የተከበራችሁና የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ሆይ፤ እትብታችሁ ስለተቀበረባት የምትወዷት ሀገራችሁ ኢትዮጵያም ሆነ ስለ ሃይማኖታችሁና ስለ ቤተ ክርስስቲያናችሁ ስታስቡ ሁሌም አስተዋይ፤ አርቆ አሳቢ፤ ብልህና ንቁ ሁኑ እንጂ ባማሩ ቃላት በመሳብም ሆነ ልብሰ ተክህኖና ግርማ ሞገስን በማየት የተንኮልና የሃሰት ሰለባ እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ።
“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ፤ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች፤ ተኩላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነብቢያት ተጠንቀቁ” ተብሏልና (የማቴ. ወ. ም. ፯ ቁጥር ፩፭)
በለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ሁሉም የሚያውቀው ነው፤ መንስኤው ማን እና ምንድን ነው ከተባለ ደግሞ እውነተኛው መልስ ሥጋዊ ጥቅምን በማስቀደም ለሥልጣን፤ ለንዋይና ለዝና ያደሩ ጥቂት ካህናት የፈጠሩት ችግር መሆኑ የተረጋገጠ ነው።
እነዚህ ችግር ፈጣሪ ጥቂት ካህናት ልብሰ ተክህኖውን ለብሰው፤ የጌታን መስቀል በመያዝ ካህን መስለው ለመታየት ይጥራሉ እንጂ አንዳችም ለካህን የተገባ ሥነ ምግባር የሌላቸው ፍሪሃ እግዚአብሔር የሚባል ነገር ጨርሶ የራቃቸው፤ በማንኛቸውም ስፍራና ቦታ ያለምንም ፍርሃትና ሰቀቀን በድፍረትና በጭካኔ የሚዋሹና የሚክዱ ናቸው። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
እምነቴ ተዋህዶ says
“እውነትን ፈልጓት፤ ታገኟታላችሁም!”በሚል ርእስ አንድ ወንድማችን ይሄው ጽፎ አስነብቦናል በዚህ ጽሁፍ ላይ አስተያየት የምሰጥባቸው ጥቂት ነጥቦች ስላሉኝ ይዤ ብቅ ብያለው። ለመነሻ ያክል ጸአፊው እየቆነጣጠሩ የሚያወግዙት ጽሁፍ ማለትም “ቤተ ክርስቲያን ግን የጸሎት ቤት ናት” የሚለውን ጽሁፍ የጻፍኩት እኔ ስሆን እኔም እንደማንኛውም የለንደን ደብረጽዮን ቤተክርስቲያን ምህመን ስሆን ላለፉት 15 ዓመታት ከማስቀደስ በዘለለ በምንም ዓይነት የቤተክርስቲያን አገልግሎት ላይ ተሳትፌ የማላውቅ እና ሥልጣነ ክህነት ያልነበረኝ የሌለኝም ካሁን በኃላም ወደፊት እንደእግዚአብሄር ፍቃድ በእድሜ መግፋት ካልመለኮስኩ በስተቀር ጸአፌው እንደሚሉት ካህን አይደለሁም። ሌላው በጣም የገረመኝ እኔ እንደማንኛውም የቤተክርስቲያን ልጅነት የተሰማኝንና የተረዳውበትን መንገድ ጻፍኩ የዚህ ጽሁፍ ጻፊ አጣመው፤ በትነው፤ ዘቅዝቀው፤ ገልብጠው፤ ገምተው፤ መዝነው፤ አቃለው፤ አዋርደው፤ አቆሽሸው፤ አጥቁረው ጻፉት ይህም አግባብ አይደለም እውነት እውነት እውነት እውነት … ስላልን ውሸት እውነት አይሆንም እውነት እውነት ነው እየተባለ እንደውሸት ሊሰበክለት ፕሮፐጋንዳ ሊነዛለት አያስፈልግም እውነት እውነትነቱ ይበቃዋልና።