• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

እናንተ እውነትን የምትደባብቁ ነግ በኔ በሉ!!

December 3, 2015 10:44 am by Editor Leave a Comment

ኢቢሲ “በቀኑ ዜና እወጃየ በጎንደር ማረሚያ ቤት ትላንት በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የሞተ ሰው የለም ብየ የዘገብኩት ኮማንደር ሰይድ ሃሰን የሚባሉ የማረሚያ ቤቱ ሃላፊ “ዋሽተው” መረጃ ስለሰጡኝ ነው … ሃቁ ግን 17 እስረኞች ከእሳቱ ለማምለጥ ሲሞክሩ እርስ በእርስ ተረጋግጠው ህይወታቸው አልፏል ይህንንም የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሸን ኮሚሽነር አስተዳደር ሃላፊ በላይ ዘለቀ የሚባሉ (ስሙንማ ይዘውታል) ገልፀውልኛል” ሲል ማምሻውን አስተባብሏል … (አላግጧል) መቸስ የሞተ ሰው የለም ብለው 17 ከሞተ … 17 ሰው ብለው ካመኑ የሟቹ ትክክለኛ ቁጥርም ሌላ ሊሆን ይችላል!! የሆነ ሁኖ ከዚህ የተዘበራረቀ አሳፋሪ ዜና … ሁለት ነገር ተረዳሁ …

1ኛ፡ ብሔራዊ ቴሌቪዥናችን ያልተረጋገጠ መረጃ የሚያቀርብ ግድ የለሽ ተቋም መሆኑን አውቀናል፤
2ኛ፡ ማረሚያ ቤቶቻችን በስራቸው ላሉት ዜጎች ህይዎት እንኳን ግድ በሌላቸው ውሸታም አልያም በስራቸው ባለ ማረሚያ ቤት ስለሚከናወነው ነገር ምንም እውቀት በሌላቸው ሰዎች እንደሚመሩ አጋጣሚው ነግሮናል፤

gondar17 ሰውኮ እጅግ ብዙ ነው … የሃዘን ቀን ሁሉ በመላው ኢትዮጵያ መታወጅ ያለበት ጉዳይ ነው … 17 ኢትዮጵያዊያን የሚያድናቸው አጥተው በማረሚያ ቤት ማለቃቸው ብሔራዊ ውርደት አቅመ ቢስነት ነው!! በዚህ ላይ የጋዜጠኞቹ ወሽካታነትና ከህዝቡ ሃዘን በላይ ተቋሞቹ ለማይረባ ፖለቲካቸው ማሰብ ያሳፍራል!!

ጋዜጠኞች በተለይ በዓል እና ድግስ በያለበት ለመገኘት ማንም የማይቀድመው የክልሉ ቴሌቪዥን በወቅቱ ከማንም በፊት በቦታው መገኘት እና ትክክለኛ መረጃ ማድረስ ነበረበት … ቢሯቸው ተዘፍዝፈው በስልክ ሰው አልሞተም … ተሳስተን ነው ሙቷል እያሉ የሚዘላብዱት ምናይነት አሳፋሪ ሙያዊ ስነምግባር ቢኖራቸው ነው?

ደግሞ ኢቢሲ “ስህተቱ የአቶ እከሌ ነው፤ እርማቱ የማንትስ ነው” እያለ የሚቀልደው የመንደር እድር ወይም የቤተ ዘመድ ጉዳይ መሰለው እንዴ?? ይሄ አንገብጋቢ የሆነ አገራዊ ጉዳይ ነው … መንግስት እኔ እጠብቃቸዋለሁ ብሎ በራሱ ሃላፊነት ስር ያስቀመጣቸውን የህዝብ ልጆች መነሻው ምንም ይሁን ምን የሞታቸው ምክንያት እሳቱም ይሁን “እርግጫ” ወይም ሌላ … ብቻ ሃላፊነቱን ባለመወጣቱ 17 ወገኖቻችን ህይወታቸው አልፏል!!

ለሟች ወገኖች መፅናናትን እየተመኘሁ መንግስትም ሆነ በመንግስት ትዕዛዝ የምትንቀሳቀሱ የሚዲያ ተቋማት ይህን ጉዳይ በዘገባችሁበት ግዴለሽና አሳፋሪ አዘጋገብ ለእናተም ቤተሰብና ላቆሰላችሁት ኢትዮጲያዊ ሁሉ ፈጣሪ የሚያፅናና ቀን ያምጣ ከማለት ሌላ የምለው የለኝም!!

(Alex Abreham አሌክስ አብርሃም)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule