ከሰሞንኛው የዓለም አቀፍ የብዙኃን መገናኛዎች ወሬ እንዳዳመጣቹህት ሰሞኑን ፈረንሳይ ውስጥ በሚታተም ቻርሊ ሄብዶ በተባለ ጋዜጣ ጥቅማችን ተነካብን ያሉ የመካከለኛው ምሥራቅ ተወላጆች በአሸባሪነት ከተፈረጁ ቡድኖች በተደረገላቸው ድጋፍ በጋዜጣው ሠራተኞች ላይ በፈጸሙት ጥቃት ባጠቃላይ 17 የሚሆኑ ሰዎች ለሕልፈት መዳረጋቸውን ተከትሎ የምዕራቡ ዓለም መንግሥታትና ዜጎች በቁጣ በመነሣት አውግዘዋል ለጋዜጣውም ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል፡፡ የፈረንሳይ መንግሥትም ይሄንን ጥቃት በፈጸሙትና በደጋፊዎቻቸው ላይ እርምጃ ወስዷል እየወሰደም ነው፡፡ ይሄ ዓይነት ጥቃት ያሠጋናል የሚሉ ሀገራትም ተመሳሳይ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡
ይሄንን ጉዳይ በተመለከተ እዚህ ሀገር ውስጥም የበሰለና ጥልቀት ያለው አይሁን እንጅ ኢ.ቴ.ቪ (ኢ.ቢ.ሲ) በልዩ ዝግጅት እና የሸገር ኤፍ.ኤም በሸገር ሸልፍ ዝግጅቱ አንሥተውት እንደየችሎታቸውና ፍላጎታቸው ተወያይተውበት ነበር፡፡ በተለይ ኢ.ቢ.ሲ (ኢ.ቴ.ቪ) ይሄንን የፈረንሳዩን ጉዳይ እጅግ በተዛባ ሁኔታ ለሐፍረትና ለምን ይሉኝ ዐይንና ጆሮውን ደፍኖና ጨፍኖ ሆን ብሎ ጉዳዩን ሊያየውና ሊያገኛኘው ይጥር የነበረው አገዛዙ በአሸባሪነት ስም በንጹሐን ዜጎች ላይ እየወሰደው ያለው ሕገ ወጥ እርምጃ ምን ያህል አግባብ እንደሆነ እማኝ እንዲሆነው ባሰበ ፍጹም ሚዛናዊነት በጎደለውና ጭፍን አቀራረብ ነበር፡፡ ነገር ግን አውሮፓውያን መንግሥታት የትኛውን በጋዜጠኝነት ሙያ ላይ የተሠማራ ዜጋቸውን የጋዜጠኝነቱን ሥራ በመሥራቱ፣ የትኛውን በተቃውሞ ወይም በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ (የእምነተ-አሥተዳደር ቡድን) ተሠማርቶ ለሀገሩ የሚችለውንና የዜግነት ግዴታው የሆነውን ተግባር ለመወጣት በመጣሩ አሸባሪ ብለው ወኅኒ እንዳወረዱ አንድ እንኳን ሊጠቅሱ አልቻሉም አይችሉምም፡፡ እንዲሁ ዝም ብለው ዙሪያ ጥምጥም ነበር እንደተሸከረከሩ ዝግጅቱን የጨረሱት፡፡ ምን ያድርጉ? ቢቸግራቸው ነው፡፡
አቶ መለስ “የፀረ አሸባሪነት ሕጉን ኮማ ሳይቀር እንዳለ ነው ከምዕራባዊያኑ የገለበጥነው” እንዳሉት ሁሉ እንዲያ ቢሆንም እንኳ ቁምነገሩ ያለው የኮማው ሳይቀር መምጣትና መቅረት ወይም እንዳለ መቀዳቱ ሳይሆን በማን ላይ አነጣጠረ? ለምን? የሚለው ጥያቄ ላይ ነው፡፡ በምዕራብ ሀገሮች በዋናነት ይሄ የፀረ አሸባሪነት ሕግ እንዲቀረጽ ምክንያት የሆነው ከእስልምና ጽንፍ የያዘ አክራሪነት ጋር በተያያዘ ጀሀድንና መሰል የእስልምናን አስተምህሮን በማንገብ በማይመስላቸው ላይ የኃይል እርምጃን የመውሰድ ዓላማ ያላቸውንና እየወሰዱም ያሉትን አካላት ለመቆጣጠርና እንቅስቃሴያቸውን መግታት ላይ በማነጣጠር ዓላማ ይዞ የተቀረጸ ነውና፡፡ በመሆኑም የአቶ መለስ ከምዕራባዊያኑ ኮማ ሳይቀር የተቀዳ የፀረ አሸባሪነት ሕግ በጋዜጠኞች፣ በፖለቲከኞች (በእምነተ-አሥተዳደራዊያን) እና ሕገ መንግሥታዊ መብታቹህ ነው የተባሉትን በጠየቁ ሰላማዊ የእስልምና ተከታዮች ላይ ተግባራዊ ማድረግ ብልጣብልጥነት ቢመስላቸውም ተራና የወረደ ድንቁርና ነው፡፡ ለምን? አቶ መለስ ሕጉን ቀዳን ባሏቸው ሀገራት ላይ ይሄንን ሕግ በመጠቀም አቶ መለስ በንጹሐን ዜጎች ላይ እየፈጸሙት ያሉት ግፍ እዚያ ሲፈጸም ዐናይምና፡፡ ይሄንን ስል ግን በሀገራችን እንደ ወያኔ ሁሉ እጅግ በሚገርም ሁኔታ ጽንፍ የያዘ ፀረ ኢትዮጵያና አልቃይዳዊ ዓላማ አቋምም ይዘው በታወረ ስሜት በመነዳት ቀድሞ ከደርቡሽ ጋር እየተሰለፉ በተደጋጋሚ የገዛ ሀገር ወገናቸውን ሲወጉ የነበሩትንና ሳይሳካላቸው የቀሩትን የአባቶቻቸውን ጅኒና ዓላማ ወርሰው ዛሬም በገዛ ሀገራቸው ሕዝባቸውና ማንነታቸው ላይ በጠላትነት የተሰለፉ፣ ሀገሪቱንና ሕዝቧን ለዓረብ በባርነት አሳልፎ ለመስጠት የሚመኙ የሚቋምጡ፣ ከቋንቋ አነጋገር እስከ አለባበሳቸው ድረስ ሁለመናቸውን ዓረባዊ ያደረጉ፣ የራሳቸውን ማንነት በመጣል በዐረባዊ ስሜትና ማንነት የተዋጡ፣ እራሳቸውን የሸጡ፣ ስለራሳቸው ማንነት ቅንጣት እንኳን ታክል ዴንታና ቁጭት የሌላቸው ደናቁርት አሸባሪና የዓረብ ባንዳ የእስልምና ተከታዮች ጨርሶ የሉም እያልኩ አይደለም፡፡ እነኝህን ግን ወያኔ በአጋርነት ስለሚመለከታቸው በመሀከላቸው ሌላ የጥቅም ግጭት ካላጋጠመ በስተቀር በእነኝህ ላይ ይዘምታል ብየ አላስብም፡፡ እንደ እነዚህ ዓይነት የእስልምና ተከታይ ወገኖች አሁን በሀገራችን እንዳሉ የተረዳሁት በተለያየ አጋጣሚ ከአንዳንድ የእስልምና ተከታዮች ጋር ስነጋገር እንዲህ ዓይነት ሰዎች ከመሀላቸው መኖራቸውን ካረጋገጡልኝ በኋላ ነው፡፡ ስለ አለባበስ ስናነሣ ተወቃሾቹ ወንዶቹ ብቻ አይደሉም ሴቶችም ቢሆን ለምሳሌ ሂጃቡን የሀገራቸውን ነጠላ ቀሚሳቸውምን የሐበሻ ቀሚስ ማድረግ ሲችሉ የሚጠቀሙት ግን ከላይ እስከ ታች የዓረብን ልብስ ነው፡፡ ይሄ ብቻውን አሸባሪነት ነው ለማለት ሳይሆን ለማንነታቸው ያላቸው ግምትና ጥላቻ ይሄንን ያህል ከሆነ ወደዚያ በሚወስደው መንገድ ላይ ናቸው ማለት ነውና ቢጠነቀቁ መልካም ነው ለማለት ነው፡፡ ቁርአናቸውም ከዕይታ መከለል መሸፈን ያለባቸውን የሰውነት አካል እንዲሸፍኑ እንዲከልሉ አዘዘ እንጅ እስልምናን ሲቀበሉ ከልብሳቸው እስከ ቋንቋቸው ሁለነገራቸውን የዓረብ እንዲያደርጉ ጨርሶ አላዘዘም፡፡
በሌላ በኩል በጣም የሚገርመው አቶ መለስ ካላቸው የነጭ አምላኪነት የተነሣ ይሄንን የፀረ አሸባሪነት ሕግ ከምዕራባዊያን ስለቀዱ ብቻ ሕጉ ዒላማው ካደረጋቸው አካላትና ከታሰበለት ዓላማ ውጭ እያደረጉ እናዳሉት በንጹሐን ዜጎች ላይ ሁሉ ተፈጻሚ የማድረግ መብትን ጨምሮ የሚያሰጣቸው እንደሆነ ማመናቸው ነው፡፡
ሸገር ሬዲዮ (ነጋሪተ-ወግ) ላይ በነበረው ውይይት ደግሞ ጎልቶ ያየሁት ስሕተት ያንን ጥቃት በጋዜጠኞቹ ላይ የፈጸሙ ሰዎችን ድርጊት በመደገፍ ሐሳብ የሰነዘሩትን የደጋፊዎቻቸውን ሐሳብ በመጋራት ጥያቄውን ደግመው ማንሣታቸው ነበር፡፡ ይህ ስሕተት መሆኑን ደውየ በዝርዝር ነግሬያቸው ስለነበር ጉዳዩን በሳምንቱ ካነሣሁላቸው ጥያቄዎች ጋራ እንደገና የተወያዩበት ቢሆንም አሁንም ሊሰልቁትና ስሕተቱን ሊያርሙት አልቻሉም ነበር፡፡ ታዋቂ የሕግ ባለሙያ የተባሉ ሰው ስሕተቱን መጋራታቸው ገረመኝ እንጅ በእርግጥ ይሄ ጥያቄ ወይም ቅሬታ በአውሮፓና በሌላ አካቢዎችም ተነሥቷል፡፡ ይሄንን ነጥብና ተያይዘው ያሉ ጉዳዮችን እናያለን፡፡ በቅድሚያ ግን የሐሳብ ነጻነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ጥቂት ማየቱ ጠቃሚና መሠረታዊም ነውና እሱን ዕንይ፡-
ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማለት ምን ማለት ነው?
በርካታ መንግሥታት በተለይም የምዕራቡ ዓለም መንግሥታት ከዘመነ አብርሆት (Enlightenment) በኋላ ለሐሳብ ነጻነት ልዩ ክብርና ግምት እንሰጣለን በማለት “በእርግጥ ግን ይህ መብት ሙሉ ለሙሉ በተግባር ላይ ውሏል? ተተርጉሟል?” የሚለው ሌላ ጉዳይ ሆኖ በየ ሕገ መንግሥቶቻቸው ድንጋጌዎች እውቅና ሰጥተውታል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ የዚህን ጉዳይ ሥያሜው ቃሉ እንደሚገልጸው ሁሉ የትኛውም ሀገር መንግሥት ፍጹማዊ የሆነ የሐሳብ ነጻነት የሰጠ ወይም ለመስጠት የሞከረ አለ ብየ አላምንም፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች መስጠት የቻሉት ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ገደብ ያለው ነው፡፡ ፍጹማዊ የሆነ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት መስጠት የሚችል መንግሥትና ሕዝብ ይኖራል ብሎ ማሰብ ፈጽሞ የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ለምን? የሚለውን ወደ በኋላ እናየዋለን፡፡
ቀደም ባለው ግንዛቤ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ማለት የሞራል (የቅስም) ድንጋጌዎችን ካለመጋፋት ካለመጣስ በመለስ በሚል መረዳት ነበር የነበረው ግንዛቤ፡፡ ከጥቂት ዐሥርት ዓመታት ወዲህ ግን ነገሩን ቃል በቃል እንደመተርጎም ይወስዳቸውና ማንም ሰው በጭንቅላቱ የሚታሰበውን ነገር ሁሉ የመግለጽ የማውጣት የማሰማት የማጋራት ነጻነት ማለት እየሆነ አድርገው ነው በሚያሳዩን ነገሮች ሊያስረዱን የሚፈልጉት፡፡ ችግሩ የሚፈጠረው እዚህ ላይ ነው፡፡ የሚታሰበው ነገር ሁሉ የሌሎቹን ጥቅም የጎዳ ወይም የሚጎዳ ከሆነስ? ሲባል እሱም ቢሆን መብቱ መሰጠት መከበር አለበት የሚሉ አሉ፡፡ አይ! ብለው ደግሞ በተለያዩ ዝርዝር ሕጎች ገደብ ለማበጀት የሚሞክሩም አሉ፡፡ “የሌሎችን ጥቅሞች የሚጎዳ ቢሆንም እንኳ ነገር ግን አግባብነት ባለው መንገድ” የሚሉት እራሳቸውም እንዲህ ይበሉ እንጅ በሐሳብ ነጻነት የማይነካ የማይገሰስ የማይደፈር የማይታለፍ ብዙ ነገሮች አሏቸው ለምሳሌ ብሔራዊ ጥቅም፣ የሀገርና የሕዝብ ደኅንነት ጉዳይ ወዘተ. ከዚህ መግባባት በመለስ ግን በነጻነት መናገር ሐሳብን መግለጽ ይቻላል ይላሉ፡፡ ይህም ሆኖ ግን ሕጎቻቸው ጥርት ያሉና የማያወዛግቡ ማድረግ ካለመቻላቸው የተነሣ በየጊዜው እንደተወዛገቡ ነው ሲወዛገቡም እንደሚኖሩ ግምቴ ነው፡፡
ከላይ “ፍጹማዊ የሆነ የሐሳብ ነጻነት መስጠት ማስተናገድ ፈጽሞ የሚቻል ጉዳይ አይመስለኝም” ማለቴ በሰው ጭንቅላት የሚታሰብ በገር ሁሉ ትክክልና አልሚ ገንቢ ስላልሆነ ነው፡፡ እያንዳንዳችን የየራሳችንን ሐሳብ በቅድመ ምርመራ (ሳንሱር) ክፍል እያሳለፍን ስለምንናገር እንጅ በጭንቅላታችን የታሰበንን የመጣውን ሁሉ ነገር እናውራው እንናገረው ብንል ማንም ከማንም ጋር መኖር ካለመቻሉም በላይ ጤነኞች መሆናችን እራሱ አጠያያቂ መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ ጭንቅላትን እግዚአበሔር ሲፈጥረው ነጻ አድርጎ ስለፈጠረው የሚሆነውንም የማይሆነውንም፣ አደገኛውንም ደኅናውንም፣ አጥፊውንም አልሚውንም ሀሉንም አሳቢ ነው፡፡ አእምሮ ከዚህ ተፈጥሮው የተነሣ እንኳንና በንቃት ላይ ሆነን እንቅልፍ ላይ ሆነንም እንኳን ቢሆን ይሄንን ሥራውን አይተውም ዕረፍት የለውምና፡፡ አእምሮ ተፈጥሮው ስለሆነ እንደዚህ ያስባልና በሚል የሚያስበው ሁሉ በነጻነት ይዘርገፍ ማለት ግን ፍጹም ጤነኝነት አይመስለኝም፡፡ አእምሮውን የሳተ (እብድ) እንኳን የሚናገረውን ይመርጣል፡፡ ፍጹማዊ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ማለት አሁን ባለው አረዳድ የሰዎችን የእድሜ የአቅም የክብር ወዘተ. ልዩነትና ደረጃ ፈጽሞ ግንዛቤ ውስጥ ባላስገባ መልኩ መቸም የትም እንደ እብድ “ምን እንደ እብድ ከዚያ በከፋ እንጅ” በጎውንም ክፉውንም ነውሩንም ደንቡንም ጸያፉንም ምኑንም ሁሉንም መቀበጣጠር መዘርገፍ ማለት ነው፡፡
በመሆኑም ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነትን ፍጹማዊ ማድረግ ወይም ገደብ አልባ ማድረግ ፈጽሞ ሊተገበር የማይችልና በእርግጠኝነትም ሁሉ ሰው እንዲሆን የማይፈልገው ሊፈጽመውም የማይችለው መብት ወይም ጉዳይ ነው ብየ ነው የማምነው፡፡ ነገር ግን እንደማኅበራዊ ፍጡርነታችን ተስማምተንና ማኅበራዊ ጤናችን ተጠብቆ በጋራ እንድንኖር የሚያስችሉንን የጋራ ጥቅሞቻችን ለአደጋ በማይዳርጉ ጉዳዮች ላይ ወይም ከዚህ አጥር ወይም መግባባት በመለስ እንደ ብሔራዊ ጥቅም ወይም ሀገር፣ የኅብረተሰብ ወይም የሕዝብ ሰብአዊና የዜግነት መብቶችን ወዘተ. ያሉ የጋራ ጥቅሞቻችንን የተሻለ የበለጠ የተመቸ ለማድረግ በሚል ማዕቀፍ ወይም የሐሳብ መሠረትነት እንዳስፈለገ መናገር ቢቻል ግን ጠቃሚ ገንቢ እንጂ አንድም ችግር ያለበት መስሎ አይሰማኝም ይሄ የግድ መደረግም አለበት፡፡ አንዳንድ ነገር ባይጠፋም የምዕራቡ ዓለም ከዚህ ደረጃ ላይ የደረሰ ይመስለኛል ችግሩ ግን በዚህ በሐሳብ ነጻነት ዙሪያ የጠራ ግንዛቤ እና መግባባት ካለመያዛቸው የተነሣ በሐሳብ ነጻነት ስም እየተፈጸመ ያለው ነገር የተዘበራረቀ፣ ገደብና ልክ አለው ሲባል ከገደብ ያለፈ እየሆነ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ይቻላል ሲባል የማይቻል እየሆነ ምስቅልቅል ውስጥ እንደተመሰቃቀሉ አሉ ይኖራሉም፡፡
ይሄን ካልኩ በኋላ ወደ ቻርሊ ሄብዶ ጋዜጣ ጉዳይ ሳልፍ ቻርሊሂብዶ ጋዜጣ ማለት ለኔ የሚታየኝ በአጋንንት የሚታተም ጋዜጣ እንደሆነ ነው፡፡ ሰዎቹ ባላቸው ፀረ ሃይማኖት አቋም በመመሥረት ትክክለኛ ባልሆነና ሳይገባቸው የአቅም ውስንነት በተጫነው ግንዛቤ ያች እነሱን የመሰለቻቸው ነገር ብቻ ያለቀለትና ትክክለኛ ሐሳብ እንደሆነ በመቁጠር ፈጣሪን ክርስቶስን እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምንም በሁሉም ጸያፍ በሆነ መንገድ እንደሚገልጹት ሊሆን ይችላል ተብሎ ፈጽሞ በማይገመትና ሊሆን ይችላል ለማለት ምንም ዓይነት ፍንጭ በሌለበት ሁኔታ ሰይጣናዊ ልቦናቸው እንዳሳሰባቸው በድንቁርና ድፍረት የማይሳለቁበት ነገር የለም፡፡ ጋዜጣው ይሄንን ሲያደርግ ክርስቲያን ነኝ ከሚለው ወገን ተቃውሞ ቢያጋጥመውም ከወቀሳ ያለፈ ነገር ግን አልደረሰበትም፡፡ ይሄ የሆነው ክርስቲያን ነኝ ከሚለው ወገን ለሃይማኖቱ ተቆርቋሪ ስለጠፋ ይሁን ወይም ደግሞ ክርስቲያን ነኝ የሚለው ክፍል ክርስትና የፍቅር ምላሽን ማለትም “ልቡና ስጣቸው ከዚህ ክፉ መንፈስ ገላግላቸው” ብሎ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እነሱ ከመጸለይ ከመጾም ከመስገድ ያለፈ የኃይል ምላሽን መውሰድ እንደማይፈቀድ ኃጢአትም እንደሆነ ስለሚያውቅ በየትኛው ምክንያት እንደሆነ ለኔ ግልጽ አልሆነልኝም፡፡
ጋዜጣው የመንግሥት መሪዎችንም አንዱ በሌላው ላይ የሐሳብ ልዕልና ካገኘ የሐሳብ የበላይነት ያለው መሪ ሌላኛውን ሲያወስበው (ግብረሰዶማዊ ግንኙነት ሲፈጽምበት) የሚያሳይ የስላቅ (የካርቱን) ሥዕል ሥለው ያትማሉ፡፡ ይሄ ድርጊታቸው እንዴት ብሎ ሐሳብን ከመግለጽ ነጻነት ጋር እንደሚገኛኝና ዓላማውም ምን እንደሆነ አይገባኝም፡፡ ጥቅምና ዓላማ አለው ከተባለ ሰዎቹ ያለባቸውን የዋልጌነት አመል ማርካት ብቻ ነው የሚሆነው፡፡
ይሄን ካልኩ በኋላ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነትን ከዚህ ጋዜጣ ጋር አያይዘን ስናነሣ “ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ተፈጥሯዊ መብት ነው ያለገደብ መተግበር አለበት” ካልን የቻርሊ ሂብዶ ጋዜጣ ሥራ ሌላም ከዚህ የከፋ ቢመጣ ትክክል ነው መብታቸውም ነው ባይ ነኝ፡፡ ልብ በሉ ጠቃሚ ነው አይደለም ያልኩት፡፡ በሌላ አነጋገር ለእብደት ሥራ ሕጋዊነት መስጠት ማለት ነው፡፡ ጋዜጣው ይሄንን ሥራውን ሲሠራ ፍጹማዊ በሆነ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ሳይሆን ከላይ በገለጽኳቸው አመክንዮዎች ሳቢያ የሰው ልጆችን ይጠቅማል ብሎ በሚያስባቸው ነገሮች ዙሪያ ለሰው ልጆች ጥቅም ሲል ሥራውን የሚሠራው ገደብ ባለው ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ነው ከተባለ ግን እየሠራ ያለው ሥራ ፍጹም የተሳሳተ ነው፡፡ ምክንያቱም ሥራዎቹ የሰዎችን የእድሜ የአቅም የክብር ወዘተ. ልዩነትና ደረጃ ፈጽሞ ግንዛቤ ውስጥ ባላስገባ መልኩ መቸም የትም ከእብድና የከፋ ነውረኛ ባለጌ በባሰ መልኩ በነውር በጸያፍ ገለጻዎች የተሞሉ ናቸውና፡፡
ይሄንን ስል ግን በብዙዎች ዘንድ እየተተቸባቸው የሰማሁት ለምሳሌ ጳጳሳቶቻቸውን ኮንዶም አስይዘው ማውጣታቸው ትክክል አይደለም እያልኩ አይደለም፡፡ ምክንያቱም በሀገራቸው እንከተለዋለን ከሚሉት ሃይማኖታዊ ሕግና አስተምህሮ ውጭ የሚወሰልቱና ከዚያም አልፈው ግብረሰዶማዊያን የሆኑ ጳጳሳት በስፋት እንዳሉ ይታወቃልና ከዚህ ሁሉም አልፈው የግብረሰዶም ግንኙነትን ሃይማኖታችን በሚሉት ድርጅት ውስጥ ሕጋዊ አድርገው የተቀበሉና ለመቀበልብ እየሠሩ ያሉ የእምነታቸው መሪዎች አሉና፡፡ በመሆኑም በሌለ ሰብእናቸው ያልሆኑትን ነን እያሉ ሕዝብን እንዳያጭበረብሩ ሃይማኖታችን ከሚሉት አስተምህሮ በተቃራኒ ያለ ማንነታቸውን ከማጋለጥና መረጃን ለሕዝብ ከማድረስ፣ የእምነት ተቋሙ ተጠያቂነት እንዲሰማው ከማድረግ አንጻር እንዲህ ሆነው መውጣታቸው ትክክል ነው፡፡ ድርጊቱ ይቀፋል ወይ? ከተባለ አዎ ይቀፋል የሚያየውንም የሚያንጽ አይመስለኝም፡፡ ክፉ ክፉ ነገርን እያሳዩና እያስነበቡ ማነጽ አይቻልምና፡፡ የሰው ሕሊና በተፈጥሮው የሚታነጸው መልካም መልካም ነገሮችን ስንመግበው ነውና፡፡ ነገር ግን ጋዜጣው እንደ ጋዜጣ መረጃ ማቀበል ማስገንዘብ መጠቆም ማሳወቅ ሥራውና ዓላማውም ነውና ይሄንን ማድረጉ የግድ ይሆናል፡፡ ይሄንን ስል ግን ግብረሰ ሰዶማዊ ግንኙነት ሲፈጽሙ በስላቅ (በካርቱን) ሥዕል ማሳየታቸው ግን ጸያፍና ትክክል ያልሆነ ድርጊት ነው፡፡
በመሆኑም ጋዜጣው እውነት የሆኑ ወይም እውነት የሚመስሉ፣ የታዩ ወይም የተሰሙ፣ የተደረጉ ወይም ሊደረጉ እንደሚችሉ በተጨባጭ የሚጠረጠሩ ጉዳዮችን በስላቅ (በካርቱን) ሥዕሎች የሞራል (የቅስም) ድንጋጌዎችን ግንዛቤ ውስጥ ባስገባ መልኩ ቢገልጽ ወይም ቢጽፍ ችግር ነው ሊባል የሚገባ አይመስለኝም፡፡ እያልኩ ያለሁት እነዚያ የሚገልጻቸው ነገሮች የሰው ልጅን የሚጎዳ እንዳይሆን በእጅጉ ሊጠነቀቅ እንደሚገባው ግልጽ መሆን ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያበረታታ የሚደግፍ አንዳች ነገር ቢያደርጉ ፍጹም ስሕተትና ልንታገሰው የሚገባ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ይህና መሰል ጸያፍና የጥፋት ድርጊቶች የሰው ልጆችን ከምድረ ገጽ የሚያጠፋ እንጅ የሚያለማ የሚያንጽ ስላልሆነ፡፡
አሁን የቻርሊ ሂብዶ ጋዜጣን ለዚያ አደጋ የዳረገውን ድርጊት ዕንይ፡- ጋዜጣውን ለዚያ አደጋ የዳረገው በመሐመድ (በእስላሞች ነቢይ) ላይ በስላቅ ሥዕል በመሳለቁ ነበር፡፡ እኔ ክርስቲያን ነኝ እንደ ክርስቲያንነቴም የመሐመድን ነቢይነት ስለማላምንበትና ስለማልቀበል ነው “ነቢዩ መሐመድ” ብየ ያልጠራሁት፡፡ ነቢዩ መሐመድ ባለማለቴ እስላሞች የሚቀየሙኝ አይመስለኝም፡፡ እነሱ ምንም እንኳን ቁርአናቸው ያንን ቢያረጋግጥም ቅሉ የዓለም መድኃኒት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ጌትነቱን ስለማያምኑበት “ጌታ ኢየሱስ” ብለው እንደማይጠሩት ሁሉ ማለት ነው፡፡
ጋዜጣው በመሐመድ ላይ ሲሳለቅ ይህ የመጀመሪያው አይደለም ለበርካታ ጊዜ ተሳልቋል፡፡ አንዳንዶቹ ግን ጠንከር ያሉ ተቺና ምሁራዊ ምላሽ የሚፈልጉ ናቸው፡፡ የጋዜጣው አዘጋጆች እንደተመኙት ያገኙት ምሁራዊ ምላሽ ሳይሆን የኃይል ጥቃት ሆነ እንጅ፡፡ ያልተመለከታቹህት ልትኖሩ ትችላላቹህና አንዱን የስላቅ ሥዕል ለመግለጽ ልሞክር፡- መሐመድ ተገቢውን የእስልምና አለባበስ (በእርግጥ ይህ አለባበስ ዓረቦች እስልምናን ከመቀበላቸው በፊትም የነበረ አለባበሳቸው ነውና የእስልምና አለባበስ ማለቱ ትክክል አይደለም በተለምዶ ስለሚባል ነውና በዚያ መልክ ውሰዱት) እንደለበሰ ቁጭ ብሎ በአንድ ትልቅ ድስት ውስጥ ወጥ ይሠራል፡፡ ድስቱ ላይ እስልምና የሚል ጽሑፍ አለ፡፡ መሐመድ ከጀርባው ካለው መደርደሪያ ላይ በብልቃጥ በብልቃጥ ሆነው የተቀመጡትን ድስቱ ላይ የሚጨመሩ ቅመሞችን እያነሣ ድስቱ ውስጥ ይጨምራል፡፡ በእነዚህ ብልቃጦች ላይ ጋዜጣው ፀረ ሰብአዊ መብቶችና የሞራል (የቅስም) ድንጋጌዎች ናቸው የሚላቸውን የተለያዩ የእስልምና አስተምህሮዎች ተጽፎባቸዋል፡፡ መጨረሻ ላይ እስልምናን የፈጠረው መሐመድ ነው ይላል፡፡
እኔ ይሄ የስላቅ ሥዕል ሐሳብን በነጻነት ከመግለጽ መብት አንጻር ነው የማየው፡፡ ዓሣሣሉ አብዛኞቹ ላይ እንደሚታየው ምንም የሚቀፍ ነገር የለበትም፡፡ በዚህ ሥዕልና መልእክቱ የተከፉ ወገኖች ካሉ ሊያደርጉ ይገባቸው የነበረው እውነታው ጋዜጣው በስላቅ ከገለጸው የተለየ ከሆነ ጋዜጣው በትችት መልክ ያቀረበው ነገር እንደተረዳው አለመሆኑንና እውነታው ከዚያ የተለየ መሆኑን ማረጋገጥ ነበር የሚጠበቅባቸው “ሐሳብን በሐሳብ” እንዲሉ፡፡ እውነትን ለያዘ አካል ሐሳብን በሐሳብ ለመሞገት ሞግቶም ለመርታት የሚቸግረው ነገር አይኖርምና፡፡ ይሄንን ከማድረግም አይቆጠብም፡፡ ለታማሁት ለተተቸሁበት ለተጠየኩት ነገር መልስ ካጣሁ ግን እዚህ ላይ ችግር አለ፡፡ የጋዜጣው አዘጋጆች ሞጋችና አሳማኝ ምላሽ ቢቀርብላቸው እንደሰው እንደ ተቋምም ልዕልና ባለው ሐሳብ የመረታት የመሸነፍ ሞያዊና የሞራል (የቅስም) ግዴታ አለባቸውና በዚህ መልኩ እነሱን ከዚህ ከሚያስከፋው ድርጊታቸው መግታት በተቻለ ነበር፡፡
ይሄንን እርምጃ በጋዜጣው ሠራተኞች ላይ የወሰዱ (በአሸባሪነት የተፈረጁ አልቃይዳ አይ.ኤስ አይ.ኤስና የመሳሰሉት) አካላት ሌላው ሊረዱት የሚገባቸው ቁምነገር ቢኖር እነሱ ያገኙትን ክርስቲያን “አንተ እስላም አይደለህም እስልምናን ትተቻለህ ትጠላለህ ስለም አልሰልምም ካልክ ግን አንገትህን እንቆርጣለን” እያሉ አልሰልምም ያለውን የስንቱን አንገት መቁረጣቸውንና እየቆረጡም እንደሆነ መዘንጋት የለባቸውም፡፡ የዚህ ተስተካካይ ምላሽ የነበረው ክርስቲያኑ ወገንም እስላሞችን ሲያገኝ አስገድዶ ክርስቲያን ማድረግ እንቢ ሲሉ ደግሞ መቅላት ነበር፡፡ ይሄንን ተግባር ግን ክርስትና የሰዎችን የመሰላቸውን የማመን የመከተል ተፈጥሯዊ ነጻነትና ሰብአዊ መብቶችን ያከበረ የጠበቀ በመሆኑ ይሄንን ተግባር አይፈቅደውም ስለሆነም አይደረግም፡፡ ይሄንን ዓይነት ግፍ በክርስቲያኖች ላይ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እየፈጸሙ ያሉ አካላት እንዲህ ዓይነቱን እርምጃ መውሰድን “በእርግጥ መብት አይደለም ነገር ግን እንደ መብት ይቆጠር ካሉ ግን” ይሄ መብት የእነሱ ብቻ እንደሆነ እንዴት ያስባሉ? ይህ እነሱ እየወሰዱት ያለው የሰውን ልጅ ከፈጣሪ የተሰጠውን ተፈጥሯዊ መብት ማለትም “መስሎ በታየው ባመነው የመኖር” መብቱን በመንፈግና የመሰለውን ያመነውን በኃይል የማስለወጥ የኃይል የማስገደድ እርምጃ በእነሱ ላይ ቢፈጸም እንደ ሚያስብና የ21ኛው መቶ ክ/ዘመን ሰው ምን ይሰማቸዋል? ይሄንን ማድረግ አስፈላጊና ተገቢም ቢሆን ኖሮማ ፈጣሪ እራሱ የሰው ልጅን ጭንቅላት ተመሳሳይ ነገር ብቻ እንዲያስብ አድርጎ ይፈጥረው አልነበረም ወይ? ፈጣሪ የሰጣቸውን ነጻነት ሰው መንጠቅ መከልከል ይችላል ወይ? መሞከሩስ አግባብ ነው ወይ?
እነዚህ በአሸባሪነት የተፈረጁ አካላት ግን እንኳንና እነሱ እንደሚያደርጉት ተመሳሳይ እርምጃ ወይም አጸፋ ተወስዶባቸው ይቅርና ግልጽ እንዲሆኑ በሚፈለጉ ጉዳዮች ላይ ሐሳቦች ጥያቄዎች ትችቶች ሲነሡባቸው እንኳን የወሰዱትና የሚወስዱት እርምጃ በተደጋጋሚ በተለያየ ቦታ እንደሚታየው ነው፡፡ እነሱ ለሌላው ወገን ከቶውንም ሊያከብሩለት የማይሞክሩትን ጨርሶ የማይሹትን መብት ሌላው ግን ለእነሱ እንዲያከብርላቸው እንዲጠብቅላቸው ይፈልጋሉ፡፡ በእነሱ እንዲፈጸም የማይፈልጉትን ነገር እነሱ ግን በሌላው ላይ እንዳሻቸው ይፈጽማሉ? ይሄ በጣም አስቂኝና ከዚህ ዘመን ሰው የማይጠበቅ ልክ የለሽ ጅልነት ኢፍትሐዊነት አለማስተዋልም ነው፡፡ ስለእነዚህ አካላት ሳስብ ሌላው የሚገርመኝ ነገር የአስተሳሰባቸውን ከንቱነት ብላሽነት ዘመን ሽሮ በዐይናቸው በብረቱ ዕያሳያቸውም እንኳን የእነሱ አስተሳሰብ ግን አሁንም ስድስተኛው መቶ ክፍለዘመን ላይ ቀጥ ብሎ ያለ ነው፡፡ ለምሳሌ እነሱ ለእስልምና ተከታዮች የምዕራባዊያን ሥልጣኔ የኪነብጀታ (የቴክኖሎጂ) ውጤት ሀራም (ውጉዝ ወይም እርም) ነው እያሉ በእሱ መጠቀምን እየከለከሉ እነሱ እራሳቸው ግን ከጦር መሣሪያ እስከ ተሽከርካሪ ከስልክ (መናግር) እስከ መቀምር (ኮምፒውተር) ድረስ ሁሉንም ለሽብር ተግባሮቻቸውና ለሌሎች ተግባሮቻቸው ይጠቀማሉ፡፡ እኔ ምን ዓይነት ሰዎች እንደሆኑ ሁሉ ይገርሙኛል፡፡ ሕይወታቸው እንደዚህ ባለ አለመብሰላቸውን ጥሬነታቸውን አላስተዋይነታቸውን ቁልጭ አድርጎ በሚያሳይ እርስ በእርሱ በሚጋጭ ሐሳብና ድርጊት የተሞላ ነው፡፡
ወደ ፈረንሳዩ አደጋ ስንመለስ የፈረንሳይ ፖሊስ ከዚህ አደጋ በኋላ ይሄንን የአሸባሪዎችን የኃይል እርምጃ ደግፈው በተለያየ መንገድ ድጋፋቸውን በገለጹ 54 ሰዎች ላይ በወሰዳቸው የእስር እርምጃዎች እስሩ ከተፈጸመባቸውና ከተለያዩ አካላት የተነሣ ቅሬታና ተቃውሞ አለ እሱ ምንድን ነው? “ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ከተባለ ለምን ለአንድ ወገን ብቻ ይሆናል? ለቻርሊ ሂብዶ ሲሆን ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለእኛ ሲሆን ወንጀል ለምን ይሆናል? እኛ ያልነው “ጎሽ ደግ አደረጉ እንደነዚህ ዓይነቶችን ባለጌ ስዶች ውርጋጦች ማለት ነው እንጅ” ነው ያልነው ይሄ ደግሞ ሐሳብ ነው ሐሳባችንን ነው የገለጽነው ሌላ ያደረግነው ነገር የለም፡፡ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት መብት ካለ ይሄ እንደወንጀል ተቆጥሮብን ሊያስጠይቀን አይገባም” የሚል ነው፡፡
እንዲህ የሚሉ ወገኖች የሳቱት ያልተረዱት ነገር ቢኖር ሐሳብ መግለጽ ማለት ምን ማለት መሆኑንና የኃይል እርምጃም ምን ማለት መሆኑን ነው፡፡ እንደኔ እምነት የቻርሊ ሂብዶ ጋዜጣ የጠቀስኩት ሥራው ወንጀል የማይሆንበት ምክንያት የመሐመድን አስተምህሮ ሲያጤኑት ከሰብአዊ መብቶችና ከሞራል (ከቅስም) ድንጋጌዎች አንጻር ለሰው ልጆች ጎጅ እንደሆነ አምነዋል ተገንዝበዋል ይሄንን ግንዛቤያቸውንም በገለጹት መንገድ አቅርበዋል፡፡ ይሄ ሐሳብ ነው የሚመለሰውም በሐሳብ ነው፡፡ የጦርነት አዋጅ አላወጁም፡፡ “አይ! እንደሱ እኮ አይደለም ተሳስታቹሀል እውነቱ እንደዚህ ነው” ብሎ የማስረዳት የመሞገት የማረም የማስተማር ፋንታው የተተችው ወገን ነው፡፡ ጋዜጣው ይሄንን ሐሳቡን በሌሎች ላይ በኃይል ለመጫን በግድ ለማሳመን ሞክሮ ቢሆን ኖሮ ይሄ ሐሳብን ከመግለጽ አልፏልና ወንጀል በሆነ ነበር፡፡ እነሱ ግን ይሄንን አላደረጉም በመሆኑም ጉዳዩ ሐሳብ ላይ ወመያየት መሞጋገት ላይ ብቻ ያተኮረ በመሆኑ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ ጉዳይ ብቻ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
በጋዜጣው ሠራተኞች ላይ የተወሰደውን የኃይል እርምጃ በመደገፍ ሐሳባቸውን የገለጹት ሰዎች ድርጊታቸው ወንጀል እንጅ ከሐሳብ ነጻነት ጋር ሊገናኝ የማይችልበት ምክንያት ሰዎችን ባለቸው ተፈጥሯዊ ሰብአዊና ሕገ መንግሥታዊ መብት መሠረት በነጻ የማሰብና ሐሳባቸውንም የመግለጽ መስሎ የታያቸውን የማመን መብታቸውን በኃይል ለመገደብ ለማፈን ለመንፈግ ለመግታት ለማስቆም ዓላማ ያደረገና የሚሞክር እነሱ የሚያስቡት ብቻ ሌላው ሳይመረምር ሳይጠይቅ በኃይል ተገዶ እውነት ነው ትክክል ነው ብሎ እንዲያምን እንዲያስብ ለማድረግ የሚጥር፣ ስለሆነ ይሄንን የሚሉ ሰዎች ምቹ አጋጣሚና ሁኔታ ቢያገኙ ተመሳሳይ ድርጊት ከመፈጸም ወደ ኋላ የማይሉ እንደሆኑ ስለሚያረዳግጥ የአሸባሪዎቹን ድርጊት በመደገፍ ሐሳብ የሰጡ ግለሰቦች ይሄ ድርጊታቸው ወንጀል ይሆናል ማለት ነው፡፡ ሐሳብን በሐሳብነቱ ለምን ተገለጸ አይገለጽ ብለው እየተቃወሙ ይሄ ሐሳብ ነው ስለዚህ መብታችን ነው ሊሉ አይችሉምና፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዥታ ያለባቹህ ወገኖች ብዥታቹህን ምን ያህል እንዳጠራሁላቹህ አላውቅም ለማንኛውም ይሄው ነው፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
YISHAK says
betam yemigermew kezih tsihufih yeteredahut neger binor,betam chifin ena fitsum le islam yalehin tilacha new. minalbat yihenin tsihuf bitsif bitsif tikuret sibe tawaki ehonalehu bileh asibeh kehone endime fitsum tesastehal. ENE BEBEKULE YE HAIL ERMIJAN ALDEGIFIM, GIN YEMENAGER MEBT ESKEMIN DIRES YEMILEW LITAY YEMITASEB GUDAY NEW. YESEWUN EMNET MANKUWASHESH KEMANIGNAWUM MORAL EKUAYA TEKEBAYINET YELEWUM. ESTI AND TIYAKE LITEYIKIH ATO AMSALU; ENGLAND WUST YEMENAGER MEBTIHIN TETEKMEH SILE NIGISTWA MELKAM YALHONE NEGER METSAF ENDEMATICHIL TAWKEWALEH? EBAKIH KE ADLIWO ENA KE CHIFININET NETSA YEHONE TSIHUF LEMAKREB MOKIR. ATSE YOHANIS DEMO ETHIOPIAN MUSLIMOCH LAY YADEREGEWUN NEGER BENEKA B”IRIH BEMEKETILEW TSIHUFIH ENDEMITAKERBILIN TESFA ADERGALEW
ibnu says
አንተም ብሎ ተንታኝ ይሄንን ዝባዝንኬህን እዛው በሃማኖትህ ጋዜጣ ላይ ዘክዝክ። ቁምነገር አለው ብዬ ጊዜዬን ማባከኔን ቆጨኝ፡፡ ከሂብዶ ቻርሊ ጋዜጠኞች አትሻልም
selam says
The brits love and respect their queen, but who said they can’t mock her? Listen to what Ben Elton said about her.
selam says
It is morally wrong to insult someone’s religion. But it isn’t a crime and people have the right to spit out what is in their head. For me, it doesn’t make a difference since God is the ultimate judge and can defend himself. He doesn’t need the machete of these bearded heartless bastards.
bint islam says
አንተ ቆሻሻ ካፊር ክፍት አፍ ኢስላምን ጠላህ አልጠላህ ምን ታመጣለህ ኢስላም ማንም ምንም ማሸነፍ አይችልም ማነው ደግሞ ቴክኖሎጂ ላይ ብዙ አስተዋፆ ያረጉት ሙስሊሞች መሆናቸውን አታቅም ካሜራ ዜሮን አልጀብራ ሆስፒታል ወዘተ ማን ጀመረው አንተ የአፄው ዘመን ጅል ጭንቅላትህ ራሱ የሀይለስላሴ ዘምን አስተሳሰብ ነው ሳይንስን የጣለው ክርስትናን ነው ከፀሀይ በፊት ብርሀን ነበር ሀሀሀሀሀሀሀ ባለጌ ልጅ እናቱን ያሰድባል ነው ግን ካልነገሩህ አይገባህም ከሰፈርህ ካንተ ጭንቅላት ውጣ ብለህ እስብ ክርስቲያን እዚህ ምድር ላይ የለም ከመጽሐፍ ቅዱስ የበለጠ ገዳይ መፅሀፍ የለም ኢስላም ይሞታል እንጂ ክብሩን አያስነካም ብንሞትም የጀነተረ ነን በንገለም ገዳዮቻችንን ነው እኛ ታቦት አናወጣላቸውም እሺ ሌሎች ክርስቲያኖች ስል ትቸዋል መናገሬን ምክኒያቱም አይበቃህምና አሸባሪ ብለው ሲዘምቱ ኢስላምን አስተዋወቁልን አውሮፓ አሜሪካ በኢስላም እየተጥለቀቀ ነው ማን ማን ሰለመ ብልህ ጠይቅ እንዳንተ ደንቆሮ እንኳን የሆኑ ሰዎች አደሉም የአለም ምርጥ ምሁሮች እንጂ እና ልታጠቁን በሞከራችሁ ቁጥር እንፈርጥማን በእጅ ያየዝነው ሀይማኖታችንን በክራንች እንይዘዋል ገላችሁ ሞክራችሁን ነበር ከድሮ ከአፄ ጀምሮ እየው አለን ከናንተ በዝተን ከናንተ የተሻለ አቅም እውቀት ሀብት ኖሮን አየህ ያለፈብንን መከራ ግን በልጠናችሁያል መቸም የአፄው ዘመን ያላጠፋን ከአሁን በላይ ንቅንቅ የሚያረገን ነገር እንደሌለ በቂ ምስክር ነው እና አፉህን በከፈትክ ቁጥር የሙስሊሙን ሀይል እያጠነከርክ እንደምትሄድ ጥር ጥር የለውም አውሮ ፓስ ቤተክርስቲያን ለመስጊድ መሸጡን ሰምተሀል ጎግል ላይ መፃፍ ብቸሰ ሳይሆን ማንብብ ልመድ ከክርስትና ወደ ኢስላም የተዘዋወርኩ ምርጥ ኢትዮጲያዊ ነኝ ከድንቁርና ወደ ብርሀን አንብብ አንብብ መል ።ላንተ ሳይሆን ላንባቢ ነው አንተ የቀባሀው ጥላሸት ለማራገፍ ያክል
bint islam says
አንገትክ ላይ ያሰርከው ክር ምን እንደሆነ ታቃለህ አህመድ ኢብን አልጋዚ ነው ያሰረልህ በሰአቱ የነበሩ ክርስቲያኖች ስልሙ ኢስላም ተቀበሉ ሲባሉ እንቢ ሲሉ በቃ አላምንም ያለ አንገቱ ላይ ክር ይሰር ተብሎ መታሰር ተጀመረ አንተ ጅል ደግሞ የእምነት መሰረት መስሎህ አንገትክ ላይ አሰርከው ማታበ ማለት ያልተቦተ ማለት ነው ማተብ አላችሁ ቀኙ አህመድ ነው ያሰረልህ
AKMEL says
BATATANKAK YASHLAHAL MAHAYAB!!!!!!