ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጅና ከዚያ በፊት በነበረው ሁኔታ የኢንተርኔት መቆራረጥና መታገድ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ማድረሱ የተጠቀሰ ሲሆን ባለፈው አንድ ዓመት አገሪቱን 9 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማሣጣቱን የአሜሪካው ብሩኪንግስ ኢንስቲቲዩት ይፋ ያደረገው ጥናት አመልክቷል። ዴልዮት የተባለው ዓለማቀፍ አማካሪ ተቋም በበኩሉ፤ የሞባይል ኢንተርኔት መዘጋት ሀገሪቱን በቀን 5 መቶ ሺህ ዶላር እያሳጣት ነው ብሏል። በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ተቃውሞና ግጭቶች መከሰታቸውን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎቶች መቆራረጥ፣ ሃገሪቱን በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ አሳጥቷል ብሏል - ዴልዮት። የኢንተርኔት አገልግሎት መቃወስ የኢኮኖሚ እድገቱን እንዲቀዛቀዝ አድርጓል ያለው "አፍሪካን ቢዝነስ"፤ ፈጠራዎች እንዳይበረታቱ፣ የገቢ ታክሶች በአግባቡ እንዳይሰበሰቡና ነጋዴዎች … [Read more...] about በኢንተርኔት መቋረጥ 9 ሚሊዮን ዶላር፣ በሞባይል ኢንተርኔት ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር ኪሣራ!
Archives for December 2016
ሚዲያ አለኝ ተብሎ የሰው ስብዕና ላይ ክተት አይታወጅም
ሚዲያ እንደ ሰዎች አረዳድ የሚሰጠው ደረጃና አቅም የተለያየ ቢሆንም ያለ አንዳች ማመንታት “ኃይል” ወይም ኃይል ያላቸው መገልገያ መሆኑ ጥርጥር የለውም። ሁሉም ሚዲያ “የሕዝብ” መሆናቸውን ቢገልጹም ፍጹም ነጻና ገለልተኛ ሆነው አይታዩም። ወደ አገራችን ሚዲያ ስንመጣ በውጭ ያሉትም ሆኑ በአገር ቤት፣ የግል የሚባሉትም ሆነ የመንግሥት የራሳቸው ወገንተኛነትና መንሸዋረር ይታይባቸዋል። ይህ እውነት ባደጉት አገሮችም ቢሆን ረቀቅ ባለ መልኩ የሚዘወተር ነው። ከሁሉም የሚቀፈው ግን ፍጹም ጭፍንነት ነው። ምክንያቱም በጭፍንነት ውስጥ አንድ ሰው ከተነገረውና ከተሞላው በቀር አሻግሮ ማየት አይችልምና ነው። “መቃብር ቆፋሪው እና የሬሳ ሳጥን ሻጩ የሚለው ተውኔት የተሰረቀ ነው” የማለት አዝማሚያ በሚስተዋልበት ስሜት የተጀመረ ቃለ ምልልስ። ሲጠናቀቅም የተለያዩ ጉዳዮች ውስጥ ትገባለህ “የባከንክ ነህ” … [Read more...] about ሚዲያ አለኝ ተብሎ የሰው ስብዕና ላይ ክተት አይታወጅም
“እውነተኛው የዘር ምንጭ?”
ዶ/ር ፍቅሬ በ “የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” መጽሐፉ አዲስ እሳት ለኵሶልናል። እሳቱ ባጭሩ፣ ሁሉም የሚስማማውን ታሪክ ይጻፍ የሚል ነው። ቍጥራቸውና ማንነታቸው ያልታወቀ አወዳሾቹ፣ “ሐቀኛ የኦሮሞ ልጅ የኢትዮጵያ ልጅ” “የመከራ ቀን ደራሽ” “የመከራ ቀን ልጅ” “የታሪክና የፍቅር አባት” “የኢትዮጵያ መድን” “የህዝብ እርቅ አባት” “አስታራቂ” “የኢትዮጵያ ቤዛ” “ነብይ” ብለውታል። ሙገሳው የለመደበት “ካብ ካብ፣ ጣል ጣል” ባህላችን ነው ብለን እንለፈው። አንዳንድ “ምሑራን” ጭሱ አፍኗቸው መስኮት ለመክፈት ይሯሯጣሉ። አንዳንዶች የጎሳ ክልል መደብዘዝ የሥልጣን ወንበር እንዳያሳጣቸው ሠግተው። ሌሎች በአገር ወዳድነት። አንዳንዶችም ያልተፈጠረ ንጹሕ ጎሳ በስውር የሚያውጁ ናቸው። ከኢትዮጵያ መንደር ውጭ ማሰብ የተሳናቸው፤ በምድር ዙሪያ የሕዝቦች አሠፋፈር፣ መፍለስና … [Read more...] about “እውነተኛው የዘር ምንጭ?”
የሕወሓትን “ሌጋሲ” በጨረፍታ
የወያኔው መንግሥት ያላወረሰን ነገር የለም፡፡ ሁለመናችንን እከክ በእከክ አድርጎናል - በቀላሉ በማይድን እከክ አውርሶን ወያኔም እኛም ጣር ላይ እንገኛለን - አሸናፊው ባልለየለት እልህ አስጨራሽ የአውራ ዶሮዎች ጦርነት ተጠምደን፡፡ የመለስና የድርጅቱ የሕወሓት ውርስ (ሌጋሲ) በአሥራዎች ቀርቶ በመቶዎች ዓመታትም ተዝቆ የማያልቅ ዕዳ አሸክሞናል፡፡ በኢኮኖሚውና በትምህርቱ ረገድ የደረሰብን ኪሣራ ምናልባት በጊዜ ሂደትና ደጋግ ዜጎች የአስተዳደሩን ልጓም ሲይዙ ሊስተካከል ይችላል፡፡ ይህም ሲባል ሚሊዮኖችን በእሳት አለንጋው እየገረፈ የሚገኘው ድህነት ጥርሱን አግጥጦና ዐይኑን አፍጥጦ ዜጎችን የበይ ተመልካች በማድረግ ከማንኛውም ጨዋታ ውጪ እያደረጋቸው እንደሆነና በትምህርቱም በኩል በዘልማድ ከኢትዮጵያ ሕዝብ 85 በመቶው እንደሆነ ከሚነገርለት የሀገራችን ገበሬ በዕውቀት የማይሻሉ ምሩቅ ማይማን … [Read more...] about የሕወሓትን “ሌጋሲ” በጨረፍታ
ኢህአዴግ በአሜሪካ የጉዞ ማዕቀብ ክፉኛ ተሽመድምዷል
አሜሪካ ባልተለመደ ሁኔታ ኢህአዴግን ከመውቀስ አልፋ እያስጠነቀቀች ነው። ኢህአዴግ በበኩሉ የጉዞ ማዕቀቡ እንዲነሳለት እየወተወተ ስለመሆኑ በተለያዩ መገናኛዎች ተደምጧል። የጎልጉል መረጃ አቀባይ የዲፕሎማሲ ምንጮች እንዳሉት አሜሪካ ለኢህአዴግ ጥያቄ መልሷ “ለጊዜው ጥሪ አይቀበልም” የሚል ሆኗል። እነዚሁ ክፍሎች እንደሚሉት ቅድመ ሁኔታ ተቀምጧል። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት የዴሞክራሲ፣ የሠብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ የሚመራ ልዑክ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ የአራት ቀን የስራ ቆይታ ባደረገበት ወቅት “በግልጽ ተወያይተናል” የሚል መግለጫ ቢሰጥም፣ እንደሚባለው ስምምነት ላይ አልተደረሰም። ለቪኦኤ አማርኛው ክፍል ብቻ መግለጫ የሰጡት ቶም ማሊኖዊስኪ “ለለውጥ የተገባውን ቃል ተግባራዊ ማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ ሃላፊነት” እንደሆነ መናገራቸው የተደረሰና … [Read more...] about ኢህአዴግ በአሜሪካ የጉዞ ማዕቀብ ክፉኛ ተሽመድምዷል
STANDING TOGETHER AS ONE
This past year of 2016 may have been the worst year in recent history for Ethiopians within the country. Many families will be facing Christmas or the New Year without the presence of a beloved family member at their side. The reasons have been many and most point to the actions or lack of actions taken by the TPLF/EPRDF. Too many have been taken from this earth early due to the deadly violence perpetrated against them by TPLF/EPRDF security forces. The ruling regime used deadly force against … [Read more...] about STANDING TOGETHER AS ONE
Ethiopia: The Peril of Complacency in our Community
Hilary Clinton’s historical defeat is no doubt one for the history books, and it is going to be minced and diced for a while. No body, not even Trump and his supporters, saw it coming. Trump, despite his braggadocio, might even have agonized in his mind to himself, “I didn’t mean to win, I swear to God! Why is it happening to me?” For those who are fond of the outcome, it is a miracle that can be compared to hitting the jackpot at the Taj Mahal Casino that Trump himself once owned; and for those … [Read more...] about Ethiopia: The Peril of Complacency in our Community
በጋምቤላ የከሸፈው “ኢንቨስትመንት”
በጋምቤላ የአኙዋክ ተወላጆች ተጨፍጭፈውና ከመሬታቸው ተፈናቅለው “ለሰፋፊ እርሻ” በሚል ሲቸበቸብ ከነበረው መሬት “ወደ ሥራ የገባው” 15በመቶው ብቻ መሆኑን ህወሃት/ኢህአዴግ አስታወቀ፡፡ ለ“እርሻ ልማት” በሚል 5ቢሊዮን ብር ብድር ተሰጥቷል፡፡ የመሬት ካርታ “ከቢሮ ውጪ በመኖሪያ ቤቶችና በጫት ቤት ውስጥ” ሲሰራ ቆይቷል፡፡ የቀድሞው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኃላፊ የነበረው ኢሳያስ ባህረ ከሥልጣኑ የተነሳው “ብድር በመስጠቱ ሂደት ለተወሰኑ የባለሃብቶች ቡድን በማድላቱ ነው” ተባለ፡፡ በጋምቤላ በደል ደረሰብን በማለት አቤቱታ ያሰሙ የትግራይ “ባለሃብቶች” ለሃይለማርያም የቀረበው ሪፖርት “የተዛባ ነው” አሉ፡፡ በጋምቤላ ይህ ነው የማይባል ግፍና የዘር ማጽዳት ተካሂዶ ከምስኪን ረዳተቢሶች የተነጠቀው መሬት ከጥቅም ውጪ ሆኗል፡፡ ገና ከጅምሩ አሠራሩ ሁሉ ትክክል እንዳልሆነ በተለያዩ ሪፖርቶች … [Read more...] about በጋምቤላ የከሸፈው “ኢንቨስትመንት”
ዘ-ሃበሻ! እባክሽ “ሙድ” አትያዢብን!
አንድ ሰው በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን በሚናገራቸው/በሚጽፋቸው ጽሁፎች አስተሳሰቡ እና ብቃቱ ይገመታል፤ የሚመራውን ድርጅት/ተቋም ብቃትም ይናገራል። እንደ ግለ-ሰብ ስለ ራስ፣ ስለ ቤተሰብ እና ስለ ጓደኛ የሚናገራቸው ወይም የሚጽፋቸው ጽሁፎች ከሙያዊ ብቃት እና ችሎታ አኳያ ብዙም የሚያስከትለው ተጽዕኖ አይኖርም። ጋዜጠኛ ነኝ ያለ ሁሉ ጋዜጠኛ እንዳልሆነ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ የጋዜጣ አዘጋጅ ስትሆን፣ ከዚያም ብዙ ተከታዩች ሲኖሩህ እና ስለ አገር እና የማህበራዊ ጉዳይ የምትጽፋቸው ሲሆን ግን ቢያንስ ከጋዜጠኛነት ሙያ፣ ከጭብጥም ሆነ ከቋንቋ አጠቃቀም አኳያ ይሄን ያህል መወረድ በ“ሙደኞች” (“ሙድ” የዘ-ሃበሻ የራሷ አማርኛ ነው) ቋንቋ ሙያዊ “ቅሽምና” ነው። ስለዚህ እኛም ዘ-ሃበሻን በ“ሙድ” ልንተች ነው። “ወያኔ በየቀኑ ህዝባችንን እየገደለና እያሰረ ሙድ ሲይዝብን...” እንዳለችው … [Read more...] about ዘ-ሃበሻ! እባክሽ “ሙድ” አትያዢብን!
የዶ/ር መረራ መታሰር ሰላማዊው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተደረገ ጥሪ ነው!!!!
መረራ ጉዲና ገና ከለጋ ወጣትነት ህይወቱ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ባልተቋረጠ ወኔና ጥራት ለአንዲት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ሲታገል የኖረ ዜጋ ነው፡፡ በዚህ ያልተቋረጠ ተጋድሎው በንገሱ ዘመን አምቦ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኖ በተማሪው ንቅናቄ በነበረው ንቁ ተሳትፎ ለአጭር ጊዜም ቢሆን እስር ቤት ተወርውሯል፡፡ በደርጉ ዘመን ደግሞ በመኢሶን ታጋይነቱ ለሰባት አመታት በእስር ተንገላቷል፡፡ ለአለፉት 25 አመታት ደግሞ የወያኔ ኢህአዴግን ግፈኛ አገዛዝ በመቃወም በሰላማዊና ህጋዊ የትግል ስልት ተሰማርቶ ከነዚህ የጥፋት ሃይሎች አንጻር እነሱ ከፋፍለህ ግዛን ሲያራመዱ የህዝቦች ወንድማማችነትን እየሰበከ፣ እነሱ ለስልጣናቸው ሲሉ በለየለት የአፋኝና የአመጽ ጎዳና ሲሰማሩ ዴሞክራሲን፣ ሰላምንና ህጋዊነትን እያነገበ ሲሞግታቸውና ሲታገላቸው በህዝባችን ፊት ተአማኒነትንና ተወዳጅነትን ያተረፈ ብርቅየ … [Read more...] about የዶ/ር መረራ መታሰር ሰላማዊው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተደረገ ጥሪ ነው!!!!