ዶ/ር ዳንኤል ተፈራና ዶ/ር ፀሀይ ለኢሳት ጋዜጠኛ ለአቶ ፋሲል የኔ ዓለም ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ለሰጧቸው መልሶች የቀረበ አስተያየት ከፈቃዱ በቀለ መግቢያ በቅርቡ ሁለት በአሜሪካን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኢኮኖሚስቶችን የኢሳት የቴሊቪዝን ጋዜጠኛ የሆነው አቶ ፋሲል የኔ ዓለም ኢትዮጵያ ከውጭ የምትበደረው ብድር መጠን እያደገ ስለመምጣቱና ስለኢኮኖሚው አጠቃላይ ሁኔታ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ በመጋበዝ በመሰላቸውና በሚታያቸው፣ እንዲሁም ከተማሩት የኢኮኖሚ ትምህርት አንፃርና ከዕምነታቸው በመነሳት ለተደረገላቸው ጥያቄ አስተያየት ለመስጠት ሞክረዋል። ፕሮፊሰር ዳንኤል ዕዳንንም ሆነ፣ የሚሰሩትን ፕሮጅክቶች ወደ ፊት ሊገኝ ከሚችለው ውጤትና አትኩሮ ቅድሚያ መስጠት የሚገባውን፣ ነገር ግን የሚታለፈው አንገብጋቤ ጥያቄ ሊያስከትል የሚችለውን አሉታዊ ውጤት በንጽጽር … [Read more...] about የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያደገ ነው ወይስ የኋሊት ጉዞ እያሳየ ነው?
Opinions
የኔ ሃሳብ
ሰይፈ ነበልባል ክርስትና እና ጋዜጠኝነት ሲወሀዱ ወደ ሰይፈ ነበልባልነት ይለወጣሉ
መግቢያ በዚህ ርእስ ይህችን ጦማር እንዳዘጋጅ የተገደድኩበት ምክንያት “የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ በመሆኔ ለቤተ ክርስቲያኔ እቆማለሁ፤ ጋዜጠኛ በመሆኔም ለህዝቤ እውነቱን አስጨብጣለሁ” እያሉ፤ ነገር ግን እንደሚሉት ሆነው የማይገኙ እንደ አቶ አዲሱ አበበ የመሳሰሉ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኞች በመካከላችን ስለተከሰቱ ነው። አቶ አዲሱ እንደሚሉት የክርስትና ሕይወትና የጋዜጠኝነት ሙያ የተዋሀዳቸው ቢሆኑ ኖሮ እጅግ በታደልን ነበር። እንደነ ተመስገን ደሳለኝ፣ እስክንድር ነጋና ርዕዮት ዓለሙን የመሳሰሉ ጋዜጠኞች ታስረው በመሰቃየት ላይ ሳሉ፤ በቂ ችሎታና ሙያ ሳይኖራቸው አቅጣጫ እየቀያየሩ በሚፈጽሙት ተደጋጋሚ በደል በአካባቢያችን ያሉትን አብያተ ቤተ ክርስቲያናት ባልወረሩና ወያኔ በሚቆጣጠራቸው መገናኛ አውታሮች ተሰልፈው የኢትዮጵያን ህዝብ የሚያፈኑ ጋዜጠኞች ቁጥራቸው ባልበዛ … [Read more...] about ሰይፈ ነበልባል ክርስትና እና ጋዜጠኝነት ሲወሀዱ ወደ ሰይፈ ነበልባልነት ይለወጣሉ
አፈ ጉባኤ አባ ዱላ …ግን ለምን አልሰሙንም?
* የኮንትራት ሰራተኛዋ አይነ ብርሃኗን ማጣትና የስም የለሿ ሟች እህት መጨረሻ ! * ሰሚ እስኪገኝ እንጮሃለን! ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓም ሰኞ በማለዳው ያገኘኋቸው ሁለት መረጃዎች የወጡት በሁለቱ አንጋፋ የሳውዲ ጋዜጦች በአረብ ኒውስ Arab News እና በሳውዲ ጋዜት Saudi Gazette ነው። በአንዱን አይቸ ቢከፋኝ፣ መፍትሔ ላይገኝ ይህን መርዶ ከንፈር ለማመስመጠጥ ብቻ መረጃ ብየ ልለጥፍ ይሆን? እያልኩ ከራሴ ጋር ሙግት ገጥሜ ነፍሴን ሳስጨንቀት በሌላኛው ጋዜጣ የወጣውን ሌላ መረጃ አንድ ወዳጀ በጓዳው የመልዕክት መሰረጫ እንደኔው ማልዶ ያጋጠመውን የወገን መከራ አደረሰኝ ። ሁለቱንም አሳዛኝ መረጃዎች ተመለከትኳቸው፣ ያማል ብቻ ተብሎ የሚታለፍ አይደለም! መዲና የተባለች እህት በጽዳት ላይ እያለች አይኗ ላይ ተፈናጥሮ የገባው መርዝ የአይን ብርሃኗን አሳጥቷት በከፋ … [Read more...] about አፈ ጉባኤ አባ ዱላ …ግን ለምን አልሰሙንም?
ጥቂቶችሊመነደጉ፤ብዙዎችአሽቆልቁለዋል!!!
“የራበው ሥራ ፈልጐ ማግኘት የማይችልና ልጆቹን ለማስተማር አቅም ያጣ ሰው ከባርነት ነፃ ነው ማለት አይቻልም፡፡” የሚለው የአሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ሊንደን ቢ. ጆንሰን ንግግር እውነትነት አሁን አሁን በጆሮዬ መደወሉ ራሴን እያስገረመኝ መጥቷል፡፡ የዛሬ አምስትና ስድስት ዓመት ገደማ ሰዎች፤ ስለኑሮ ውድነት ሲጽፍ ብዙዎቻችን እያነበብን ፈገግ ከማለት በቀር ብዙ ልባችን አልተነካም ነበር፡፡ ምናልባትም በጣም አልፎ አልፎ ከምናነባቸው መጣጥፎች ይልቅ መንግስት ስለ ልማት የሚነፋው ጥሩንባ አደናቁሮን ይሆናል፡፡ አሁን አሁን የመንግሥት መዝገበ ቃላት “ልማት” የሚለው ትርጓሜ ግራ እያጋባን መጥቶ ጭራሽ ወደ ብስጭት የተመነዘረብን ብዙ ነን ብዬ አስባለሁ፡፡ መንግስት ልማት የሚለው ከእኛ አፍ “ቫት” እያለ የሚነጥቃትን ገንዘብ ሰብስቦ ለሌቦች ካጠገበ በኋላ፣ በፍርፋሪዋ የሚሠራትን መንገድና ጤና ጣቢያ … [Read more...] about ጥቂቶችሊመነደጉ፤ብዙዎችአሽቆልቁለዋል!!!
የጠለምትና የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የጎንደሬዎች . . .
በጠለምት፣ በበየዳ፣ በጃናሞራ፣ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በአርማጨኾ ነዋሪው እየተባረረ፣ ሀብቱ እየተዘረፈ፣ ያንገራገረው እየተገደለ፤ ሰው በምሬትና በሰቀቀን ኑሮውን መግፋት አቅቶት አጣብቂኝ ላይ ገብቷል። ትናንት ቡያ ነበር ክልሉ። ትናንት በሀከር ነበር ክልሉ። ቀጥሎ ራስ ደጀንን ወደነሱ አካተቱት። ጠገዴን ጠቀለሉት። ገፍተው ስሜን አውራጃን በሙሉ ጠቀለሉ። ወገራ አውራጃን ሽራርፈው ወሰዱና ጎንደር አውራጃን ተጠጉ። አሁን ዘለው የጎንደር ከተማውን ገነት ተራራ፤ የትግራይ መሬት እያሉ ለትግራይ ልጆቻቸው እያሰተማሩ ነው። ጎንደር ከምድረ ገጽ እንድትጠፋ እየተገፋ ነው። ይህ የመኖርና ያለመኖር፤ ውሎ የማደርና በወጡበት የመቅረት፤ ተገፍቶ ተገፍቶ የገደል ጫፍ ላይ የተንጠለጠለ ሕይወት ሕዝቡን ሰቅዞ ይዞታል። ይህ ጉዳይ የጎንደሬዎች ብቻ ጉዳይ አይደለም። አዎ! በዋግም ተመሳሳይ ተግባር እየተፈጸመ … [Read more...] about የጠለምትና የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የጎንደሬዎች . . .
እውነትን ፈልጓት፤ ታገኟታላችሁም!
የተከበራችሁና የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ሆይ፤ እትብታችሁ ስለተቀበረባት የምትወዷት ሀገራችሁ ኢትዮጵያም ሆነ ስለ ሃይማኖታችሁና ስለ ቤተ ክርስስቲያናችሁ ስታስቡ ሁሌም አስተዋይ፤ አርቆ አሳቢ፤ ብልህና ንቁ ሁኑ እንጂ ባማሩ ቃላት በመሳብም ሆነ ልብሰ ተክህኖና ግርማ ሞገስን በማየት የተንኮልና የሃሰት ሰለባ እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ። “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ፤ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች፤ ተኩላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነብቢያት ተጠንቀቁ” ተብሏልና (የማቴ. ወ. ም. ፯ ቁጥር ፩፭) በለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ሁሉም የሚያውቀው ነው፤ መንስኤው ማን እና ምንድን ነው ከተባለ ደግሞ እውነተኛው መልስ ሥጋዊ ጥቅምን በማስቀደም ለሥልጣን፤ ለንዋይና ለዝና ያደሩ ጥቂት ካህናት የፈጠሩት ችግር መሆኑ የተረጋገጠ … [Read more...] about እውነትን ፈልጓት፤ ታገኟታላችሁም!
ወ/ሮ ገነት ዘውዴ እውን ነገሩ እንዲያ ነውን?
ወ/ሮ ገነት ዘውዴ (ዮዲት ጉዲት) ይቅርታ መሳደቤ አይደለም ሰው የሚያውቃቸው በዚህ ስም በመሆኑና የሚኮሩበትም በመሆኑ እንጅ፡፡ እናም ወ/ሮ ገነት በቅርቡ በሸገር የኤፍ ኤም ሬዲዮ (ነጋሪተ- ወግ) “የሸገር እንግዳ” በተባለው ዝግጅት እንግዳ ሆነው አዘጋጇ ጋዜጠኛ ወ/ሮ መዓዛ ሦስት ቅዳሜ አዋይተዋቸው ነበር፡፡ በዚያ ጨዋታቸው ወ/ሮ ገነት ከተናገሩት ብዙው ነገር ከንክኖኝ ከጊዜ አንጻር ባይሆን በጥቂቶቹ ላይ ጥቂት ነገር ለማለት አስቤ እየጫጫርኩ እያለሁ እንዲያውም በወ/ሮዋ በሐሰት ስማቸው ከጠፋ ወገኖችና ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው አንደኛው በጥሩ ምሁራዊ ተዋስኦ የተዋዛ ምላሽ ሰጥተው አሻሩልኝ፡፡ ይሁንና ወ/ሮዋ የተናገሩት አጉል ነገር በርካታ በመሆኑ ሁሉንም ለመዳሰስ ከጊዜና ከቦታ አንጻር የማይቻል በመሆኑ ዶክተሩ ለሁሉም አጉል ነገር መልስ ሳይሰጡ ቀሩ፡፡ እኔም እንማማርባቸው ዘንድ … [Read more...] about ወ/ሮ ገነት ዘውዴ እውን ነገሩ እንዲያ ነውን?
የወያኔ ከንቱ ፈሊጥ! “ጅብን ሲወጉ በአሕያ ተጠግቶ ነው”
ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጅብ እንደሆነ አድርጎ ያስባል፡፡ ይታያቹህ! ከየትኛውም ሀገር ሕዝብ በተለየ መልኩ ታጋሹን፣ ቅኑን፣ ቅዱሱን፣ ስስት ስግብግብነት የሌለበትን፣ አስተዋዩን፣ እሱ እየተቸገረ እየተራበ እነሱን ያጠገበውን ያደለበውን ቸር ምስኪን ሕዝብ ጅብ ነው ብሎ ማሰቡ አይደንቃቹህም? ምን ይደረግ ድንቁርና ተጭኗቸው ይሄን አስከፊ ድንቁርናቸውን ገንዘባችን ብለው አጥብቀው ይዘውት በየት በኩል አስተውለው ይሄንን ማንነቱን ይረዱለት? እናም ጅብ ነው ብለው በማሰባቸው አሕያ እየፈለጉ እሱን በመጠጋት በእሱ በመከለል ሲዎጉት ቆይተዋ ሰሞኑንም በሰፊው ይሄንን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ወያኔ በዚህ በያዝነው በታሕሳስ ወር 2007ዓ.ም. ከታዋቂ ሰዎችና “ከከያኔያን (Artists)” ለ ሕዝብ ለሕዝብ አቅንኦተ ግንኙነት (Public diplomacy) እና ሕዝብን ለመደለል ተልእኮ በቻለው መጠን እሽ … [Read more...] about የወያኔ ከንቱ ፈሊጥ! “ጅብን ሲወጉ በአሕያ ተጠግቶ ነው”
“መንግሥት ከደላሎች ጋር አይደራደርም” ኃይለማርያም
ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት መንግስት በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ በኢትዮጵያውያን ላይ የተከሰተውን ስቃይ እና በደል ተከትሎ ለስራ ወደ አረብ ሀገራት በሚደረግ ጉዞ ላይ እገዳ መጣሉ ይታወሳል። በተለይ ያለአንዳች የህይወት ዋስትና ወደ ተጠቀሱት ሃገራት በኮንትራት የሚሄድ ሰራተኞችን ከገጠር እስከ ከተማ በዘለቀ ድለላ ህጋዊ ፈቃድ አግኝተው ዜጎችን እያጋዙ የነበሩ የአሰሪ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤት ቢሮዎች መዘጋታቸው አይዘነጋም። ዘግይቶም ቢሆን መንግስት በወቅቱ ወሰደ በተባለው እርምጃ የአያሌ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ከአስከፊው የአረብ ዓለም ስቃይ መታደግ ቢችልም ከግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቻችንን ህይወት ስላለበት ሁኔታ የተጠቀሱትን የኤጀንሲ ባለቤቶች በህግ ለመሞገት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ቴድሮስ አድሃኖም የገቡትን ቃል … [Read more...] about “መንግሥት ከደላሎች ጋር አይደራደርም” ኃይለማርያም
“የድሆች መናጢነት የሚመጣው ሰነፍ ስለሆኑ አይደለም” አዳም ረታ
". . . ፖለቲካ ለሀገር ማሰብ ነው፡፡ ፖለቲካ መታደል ከተጨመረበት ለአገርና ውስጥዋ ለሚኖረው ለሕዝብ መልካም ለመስራት መጣር ነው፡፡ ከራስ በላይ ነፋስ በሚባለው ነገር አላምንም፡፡ ከራስ በላይ ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ሰፈር፣ ወረዳ፣ አውራጃ ክፍለሀገርና አገር አሉ፡፡ የቻለበትም አህጉርና አለምን በልቦናው ይከታል፡፡ "የአገራችን አንድ የሚታይ ማንም የሚያወራበት ፀባይዋ በደሃና በተራራ የተሞላች መሆኗ ነው፡፡ አንድ ሰው በሀገሩ ደሃ መሆን የለበትም:: ቢያንስ መሰረታዊ ፍላጎቶቹና መብቶቹ መጠበቅ አለባቸው፡፡ የድሆች መናጢነት የሚመጣው ሰነፍ ስለሆኑ አይደለም፡፡ የለፉበት ውጤት በጥቂት ማንአለብኝ ባዮች ስለሚዘረፍ ነው፡፡ "እነዚህም ዘራፊዎች ዝርፊያቸውን ያለሀሳብ ለማካሄድ ማስፈራራትንና ራሳቸው ያወጡትን ህግ ይጠቀማሉ፡፡ ድሆች ወይም ጭቁኖች መብታቸውን ለማስከበር የሚነሱት ከወደቁበት … [Read more...] about “የድሆች መናጢነት የሚመጣው ሰነፍ ስለሆኑ አይደለም” አዳም ረታ










