በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ በአቶ ኦባንግ ሜቶ በተጠራው ስብስባ ላይ የመገኘት እድል አጋጥሞኝ ነበር:: በስብሰባው ላይ ከተለያዩ የአለም ክፍሎችና ከአሜሪካ ግዛቶች የተሰባሰቡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል::
የስብሰባው መሪ ሀሳብ “ስለ እያንዳንዳችን ከመናገር እያንዳንዳችን እንነጋገር” የሚል ድፍረትን፣ ግልፅነትን፣ መከባበርን፣ መነጋገር መቻልን ሃላፊነት በተሞላበት ስሜት ይቀርቡ በነበሩት አስተያየቶች የሚያረጋግጡ ከመሆናቸውም በላይ የተለየዩ የፖለቲካ አመለካከት፣ እምነት እንዲሁም የተለየዩ ብሄረሰቦች ዉሁድ ኢትዮጵያውያን በአንድ ጠረጴዛ ዙርያ ተቀምጠው ያነሱዋቸው የነበሩት ሃሳቦች በጥንታዊት ኢትዮጵያና በአዲሲቱ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ገመድ ጉተታ ግራ ለተጋቡ ጥሩ አስተማሪ መድረክ ነበር::
ኢትዮጵያ የምትባል ጥንታዊት ሃገርን የሲኦል መገለጫ አድርገው ለሚስሉዋት የህወሃት ኢሃዴግ ደጋፊዎችና ተመሳሳይ አመለካከት ያላቸው የፖለቲካ ሰአሊዎች ወይም ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ያላቸውን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቁርኝት በፖለቲካ ብሩሽ ለማጥፋት የሚንደፋደፉ ያሉትን ያህል አዲሲቱን ኢትዮጵያን በጎሪጥና በሃሳባቸው የተለየ ቅርፅ ሰጥተው ለሚባንኑትም ሁለቱም አካሄዳቸው ሃገራችንን መጉዳቱን የስብሰባው ተሳታፊዎች አማካይ መንገድ እንዳለ በማሳየት ለዚህም ብቸኛ መንገዱ እውነትን መጋፈጥና መነጋገር ብቻ እንደሆነ ያሰመሩበት ጉዳይ ነው::
ስለ ዲሞክራሲ ማውራትና በዲሞክራሲ ህይወት ውስጥ መኖር ያለውን ልዩነት በተሳታፊዎቹ አቀራረብና በመድረኩ አመራር ያለው የዳበረ የፖለቲካ ግንነት አመላካች ነበር::
ይህ ወቅቱ የጠየቀውና አብዛኛው መድረክ ያጣና የታፈነ ኢትዮጵያዊ ድምፅ በመሆኑ ወንድማችን ኦባንግና ሶሊዳሪቲ ይህን መድረክ በመክፈታቸው ከፍተኛ ምስጋናና ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል:: ከተለያዩ ክፍለ አለማትና ከአሜሪካ ስቴቶች በስፍራው ተገኝታችሁ አሁን በሀገራችን የሚታየውን ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ የበሰሉ ሃሳቦችን ላቀረባችሁ ምሁራን የሃይማኖት አባቶችና እናቶች ታላቅ አክብሮትና ምስጋና ይድረሳችሁ::
ኢትዮጵያውያን ዝርዝር ሂደቱን ክፍል 1፣ ክፍል 2 እና ክፍል 3 ከዚህ ማግኘት ትችላላችሁ::
በተለይም በዲያስፖራው የሚታየው ጫፍና ጫፍ ቆሞ በስልጣን ላይ ካለው አምባገነን የህወሃት ኢሃዴግ መንግስት ባልተናነሰ ሁኔታ ባለፉት አመታት ኢትዮጵያውያንን እየከፋፈሉ ያሉት ጥቂት የፖለቲካ ሃይሎችና በስመ ደጋፊነት የተሰለፍን ወገኖች አካሄድ ትግሉን ወደ ሁዋላ ከማስኬድ በስተቀር ያስገኘው ፋይዳ እንደሌለውና አሁንም መፍትሄው ድፍረትና የመቻቻል ፖለቲካ ብቻ እንደሆነ ከምንም በፊት ለእውነት እራስን ም ማስገዛት ተቀዳሚ ተግባር ና የፖለቲካው ወሳነ ሃይል ህዝብን ማእከል ያደረገ ትግል ብቻ መ ሆኑን ከዚህ ስብሰባ መገንዘብ ይቻላል::
ዲያስፖራው የኢትዮጵያን ፖለቲካ በአብዛኛው የሚገመግምበት መድረኩ የፓልቶክ ክፍሎች በመሆናቸው በአካል ተገናኝቶ በመነጋገርና በኮምፒዩተር ጀርባ ሃሳብንም ሆነ ልዩነትን ማስተናገድ ያላቸውን ልዩነት በመገንዘብ ለአካላዊ ግንኙነት ትኩረት በመስጠት መሰባሰቡ ያለውን ፋይዳ መገንዘቡ የወቅቱ ጥያቄ ይመስለኛል::
በፓልቶኮች የሚደረጉ ውይይቶች በአብዛኛዎቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉና ዲሞክራሲያዊ ባህርያቸውም እያደገ የመጣና የትግላቸውም ማእከል በሃገር ቤት ያለው ትግል መሆኑ የሚያበረታታ ሲሆን የሶሊዳሪትና የአቶ ኦባንግ አካሄድ ለዲያስፖራው ፖለቲካ መጎልበት አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተስፋ አለኝ::
Gishag70@yahoo.com
Leave a Reply