ንብረትነቱ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እንደሆነ በሚነገርለት ካፍቴሪያ ውስጥ የሚፈጸመው ግፍ አይሏል ። ከዛሬ 10 ዓመት በፊት እዚህ ኮሚኒቲ ካፍቴሪያ ውስጥ በተለያየ የሙያ ዘርፍ ሰማርተው እያገለገሉ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን አብዛኛዎቹ በወጣትነት እድሚያቸው የተቀጠሩ ናቸው።
ታዲያ ለወጣትነት እድሜ ጉልበታቸው ሳይሰቱ ነገን በተስፋ በመናፈቅ ተመጣጣኝ ባልሆነ ክፍያ በቀን ከ 8 ሰዓት በላይ አውዳአመታትን ሳይቀር ያለ እረፍት በስራ በማሳለፍ ኮሚኒቲውን አገልግለዋል። ሰራተኞቹ በተሰማሩበት የስራ መስክ በሚከፈላቸው ደሞዝ እንደማንኛውም ማህበረሰብ ቤትሰብ አፍርተዋል ። እነዚህ ወገኖች እንደመነሻ በተቀጠሩበት አነስተኛ ደሞዝ ከግዜ ወደ ግዜ እየከበደ የመጣውን የስደት ዓለም ህይወት መቋቋም ተስኗቸው ገሚሱ በብስጨት በደረሰበት የጤና መታወክ ለህለፍት ሀይወት ሲዳረግ በስኳር በሽታ አይኑ ታውሮ የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ቤተሰቡን የበተነም እንዳለ ይነገራል። የተቀሩት እንደ ስራ ባልደረቦቻቸው አስከፊው ዕጣ ደርሷቸው ከስራ ገበታ ስኪፈናቀሉ በደም ግፊት እና ተጓዳኝ በሆኑ በሽታዎች የተጎስቆለ አካላቸውን በቁም እያስታመሙ አቤት ቢባል አድማጭ በሌለበት ሰማይ ስር የመጣውን ሁሉ ችለው ከእጅ ወደ አፍ የሆነቸውን ኑሮ ለማሸነፍ በውዴታ ግዴታ ኮፍቴሪያውን ማገልገላቸውን ቀጥለዋል።
ሁሌም ሃዘን እንጂ ደስታ ውስጣቸውን የማይሰማው እነዚህ ወገኖች የወጣትነት ፊት ገጽታቸው ተቀይሮ ያለ እድሜያቸው የተሸብሽው ቆዳቸው ከሰውነት ጓዳና በመውጣት ውስጣቸው ፍጹም፡ ሰላም እንድሌለ ያሳብቃል። ኮሚኒቲውን ለቀው እንዳይሄዱ ጉልበታቸው ዝሎ አቅም አልባ ሆነዋል ! የእድሜውም ጉዳይ በሌላ በኩል በዕንቀርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባቸዋል። ብቻ በአጠቃላይ በ 4 አመት አንድ ግዜ እየጠበቁ ከኮሚኒቲው መተዳደሪያ ደንብ እና ስረዓት ውጭ በኤንባሲው አስተባባሪነት በብሄር እይተቦደኑ ያለችሎታቸው የአመራሩን ቦታ በሚጨብጡ የኮሚቲኒው አስተዳዳሪዎች በሚደርሰባቸው ዛቻ እና ማስፈራሪያ ከደሞዝ ጭማሪ ይልቅ ከስራ ገበታቸው እንዳይፈናቅሉ በስጋት ተሸብበው ፈጣሪ መህረቱን እንዲያወርድላቸው ይማጸናሉ። ለነዚህ የኮሚቲው አንጋፋ ሰራተኞች ክብር ብሎ ነገር አይታሰብም ምግብ በላህ ሻይ ጠጣህ የለስላሳ ማቀዝቀዣ ለመክፈት አሰብክ ተብሎ የጎሪጥ ክትትል እየተደረገባቸው ከሚሰነዘርባቸው አሳፍሪና አስዛኝ ክስ ባሻገር ህይወታቸውን ሙሉ በማገልገላቸው ብቻ ለሞራል የሰርተፍኬት ሽልማት እንኳን አጊተው አያውቁም። አንዳንዴም በተጠቀሱት አመራር አባላት እንደ ሰራተኛ ሳይሆን እንደ ሌባ በአይነ ቁራኛ ይጠበቃሉ። አፋቸውን በሁለት እጆቻቸው ግጥም አድርገው ካልያዙ የመናገር ሰበአዊ መብታቸው ተገፎ አመራር ዘለፉችሃል በሚል ክስ በዝቅተኛ ደሞዛቸው ላይ ከፍተኛ ቅጣት ይጣላል አሊያም ከስራ ገበታቸው ይታገዳሉ፡፡ አልፎ አልፎም አይጥ በበላ ዳዋ እንዲሉ በሁለት አመት አንዴ ከአንድ ገጽ በማይበልጥ ብጣሽ ወረቀት ለማህበሩ አባላት ለይስሙላ በሚቀርብ ሪፖርት በኮሚኒቲው ካፍቴሪያ ካዝና ላይ ለተፈፀመው ነውረኛ ተግባር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠያቂ ሆነው ጣት ይቀሰርባቸዋል።
ሳውዲ አረቢያ ምድር ላይ ይህ ሁሉ ግፍ እና በደል በነዚህ ኢትዮጵያውያን ላይ እይተፈፀመ ያለው በባእዳኑ ሳውዲያን ሳይሆን ሰንደቃላማችን ከፍ ብሎ የሚውለበለብበት ግቢ ውስጥ በሚገኙ ወገናውዊነት በማይሰማቸው ጨካኝ ኢትዮጵያውያን መሆኑ ነገሩን አነጋጋሪ እና ውስብስብ ያደርገዋል። ወትሮስ ለማን አቤት ሊባል ! ዛሬ እነዚህ ግፉሃን ልጆቻቸውን ማስተማር ተስኗቸው ተጨማሪ ግቢ ፍለጋ ከካፍቴሪያው የስራ ሰአት ውጭ በመከራተት አስቀያሚ የስደት ዓለም ህይወታቸውን መግፋት ግድ ቢሆንባቸውም ሁሉም ነገር ግን ጨልሞል።በተላይ የሳውዲ አረቢያ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት የአሰሪ እና ሰራተኛ ደንብ አስመልክቶ ባወጣው ህግ ማናኛውም የውጭ ሃገር ዜጋ አሰሪው ከሚያሰማራው የስራ መስክ ውጭ የትም ሄዶ መስራት እንደማይችል ከተነገረ ወዲህ ለነዚህ ወገኖች የስውዲን አረቢያን ህይወት ያለተጨማሪ ግቢ መግፋት የማይታሰብ በመሆኑ ለከፋ ስቃይ እና መከራ ተዳርገዋል።
Ethiopian Hagere Jed Bewadi ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የላኩት
ማሳሰቢያ ከመረጃው ጋር ተያያዥ የሆነ ምስል ትክክለኛ የኮሚኒቲው ካፍቴሪያ መሆኑን መግለጽ እንወዳለን
Leave a Reply