* የናሚቢያው ፕሬዚዳንት የሞ ኢብራሂም ሽልማትን አሸነፉ የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን በየዓመቱ በሚያወጣው የአፍሪካ መልካም አስተዳደር ጠቋሚ ኢትዮጵያ ከ52 አገሮች 32ኛ ወጣች፡፡ እ.ኤ.አ. የ2014 የሞ ኢብራሂም የመልካም አስተዳደር ጠቋሚ ከ30 ገለልተኛ የአፍሪካና ዓለም አቀፍ ታማኝ ምንጮች የተገኙ ከመቶ በላይ መለኪያዎችን በመገምገም ነው የአገሮች የመልካም አስተዳደር ደረጃን ማውጣቱን የገለጸው፡፡ ዋነኛ መለኪያዎቹ አራት ምሰሶዎች መሆናቸውን የሚገልጸው ሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን፣ እነዚህም ሕዝቦች ከመንግሥታቸው የሚጠብቋቸውና መንግሥትም ማቅረብ የሚጠበቅበት ግዴታዎችን የሚዳስስ ነው፡፡ እነዚህ መሠረታዊ ምሰሶዎች የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ የመናገር ነፃነት፣ የንፅህናና የንብረት ባለቤትነት መብቶች ጥበቃን የሚዳስሱ ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት ሞሪሺየስ፣ ኬፕ ቨርዴና ቦትስዋና ከአንድ እስከ … [Read more...] about በመልካም አስተዳደር ከአፍሪካ 52 አገራት ኢትዮጵያ 32ኛ!
Archives for March 2015
ምርጫ እና ምርጫ በ2007!
ምርጫ 2007ን ከሌሎች ምርጫዎች ሁሉ ልዩ የሚደርገው ምርጫ ቦርድ ከምርጫው በፊት ፓርቲዎችን (ተፎካካሪ) በማፍረስ ጀምሮ የሰማያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎችን (ከ200 በላይ) አልመዘግብም ማለቱ እና በአዲስ አበባ ምርጫ ክልል ደግሞ ወደ ምርጫው ለመግባት ተወዳዳሪው በዕጣ መለየት አለበት ማለቱ ነው፡፡ ዕጣው ደግሞ ለሁሉም ፓርቲዎች ሳይሆን ሰማያዊን ጨምሮ ጥቂቶች ላይ የተደረገ ነው፡፡ ይኸውም በማፍረስ እና በመከልከል ተጀምሮ ”ምርጫ በሎተሪ” መሆኑ ነው፡፡ በዓለም ላይ በታሪክ ዴሞክራሲ በዕጣ ይረጋገጣል ሲባል ኢትዮጵያ ብቸኛ እና የመጀመርያ አገር ስትሆን በኢትዮጵያም ለመጀመርያ ጊዜ ሰማያዊ ፓርቲ በመወዳደሩ እና እንደሚያሸንፍ ስለታመነ እንጅ በ2002 በአንድ የምርጫ ክልል ከ18 በላይ ፓርቲዎች መወዳደራቸው አይካድም፡፡ እርግጥ ነው ህግ ከተባለ አዋ/ቁ 532/99 አንቀጽ 49 እንደ … [Read more...] about ምርጫ እና ምርጫ በ2007!
አስቂኙ የአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ቃለ መጠይቅ!
የኢሳት ራዲዮና ቴሌቪዥን (ነጋሪተ ወግና ምርዓየ ኩነት) ጋዜጠኞች ከሕዝባዊ ግንባር መሪ አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ተከታተልነው፡፡ ያው አስቀድሜ እንደገመትኩት በአሮጌው ድሪቶ ላይ አሮጌ ጨርቅ ድረታና እብለት ክህደት እንጅ የነበረውን አሮጌውንና ያላዋጣውን በመተው በአዲስና በተመከረ በተማረ ልብ አዲስ ሐሳብ አዲስ መንገድ ለመቀየስ አልተፈለገም፡፡ የሚጠበቀውና አስፈላጊው ግን ይሄኛው ነበር፡፡ ለነገሩ ከአንባገነን ሥርዓት ባለሥልጣናት ይሄ የሚጠበቅ አይደለም እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች እንኳን በአንድ ሰው ዕድሜ ሽህ ዓመታት የመኖር ዕድል ቢሰጣቸው እንኳን እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ሱሪያቸውን በአንገት ለማጥለቅ እንደታገሉ ያልፋሉ እንጅ አይ ሐሳቤ መንገዴ ይሄንን ያህል ዘመን ብታገልም ሊሠራ አልቻለም፡፡ ሊሠራ ያልቻለበትም የራሱ ምክንያት ችግር ስላለበት ሳይሆን … [Read more...] about አስቂኙ የአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ቃለ መጠይቅ!
የረዳት አብራሪ ሐይለመድህን አበራ ጉዳይና የአንድ አመት ጉዞው ባጭሩ
እለተ ሰኞ ፌብሯሪ 17 ቀን 2014 ዓ/ም ማለዳ አንድ ንብረቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነና በበረራ ቁጥር ET 702 የተመዘገበ ቦይንግ 767 የመንገደኞች ማመላለሻ አውሮፕላን በጣሊያን በኩል አድርጎ ወደ ስዊዘርላንድ የአየር ክልል ይገባል። የስዊዝ የአየር ክልል ጠባቂዎችም በጧት የመጣባቸውን ጥቁር እንግዳ ማንህ ወዴት ነህ ማለት። የአውሮፕላኑን የበረራ ሂደት ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት የተቆጣጠረው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራም ቆፍጠን ብሎ አኔ ነኝ ! ማለት። አንተ ማን? ምነው ምን ፈልገህ ነው ወደ አየር ክልላችን የገባኸው? የአየር ክልል ተቆጣጣሪዎቹ ቀጣይ ጥያቄ ነበር ። የበርካታ ወገኖቹን የብሶትና የግፍ መልዕክት ይዞ በስዊዝ አየር ላይ የሚያንዣብበው ሃይለመድህንም "ለጊዜው የምፈልገው የስዊዝ መንግስት የፖለቲካ ጥገኝነት እንዲሰጠኝ ፣ ለኢትዮጵያ … [Read more...] about የረዳት አብራሪ ሐይለመድህን አበራ ጉዳይና የአንድ አመት ጉዞው ባጭሩ
ምርጫ በኢትዮጵያ ምን ይመስላል?
በሃገራችን ታሪክ ውስጥ ብሄራዊ ምርጫ የተጀመረው እንደ ኣውሮፓውያን ኣቆጣጠር በ1957 በዓጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ሲሆን በ1955 የወጣውን ህገ -መንግስት መሰረት ያደረገ ንጉሱንና የላይኛውን ቤት ወይም ሴነቱን የማይመለከት ነገር ግን የተወካዮች ምክር ቤት ኣባላትን መምረጥ ተጀምሮ ነበር። እማኞች ሲነግሩን ምርጫውና ቆጠራው ግን ሃቀኛ ነበር ኣሉ። ታዲያ ንጉሱ በነበሩበት ዘመን የነበሩት ምርጫዎች ጅማሪያቸው መልካም ቢሆንም ዓለም በማህበራዊ ለውጥ ላይ በነበረችበት በመጨረሻው ሰዓት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ወደ ህገ-መንግስታዊ ሞናርኪ ቀይሮ የፖለቲካውን ስልጣንና የህዝቡን ተሳትፎ ማስፋት ስላልተቻለ ወታደራዊ ደርግ ኣብዮቱን ኣንግቦ ብቅ ኣለ። ደርግ ወታደራዊ መንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላ የሶሻሊዝም ርእዮት ተከታይ ነኝ በማለቱ በየማህበራቱ የሚደረጉት ምርጫዎች ሁሉ ከዚያው ከኣንድ ምንጭ … [Read more...] about ምርጫ በኢትዮጵያ ምን ይመስላል?
ወሬ ሲነግሩህ ሃሳብ ጨምርበት
ምኒልክ ጥቁረቱን ክዶ ነበር የሚል ቀደዳ በፌስቡክ ሲዞር ኣየሁ ልበል? ትልልቅ ቅጥፈቶች ጀርባ ኣንድ ትንሽ መነሻ ይኖራል፡፡ መነሻውን እንመርምር እስቲ፡፡ ያድዋ ድል ማግስት የምኒልክ ዝና የጠራቸው የውጭ ኣገር ሰዎች ኢትዮጵያን መጎብኘት ጀምረው ነበር፡፡ ከኒህ እንግዶች ኣንዱ የሄቲው ታጋይ ጋዜጠኛ ቤኒቶ ሲልቪያን ነው፡፡ ሲልቪያንና ምኒልክ ያደረጉትን ጭውውት ስኪነር የተባለ ኣሜሪካዊ ዘግቦታል፡፡ በጭውውታቸው መሀል ምኒልክ ለሄቲው ሰውየ I am not a Negro I am a Caucasian ማለቱን ስኪነር ዘግቧል፡፡ ምኒልክ ኔግሮ ኣይደለሁም ብለው ከሆነ ደግ ኣደረጉ ከማለት ውጭ የምለው የለኝም፡፡ ምኒልክ ጥቁር እንጂ ኔግሮ ኣይደለም።ኔግሮ የውርደት ስም ሲሆን ጥቁር የክብር ስም ነው፡፡ ኮኬሽያን የሚለው ቃል ግን ያስተርጓሚ ስተት መሆን ኣለበት፡፡በምኒልክ ዘመን ሰዎች ዘርን … [Read more...] about ወሬ ሲነግሩህ ሃሳብ ጨምርበት
ዝክረ አድዋ!!
ልክ የዛሬ 119 ዓመት እብሪተኛውን ጣልያን አድዋ ላይ ገጥሞ አይቀጡ ቅጣት የቀጣው የኢትዮጵያ ጦር በእምዮ ምኒሊክ ፊታውራሪነት በድል ተመልሶ አዲስ አበባ ሲገባ ህዝቡ በታላቅ እልልታና ጭፈራ ተቀበላቸው፤ ወዲያውም ግዳይ ሲጣልና ሲፎከር ለጀግኖቹ ክብር የሚከተለው ተገጠመለታቸው፡- ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡ *************** ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ፡፡ በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡ ምኒሊክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ፡፡ አባተ በመድፉ አምሳውን ሲገድል ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል የጎጃሙ ንጉስ ግፋ በለው ሲል እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሀን ዳዊቱዋን ዘርግታ ስምዓኒ ስትል፡፡ ተማራኪው ባዙቅ ውሃ ውሃ ሲል ዳኛው ስጠው አለ ሠላሳ … [Read more...] about ዝክረ አድዋ!!
Larger-than-life characters, intrigue part of history behind Battle of Adwa
“(ከአድዋ ሌላ) አፍሪካውያን ጦርነት ያሸነፉባቸው ሌሎች በማስረጃ የሚጠቀሱ አሉ፡፡ የእንግሊዝን ጦር ያሸነፈው ዙሉ ዓይነተኛ ምሳሌ በማድረግ መጥቀስ ይቻላል፤ ይህም በየጊዜው በተሰራ ፊልም ታዋቂ ለመሆን ችሏል፡፡ ሆኖም ድሉ ጊዜያዊ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ዙሉዎች ተሸንፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ ግን ከዚህ ለየት ያለ ነው፤ (ምኒልክ ጣልያንን አድዋ ላይ ካሸነፉ በኋላ) በንጉሠነገሥቱ የግዛት ዘመን ያልተሸነፈች ብቸኛ አገር ናት” ሬይሞንድ ጆናስ “The Battle of Adwa - 1896” ደራሲ፡፡ Raymond Jonas went to the Boston Museum of Fine Arts one day when he was in town for a conference, aiming to see an exhibit of European art. But on the way out, he stumbled onto a … [Read more...] about Larger-than-life characters, intrigue part of history behind Battle of Adwa
ኢሳያስ አፈወርቂን በጨረፍታ
"አንድም ቀን ስቀን አናውቅም!" አሉ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም። ይህን በሚሉ ጊዜ እፊታቸው ላይ ፈገግታ ይታይ ነበር - ምሬቱ እንዳለ ሆኖ። ኢሳያስ አፈወርቂ ሲስቁ አይተናቸው አናውቅም። ግን ኮስተር ብለው የሚናገሩት ነገር እኛኑ አያሳቀን ነው። "ካሳ ይገባናል! ካሳ ስጡን" ሲሉ አሳቁን። ቀጠል አድርገውም "ምጽዋና አሰብን ወያኔ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲጠቀምበት ፈልገው" እንደነበር ተናግረው አሳቁን። "...የሰራነው ጥፋት ስለሌለ የሚጸጥተን ነገር የለም።" አሉ እጃቸውን እንደ ጲላጦስ እያጠቡ። ከዚህ ቀደም ለስዊድኑ ጋዜጠኛ የአስመራው የፖለቲካ ስርዓት ስዊድን ካለው ስርዓት የተሻለ እንደሆነ አስረግጠው ነገሩት። ስለ ብሄራዊ ምርጫ ለጠየቀቻቸው የአልጃዚራዋ ጋዜጠኛም "ምርጫ ምንድነው?" ብለዋት ነበር። ከዚህ በላይ ምን የሚያስቅ ነገር አለ? የፈለጉት ካሳ ግን ምን ይሆን? … [Read more...] about ኢሳያስ አፈወርቂን በጨረፍታ
የወያኔ ሰላይ ከሆላንድ ተባረረ!
ሮተርዳም፣ ጥቅምት 28 ቀን 2015 - በስደት ስሙ አለማየሁ ስንታየው በመባል የሚታወቀው የህወሃት ሰላይ ከኔዘርላንድስ ተባረረ። አለማየሁ ስንታየሁ ቋሚ ነዋሪ ከነበረበት ከኔዘርላንድስ እንዲባረር የተደረገው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በከፈቱበት የስለላ ክስ መሆኑም ታውቋል። የሮተርዳም ከተማ ፍርድ ቤት በአለማየሁ ላይ የተመሰረተውን የስለላ ክስና ማስራጃ ለረጅም ጊዜ ሲመረምር ከቆየ በኋላ የግለሰቡ የመኖርያ ፈቃድ እና ቤት እንዲነጠቅ፣ የሆላንድን ምድርም በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ውሳኔ አስተላልፏል። ከሆላንድ የምመራ ቡድን እንደተረዳነው ከሆነ - የግለሰቡ ቤት ሲፈተሽ ወያኔ የሰጠው እውነተኛ መታወቂያ እና በርካታ የስለላ ሰነዶች ተገኝተውበታል። በእርዳታ ስም የተቋቋመለት ድርጅትም ተፈትሾ ማስረጃዎች እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል። ይህ ሰው ትክክለኛ ስሙ ዘለቀ ፎላ … [Read more...] about የወያኔ ሰላይ ከሆላንድ ተባረረ!