ልክ የዛሬ 119 ዓመት እብሪተኛውን ጣልያን አድዋ ላይ ገጥሞ አይቀጡ ቅጣት የቀጣው የኢትዮጵያ ጦር በእምዮ ምኒሊክ ፊታውራሪነት በድል ተመልሶ አዲስ አበባ ሲገባ ህዝቡ በታላቅ እልልታና ጭፈራ ተቀበላቸው፤ ወዲያውም ግዳይ ሲጣልና ሲፎከር ለጀግኖቹ ክብር የሚከተለው ተገጠመለታቸው፡-
ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡
***************
ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ፡፡
በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ
ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡
ምኒሊክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ
ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ፡፡
አባተ በመድፉ አምሳውን ሲገድል
ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል
የጎጃሙ ንጉስ ግፋ በለው ሲል
እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሀን
ዳዊቱዋን ዘርግታ ስምዓኒ ስትል፡፡
ተማራኪው ባዙቅ ውሃ ውሃ ሲል
ዳኛው ስጠው አለ ሠላሳ በርሜል፡፡
እንደ በላኤ ሰብዕ እንደመቤታችን
ሲቻለው ይምራል የኛማ ጌታችን
መድፉን መትረየሱን ባድዋ መሬት ዘርቶ
እንክርዳዱን ነቅሎ ስንዴውን ለይቶ
የተዘራውን ውል አጭዶና ወቅቶ
ላንቶኔሊ አሳየው ፍሬውን አምርቶ
እንፋቀር ብሎ ለምኖ መሬት
ንግድ ሊያሰፋበት ሊዘራ አታክልት
እያመጣ ሊሰጥ ግብሩን ለመንግስት
ለጉዋዙ ማረፊያ አገር ቢሰጡት
ተጠማኝ ሰንብቶ ሆኖ ባለ ርስት
ወሰን እየገፋ ጥቂት በጥቂት
እውነት ርስት ሆነው ተቀበረበት
ባሕር ዘሎ መምጣት ለማንም አትበጅ
እንደተልባ ስፍር ትከዳለች እንጅ
አትረጋምና ያለ ተወላጅ፡፡
የዳኛው አሽከሮች እየተባባሉ
ብልት መቆራረጥ አድነት ያውቃሉ
አድዋ ከከተማው ሥጋ ቆርጠው ጣሉ፡፡
የእስክንድር ፈረስ መቸ ተወለደ
የሚኒሊክ ፈረስ በክንፎቹ ሄደ
ደንገላባ ሲዘል እየተጓደደ የሮማውን ኩራት በእግሩ አሰገደ
አገርህን ሚኒሊክ እንዳሁን ፈትሻት ባያይህ ነውና ጠላትህ የሚሻት
እጁን ቀምሼ አላውቅ እያለ ሲያማህ
ቀመሰና እጅህን መጥቶ ጠላትህ
ሮም ላይ ተሰማ ለጋስ መሆንህ፡፡
(ምንጭ: This day in Ethiopian History facebook page)
Leave a Reply