• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከሸአቢያ መልካም ነገርን ከኩርንችት የወይን ፍሬን ማግኘት ይቻል ይሆን?

January 7, 2015 08:14 am by Editor 2 Comments

ኢትዮጵያ ሆይ! አሁንስ ተስፋሽ ማን ነው እግዚአብሔር አይደለምን?

መቸስ በጣም ይገርማል! ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ መከራችን ሊያልቅ ነው ስንል ገና መጀመሩ ነው እንዴ ጃል? ጉድ እኮ ነው! የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ለመሆኑ ከዚህ በላይ ሌላ የመከራ ዘመናት መሸከም የሚችል ትከሻ አለህን?

የአርበኞች ግንባር ግንቦት 7 ሌሎችም በትጥቅ ትግል ላይ ያሉ ኃይሎች ውሕደት ሊፈጽሙ እንደሆነ ካስታወቁ ወራት ተቆጥረዋል፡፡ ጉዳዩ ለዚህ ደርሶ በይፋ ለሕዝብ ከማስታወቃቸው በፊትም ከዚህ መግባባት ላይ ለመድረስ አጭር የማይባል ጊዜ እንደወሰደ መገመት ይቻላል፡፡ ይሄም ሆኖ “ታጋይ ኃይሎቹ ሊዋሐዱ እንደሆነ ካስታወቁ በኋላ ግን ዓላማቸው ያን ያህል ግልጽና ተጣጣሚ የሚፈልጉትም ከሆነ ምን አንጓተተው?” የሚለው ጥያቄ ከብዙዎች የሚነሣ ጥያቄ ነበረ፡፡ አሁን ግን የዚህ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ግልጽ እየሆነ መጥቶ የሸአቢያ ሸረኛ እጅ መሆኑ ታውቋል፡፡

ቀድሞም ቢሆን ወያኔ አጎራባች ሀገሮችን በሙሉ የሀገራችንንና የሕዝቧን ብሔራዊ ጥቅሞች  አሳልፎ እየሰጠ በጥቅም ስለያዛቸውና እሱ በትግል ላይ እያለ ከሱዳን ያገኝ የነበረውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ዓይነት እንኳን ባይሆን ተገን ብቻ እንኳን ከአጎራባች ሀገሮች ማግኘት የሚቻልበትን ዕድል ሙሉ ለሙሉ ዝግ ስላደረገው ቢጨንቃቸውና አማራጭ ቢያጡ በሀገራችን በሰላማዊ ትግል መንግሥታትን መቀያየር የሚቻልበት የትግል አማራጭ ሙሉ ለሙሉ ዝግ በመሆኑ የቀረልን የተተወልን አማራጭ የትጥቅ ትግል ከሆነ ያለን ብቸኛ አማራጭ ሰሜናዊው የሀገራችን ክፍል ባሕረ ምድር (ጣሊያኖች ኤርትራ ብለው የሠየሟት ይሄንን ተቀብለን እኛም መጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎቹም ሳይቀር ኤርትራ እያልን የምንጠራት) ብቸኛዋ አማራጭ በመሆኗ እንጅ የሸአቢያን ማንነት ዘንግተው ሸአቢያን ከማመን አንጻር እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ይመስለኛል፡፡ ዋናው የመርዙ ሰንኮፍ ማን ሆነና? ይሄንን እንዴት እንረሳለን?

እኔ በግሌ ለአርበኞች ግንባርና ለግንቦት 7 ድጋፌን የምሰጠው እጅና እግርን አጣጥፎ ግፍን እየተጋቱ የሌለ ነገርን ተስፋ እያደረጉ አርፎ ተቀምጦ ከመረገጥ ችግር እንዳለ ቢታወቅም የተገኘውን አማራጭ ሁሉ መጠቀም አማራጭ የሌለው ጉዳይ በመሆኑ ነበር እንጅ እነዚህን ወገኖቻችንን ሀገራችንን እንደሚመቻት እንደሚበጃትና እነሱም እንደሚመኙት ሳይሆን ሸአቢያ ለራሱ እንደሚመቸውና እንደሚበጀው ለማድረግ ጣልቃ እንደሚገባባቸውና በርካታ መሰናክሎችን እንደሚጋርጥባቸው ጠፍቶኝ አልነበረም፡፡

ለዚህች ሀገር ጠላት ካልን ከወያኔም ሸአቢያ እንደሚከፋ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን ሸአቢያ ለራሱ ጥቅም ሲል ወያኔ እንዲጠፋለት የሌት ተቀን ምኞቱና ሕልሙ ስለሆነ እራሱም እንዳያደርገው አቅም ስለሌለው ለወያኔ አቅም የሆነውን የኢትዮጵያን ሕዝብ የሱን ጥቅም ለማስጠበቅ የተነሡ ልጆቹን በመያዝ በሚያደርጉት ትግል ወያኔን ለመጣል በማሰብ “የጠላቴ ጠላት ወዳጀ” በሚል ስሌት ተቀበላቸው እንጅ ለኢትዮጵያ መልካምና ቀና ከማሰብ ከመመኘት እንዳልሆነ አሁንም በጣም ግልጽ ነው፡፡

እነዚህ ወገኖቻችን በተግባር ምን እንዳጋጠማቸው ባላውቅም የሀገርን ጥቅም አሳልፈው ለመስጠት እንዳይገደዱ፣ የሸአቢያንም አላስፈላጊ የስምምነት ጫና ለመቋቋም ማድረግ ያለባቸውን ጥንቃቄ ያደረጉ ይመስለኛል፡፡ ዓላማቸው በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በኃይል የተጫነውን አንባገነንና የጥፋት ኃይል ወያኔን ከሥልጣን እስከማስወገድና የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት እስከማድረግ ድረስ ብቻ እንጅ በወያኔ ተተክተው በሥልጣን ኮርቻ ላይ ለመፈናጠጥ እንዳልሆነ ግልጽ አድርገዋል፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵያና በሕዝቧ ጥቅሞችና ሀብት ላይ ከማንም ጋራ የመደራደር ኃላፊነትና መብት ስለሌላቸው ይሄንን ማድረግ እንደማይችሉ ለሁሉም አረጋግጠዋል፡፡ ሸአቢያ ይህ የወገኖቻችን አቋም እነሱን በመጠቀም ጥቅሙንና ፍላጎቱን ለማስጠበቅ እንዳይችል አድርጎታል፡፡ ስለሆነም ይሄንን ፍላጎቱን የሚያሟላ ሌላ አማራጭ በማፈላለግና በመፍጠር ተግባር ተጠምዶ ቆይቶ ጥረቱ ያዘለትና ደሚሕትን ወይም ትሕዴንን መፍጠር ቻለ፡፡ በአጭር ጊዜም የአርበኞች ግንባርንና ግንቦት ሰባትን ብለው ወደ ባሕረ ምድር (ኤርትራ) የሚገቡትን ዜጎችን ሁሉ ወደ ደሚሕት ማለትም ትሕዴን (የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) በማስገባት ትሕዴንን ከፍተኛ የተዋጊ ቁጥር እንዲኖረውና እንዲጠናከር በማድረግ የሩቅ ትልሙን ለማሳካት ጥሩ መሠረት ፈጠረ፡፡

ሸአቢያ ትሕዴንን እንዲህ ካደረገ በኋላ ለግንቦት ሰባትና ለአርበኞች ግንባር ያለው ስሜት እየተቀዛቀዘ መጥቷል አሁን እነሱን ሊጠቀምባቸው የሚፈልገው ለመቆመሪያ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማታለያ ለመደለያነት ያህል ነው፡፡ ይሄንንም እነኝሁ ወገኖቻችን ጠንቅቀው ያውቁታል ብየ እገምታለሁ፡፡ ሸአቢያ ኢትዮጵያን የሚል ለሀገሩ ታማኝ የሆነ ኃይል ለእሱ እንደማይበጀው ያስባልና በእርግጥም ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ታማኝ ለሆነ ኃይል ምን ዓይነት አመለካከት አስተሳሰብ ሊኖረው እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው፡፡ እኛን ሀገርን ብለው ትግል የወጡ ወገኖቻችን አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ስለ መፍትሔው እያንዳንዱ ዜጋ ጠልቆ ማሰብ ይኖርበታል “በቃ! ተስፋ የላቸውምና እነሱን መተው መርዳትና መደገፍ ማቆም ነው መፍትሔው” ብሎ የሚል ደንቆሮ ዜጋ እንደማይኖር ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በእኔ ግምት እነሱን መታደግና የወጡለትን ዓላማ ለስኬት ማብቃት የምንችለው በገፍ ወደ እነሱ በመግባት ያለውን የኃይል ሚዛን አለመመጣጠን መቀልበስ የቻልን እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ በተቻለ መጠንም ደሚሕትን መቀላቀል ሳይፈልግ ትግሬም ሳይሆኑ ወደ ደሚሕት እንዲቀላቀል የተደረገው አብዛኛውን የደሚሕትን ታጋይ ወደ ሚፈልገው አርበኞች ግንባር ወይም ግንቦት 7 እንዲቀላቀሉ ማድረግ የሚቻልባቸው መንገዶች መሞከር መመቻቸት ይኖርበታል፡፡

በበርካታ ምክንያቶች ወያኔና ሸአቢያ ቀድሞ የነበራቸውን ቃልኪዳን ዝምድና ወዳጅነት አንድነትና ጥምረት ከምናውቀውም በላይ ነበር፡፡ ያ የወያኔ ቃል ኪዳንና ዝምድና እንኳን በእኛ በእነሱም እንኳ መቸም ይደፈርሳል ይፈርሳል ተብሎ ሳይጠበቅ ሳይታሰብ ተአምር ሊባል በሚችል ደረጃ የሆነውን ለማመን ሁሉም በተቸገረበት መልኩ ቃል ኪዳናቸው ፈረሰ የሆነው ሁሉ ሆነ፡፡ ያ ቃል ኪዳናቸው ዳግም ላይታደስ ፈረሰ፡፡ ይህ ማለት ግን ሸአቢያ ወያኔ ከወጣበት ኅብረተሰብ ሌላ ኃይል ቢወጣለት ደስታው አይደለም ቃልኪዳንም አይመሠርትም ማለት አልነበረም፡፡ ቅድሚያ የሚሰጠውና ተመራጭ የሚያደርገው ጉዳይ ይሄ እንደሆነ ማንም ሊያውቀው ይገባል፡፡ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን በተመለከተ ሸአቢያ ድሮም አሁንም ወደፊትም ያው ነው መቸም ይለወጣል ብየ አልገምትም፡፡

የደሚሕት ኃይል በዚህ መልኩ ተጠናክሮ ከመውጣቱ ጋራ በተያያዘ ሸአቢያ የልቡ ደርሷል የሐሳቡ ሰምሯል፡፡ ስለሆነም ሸአቢያ ሳይወድና ሳይፈቅድ ወያኔን ለማጥቃት ሲል ብቻ ኢትዮጵያን ከሚጠቅሙ ኢትዮጵያን ካሉ ኃይሎች ጋር ከአርበኞች ግንባርና ከግንቦት 7 ጋር አብሮና ተባብሮ ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ማድረግ ግድ ሳይለው ኢትዮጵያን በተመለከተ ቀድሞ ከነበረው አቋሙ አንዲት ጋትም ብትሆን ፈቀቅ ማለት ሳያስፈልገው በብዙ ምክንያቶች ወገኑ ዘመዱ የቃልኪዳን አጋሩ አድርጎ ከሚቆጥረው ኅብረተሰብ የሚፈልገውን ኃይል አግኝቷልና ከላይ እንዳልኩት ለመደለያ ለመቆመሪያ ካልሆነ በስተቀር የግንቦት 7ን እና የአርበኞች ግንባርን ኃይሎች ትርጉም ያለው ፋይዳ አዘል ሚና ሊጫወቱ በሚችሉበት መልኩ ተጠናክረው መውጣታቸውን ፈጽሞ አይሻም፡፡ እያደረገ ያለው ጣልቃገብነትም ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው ይሄንን ሀቅ ነው፡፡

እኔ እንደ ደምሒት(ትሕፌን) እና አረና ትግራይ ዓይነት ብሔር ተኮር ለሆነ የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ የትጥቅ ትግል ኃይል በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ጥሩ አመለካከት የለኝም፡፡

  1. ከወያኔ እንደተማርነው የብሔረሰብን ጉዳይ የፖለቲካው ጅማሬና ፍጻሜ ያደረገ የትኛውም ፓርቲም ሆነ የትግል ኃይል ሥልጣን ቢይዝ ጉዳዩ ዓላማው ተግባሩ ሁሉ ብሔሬ የሚለውን ብሔረሰብ ለመጥቀም ተጎድቷል ከሚለው ለመካስ እሱም በተራው በሌሎቹ ላይ ለመፈናጠጥ ለመፋነን ከመጣር የተለየ ሊያደርግ አይችልም፡፡ እጅግ አሳዛኝ በሆነ ደረጃ እንጭጮች ናቸው ጠባቦች ናቸው ያልበሰሉ ናቸው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሕዝብና ለሀገር ትርጉም ያለው ሥራ ሊሠሩ የሚችሉትና ፋይዳ የሚኖራቸው ሥልጣን በያዙ ጊዜም ፍትሕና እኩልነትን ለማስፈን የታመኑ የተጉ ሊሆኑ የሚችሉት ጠባብ ከሆነው የብሔር ተኮር አስተሳሰብ ወጥተው እንደ ሰው አስፍተው ማሰብ ሲችሉና እንደ ዜጋም ሀገር የምትባልን ሥዕል በጭንቅላታቸው ውስጥ ማስፈር ቦታም መስጠት ሲችሉ ብቻ ነው፡፡

አለዛ ግን ሥልጣን በያዙ ጊዜ እንደወያኔ ሁሉ የሌሎቹን ብሔረሰቦች መብቶችና ጥቅሞች እየረገጡ ተጎዳ ተበደለ ተጨቆነ ተጋደልንለት ሞትንለት መሥዋዕትነት ከፈልንለት የሚሉትን ብሔረሰባቸውን ብቻ ለመካስ ለመጥቀም ለማስደሰት ነው የሚጥሩት እንጂ ሁሉንም ዜጎች በእኩል ተመልክተው የፍትሕንና የእኩልነትን ጥያቄ የሚመልሱ የሚፈቱ አይሆኑም ተፈጥሯቸው አይፈቅድላቸውምና፡፡ ከዚህ ቁንጽል አስተሳሰብ መውጣት አስካልቻልን ጊዜ ድረስ የደም መፋሰስ በዚህች ሀገር ውስጥ ይቆማል ብላቹህ ተስፋ አታድርጉ፡፡ ትሕዴንና አረና ትግራይ ስማቸው እንደሚያመለክተው ሐሳባቸውና ዓላማቸው የትግራይን ሕዝብ ከወያኔ በተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ እንጅ እንደኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያን አስበው ኢትዮጵያ አቀፍ ዓላማና ሐሳብ አንግበው ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ማዕከል በማድረግ አይደለም፡፡ እነዚህ አካላት በተደጋጋሚ ሲገልጹት እንደተሰማው ለመመሥረታቸው ምክንያታቸው “የትግራይ ሕዝብ በወያኔ ተከድቷል የተገባለት ቃል አልተፈጸመለትም” የሚል ነው፡፡ በመሆኑም ዓላማቸው በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ከወያኔም የከፋ ወያኔ ለመሆን ነው ማለት ነው፡፡

2. ደሚሕቶች ከአርበኞች ግንባር ጋር አብሮ ለመሥራት በተነጋገሩ ጊዜ ሊያግባባቸው ያልቻለው ጉዳይ ኢፍትሐዊ በሆነና በግፍ በታጀበ መንገድ ከጎንደርና ከወሎ እየተቆረሰ ወደ ትግራይ የተከለለው መሬት ጉዳይ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ከልብ ይሁን አይሁን ባይታወቅም ደሚሕቶች በመርህ ደረጃ ከአርበኞች ግንባር አቋም እንዲይዙ የተጠየቁትን ቢስማሙበትም ለጊዜው ግን “የትግራይን ሕዝብ ድጋፍ ያሳጣናል” በሚል ሰበብ “ከጎንደርና ከወሎ ተቆርሰው ወደ ትግራይ የተከለሉትንና እየተከለሉ ባሉ መሬቶች ላይ አቋም ወስደን ለሕዝብ ይፋ የምናደርገው ነገር ስለማይኖር ከድል በኋላ እልባት እንስጠው አሁን ግን በትግሉ ላይ እናተኩር” የሚል የብልጥ አይሉት የሞኝ አቋም በመያዛቸው መግባባት ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ ደሚሕቶች የትግራይን ሕዝብ ማዕከል ባደረጉ በሌሎች ጉዳዮች ላይም እንደወያኔ ሁሉ የተሳሳተ አቋም መያዛቸው ኃላፊነት የጎደለውና የትግራይን ሕዝብ “እንዲህ ብሎ ያምናል” እያሉ ከሚጠቅሱት ስሕተቱ እንዲታረም እንዲማር ዕድል የማይሰጥ፤ ሕዝብን ለመምራት የተዘጋጀ ፓርቲና ኃይል ሊወስደው ከሚገባው ኃላፊነትና ተጋፍጦ (risk) አንጻር የማይጠበቅ፣ ዘለቄታዊ ለሆነ የሀገር ጥቅም የማይበጅ በመሆኑ የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት ወይም አቋም ነው የሚባሉ ነገሮች በርግጥም የትግራይ ሕዝብ እንደነዚህ ዓይነቶችን ከአንድ ሕዝብ የማይጠበቁና አሳፋሪም የሆኑ አቋሞችን ይዞ ከሆነ ሕዝቡ የያዘው አቋም ትክክል እንዳልሆነ እየተናገሩ ከወዲሁ ካልተጋፈጡትና አቋም ካልያዙበት በስተቀር ወያኔ ከወደቀ በኋላም “አሁን ለጊዜው ከትግራ ሕዝብ ጋር ላለመቀያየም ድጋፉን ላለማጣት” በሚል ትክክል እንዳለመሆኑ የያዙትን አቋም ሊለውጡ የሚችሉበትን ዕድል እንደማያገኙ እያወቁ አቋም ለመውሰድ ባለመፈለጋቸው፡፡

ምክንያቱም እነኝህ ወገኖች ማለትም ደሚሕትና አረና ትግራይም ሥልጣን ይዘው ሕዝብን ለማሥተዳደር እንደመፈለጋቸው ወደፊት የሚፈልጉትን ሥልጣን ሊያገኙት የሚችሉት በሕዝብ ምርጫ በመሆኑ ትክክልና መፈጸም ያለበትን ጉዳይ ሁሉ “የትግራይ ሕዝብ ይህ እንዲሆን ስለማይፈልግ” እያሉ “ድጋፉን ላለማጣት በዚህ ወቅት አቋም ልንይዝበት አንችልም ከድል በኋላ ግን አይቸግረንም” ብለው በትግል ወቅት ቀጠሮ ይዘውለት የነበረውን ጉዳይ ከድል በኋላ አሁን ጊዜው ነውና ለሕዝቡ እናውጅ ቢሉ በሕዝብ ተመርጠው ሥልጣን ይዘው ለማሥተዳደር ያላቸውን ምኞት ይሄንን ትክክለኛ እርምጃ በመውሰዳቸው ምክንያት ሕዝቡ ስለሚከፋባቸው በዚህ ምክንያት በሕዝቡ ተመርጠው ሥልጣን መያዝ የሚችሉበትን ዕድል ሊያገኙ ስለማይችሉ ሥልጣኑን ደግሞ ማጣት ስለማይፈልጉ ያኔም ቢሆን “የትግራይን ሕዝብ ያስከፋብናል” በሚል ምክንያት አቋምና ውሳኔ የመውሰድ አቅሙን ቁርጠኝነቱን ዕድሉን ሊያገኙ ከቶውንም ስለማይችሉና መወሰን አቋም መያዝና ሕዝቡንም ማረም ማስተማር ማሳመን ካለባቸው ትክክለኛው ሰዓት አሁን ሆኖ እያለ ይሄንን ማድረግ ባለመፈለጋቸው ነው፡፡

አሁን የሸአቢያ ምኞትና ዝግጅት ደሚሕትን (ትሕዴንን) አጠናክሮ ከእነሱ ጋር በመሆን ወያኔን ጥሎ በኢትዮጵያ ላይ የእሱ ታዛዥ ጥቅም አስከባሪ የሆነ የትሕዴንን መንግሥት መሥርቶ ኢትዮጵያን እየቦጠቦጠ የአፍሪካ ሲንጋፖር ሲል የሚጠራትን ኤርትራን መገንባት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ያለህ አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ነው “የግድህን ከእንቅልፍህ መንቃት! ቆራጥ መሆን!” በሸአቢያ ላይ ጥገኛ የሆነ አስተሳሰብ ይዘህ ከነበረ እሱን ጣል እርግፍ አድርግና ዛሬ ነገ ሳትል በእጅህ ባለው ነገር ምን አድርገህ እራስህን ነጻ ልታወጣ እንደምትችል በአስቸኳይ ጊዜ ሳትፈጅ ምድር አንቀጥቃጭ ዐመፅ ቀስቅሰህ ወያኔን ጠራርገው፡፡ ትንሽ ነው የሚበቃው ይሄንንም ያህል ከባድ አድርገህ አታስበው፡፡ መስሎህ ነው እንጅ እኮ ቆርጠህ የተነሣህ ጊዜማ እኮ ሠራዊቱም ካንተ ጋር ነው የሚሰለፈው፡፡ ሌላ ምንም አማራጭ የለህም ቶሎ ንቃ! ቁረጥ! ጨክን! እርምጃህን ውሰድ፡፡

ለኢሳት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሳላሳስብ ማለፍ የማልፈልገው ጉዳይ ቢኖር ሌሎች ጣቢያው ሊገነዘባቸው የሚገባው ጉዳዮችን ሌላ ጊዜ የምመለስበት ሆኖ ለአሁኑ ግን ከላይ ከገለጽኩት ተጨባጭ ሥጋቶችና ከሚታወቁ ብዙ ችግሮች አንጻር በቅርቡ ጣቢያው ለትሕዴን የሰጠውን የአየር ሰዓት ሽፋን ዕድል የኢትዮጵያንና የሕዝቧን ዕድል የሚያስጠብቅ ባለመሆኑና ኢሳት እንደ የሕዝብ ልሳንነቱ ለሀገርና ለሕዝብ ካለው ዓላማና ሕልም አንጻር ይህ የወሰደው ውሳኔ ተጻራሪ በመሆኑ ይሄንን የተሳሳተ ውሳኔውን በፍጥነት እንዲያጥፍ እንደ አንድ ዜጋ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አዝማሚያቹህ እንደሚጠቁመው ለሌሎች ኃይሎችም ተመሳሳይ ዕድል የመስጠት ዝንባሌ ያላቹህ መስሎ ስለተሰማኝ በተለይ የኦነግ ኃይልም ተመሳሳይ ጥያቄ ቢያቀርብ እንደምታውቁት ሁሉ ይህ ኃይል ኢትዮጵያ ውስጥ ከወያኔ ጋር በመተባበር የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸመና ወደፊትም ለመፈጸም ሕዝብን የሚመርዙ የጥፋት ስብከቶቹን እንደ ጁሀር ያሉ አባሎቹንና ደጋፊዎቹን በመጠቀም እየነዛ ያለ የጥፋት ኃይል በመሆኑ ዕድሉ እንዳይሰጠው ይልቁንም ያንን የዘር ማጥፋት ወንጀል ትዕዛዝ ሰጥተው ያስፈጸሙ አመራሮቹንና ታጣቂዎቹን ከያሉበት ለፍርድ ሊቀርቡ በሚችሉበት ጉዳይ ላይ የሚጠበቅባቹህን እንድታደርጉ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡

ወያኔም ወያኔ ፤ ሸአቢያም ሸአቢያ

አምላክ ያመጣብን ፤ መቅጫ ማስተማሪያ

ግን እኛም አልተማርን ፤ በዚህ በታረሚያ

ጌታ እንዴት ታደርገን ፤ እኛን እዚህና እዚያ

ቀኑስ እንዴት ይሆን ፤ ነገ ከነገ ወዲያ

እጣዋስ ምንድን ነው? ፤ ይህች ሀገር ኢትዮጵያ

ከጅቦች አፍ ገብታ ፤ ሳትደቅ እንደ ሥጋ

የምትተርፍበትን ፤ ታምርህን ስጓጓ

ከበቀደም ትናንት ፤ ከትናንትም ዛሬ

እንዲህ አወሳስበህ ፤ የሰጠኸን ለአውሬ

በቃ ላትል ነው ወይ? ፤ ልንቀር በመረሬ፡፡

በደል ብንበድልህ ፤ ብናምፅም በአንተ

እስከ አሁን ያየነው ፤ በሁሉ የተጋተ

እሱ በቂ ሆኖ ፤ ሒሳቡ ሊዘጋ

በቃቹህ ልትለን ፤ መስሎኝ ቀን ሊነጋ

ለካ እሱ ገና ነው ፤ የዐመፃችን ዋጋ

ከትናንትም ዛሬ ፤ ከዛሬም ለነገ

መቷል መዓት መከራ ፤ መርግ የተመረገ

የዚህ ዘመኑ ሕዝብ ፤ ካለህ ቅን ልቡና

ይሄ ሁሉ ቅጣት ፤ የግፍ ግፍ ገመና

ውርደት ውድቀት ጉዱ ፤ የማያልቅ ቀኖና

ይደፍረኛል ብለህ ፤ ባልገመትከው መና

ስትንቀው በኖርከው ፤ ያበላህ ያሳር ቁና

የናቁት ያደርጋል ፤ ያስቀራል እራቁት

ተብሎ የተተረተው ፤ ደርሶብህ እንደትንቢት

በሠራኸው ኃጢአት ፤ በዐመፃህ ነውና

መከራ ላይ ችጋር ፤ በያይነት ፈተና

እየደራረበ ፤ ያሸከመህ ጫና

መክሮህ አስተምሮህ ፤ ለዚያ ሕይዎት አብቂ

ለአምላክ ያደረ ፤ ቃል ሕጉን ጠባቂ

አባት ሐዋርያ ፤ ባይኖርም አጽዳቂ

በአምላክ ላይ ዐምፆ ፤ ከእጁ ማምለጥ ደኅና

ከቶ የማይታሰብ ፤ የማይሆን ነውና

ባንዣበበው እሳት ፤ ተበልተን ሳንጠፋ

ይሄን ጊዜ ፈጥነን ፤ ንስሐ እንግባ

በልቶ ሳይጨርሰን ፤ ጭራቅ እያደባ፡፡

መሐሪው ፈጣሪ ፤ ፈልጎ ሊምረን

አጥብቆ ሲጠራን አጥብቀን ከሸሸን

መግቢያችን ገደል ነው ፤ እየተጠላለፍን፡፡

ንስሐችን ገብተን ፤ በጽድቁ ብናድር

በዐመፃችን ምክንያት ፤ ሆኖ ታላቅ ቀንበር

እንደ ጋራ ከብዶ ፤ የተጫነን ጠጠር

ከጠጠርም ቀሎን ፤ ባገኘነው ነበር፡፡

ንስሐ ካልገባን ፤ በዐመፃ ከቀጠልን

ጠጠሩ እንደጋራ ፤ ከብዶ እንደተጫነን

እሾኩ የጦር ያህል ፤ ሰቅዞ እንደወጋን

እንኖራለን እንጅ ፤ ግፍ እየተጋትን

ግፈኞች ተነቅለው ፤ አይመጣም መልካም ቀን፡፡

ንስሐ እንግባ ፤ እንበለው ማረን

ምህረቱን እንዲያወርድ ፤ ከአሳር እንዲያወጣን

እሾኩን እንደሾክ ፤ ጠጠሩን እንደጠጠር

ነቅለን አስፈንጥረን ፤ ሰላም እንድንኖር

ይሄንን ለማድረግ ፤ እንዲያስችለን እግዜር፡፡

እሽ በጅ ብትሉ ፤ ለኔ ብትታዘዙamsalu

የምድርን በረከት ፤ ትበላላቹህ ብዙ

እንቢ ብትሉ ግን ፤ በእኔም ብታምፁ

ሰይፍ ይበላቹሀል ፤ እንድትገሰፁ

ብሏልና ቃሉ ፤ ይሄው ነው ሕግ ደንቡ

ምህረቱን ካሻቹህ ፤ ንስሐውን ግቡ፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Abegaz says

    January 7, 2015 05:12 pm at 5:12 pm

    You are living in the past. This notion of making Eritrea as enemy when the main enemy, woyanie is in our backyard, is sheer nonsense. Please move on. Eritrea is now a different coutry an important ally in the war against woyanies. Please learn from woyaies. They occupied Menilik’s place through the help of shabia. Why not us work with shabia? nothing wrong.

    Reply
  2. Birhane says

    January 18, 2015 07:48 pm at 7:48 pm

    Fesam lemin berha wetiteh atiwagam ende weyanewoch. Hamut yeleleh.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule