• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አፈ ጉባኤ አባ ዱላ …ግን ለምን አልሰሙንም?

January 5, 2015 08:22 am by Editor Leave a Comment

* የኮንትራት ሰራተኛዋ አይነ ብርሃኗን ማጣትና የስም የለሿ ሟች እህት መጨረሻ   !
*  ሰሚ እስኪገኝ እንጮሃለን!

ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓም ሰኞ በማለዳው ያገኘኋቸው ሁለት መረጃዎች የወጡት በሁለቱ አንጋፋ የሳውዲ ጋዜጦች በአረብ ኒውስ Arab News እና በሳውዲ ጋዜት Saudi Gazette ነው። በአንዱን አይቸ ቢከፋኝ፣  መፍትሔ ላይገኝ ይህን መርዶ ከንፈር ለማመስመጠጥ  ብቻ መረጃ ብየ ልለጥፍ ይሆን?  እያልኩ ከራሴ ጋር ሙግት ገጥሜ ነፍሴን ሳስጨንቀት በሌላኛው ጋዜጣ የወጣውን ሌላ መረጃ አንድ ወዳጀ በጓዳው የመልዕክት መሰረጫ እንደኔው ማልዶ ያጋጠመውን የወገን መከራ አደረሰኝ ። ሁለቱንም አሳዛኝ መረጃዎች ተመለከትኳቸው፣ ያማል ብቻ ተብሎ የሚታለፍ አይደለም!

መዲና የተባለች እህት በጽዳት ላይ እያለች አይኗ ላይ ተፈናጥሮ የገባው መርዝ የአይን ብርሃኗን አሳጥቷት በከፋ አደጋ ላይ ወድቃለች፣ ሴት አሰሪዋ መዲናን ለማሳከም ደፋ ቀና ቢሉም ለህክምና የተጠየቀው ወጭ ለአቅማ ቸው በላይ በመሆኑ ነገሮች የተወሳሰቡ መሆኑ ተጠቁሟል መረጃው የሳውዲ ጋዜጥ ነው….! መረጃውን በፊስ ቡክ ካሰራጨሁት በኋላ ለማጣራት ሞክሬ እንደተረዳሁት ስትታመም ስትጎዳ ሊያሳክሙ፣ በአሰሪና ሰራተኛ ህግ ከለላ በጅዳ ቆንስል የመጣችው እህት ጉዳዩዋን የሚከታተልላት ቀርቶ የመዲናን ለዚህ አደጋ መጋለጥ የሚያውቅ የመንግስት ተወካይ የለም!

ሌላዋ እህት የሆነችውን አረብ ኒውስ በአንዲት የጋዜጣው ጠርዝ ካይ እንዲህ ሲል በአጭር አረፍተ ነገር አስፍሮታል “ኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኛ አል ጀውፍ በተባለ የሃገሪቱ ግዛት በአሰሪዋ ቤት ራሷን በመስቀል ራሷን በራሷ ገድላለች” ይላል  … መረጃው የአረብ ኒውስ ነው …. ! ስለዚህች እህትም ቢሆን በአቅራቢያው ያለው የሪያድ ኢንባሲ መረጃ የለውም፣ መረጃውን ቀድመው ይወቁት አልልም፣ ቢያንስ ከእኛ እኩል በየጋዜጣው የሚወጣውን እንኳ አለማወቃቸውን እኩለ ቀን ላይ ወደ ሪያድ ኢንባሲ ደውየ ለማወቅ ችያለሁ! ሁሉም ያማል!

ከሳምንት በፊት እኔ ከምኖርበት ጅዳ ከተማ ልጆችን ወደ ት/ቤት በማeth woman hangedድረስ ላይ እያለች በተፈጠረ መኪና ግጭት የያዘቻቸውን ህጻናት አትርጋ እሷ መስዋዕትነት የከፈለችን ትጉህ እህት ያዩ አረቦች ተገርመው በምትሰራበት ቢተ ሲጫወቱ የሰማች እህት ታሩኩን በደፈናው ብትነግረኝም ዝርዝር መረጃ አለነበረውምና በዝምታ አልፊው ነበር።  ዛሬ እኩለቀን ላይ ከላይ የጻፍኩትን የሁለቱን ጋዜጦች መረጃ የተመለከተ ወንድም አንዲህ የሚል መልዕክት ደረሰኝ ይህን “ሄሎ ነብዩ ሰላም ነህ ነብዩ በአንድ ጉዳይ ፈልጌህ ነበር። ስልክህን  ልትልክልኝ በትህትና እጠይቃለህ በጣም የማከብሪህ  እና ማደንቅህ … ” ይላል፣ አመስግኘ ስልኬን ሰጠሁት፣ ምሽቱን ደውሎልኝ ከባድ የመኪና አደጋ ደርሶባት ራሷን የማታውቀውን እህት ጉዳይ አንስቶ በዝርዝር አጫወተኝ ፣ ይህች እህት ያን ሰሞን የአሰሪዎቿን ልጆች አትርፋ መኪናው የዳጣት ለመሆኗ ብዙ መሄድ አላስፈለገኝ። ከወዳጀ ጋር ይህችን ምንዱብ የአልጋ ቁራኛ ለማየት ቀጠሮ ብንይዝም አልስቻለኝምና ወደ ተባለው ሆስፒታል ሄጀ የማትሰማ የማትናገረውን እህት አይቻት ሰላሜን በገዛ እጀ አጥቸ ተመለስኩ!

ማለዳ በሰማሁት ባነበብኩት ምሽት  ላይ ባየሁት ውስጤን  ጥሩ ስሜት አልተሰማው ምና ከንዴት በሽታ ውጭ ምንም ላላመጣ በስጨት አልኩ  ፣ ዝም ማለት ግን አልለመደ ብኝምና እናገረዋለሁ!  … ደግሞ ብስጭቴን ስጽፈው ይቀለኛልና መቸክቸክ ያዝኩ …

ሰሚ ያጣ ጩኸት …

መረጃ ማቀበሉ በህግ አስፈጻሚ አካላት በኩል ውጤት አለማምጣቱን አሰላስየው የአፈ ጉባኤ አባ ዱላን ሰሞነኛ የሳውዲ ጉብኝትና መፍትሔ እንደማያመጡ እያወቀ እንደኔው ባለመተንፈሱ የተበሳጨውን የጅዳና የሪያድ ነዋሪ አስታወስኩ! ከምንሰማ ከምናየው የዜጎች አበሳ ጋር ሰሚና ሁነኛ የመብት አስከባሪ የበላይና የበታች ሹማምንት አጥተን በስቃይ ላይ ለመሆናችን ምስክሮች የምናቀርባቸው መረጃዎች ናቸው። በሳውዲ 350 ሽህ የኮንትራት ሰራተኛ እንዳለ በመንግስት ተረጋግጦ እየተነገረን ፣ የተበተኑት መብት ሳይጠበቅ አዳዲስ መከረኞችን አምጥተን ልንደፋ  ዝግጅቱ የተጠናቀቀ ይመስላል ።  እኛ ይህ ነገር በተቀናጀ ጥናት፣ በበቂ ዝግጅት ፣ በበሳል አመራር  ካልተመራ ሌላ አደጋ አለው እያልን ነው።  መከራ ብሶቱን ፣ አሰከፊ ምስሉን እያሳየን “አረ ያገር ያለህ!”  እያልን እጮህን ነው! ሰሚ ህግ አውጭና ህግ አስፈጻሚ ግን የለም! ሰሚ ያጣው ጩኸታችን ሰሚ እስኪገኝ ግን ዝም አንልም፣ እንጮሃለን!

ግን ለምን አልሰሙንም?

የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በሳውዲ አረቢያ ጉብኝት አድርገዋል። የሰራተኛ ሚኒስትር አድል ፈቂን ጨምሮ በርካታ የመንግስ ሃላፊዎች አግኝተው እኔና መሰሎቸ ሌት ተቀን ስለምንናገረው በቂ ዝግጅት ሳይደረግ ስለተላኩ የእኛ ዜጎች ለአባ ዱላ ነግረውልናል።  አፈ ጉባኤ አባ ዱላ በኮንትራት ሰራተኞች ጉዳይ ከሳውዲዎችና መብታችን ካላስጠበቁልን የሪያድ ኢንባሲና የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች፣ በሃላፊዎች  ከተመረጡ  የሪያድ የጅዳ “የተከበሩ ምርጥ” ዜጎች፣  ከኢህአዴግ የድርጅትና ከተለያዩ ጥሪ ከተደረገላቸው የ ማህበር አባላት ጋር  መክረዋል።

eth woman in saudiአፈ ጉባኤውና ልዑካኑ በአንጻሩ በማህበራዊ ኑሮው ፣ በመብት ጥበቃው ፣ በኮንትራት ሰራተ ኞች የለት ተለት የመረረ እውነት ተመልካችና ገፋች የሆነውን ነዋሪ ጠርተው ቀርቶ ሊያይ ሊያነጋገራቸው ሄዶ በሆድ አደር አጋፋሪዎች ተከልክሏል። ነዋሪ ዜጋው እንዲህ ተገፍቶ  የሃገሪቱ የበላይ ህግ አውጭ የሆነው የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሳያዩትና ሳያነጋግሩት ሔደዋል ። የአፈ ጉባኤ አባ ዱላን ማግኘትና ብሶቱን ማሰማት የፈለገው ነዋሪ ጉጉት ምን ይሆን ? ብየ ጠያይቄም ነበር ። ያገኘሁት የምላሽ እውነታ ነዋሪው ማቆሚያ ስለጠፋው የኮንትራት ሰራተኞች አበሳ ለመናገር መተንፈስ እንጅ መጓጓቱ መፍትሔ ከባለስልጣኑ ይገኛል ብሎ አለመሆኑን ተረድቻለሁ።  እውነት ነው አባቶች  “ድሃ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ… ” እንደሚሉት ሆነና  ነዋሪው ሆየ ብሶቱን ማሰማቱ ህመሙን ያቀልለት መስሎታል  ! ፕሬዚደንትና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ እስካሁን ሳውዲ ለመጡት ከፍተኛ ባለስልጣኖች የአለ የሌለ የተባለውን ጥያቄ አቅርቦ ምልስ እንዳልተገኘ አሳምሮ የሚያውቀው ነዋሪ በዚህና በዚያ ተስፋ  ቆርጧል… ግን ተስፋ ቆርጦም መናገር መተንፈስ ይፈልጋል!

የአስፈሪው ቀን መቅረብ  ምልክቶች …

በሳውዲ መንግስት የተዘጋው የኮንትራት ሰራተኞች ይጀመራል ተብሎ በዋና ዋና ደላሎች ወሬው ከተነዛ ወዲህ በመንግስት በኩል የረቂቅ ደንቡ መውጣቱን ሰምተናል ። ጸድቆ ጉዞው ሊጀመር ተቃረበ ሲሉን ደግሞ አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ ከሳውዲ ባለስልጣነናት ጋር ስለአዲሱ ረቂቅ ህግ መምከራቸውን ሰምተናል! ከሳውዲዎች ጋር   ስለመከሩ ስለዘከሩበት ህግ በሳውዲ ነዋሪ ከሆነው ኢትዮጵያዊ ጋር አለመምከራቸው ግን ታላቅ ታሪካዊ ስህተት ነው ባይ ብዙ ነን!

ነዋሪው ብሶቱን ለመናገርም ሆነ ከመምከር መወያየቱ የሚገኝ ፋይዳ አለ ብሎ ሳይሆን እንደ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ ባለ ስልጣን ለምን ዜጎችን እኩል አይተው አላነጋገሩንም ? ሃሳባችን ለምን አያደምጡትም? ለምን አልሰሙንም?  ለምን የታመቀ ችግራችን ቢያንስ አላዳመጡንም? በኦሮሞ ልማት የተመረጡ አባላት ሰብስበው ለቴሌቶን ብር ከመሰብሰብ በስደት ስላለው ስለከፋው ዜጋ መምከር ለምን አለቀደመም? አፈ ጉባኤ አባ ዱላ  እንደ ኢትዮጵያ የተወካዮች ምክር ቤት ሳውዲን እየጎበኙ ለምን ወደ ዘውግ አድልተው ወርደው ጊዜን ማባከብ አስፈለጋቸው?

በጉብኝታቸው ሁሉንም ባንድ የኢትዮጵያ ባንዴራ ማሰተባሰበርና ማመካከር ሲገባ ቅድሚያ ለኦሮሞ ማህበር ከዚያን የኢህአዴግ አደረጃጀት እያሉ ስደተኛውን ከመበታተንና በማዕከላዊነት ያልተማከለ ፣በዘውግ አስተዳደር የከረረ  አካሄድን እንድናይ ለምን አደረጉ?   አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ከምንም በላይ በሁለት ሃገራት የሰራተኛ ውል ማዕቀፍ ውጭ ወደ ሳውዲ የመጡና እንደ ጨው የተበተኑትን የኦሮሞ ፣የአማራ፣ የትግራይ ፣ የጉራጌ እና የቀሩትን ብሔረሰቦች የአብራክ ክፋዮች ሁኔታ ለመረዳት የጉዳዩ ባለቤትና መከራውን ገፋች ነዋሪውን አላነጋገሩትም። መፍትሔው መብታችን ማስከበር ቀርቶ ዜጎች ያለንበትን ሁኔታ መሸፋፈን ከሚቀናቸው ከቆንስልና ከኢንባሲ ተወካዮች እስከ ድርጅትና ማህበራት ያሉትን “ምርጥ” የተባሉ ነዋሪዎች ማነጋገር መፍትሔ ነውን ?  አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ነዋሪውን በነቂስ ጠርተው በመሰብሰብ ለምን ስለመጡበት ጉዳይ ማብራሪያም ሆነ የነዋሪውን ሃሳብ አልወሰዱም ?  የሚሉ በርካታ ውሃ የሚያነሱ እውነት ያላቸው ጥያቄዎችን ነዋሪው ሲያሰማ አድምጫለሁ! እኔም ሆንኩ ነዋሪው በእስካሁኑ ሂደት ያየነው ለውጥ ኑሮ ባያስደስተንም ባለስልጣን በመጣ በሄደ ቁጥር ድመጻችን ይሰማ ዘንድ እንሻለን፣ የለውጥ ተስፋ ባይታየንም የወገናችን አበሳ ግን መናገር አናቆምም! አዎ! ሰሚ እስክናገኝ እንጮሃለን!

እስኪ ቸር ያሰማን!

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule