• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ያለነፃነት የኢኮኖሚ ዕድገት አይኖርም!

January 20, 2015 07:32 pm by Editor Leave a Comment

የሰው ልጅ፣ ከሌሎች ፍጡራን በተለየ ከታደለው ፀጋ ውስጥ አንዱ ስልጣኔ ናፋቂ መሆኑ ነው፡፡ የሰው ልጅ የዝግመተ-እድገት ታሪክ የሚነግረን፣ አለም አሁን ለደረሰችበት የሀያ አንደኛው ክፍለ-ዘመን ስልጣኔ፣ መንስኤው ስልጣኔ ናፋቂ የሆነው የሰው ልጅ በየዘመኑ ያከናወናቸው እንቅስቃሴዎች ድምር ውጤት መሆኑን ነው፡፡ የሰው ልጅ፣ ከሌሎች የፈጣሪ ፍጡራን በተለየ ስልጣኔ ናፋቂ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ከሌሎች ፍጡራን በተለየ ፈጣሪ የማሰብ ፀጋ ስለቸረው ነው፡፡ “ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙላት” እንዲል ቃሉ፤ የሰው ልጅ ዘር መብዛቱን ተከትሎ፤ እንደ ህዝብ በቡድን መኖር ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ የጋራ የሆነ ሀብትን ለመጠቀምም ሆነ እንደ ግለሰብ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ፍትሀዊነት ህግ እና ደንብን ማእከል ያደረገ መንግስታዊ ስርአትን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረ እነሆ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ ይህም ለስልጣኔ መንስኤ የሆነው ከፈጣሪ የተቸረው የማሰብ ነፃነት በመንግስታዊ ስርአቱ ላይ የተንጠለጠለ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በዚህ የውክልና አስተዳደር ውስጥ የኢኮኖሚ እድገት አንዱ ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ፣ ከሚከወኑ ክንውኖች ውስጥ በኢኮኖሚ የዕድገት መጠን ልክ የህብረተሰቡ ኑሮ መሻሻል ዋነኛው ነው፡፡ ከላይ በጠቀስኩት ምክንያት የማሰብ ነፃነት በመንግስታዊ ስርአቱ ላይ የተንጠለጠለ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ትልቁ ጥያቄ እና ክርክር፤ በኢኮኖሚ እድገት ሂደት ውስጥ ነፃነት እና የኢኮኖሚ እድገቱ አብረው መጓዝ አለባቸው ወይስ አንዱ መቅደም አለበት? የሚለው ሆኗል፡፡

በዲሞክራሲያዊ ስርአት ውስጥ የነፃነት እስከየትነት

የዲሞክራሲያዊ ስርአትን አይነት ወደ ጎን ትተን፣ በሁሉም ዲሞክራሲያዊ ስርአት ውስጥ የነፃነት መገለጫን ስናይ፣ በዲሞክራሲያዊ ስርአት ዋነኛ ማእከል የብዙሀኑ ፍላጎት የሚገዛበት ሆኖ፣ በየትኛውም አይነት ዲሞክራሲያዊ ስርአት ጥበቃ የሚደረግላቸው መብቶች ውስጥ የግለሰቦች፣ የመፃፍ፣ የመናገር፣ በነጻነት የመደራጀት፤ ያለምንም ገደብ የመንቀሳቀስ፣ እንደ ግለሰብ የፈለገውን እምነት የማመን፤ በተመቸው ቋንቋ የመናገር ወዘተ ይጠቀሳሉ በአንድ ወቅት በብዙሀኑ ድምፅ ተበልጠው በቁጥር ስሌት የተሸነፈ አመለካከት የያዙ ሰዎች፤ እነኝህን መብቶች ተጠቅመው አመለካከታቸውን የብዙሀኑ ለማድረግ የመሞከርና በሕግ በተቀመጠው የምርጫ ስነ-ስርዓት ተጠቅመው የቀድሞውን የብዙሀን መንግስት ቀይረው እነሱ ብዙሀን የመሆን ሙከራ የማድረግ መብቶችም እንዲሁ የስርዓቱ አባባዎች ናቸው፡፡

በተጨማሪም በየትኛውም አይነት ዲሞክራሲያዊ ስርአት ጥበቃ የሚደረግላቸው መብቶች ውስጥ በፈቃደኝነት የተመሰረቱ የወል ስብስቦች (የሀይማኖት፣ የብሄር፣ የባህል፣ የሞያ ስብስቦች ወዘተ)፣ ባጠቃላይ የማህበረሰቡን እና የሌሎች ዜጎችን መብቶች በማይነካ መልኩ እስከተደራጁ ድረስ የጋራ ጉዳያቸውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት የማካሄድ መብታቸው የተከበረ ነው፡፡ .ባህላቸውንና እምነታቸውን፣ በፍቃደኝነት የሚቀበላቸው እስካገኙ ድረስ የማስፋፋት፣ የውስጥ ጉዳያቸውን የሚያካሂዱበትን የራሳቸውን ህግ እና መዋቅር የመዘርጋት፣ በሚመቻቸው መንገድ ተደራጅተው በጋራ በተቀመጠው ህግ መሰረት የጋራ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ የመንግስትን የጋራ ውሳኔ ለማግባባት መሞከርን፣ በተቀመጠው ህግ መሰረት አቤቱታ የማቅረብ፣ ባደባባይም ተቋውሞ የመግለፅ መብቶችን ያካትታል፡፡ በእኔ እምነት፣ ነፃነት ለኢኮኖሚ እድገት መንስኤ ነው ወይስ ነፃነት ከኢኮኖሚ እድገት በኋላ የሚመጣ ነው የሚለውን ለመፈተሽ የዲሞክራሲ ስርአትን ማእከል በማድረግ ማየት እንደሚያስፈልግ አመላካች ይመስለኛል፡፡

ዲሞክራሲ እና የኢኮኖሚ እድገት ምን እና ምን ናቸው?

በድህነት የሚኖሩ ህዝቦች፣ ቢያንስ መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እስኪያሟሉ ድረስ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ጥያቄ ሁለተኛ ነው ብለው የሚሞግቱ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች ረሀብ፣ በሽታ እና ድንቁርና መገለጫቸው የሆኑ ደሀ ሀገራት፤ ከምንም በፊት ትኩረት ሊሰጡ የሚገባው የኢኮኖሚ እድገትን ማፋጠን ላይ መሆኑን በመግለፅ ነፃነትእና የዲሞክራሲ የሚያስፈልገው የኢኮኖሚ እድገቱ የሆነ ደረጃ ላይ ደርሶ ነፃነትን ለማጣጣም የሚችል ማህበረሰብ ሲፈጥር ብቻ ስለ መሆኑ ይከራከራሉ፡፡ እንደዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ሁሉ፤ ያለ ነፃነት የኢኮኖሚ እድገት የማይታሰብ ነው ብለው የሚሞግቱ ሰዎች የሚያቀርቡት ምክንያት የኢኮኖሚ እድገት ሊኖር የሚችለው፣ ነፃ በሆኑ ግለሰቦች እንቅስቃሴ መንስኤነት መሆኑን በማንሣት ነው፡፡

ዓለም-አቀፍ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት፣ እርዳታን እና ብድርን ተቀብለው የህዝባቸውን ኑሮ ባሻሻሉ እና ባላሻሻሉ የአፍሪካ ሀገራት መሀል ያለው ልዩነት መንስኤው በሀገራቱ መንግስታዊው ስርአት ውስጥ ያለው የተጠያቂነት እና የመልካም አስተዳደር ልዩነት ነው፡፡ በተጨማሪም ዲሞክራሲ ከኢኮኖሚ እድገት በኋላ ነው የሚለው መከራከሪያ ዋጋ ቢስ ስለመሆኑ አመላካች ነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ስርአት ውስጥ የሚገነባው ጠንካራ እና ነፃ ፕሬስ፣ ውስን የሆነውን ሀገራዊ ሀብት ለኢኮኖሚ እድገት በሚል የዳቦ ስም ለግላቸው ጥቅም የሚያውሉ ባለስልጣናትን በማጋለጥ፣ መንግስታዊ ሌብነትን በመከላከል ረገድ ያለው ድርሻ ሌላኛው የዲሞክራሲ እና የኢኮኖሚ እድገትን አይነጣጠሌነት የሚያሳይ ነው፡፡

ለኢኮኖሚ እድገት ዋናው መንስኤ ምርታማነት ሲሆን፣ ለምርታማነት ምክንያት ከሆኑት ውስጥ አንዱ ደግሞ የሰው ሀይል ነው፡፡ የሰው ሀይልን በዋነኛነት ለምርታማነት መንስኤ እንዲሆን ያደረገው ጉልበቱ ሳይሆን የማሰብ ተሰጥኦው ነው፡፡ ለምርታማነት መንስኤ የሆነው የሰው ሀይል፣ የማሰብ ሀይሉን አበልፅጎ ለምርታማነት ምክንያት እንዲሆን ዋነኛው ግብአት ደግሞ ነፃነት ነው፡፡ የሰው ልጅ፣ ያለማንም ተፅእኖ የማሰብ ነፃነቱ ሲዳብር አዳዲስ ሀሳቦችን የማፍለቅ ችሎታው፣አዳዲስ አሰራር የመጠቀም ድፍረቱ ባጠቃላይ ለምርታማነት ያለው ተነሳሽነቱ ይዳብራል፡፡ ይህም ከምንም በላይ የሰው ልጅ ተፈጥሮ በራሱ ዲሞክራሲን እና የኢኮኖሚ እድገትን አንድ ላይ ለማስኬድ እንጂ ኢኮኖሚ እድገትን በማስቀደም ዲሞክራሲን በኋላ ለሚል ንድፈ-ሀሳብ ምቹ አለመሆኑን ያሳያል፡፡

መጀመሪያ ድህነትን እንቅረፍ ዲሞክራሲ በሂደት ነው የሚለው ብሂል የአንባገነኖች መቆመሪያ እንደሆነ የሚያፀኽይ ነው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ የኢኮኖሚ እድገት ሊኖር የሚችለው ነፃ በሆኑ ግለሰቦች እንቅስቃሴ ብቻ መሆኑን እውነታ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ (ምንጭ: ፍኖተ ነጻነት)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule