• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“መንግሥት ከደላሎች ጋር አይደራደርም” ኃይለማርያም

December 26, 2014 01:02 am by Editor Leave a Comment

ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት መንግስት በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ በኢትዮጵያውያን ላይ የተከሰተውን ስቃይ እና በደል ተከትሎ ለስራ ወደ አረብ ሀገራት በሚደረግ ጉዞ ላይ እገዳ መጣሉ ይታወሳል። በተለይ ያለአንዳች የህይወት ዋስትና ወደ ተጠቀሱት ሃገራት በኮንትራት የሚሄድ ሰራተኞችን ከገጠር እስከ ከተማ በዘለቀ ድለላ ህጋዊ ፈቃድ አግኝተው ዜጎችን እያጋዙ የነበሩ የአሰሪ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤት ቢሮዎች መዘጋታቸው አይዘነጋም። ዘግይቶም ቢሆን መንግስት በወቅቱ ወሰደ በተባለው እርምጃ የአያሌ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ከአስከፊው የአረብ ዓለም ስቃይ  መታደግ ቢችልም ከግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቻችንን ህይወት ስላለበት ሁኔታ የተጠቀሱትን የኤጀንሲ ባለቤቶች በህግ ለመሞገት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ቴድሮስ አድሃኖም የገቡትን ቃል መተግበር አለመቻላቸው ብዙዎችን አሳዝኖል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሰሞኑን በዚህ ዙሪያ በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀረበው ረቂቅ  ተስፋ ተጥሎበት የነበረውን የዜጎች ደህነነት የማስጠበቅ እርምጃ መቅኔ አስጥቶት መንግስት ከኤጀንሲ ባለቤቶች ጋር በሌላ አቅጣጫ እየደረገ ያለው ድርድር በስረዓቱ በባለስልጣናት ዘንድ በዚህ ዙሪያ አንድ አቋም  አለመኖሩ  ይነገራል። ከዚህ ቀደም በሁለት ሃገራት መካከል ስምምነትና በቂ ዝግጅት ሳይደረግ በሳውዲ ብቻ ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጥ ዜጋ ህጋዊ ፈቃድ ባላቸው ኤጀንሲዎች በየገጠር ከተሞች ተግዘው “ያሉበትን ይዞታ እንዲህ ነው” ብሎ መረጃ መስጠት ቀርቶ፣ የትና በምን ሁኔታ እንደሚገኙ የሚያውቅ ኤጀንሲም ሆነ የመንግስት ተወካይ በሌለበት መንግስት  ከተጠቀሱት ወንጀለኞች ጋር በዜጎች ህይወት መደራደሩ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር መሆኑን ታዛቢዎች ይገልጻሉ፡፡

ሰሞኑንን ለሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ጠ/ሚ/ር ሐይለማርያም ደሳለኝ መንግስታቸው ከደላሎች ጋር እንደማይዋዋል ቢያረጋግጡም እነዚህ ወገኖች በተለያዩ የመንግስት መዋቅሮች ውስጥ ሰርገው በመግባት የአንዳንድ ደካማ ባለስልጣናት  እጅ በመጠምዘዝ መንግስት ከደላሎች ጋር እንዲደራደር ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል። አብዛኛዎቹ የኤጀንሲ ባለቤቶች ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ጭምር  በጥቅም የተቆራኙ ከመሆናቸውም በላይ ከልማት ማህበራት አንስቶ የኢህአዴግ አባል መሆን የሚያስችላቸውን መታወቂያ ካርድ በመውሰድ በህዝብ ሰም እየማሉ የአዞ እንባ በማንባት ከልካይ በሌለበት እንሱ ፈላጭ ቆራጭ በሆኑበት ስረአት ውስጥ በዜጎቻችን ህይወት መክበራቸው ይታወቃል።

በዋንኛነት መቀመጫቸውን ሳውዲ አረቢያ ጅድ እና ሪያድ ከተማ ያደረጉ እነዚህ ወገኖች ከዲፕሎማቱ ጋር ባላቸው የእከክለኝ ልከክለህ ወዳጅነት ሲሻቸው በቆንስላው ቢሮ በመፈንጨት መብቴ ይከበርልኝ ያለውን ዜጋ ከተቃዋሚ ሃይሎች ጋር በመፈረጅ ምንም አይነት ስለነሱ ምንም እንዳይተነፍስ በማስፈራራት ሲሻቸው በህገወጥ የሃዋላ ንግድ በፍረጠመው ጡንቻቸው በጠራራ ጸሃይ የሃይል ጥቃት ለመፈጸም ይቃጣቸዋል።  የአሰሪ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤቶችን ያስከፋው ሰሞነኛው የጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም መግለጫ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውሩ በተለይ ወጣቶች የተሳሳተ መረጃ ተስፋ ሰንቀው እዚያ ላይ ተሰማርቼ ማጨድ አለብኝ በሚል የተሳሳተ ግንዛቤ መሆኑን አውስተው አንዳንድ ሰዎች ይህ ፍልሰት የበዛው ወደ አንዳንድ የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የሚደረገው ጉዞ በመከልከሉ ምክንያት ነው የሚለውን ፍጹም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በመሞገት ዜጎች በህጋዊ መንገድ መጓዝ በአውሮፕላን ሆነ እንጂ ከዚያኛው የሕገወጥ ጉዞ አንደማይሻልና  አስረድተዋል። ጠ/ሚ/ሩ በማያያዝ ሃሳብቸውን ሲያጠናክሩ የዜጎች ህይወት በአስተማማኝ መልኩ ሊጠበቅ የሚችለው ከደላሎች ጋር በመደራደር ሳይሆን ከመንግሥታት ጋር ስምምነት ሲኖር ብቻ መሆኑን ደግመው አረጋግጠዋል፡፡

እስካሁን እልባት ባላገኘው የአረብ ሃገር ኮንትራት ሰራተኞች ጉዞ የህይወት ዋስትና ጉዳይ በተለያዩ ጊዜያቶች በኢህአዴግ ባለስልጣናት ዘንድ የሚሰጠው መግለጫ እርስ በእርሱ የተጣረዘ መሆኑን የሚናገሩ ታዛቢዎች የሰራተኛ እና አሰሪ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤቶች እንደወትሮው ቢሮቻቸውን ከፈተው በዜጎች ንግድ ላይ ለመሰማራት በማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ይህ ይጨመር አሊያም ይቀነስ በማለት እየተዋዋሉ ባሉበት ሁኔታ መንግስቴ ከደላሎች ጋር አይደራደረም  የሚለው የጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ መግለጫ ግልጽነት የሌለው እና አብዛኛውን ወገን ግራ ያጋባ መሆኑ ይነገራል።

Ethiopian Hagere Jed Bewadi ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የላኩት

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule