ኢትዮጵያ አዲስ የብር ኖቶችን ማስተዋወቋን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝዉዉር እየተስተዋለ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የብር ኖት ለዉጥ መደረጉን ተከትሎ ባደረገዉ የኦፕሬሽን እና የድንገተኛ ፍተሻ ስራ በርካታ ቁጥር ያለዉ ገንዘብ በቁጥጥር ስር አዉሏል፡፡
በጥቁር ገበያ ሲንቀሳቀስ የነበረ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም በየኬላዎች በተደረገዉ ድንገተኛ ፍተሻ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 1.6 ሚሊዮን ብርን ጨምሮ 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በድምሩ 10.6 ሚሊዮን የኢትጵያ ብር በላይ በቁጥጥር ስር ማዋሉን በኮሚሽኑ የሙስና፣ ገቢዎች እና ልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክተር ኮማንደር ግርማ ተሰማ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽኑ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝዉዉሩን ለመቆጣጠር ከሌሎች የጸጥታ እና የደህንነት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን በመግለጽ ህብረተሰቡም ከጸጥታ አካሉ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል ሲል ኤኤምኤን ዘግቧል። ©የአዲስ አበበ ፖሊሰ ኮሚሽን
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply