
በህገ-ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጣ የነበረ 132 ሺህ 860 የአሜሪካን ዶላር እና 9.2 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተሰኘ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።
በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቴክኖሎጂ ተደገፎ በተደረገ ጥብቅ ፍተሻና ክትትል ከአዲስ አበባ ወደ ናይጄሪያ ሊጓጓዝ የነበረ 9.2 ኪሎ ግራም ኮኬይን እንዲሁም መዳረሻውን ዝምባብዌ ያደረገ 132 ሺህ 860 የአሜሪካን ዶላር በቁጥጥር ስር መዋሉ ነው የተገለፀው።
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለኢቲቪ በላከው መረጃ እንደገለጸው፤ በህገወጥ ድርጊቱ ተጠርጥረው የተያዙት ግለሰቦች በኢትዮጵያ ለቀናት ባደረጉት ቆይታ ከግብረአበሮቻቸው ጋር ግንኙነት በመፍጠር በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ነበር።
ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ክትትል የሚያከናውነው ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም ከናይጄሪያ ወደ አዲስ አበባ የገባው ናይጄሪዊ ግለሰብ መስከረም 18 ቀን 2013 ዓ.ም ጠዋት ግምቱ 920 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የሆነ 9.2 ኪሎ ግራም ኮኬይን ከአዲስ አበባ ወደ ናይጄሪያ ይዞ ለመጓዝ ሲሞክር በቴክኖሎጂ በተደገፈ ጥብቅ ፍተሻና ክትትል በቁጥጥር ሥር እንዲውል አድርጓል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply