
መረራ ጉዲና ገና ከለጋ ወጣትነት ህይወቱ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ባልተቋረጠ ወኔና ጥራት ለአንዲት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ሲታገል የኖረ ዜጋ ነው፡፡ በዚህ ያልተቋረጠ ተጋድሎው በንገሱ ዘመን አምቦ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኖ በተማሪው ንቅናቄ በነበረው ንቁ ተሳትፎ ለአጭር ጊዜም ቢሆን እስር ቤት ተወርውሯል፡፡ በደርጉ ዘመን ደግሞ በመኢሶን ታጋይነቱ ለሰባት አመታት በእስር ተንገላቷል፡፡ ለአለፉት 25 አመታት ደግሞ የወያኔ ኢህአዴግን ግፈኛ አገዛዝ በመቃወም በሰላማዊና ህጋዊ የትግል ስልት ተሰማርቶ ከነዚህ የጥፋት ሃይሎች አንጻር እነሱ ከፋፍለህ ግዛን ሲያራመዱ የህዝቦች ወንድማማችነትን እየሰበከ፣ እነሱ ለስልጣናቸው ሲሉ በለየለት የአፋኝና የአመጽ ጎዳና ሲሰማሩ ዴሞክራሲን፣ ሰላምንና ህጋዊነትን እያነገበ ሲሞግታቸውና ሲታገላቸው በህዝባችን ፊት ተአማኒነትንና ተወዳጅነትን ያተረፈ ብርቅየ የኢትዮጵያ ልጅ ነው፡፡ (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply