ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት መንግስት በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ በኢትዮጵያውያን ላይ የተከሰተውን ስቃይ እና በደል ተከትሎ ለስራ ወደ አረብ ሀገራት በሚደረግ ጉዞ ላይ እገዳ መጣሉ ይታወሳል። በተለይ ያለአንዳች የህይወት ዋስትና ወደ ተጠቀሱት ሃገራት በኮንትራት የሚሄድ ሰራተኞችን ከገጠር እስከ ከተማ በዘለቀ ድለላ ህጋዊ ፈቃድ አግኝተው ዜጎችን እያጋዙ የነበሩ የአሰሪ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤት ቢሮዎች መዘጋታቸው አይዘነጋም። ዘግይቶም ቢሆን መንግስት በወቅቱ ወሰደ በተባለው እርምጃ የአያሌ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ከአስከፊው የአረብ ዓለም ስቃይ መታደግ ቢችልም ከግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቻችንን ህይወት ስላለበት ሁኔታ የተጠቀሱትን የኤጀንሲ ባለቤቶች በህግ ለመሞገት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ቴድሮስ አድሃኖም የገቡትን ቃል … [Read more...] about “መንግሥት ከደላሎች ጋር አይደራደርም” ኃይለማርያም
Opinions
የኔ ሃሳብ
“የድሆች መናጢነት የሚመጣው ሰነፍ ስለሆኑ አይደለም” አዳም ረታ
". . . ፖለቲካ ለሀገር ማሰብ ነው፡፡ ፖለቲካ መታደል ከተጨመረበት ለአገርና ውስጥዋ ለሚኖረው ለሕዝብ መልካም ለመስራት መጣር ነው፡፡ ከራስ በላይ ነፋስ በሚባለው ነገር አላምንም፡፡ ከራስ በላይ ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ሰፈር፣ ወረዳ፣ አውራጃ ክፍለሀገርና አገር አሉ፡፡ የቻለበትም አህጉርና አለምን በልቦናው ይከታል፡፡ "የአገራችን አንድ የሚታይ ማንም የሚያወራበት ፀባይዋ በደሃና በተራራ የተሞላች መሆኗ ነው፡፡ አንድ ሰው በሀገሩ ደሃ መሆን የለበትም:: ቢያንስ መሰረታዊ ፍላጎቶቹና መብቶቹ መጠበቅ አለባቸው፡፡ የድሆች መናጢነት የሚመጣው ሰነፍ ስለሆኑ አይደለም፡፡ የለፉበት ውጤት በጥቂት ማንአለብኝ ባዮች ስለሚዘረፍ ነው፡፡ "እነዚህም ዘራፊዎች ዝርፊያቸውን ያለሀሳብ ለማካሄድ ማስፈራራትንና ራሳቸው ያወጡትን ህግ ይጠቀማሉ፡፡ ድሆች ወይም ጭቁኖች መብታቸውን ለማስከበር የሚነሱት ከወደቁበት … [Read more...] about “የድሆች መናጢነት የሚመጣው ሰነፍ ስለሆኑ አይደለም” አዳም ረታ
ከሁለት ሳምንት እንግልት በኋላ ቴዲ አፍሮ ወደ አውሮፓ በረረ
ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከሁለት ሳምንት እንግልት በኋላ ዛሬ ምሽት ከቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ተነስቶ ወደ ኦስሎ ኖርዌይ ጉዞውን ጀምሯል። ኢትዮጵያዊው የፖፕ እና ሬጌ ሚዚቃ አቀንቃኝ በአውሮፓ ከተሞች የሙዚቃ ዝግጅቱን ለማድረግ ከአዲስ አበባ ተነስቶ የነበረው በወሩ መጀመርያ ላይ ነበር። ባለፈው ሃሙስ ዲሴምበር 4፣ 2014 ቦሌ አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ጣብያ እንደደረሰ የደህንነት አካላት እንዳገቱት እና ፓስፖርቱንም እንደቀሙበት በልዩ ልዩ የዜና ምንጮች መዘገቡ ይታወሳል። አርቲስቱ ለምን ወደ ውጭ እንዳይወጣ እንደታገደና ፓስፖርቱም ለምን እንደተቀማ እስካሁን በይፋ የተነገረ ነገር የለም። አንዳንድ የዜና ምንጮች ጉዳዩን ቀረጥ ካለመክፈል ክስ ጋር አያይዘው አቅርበውታል። ይህ መላ ምት ፍጹም ስህተት ነው። ምክንያቱም ድምጻዊው በጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ … [Read more...] about ከሁለት ሳምንት እንግልት በኋላ ቴዲ አፍሮ ወደ አውሮፓ በረረ
ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስትር!
ብዙ ተብሏል። እኔም አንድ ነገር ልጨምርና ልገላገለው። “የጊዮርጊስን መገበሪያ የበላ ሲለፈልፍ ይኖራል” ነው የሚባለው? ተናግሮ ከሚያናግር ይሰውራችሁ! ውሀን ምን ነበር የሚያናግረው? ድንጋይ! የሰውም ድንጋይ እራስ አለ! ይቅርታ አንጀቴ አርሮ ነው! ሦስት መንግስታትን የማየት ዕድል አጋጥሞኛል። ተወልጄ፣ አድጌ፣ ተምሬ ለዩኒበርሲቲ የበቃኹት በንጉሠ ነገሥቱ ዘመነ መንግሥት ነበር። ዕውነቱን እንናገር ከተባለ፣ ንጉሡ ሲናገሩም ሆነ ሲራመዱ፣ የርዕሰ ብሔርነት ግርማ ሞገስ ነበራቸው። “በንጉሥ መገዛቱ ጊዜ ያለፈበት፣ ያረጀ ያፈጀ፣ ገበሬውን በገባርነት ጠፍንጎ የያዘ፣ አገሪቱ በዕድገት ወደፊት እንዳትራመድ ያገዳት፣ ኋላ ቀር የፊውዳል ሥርዓት ነውና ወደሶሻሊዝም እንለውጣት” የሚሉ ድምጾች ከተማረው ክፍል አካባቢ እያየሉ መጡና እኛንም እንደጎርፍ ይዘውን ነጎዱ። ተከተልናቸው። “መሬት ለአራሹ … [Read more...] about ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስትር!
የኦባንግ ጉዞና ለዲያስፖራው ፖለቲካ ያለው አስተዋጽኦ
በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ በአቶ ኦባንግ ሜቶ በተጠራው ስብስባ ላይ የመገኘት እድል አጋጥሞኝ ነበር:: በስብሰባው ላይ ከተለያዩ የአለም ክፍሎችና ከአሜሪካ ግዛቶች የተሰባሰቡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል:: የስብሰባው መሪ ሀሳብ “ስለ እያንዳንዳችን ከመናገር እያንዳንዳችን እንነጋገር” የሚል ድፍረትን፣ ግልፅነትን፣ መከባበርን፣ መነጋገር መቻልን ሃላፊነት በተሞላበት ስሜት ይቀርቡ በነበሩት አስተያየቶች የሚያረጋግጡ ከመሆናቸውም በላይ የተለየዩ የፖለቲካ አመለካከት፣ እምነት እንዲሁም የተለየዩ ብሄረሰቦች ዉሁድ ኢትዮጵያውያን በአንድ ጠረጴዛ ዙርያ ተቀምጠው ያነሱዋቸው የነበሩት ሃሳቦች በጥንታዊት ኢትዮጵያና በአዲሲቱ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ገመድ ጉተታ ግራ ለተጋቡ ጥሩ አስተማሪ መድረክ ነበር:: ኢትዮጵያ የምትባል ጥንታዊት ሃገርን የሲኦል መገለጫ አድርገው ለሚስሉዋት የህወሃት … [Read more...] about የኦባንግ ጉዞና ለዲያስፖራው ፖለቲካ ያለው አስተዋጽኦ
ግፍና አፈና ዐመጽን ይወልዳሉ!
የዐመጸኛ አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው (መ. ምሳሌ ም. 22፣ ቁ. 14) ሰብአዊ መበቶችን በመጣስ፣ ግፍ በመፈጸምና አፈናን በማጠናከር እደሜ የሚሸምት የአገዛዝ ሥርዓት የእያንዳንዱን ሰው መንፈሳዊና አካላዉ ጥንካሬ የማዳከም፣ ቅስምን የመስበርና ፍርሃትን የማንገስ ከፍተኛ አቅም እንዳለው ሁሉ በብሶት የሚወለዱ፣ እምቢኝ ለግፈኞች፣ እምቢኝ ለአንባገነኖች፣ እምቢኝ ለነጻነቴ የሚሉ መንፈሰ ጠንካራ ጀግኖችንና ታጋዮችንም ይወልዳል:: የአለማችን ስመ ጥርና ዘመን የማይረሳቸው የነጻነት ታጋዮች እነ ማህተመ ጋንዲ፣ ማርቲን ሉተር ኪነግ፣ ማንዴላ፣ ኡንግ ሳን ሱ ኪ እና ሌሎችም ብዙዎች የፈለቁት በብሶት ከተሞላ፣ ጭቆና ካንገሸገሸውና በአፋኝ ሥርዓት ከታመቀ ማኅበረሰቡ ጉያ ነው:: አንድን ማኅበረሰብ በአፈሙዝ፣ በሕግና በገንዘብ ኃይል ጭፍሎቆና አፍኖ ማቆየት የሚቻለውም ለተወሰነ ጊዜ ብቻ መሆኑን … [Read more...] about ግፍና አፈና ዐመጽን ይወልዳሉ!
The Role of Civil Society Organization (CSOs) in the Upcoming Elections in Ethiopia
Fourth International Conference of Ethiopian Women in the Diaspora March 7, 2015 Washington DC, USA The Role of Civil Society Organization (CSOs) in the Upcoming Elections in Ethiopia Call for papers Civil society organizations (CSOs) flourished in Ethiopia from early 1990s to 2005 better than ever before. Some of these civil society organizations focused on service delivery, others on civil rights, gender equality and good governance, and still others on consciousness raising and … [Read more...] about The Role of Civil Society Organization (CSOs) in the Upcoming Elections in Ethiopia
ሱስ ትውልድና ሀገር!
በእኅታችን በሐና ላላንጎ ላይ ያ አደጋ በደረሰ ጊዜ ይሄንን ከባድ ዜና በለጠፉ ዋና ዋና ድረ ገጾች ላይ አንድ አስተያየት ሰጥቸ ነበር “ሆን ተብሎ በሱስ ትብትብ እንዲተበተብ ከተደረገ የዚህ አገዛዝ ትውልድ ከዚህ የተለየ ምን ይጠበቃል? እንደ ማኅበረሰብ ወንድም እኅቶቻችንን እናም ልጆቻችንን ከዚህ የሱስ ማጥ ውስጥ ካልታደግን በስተቀር ገና ከዚህ የከፋ ብዙ ነገርም ያሰማናል ያሳየናል” የሚል፡፡ አንዳንዶቹ የአገዛዙ ደጋፊዎች አጋጣሚውን ሆን ብየ ለፖለቲካ ፍጆታ ለመጠቀም የፈለኩ መስሏቸው አስተያየቴ ትክክል እንዳልሆነ ሲናገሩ አንዳንዶችም በመሳደብ ከአስተያየቴ ስር ምላሽ ሰጥተው ነበር፡፡ እኔ ግን ስም ለማጥፋትም አጋጣሚውን ለመጠቀምም አልነበረም፡፡ ያልኩት ነገር ለመሆኑ መረጃው ስለነበረኝ እንጅ፡፡ ወያኔ ፍጹም በደነቆረ አመክንዮና በጠላትነት ሰብእና ትውልዱን ሆን ብሎ በሱስ ማጥ … [Read more...] about ሱስ ትውልድና ሀገር!
የኢትዮጵያን ዲሞክራሲ ለመዉለድ ስንት ዘመን ይፈጃል?
የምርጫ ወግ ምርጫ ደርሷል አይደል? ለዛ መሆን አለበት በአንድ በኩል ኤብጭ ‘ምርጫ ቦርድ ለምርጫ አስፈፃሚዎች ስልጠና ሰጠ … ኮሮጆ አሰራጨ’… ሌሎች መገናኛ ብዙሃን ደግሞ ‘ምናምን የሚባል ፓርቲ ሰልፍ ጠራ’ … ‘የነእከሌ ፓርቲ ትየንተ ህዝብ በፖሊስ ሃይል በሃል ተበተነ’ ….. ዱዱዱዳ…እንዲያም እንዲህም የሚሉ ወሬዎች መስማት ከመሰንበቻዉ የተለመደ ሆኗል፡፡ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የኢትዮጵያን ዲሞክራሲ ለመዉለድ ስንት ዘመን ይፈጃል?
አስገራሚው ትዕይንት “በተስፋዋ” የአረብ ምድር በሳውዲ!
* የሳውዲ መንግስት "ህገ ወጦችን" የማጽዳቱ ዘመቻ ቀጥሏል * ስፍር ቁጥር የሌላቸው ዜጎች ከሞት ጋር ተፋጠው እየተሰደዱ ነው * የሳውዲ መንግስት ማስጠንቀቂያና እርምጃ . . . የሳውዲ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውንና ህጉ በማይፈቅደው መንገድ የመኖሪያ ፈቃዳቸው ካለው ሙያ ውጭ የሚሰሩ የማናቸውንም ሀገር ዜጎች በመላ ሀገሪቱ ለማጽዳት የተደራጀ ዘመቻ ከተጀመረ ወር ደፍኗል። በየቀኑ በመንግስትና በግል መገናኛ ብዙሃን የሚለቀቁት የማስጠንቀቂያ መረጃዎች ከበድ ከበድ ያሉ ናቸው። ዛሬ ማለዳ "ህገ ወጦችን ጠራርገን እናስወጣለን" ያሉትን የሰራተኛ ሚኒስትር አድል ፈቂን ይዞ የወጣው አረብ ኒውስ ሚኒስትሩ ሃገራቸው ለህገ ወጥ ሰራተኞች ቦታ እንደሌላት በአጽንኦት መጠቆማቸውን ያስረዳል። የሰራተኛ ሚኒስትሩ በማከልም መንግስት ህገ ወጦችን እግር በእግር እየተከታተለ በመያዝ … [Read more...] about አስገራሚው ትዕይንት “በተስፋዋ” የአረብ ምድር በሳውዲ!










