ህንፃ ግንባታ ግልጋሎት የሚውል ሲሚንቶ በራሳቸው መኪና ጭነው ወደ አካባቢው ተጉዘው የነበሩ ጥንዶች ንብረትም መቃጠሉ ታውቋል። በዚህ ድርጊት ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩም 30 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።
በተፈፀመው ድርጊት የአካባቢው ማኅበረሰብም ሆነ መንግሥት ማዘኑን አቶ አንማው ገልፀው በድርጊቱ ተሳትፈዋል የተባሉትን ማሰር መቀጠሉን ጠቁመዋል።
ምንጭ፦የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ
Tesfa says
እባብ ያየ በገመድ ይደነግጣል እንዲሉ የሃገራችን ሰው በራሱ የቀትር ጥላ ዙሪያ መደንበር ከጀመረ ዘመናት ተቆጥረዋል። የዛሬውን መደንበር ከአለፉት ድንባሬዎች ለየት የሚያረገው ደግሞ ሰው የሚከተለው ዘርና ቋንቋ ነክ የክልል ፓለቲካ በመሆኑ ነው። በሆያ ሆየ የሰው ደም የሚፈስባት ይህች ሃገር ባላንጣዋ ብዙ ቢሆንም ይበልጥ ችግሯን የሚያባብሱት በአብራኳ የተፈጠሩ አጥፊ ሃይሎች ናቸው። ብቀላ ብቀላን እየወለደ ስንገዳደል ኖረናል እንኖራለንም። ሰው በዓይኑ ባላየው ነገር ምሥክር የሚቆምባት ሃገራችን በዘር ፓለቲካ የሰከረ የሚራወጥባት ምድር ሆናለች። የሌላውን ሥራ እየኮነነ ራሱ ተመልሶ የኮነነውን ተግባር የሚደግም አረመኔ ብቻ የተጠራቀመባት። ይህን የግፍ ግድያ ከሻሸመኔው ግድያ የሚለየው አንዳች ነገር የለም። የሰው ደም ያፈሰሰ ሁሉ ደሙ ይፈሳል የሚለው የእምነት ትምህርት ችላ ተብሎ ሁሉም በየጎጡ የሚያቅራራበት የውሸት መለከት ነፊዎች የድረሱልኝ ጥሪ የሚያናፍሱበት ይህች ሃገር መቼ ይሆን መከራዋ የሚገታው? ቆይቶ ማየት ነው።
አብነት says
ትክክል በጣም ያሳዝናል እንድ ባልተጣራ ወሬ በስው ነፍስ መፍሪድ መቆም አለበት :: እንዴት ኢትዪጵያዊ ነገ በኔ ኡይገባውም ?? ሁለት የዚህ ባማራ ላይ መድሀኒት ተደርጎ ነበር የሚለው ታሪክ በገለልተኛ እንዲመረመር መደረግ እለበት ለምን ለማጣራት እርምጃ ይወሰድ ተብሎ ለዶር አብይ ጥያቄ ኣልቀረበም ? ከታመነበት :: ዝም ብሎ ማውራት የነዚህ ልጆችን ደም አፈሰሰ :: እናት እኮ አላቸው ቤተሰብ አላቸው :: የሰማነውንነገር የማጣራት ባህል በፍጥነት ማጎላበት ይኖርብናል ለአገራችን ካሰብን ::
gi Haile says
ምን ያድርጉ በጣም ያሳዝናል ይህ ሁሉ በቀደመው 27,አመት ጊዜ ውስጥ በእክምናው ዘርፎች ብዙ እገወጥ ተግባራት ተፈጽመዋል ይባላል። ተሸፋፍኖ የቀረው በክትባት መልክ ብዙ ሴቶች እንዳይወልዱ ተደርጓል የሚል ወሬዎች ይወራሉ መንግሥት ግን ይህንን ጉዳይ ችላ ብሎ መመልከት እና በድብቅ ማቆየቱ ተገቢ አይደለም ።ሕዝብ መልስ ይፈልጋል የቀደሙት የጤና ጥበቃ ምንስቴር ዶር ቴዎድሮስ አዳኖም ለዚህ የሕዝብ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ነበረባቸው። አሁንም ለነዚህ ልጆች መሞት ተማሪዎች የማያውቁት ነጠር ግን ሕዝቡ በሆዱ የያዘው ቂም በቀል ነውና። በመጀመሪያ በሕዝብ ጤና ለሠይ ተፈጸመ የተባለው ነገር እውነት ከሆነ መጣራት አለበት ለሕዝብም ይፋ ሊደረግና ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል ። እነዚህ ተማሪዎች ግን የሞቱት በማያውቁት ነገር ነውና በጣምም ያሳዝናል። እውነትን በመደበቅ ወገኖቻችን ማጣታችን ግፍ የግፍም ግፈሰ ነዉ ። አይጥ በበለ ዳዋ ተመታ መለት ይህ ነው ።
obika says
Beahunu gize itiyopiya wusxi mannim inde fallage sawun magdal yetelamade new. Injiner simanyew simotuminim altebalem wallagga 70000 sew siffanaqal zim yesumale liyyuhayil tan hullu saw sigedil zim . jamal kashogi siggaddal midire awuropa tenawete. Ine indemimasileny anbessa park wusxi yaallen yimwsilenyal.