በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ በወጣቶች ክፍል አስተባባሪነት በዛሬው እለት ሰኞ (January 26,2015) በኖርዌ ኦስሎ በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በኖርዌይ የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በህብረት ሁነው ከ14፡00-15፡00 ስዓት ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ በደማቅ ሁኔታ አካሄዱ። የሰልፉ ዋና አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ የነበሩትንና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአረመኔው፣ ሰው በላ፣ ጨቋኙና በአንምባ ገነኑ የወያኔ ፋሺስታዊ ቡድን የአለም አቀፍ የሰባዊ መብትን ህግ በጣሰ መንገድ በሰኔ 2014 ታፍነው እስኳሁንም ድረስ ፍትህ ተነፍገው በእስር ቤት መታሰራቸውን ለመቃወም እንዲሁም የእንግሊዝ መንግስት አርበኛው የነጻነት ታጋዩ አንዳርጋቸው እየተፈጸመበት ያለውን ተፈጥሮአዊና … [Read more...] about ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ኦስሎ እንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ
Opinions
የኔ ሃሳብ
የደደቢት ጉዞ መዘዝ፤ ከሰራዊት ፍቅሬ እስከ ታገል ሰይፉ
በመጀመርያ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ደጋፊና ተደጋፊ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን በሙሉ ጠሯቸው። ሰበሰቧቸው። እንዲህም አሏቸው። "ወደ ደደቢት አብራችሁን ትሄዳላችሁ፤ እዛ እንደደረሳችሁም አመጣጣችንንና አካሄዳችንን በደንብ አድርጋችሁ ታጤናላችሁ። ከዚያ ስትመለሱ ሁሉንም ነገር ለህዝቡ ትናገራላችሁ።..." በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሃገር መሪ ሆነው የሚሰሩት እኝህ ሰው መልዕክታቸውን በዚህ አላበቁም። አይናቸውን ፈጠጥ፤ ጉሮሯቸውንም ጠረግ-ጠረግ አደረጉና ንግግራቸውን ቀጠሉ "ስለረጅሙና መራራው ትግላችን፤ ከጅምራችን እስከ አያያዛችን የታዘባችሁትን ሁሉ ንገሩን። ጥሩውንም ይሁን መጥፎውን ነገር ሳትደብቁ ተናገሩ።..." ድምጻዊው በዝማሬ፣ ጸሃፊው በድርሰት፣ ተዋንያኑ በተውኔት ስለ ህወሃት የአርባ አመት ጉዞ እንዲመሰክሩ የተሰጠች … [Read more...] about የደደቢት ጉዞ መዘዝ፤ ከሰራዊት ፍቅሬ እስከ ታገል ሰይፉ
የሐመር አርብቶ አደሮችና የፖሊስ ግጭት ወቅታዊ መረጃ
በጥር 7/2007 ሐሙስ ዕለት በሐመር ወረዳ በ"ላላ" ቀበሌ በሐመር ብሔረሰብ አርብቶ አደሮችና ፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት የደረሰዉ ጉዳት የሚከተለዉን ይመስላል፤ ሀ/ የሞቱ-- 1. ሻምበል ለማ አሸናፊ 2/ ወ/ር ሙሴ ማቱሳላ 3/ ወ/ር ደፋሩ ጦና 4/ ወ/ር ካሬ 5/ ወ/ር በኃይሉ 6/ ስሙ ለግዜዉ ያልታወቀ የልዩ ኃይል ባልደረባ 7/ ስሙዋ ለግዜዉ ያልታወቀ ሴት ባለሙያ 8/መምህር መሳይ ነሽ መርነህ ለ/ የቆሰሉ 1/ አቶ ቹሜሬ የረር /የደቡብ ኦሞ ዞን ፍትህ ጸጥታና ደንብ ማስከበር ምክትል ሀላፊ 2/ ምክትል ሣጅን ጌታሁን ቶላ 3/ ወ/ር ተሰማ መሰረት 4/ ወ/ር ጌታቸዉ ጻንቃ 5/ ወ/ር ቱላ ኪያ 6/ ባሻ ወንድማገኝ ጨነቀ 7/ ወ/ር ሚልኪያስ ግራኝ 8/ ወ/ር ዘለቀ (አባታቸዉ ያልታወቀ) 9/ አቶ ደምሳሽ ሞላ (የዞኑ ሴቶችና ሕጻናት መምርያ … [Read more...] about የሐመር አርብቶ አደሮችና የፖሊስ ግጭት ወቅታዊ መረጃ
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ካፍቴሪያ ሰራተኞች ድምጽ አልባው እሮሮ!
ንብረትነቱ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እንደሆነ በሚነገርለት ካፍቴሪያ ውስጥ የሚፈጸመው ግፍ አይሏል ። ከዛሬ 10 ዓመት በፊት እዚህ ኮሚኒቲ ካፍቴሪያ ውስጥ በተለያየ የሙያ ዘርፍ ሰማርተው እያገለገሉ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን አብዛኛዎቹ በወጣትነት እድሚያቸው የተቀጠሩ ናቸው። ታዲያ ለወጣትነት እድሜ ጉልበታቸው ሳይሰቱ ነገን በተስፋ በመናፈቅ ተመጣጣኝ ባልሆነ ክፍያ በቀን ከ 8 ሰዓት በላይ አውዳአመታትን ሳይቀር ያለ እረፍት በስራ በማሳለፍ ኮሚኒቲውን አገልግለዋል። ሰራተኞቹ በተሰማሩበት የስራ መስክ በሚከፈላቸው ደሞዝ እንደማንኛውም ማህበረሰብ ቤትሰብ አፍርተዋል ። እነዚህ ወገኖች እንደመነሻ በተቀጠሩበት አነስተኛ ደሞዝ ከግዜ ወደ ግዜ እየከበደ የመጣውን የስደት ዓለም ህይወት መቋቋም ተስኗቸው ገሚሱ በብስጨት በደረሰበት የጤና መታወክ ለህለፍት ሀይወት ሲዳረግ በስኳር በሽታ … [Read more...] about በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ካፍቴሪያ ሰራተኞች ድምጽ አልባው እሮሮ!
Should Ethiopians Boycott the Upcoming Fake Election in Ethiopia?
Should Ethiopians Boycott the Upcoming Fake Election in Ethiopia? More Crackdowns Lock Out Opposition Groups from Political Participation “If we do not have a proper multiparty democracy, this country is going to end up like Somalia. This is imperative” he said. “It is up to the people to decide on how many seats should be given to the opposition and how many to the ruling party.” (Prime Minister Hailemariam Desalegn)[i] PRESS RELEASE. December 16, 2015. Washington, DC, The Solidarity … [Read more...] about Should Ethiopians Boycott the Upcoming Fake Election in Ethiopia?
እውነትን ፈልጓት፤ ታገኟታላችሁም!!
በክፍል አንድ ጽሑፍ ውስጥ ለመግለጽ እንደተሞከረው ሁሉ እነዚህ ከእውነት ይልቅ ሃሰትን፤ ክቅንነት ይልቅ ተንኮልና ጭካኔን የመረጡ ጥቂት ካህናት ሕዝበ ክርስቲያኑን ለመከፋፈልና አንዱን ከሌላው ጋር በአስተሳሰብ አለያይቶ ለማጋጨት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ከዚህም ውስጥ በዚሁ በቅርቡ በፌስ ቡክ ላይ በለቀቁት ጽሑፋቸው በርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የደረሰው ችግር “ሰዎች ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን ጠንቅቆ ባለመረዳትና የራሳቸው ትርጉም በመስጠት.....” የሚል ጠቅሰዋል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) እውነትን ፈልጓት፤ ታገኟታላችሁም!! ክፍል አንድን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ ጸሃፊውን በዚህ አድራሻ ማግኘት ይቻላል: MaAyal@aol.com … [Read more...] about እውነትን ፈልጓት፤ ታገኟታላችሁም!!
ያለነፃነት የኢኮኖሚ ዕድገት አይኖርም!
የሰው ልጅ፣ ከሌሎች ፍጡራን በተለየ ከታደለው ፀጋ ውስጥ አንዱ ስልጣኔ ናፋቂ መሆኑ ነው፡፡ የሰው ልጅ የዝግመተ-እድገት ታሪክ የሚነግረን፣ አለም አሁን ለደረሰችበት የሀያ አንደኛው ክፍለ-ዘመን ስልጣኔ፣ መንስኤው ስልጣኔ ናፋቂ የሆነው የሰው ልጅ በየዘመኑ ያከናወናቸው እንቅስቃሴዎች ድምር ውጤት መሆኑን ነው፡፡ የሰው ልጅ፣ ከሌሎች የፈጣሪ ፍጡራን በተለየ ስልጣኔ ናፋቂ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ከሌሎች ፍጡራን በተለየ ፈጣሪ የማሰብ ፀጋ ስለቸረው ነው፡፡ “ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙላት” እንዲል ቃሉ፤ የሰው ልጅ ዘር መብዛቱን ተከትሎ፤ እንደ ህዝብ በቡድን መኖር ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ የጋራ የሆነ ሀብትን ለመጠቀምም ሆነ እንደ ግለሰብ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ፍትሀዊነት ህግ እና ደንብን ማእከል ያደረገ መንግስታዊ ስርአትን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረ እነሆ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ ይህም ለስልጣኔ … [Read more...] about ያለነፃነት የኢኮኖሚ ዕድገት አይኖርም!
ምርጫ ቦርድ፣ ማጭበርበሩን ያቁም!
በሕወሓት አመራርና አጃቢዎች የተፈበረከው ምርጫ ቦርድ ባለፉት 20 አመታት ለ4 ጊዜ ከፌደራል እስከ ቀበሌ ምርጫ አካሂዷል። ሁሉም ምርጫዎች ግን የዴሞክራሲ መስፈርትን የሚያሟሉ እንዳልነበሩ ዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ጭምር አረጋግጠዋል። በ2007 ዓ.ም የምርጫ ውድድርም ሕወሓቶች፣ በዚሁ አመት ሃቀኛ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ጭራሹን ላለማሳተፍ፣ ለአመታት ያህል የቤት ስራ እየሰሩ ቆይተዋል፡፡ ለዚሁ አላማ ግቡን ለመምታት አስቀድመው እጅግ ብዙ ብቁ ምሁራንን እና ወጣት የፖለቲካ አመራሮችን “ለስልጣናችን አስጊ ናቸው” በማላት በሀሰት ወንጅለው አስረው በማሰቃየት ላይ ይገኛሉ። ብዙ የተቀናቃኝ ፓርቲዎች አባላት ላይም ስጋት ፈጥረዋል፤ ከትምህርትና ከስራም አፈናቅለዋል። ፓርቲዎችን ለመበታተን ብዙ ሰርጎ-ገቦችን በማስረፅ አለመተማመን በመፍጠር፣ እንዲከፋፈሉ ለማድረግ ብዙ ገንዘብ ረጭተዋል። ተቃናቃኝ … [Read more...] about ምርጫ ቦርድ፣ ማጭበርበሩን ያቁም!
የአምባገነኖች ፀሐይ ጠልቃለች!
በእኛ በኢትዮጵያ ህዝቦች ዘንድ ለ23 ዓመታት ተመዝኖ ቀሎብናል - ይህ የጥቂት ሽፍታዎች ቡድን! የመንግስትነት ስም ሊመጥነው የማይችል የውንብድናና የማፍያ ተግባር በ’መንግስትነት’ ሽፋን ሲራመድም ቆይቷል - ላለፉት ሁለት አስርታት፡፡ ዛሬ፡- ይህን በገሃድ የሚታይ ጥሬ-ሀቅ ያልተገነዘበ አንድም ኢትዮጵያዊ አይገኝ፡፡ ይህንን የጥቂቶች "የምዝበራ ፖለቲካል-ኢኮኖሚ" ለመሸፈን እና የተለየ ልባስ/ጭንብል ለማልበስ፤ እነዚህ መዝባሪዎች አያሌ ፎቆቻቸውን ከህዝብ በመዘበሩት የህዝብ አንጡራ-ሃብት አማካይነት ህዝብን ባፈናቀሉበትና ከቀዬው-በነቀሉበት በዚያው ስፍራ ላይ ለማቆም ችለዋል፡፡ ፎቆቻቸውን ያነፁት የእነርሱ-ዝርፊያ የሃገር-‘ልማት’ እንዲባልና በዚህም ሰፊው-ህዝብ ተደናግሮ ይህንን በአገር ላይ የሚሠራ "ጥፋት" በበጐ ጐኑ እንዲመለከተው ለማድረግ ነው፡፡ ‘ልማት’ እና የዘር-ልዩነት ላይ … [Read more...] about የአምባገነኖች ፀሐይ ጠልቃለች!
ቅዱስ ገብርኤል ሥነ ባህርይን (ሞራልን) አከበረ!
ታህሳስ 19 ቀን በቅዱስ ገብርኤል ስም የሚታሰበው በዓል፤ እግዚአብሔር ሥነ ባህርይን (ሞራልን) እንዲያከብር ቅዱስ ገብርኤልን የላከበት ቀን ነው። ማሳሰቢያ፦ በቅዱስ ገብርኤል ስም በየስርቻው ቤተ ክርስቲያን ከፍተው ህዝብን በመዝረፍ ላይ የሚገኙት ብዙዎቹ “ቅዱስ ገብርኤል ተከበረ እንጅ አከበረ ” የሚለውን ሰምተውት ስለማያውቁ፤ “ቅዱስ ገብርኤል አይከበር አለ ” እያሉ፤ አንብበው ከእውነቱ መድረስ የማይችሉትን አንዳንድ የዋሆችን ውዥንብር ውስጥ መክተታቸው አይቀርም። እኔ ኢትዮጵያን በመምራት ያሉ ፖለቲከኞችና በየስርቻው ቤተ ክርስቲያን የሚከፍቱትን የአስመሳይ ነጋዴዎች ባህርይ፤ አባቶች ስለበዓሉ አላማና ምክንያት ካስተማሩኝ ጋራ ሳንጻጽረው፤ ቅዱስ ገብርኤል ካከበረበት ምክንያትና ዓላማ ጋራ ምንም ግንኙነት እንደሌለው ገለጽኩ እንጅ ቅዱስ ገብርኤልማ ክብር ይገባዋል … [Read more...] about ቅዱስ ገብርኤል ሥነ ባህርይን (ሞራልን) አከበረ!









