መግቢያ
በዚህ ርእስ ይህችን ጦማር እንዳዘጋጅ የተገደድኩበት ምክንያት “የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ በመሆኔ ለቤተ ክርስቲያኔ እቆማለሁ፤ ጋዜጠኛ በመሆኔም ለህዝቤ እውነቱን አስጨብጣለሁ” እያሉ፤ ነገር ግን እንደሚሉት ሆነው የማይገኙ እንደ አቶ አዲሱ አበበ የመሳሰሉ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኞች በመካከላችን ስለተከሰቱ ነው። አቶ አዲሱ እንደሚሉት የክርስትና ሕይወትና የጋዜጠኝነት ሙያ የተዋሀዳቸው ቢሆኑ ኖሮ እጅግ በታደልን ነበር። እንደነ ተመስገን ደሳለኝ፣ እስክንድር ነጋና ርዕዮት ዓለሙን የመሳሰሉ ጋዜጠኞች ታስረው በመሰቃየት ላይ ሳሉ፤ በቂ ችሎታና ሙያ ሳይኖራቸው አቅጣጫ እየቀያየሩ በሚፈጽሙት ተደጋጋሚ በደል በአካባቢያችን ያሉትን አብያተ ቤተ ክርስቲያናት ባልወረሩና ወያኔ በሚቆጣጠራቸው መገናኛ አውታሮች ተሰልፈው የኢትዮጵያን ህዝብ የሚያፈኑ ጋዜጠኞች ቁጥራቸው ባልበዛ ነበር።
የሚሆነው እየሆነ ነውና፤ የክርስትና እና የጋዜጠኝነት ባሕርያት ውህደት አለኝ ብለው በድፍረት ስለተናገሩ፤ በሁለቱ መካከል ያሉትን ተመሳሳይነትና ልዩነት ለማሳየት ወደ ሥረ ነገሩ ከመግባቴ በፊት፤ በዚህ ርእስ ይህችን ጦማር ለመጻፍ ሳስብ በኔ ላይ የሚያስከትለውን ጥያቄ በመዘንጋትና የሚከተለኝን ተቃውሞ ቀላል አድርጌ በመውሰድ አይደለም። እንኳን ስላልተሰለፍኩበት ጋዜጠኛነት ሙያ፤ ስለተሰለፍኩበት ስለነገረ መለኮት ከዚህ ቀደም ለመጻፍ በጀመርኩበት ጊዜ ግማሹ “ውሸቱን ነው” ሌሎቹ ደግሞ ‘መናፍቅ ነው” ለሌሎቹ “ከግል ጥላቻ ነው” ጥቂቶቹ ደግሞ “ሲኖዶሱ የተወውን ምን አገባው” ይሉ ነበር። ከዚያም ርቀው በቅስናየ ላይ ጥያቄ የነበራቸውም ነበሩ። ከነዚህም አንዱ እራሳቸው ክርስቲያኑ ጋዜጠኛ አቶ አዲሱ ነበሩ። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply