ቀኑ፡ እሁድ የካቲት 6፤ 2008ዓም/February 14, 2016 ሰዓቱ፡ 1:00 - 5:00 PM ቦታ፡ Sheraton Silver Spring Hotel 8777 Georgia Ave, Silver Spring, MD 20910 ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) እሁድ የካቲት 6፤ 2008ዓ.ም./ February 14, 2016 ከ1:00 - 5:00 PM በሚያደርገው የእኛ ለእኛ ሕዝባዊ ውይይት ላይ እንዲገኙ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ዋናው የትኩረት ሃሳብ በአገራችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ኢፍትሃዊነት፣ ግፍ፣ እስር፣ ግድያ፣ እንዲሁም የአየር መዛባትና አስተዳደራዊ ብልሹነትን ተከትሎ የተከሰተው ችጋር፤ በሌላ በኩል ደግሞ እየጨመረ የመጣውን ሕዝባዊ ዓመጽ ወዴት አቅጣጫ ሊወስደን ይችላል? የሚል ሲሆን ከዚህ አንጻር በሚቀጥሉት ሳምንታት፣ ወራት፣ … የሚከሰተው ነገር የኢትዮጵያን … [Read more...] about እኛ ለኛ ሕዝባዊ መድረክ!
Opinions
የኔ ሃሳብ
Ethiopia and the two Abays
In todays’ Ethiopia the word Abay has become a source of worry for a few and brings despair and anger to the many. We have two Abays that are in the news and they are both causing us internal and external problems. Abay the river አባይ ወንዝ is as victim as the rest of Ethiopia. Poor Abay of Egypt and the great pyramids, the longest river in the world and a name that evokes greatness and pride among Ethiopians is reduced to becoming a prop for Woyane ponzi scheme. The Dam that will never be built … [Read more...] about Ethiopia and the two Abays
የኢትዮጵያ ሙስሊም ፈተና በ224 ደቂቃዎች
ክፍሉ ከኮሪደሩ ላይ ከተንጠለጠለ አምፖል በሚመጣ ብርሃን ፈገግ ብሏል፡፡ እኔም ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ወደ ክፍሉ ስገባ ከክፍሉ አንደኛው ጫፍ ላይ አንድ ቀጠን ያለ ሰው ድምፁን በትንሹ ከፍ አድርጎ ቁርዓን ‹እየቀራ› ነበር፡፡ በክፍሉ ሌላኛው ጫፍ ላይ ደግሞ አንድ ፍራሽ፣ አንድ የውሃ ጀሪካን እና ትንሽ ልብሶች በፌስታል ውስጥ ተቀምጠዋል፡፡ በሌላኛው የክፍሉ ጫፍ ደግሞ የሽንት ባልዲ - ሽታውን ለመቀነስ ሲባል በግማሽ ውሃ ተሞልቶ ተቀምጧል፡፡ ክፍሉ ውስጥ እንደገባሁ አንዱ ጫፍ ላይ ትንሽ ቆም ካልኩ በኋላ በክፍሉ ውስጥ ያገኝሁት ብቸኛው ሰው ፍራሹ ላይ እንድቀመጥ በእጁ ሲጠቁመኝ ቁጭ አልኩ፡፡ ፍራሽ ላይ እንደተቀመጥኩ በፍራሹ ጫፍ ላይ የጆን ግሪሻም ‘The Last Juror’ መፅሃፍ ተቀምጦ አየሁት፤ አንስቼ ስመለከተው ክፍሉ ውስጥ ያገኘሁት ሰው ቁርዓን መቅራቱን ጨርሶ እንግሊዝኛ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ሙስሊም ፈተና በ224 ደቂቃዎች
ከሰርቢያው ነውጥ አልባ ትግል ውጤታማነት ኢትዮጵያችን ምን ትማራለች?
ከክሮሺያ እና ከቦስኒያ ጋር በሁለት ጦርነቶች ተሸንፎ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ያደቀቀው የሚሎሶቪች መንግስት በህዝቡ ዘንድ ይሁንታን ባጣበት ሁኔታ ላይ እያለ እ.አ.አ በ1996 ዓ.ም በተካሄደው የክልል ከተሞች ምርጫ በስርቢያ አጠራር ዛየኖ ወይም ቱጌዘር የተሰኘው ፓርቲ በ40 የክልል ከተሞች ውስጥ ማሸነፍ ችሎ ነበር። ሚሎሶቪች ግን ለምርጫ ቦርዳቸው ውጤቱን እንዳያጸድቅ ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፉ። በዚህም ሳቢያ ተማሪዎች ለ55 ቀናት እለት በእለት ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ተቃውሞ የመንግስት ተወካይ ከተማሪዎች ተወካይ ጋር ባደረጉት ስምምነት ለዛየኖ ወይም ቱጌዘር ለተባለው ፓርቲ በማን አለብኝነት ተነፍጎ የነበረውን 40 መቀመጫዎች መልሶ ማግኘት ቻለ። በተገኘው ድል መጠነኛ የስነልቦና ጥንካሬን ያገኙት እኚሁ ሰልፈኛ ተማሪዎች ለሚሎሶቪች ውድቀት ዋና ተዋናይ ለሆነው ኦትፖር ለተሰኘው ድርጅት … [Read more...] about ከሰርቢያው ነውጥ አልባ ትግል ውጤታማነት ኢትዮጵያችን ምን ትማራለች?
የማስተባበር ጥሪ
መንደርደሪያ ባሁኑ ጊዜ በሃገራችን ለፍትህ፤ ለነጻነትና ለዴሞክራሲ የሚደረገውን ትግል አስመልክቶ፤ ተደጋግሞ የሚነሳው ጥያቄ ተቃዋሚዎች ለምን ተባብረው አይታገሉም? የሚለው ነው። ጥያቄውን ያነሳው ማን ነው ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ ማን ያላነሳው አለ ብሎ መጠየቁ ተገቢ ይመስለኛል። እኔም አልደግመውም። የሃገሪቱን የተወሳሰበ ሁኔታ ስናጤን፤ በመተባበር ለመታገል በቅድሚያ በሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ግልጽ የሆነ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የሞትና የሽረት ጥያቄ አድረጎታል። እነዚህ ሁለት ሁኔታዎችም፤ የትግራይ ሕዝብ ነጻነት ግንባር (ወያኔ) የባርነት አገዘዝ መወገድ አለበት የሚለው ባንድ ወገን፤ ከባርነት አገዛዙ መወገድ በሁዋላ የምትገነባው ኢተዮጵያ በሌላው ወገን ናቸው። ቀዳሚውን የትግራይ ሕዝብ ነጻነት ግንባር (ወያኔ) የባርነት አገዛዝ መወገድ አለበት የሚለውን በተመለከተ፤ በተለያየ … [Read more...] about የማስተባበር ጥሪ
ጥምቀትና ጎንደር Vs የትዝብት ወግ
“ጥምቀትን በጎንደር መታደም መባረክ ነው” ይህ የብዙሃኑ የእምነቱ ተከታዮች የምስክርነት ቃል ነው፡፡ ጥምቀትና ጎንደር የገጠሙ እለት እንኳንስ ለጎብኝዎች ለነዋሪዎችም ታይተው አይጠገቡም፡፡ የጎንደር ጥምቀት በዓል ከመላ ኢትዮጵያ አከባበር የሚለይባቸው በሁለት ተያያዥ ምክንያቶች ይመስለኛል፡፡ ከቀድመው የመሳፍንት እና የአፄዉ ስርዓት ጋር በተያያዘ ከተማዋ ለረዥም ዓመታት መናገሻ ከተማ ሆና መቆየቷ፣ በጊዜው የነበረው ኃይማኖታዊ መንግስት በመሆኑ አብዛኛው ነዋሪ ጥብቅ የኦርቶዶክስ ክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ከሌላው አካባቢ (ከተማ) በተለየ መልኩ “የአርባ አራቱ ታቦታት” መገኛ መሆኗ የመጀመሪያው ምክንያት ሲሆን፤ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በአስራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ከአፄ ፋሲል ቤተመንግሥት ምስረታ በኋላ ከቤተ መንግሥቱ በስተ ምዕራብ በኩል አራት … [Read more...] about ጥምቀትና ጎንደር Vs የትዝብት ወግ
የህወሓት ተስፋፊነት በኢትዮጵያ
በሰሜን በጌምድር (ጎንደር) ወልቃይት ፀገዴ፣ ፀለምት በአማራው ላይ ተስፋፊው ተሓህት/ህወሓት የፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጀል ይህ ታሪካዊ መረጃ በተቀነባበረ መልኩ የሚጀምረው ገና ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ሲፈጠር ጀምሮ አስቀድሞ ለማጥፋት ያነጣጠረው በአማራው ህዝብ ላይ እንደሆነ በማስገንዘብ ነው። ከዚህ በመነሳት የተሓህት ፕሮግራም ገና ከ1967 ጀምሮ የረቀቀው በዲማ ኮንፈረንስ በየካቲት ወር 1968 ከ150 ያነሱ የተሓህት ታጋዮችን በማሰባሰብ ሕጋዊ ሆነ ተብሎ ቢነገርም፣ ሁሉም ታጋዮች ግን አልተቀበሉትም። በመጥፎ መልኩ የተዘጋጀውና አማራውን በማውገዝና ጠላት ብሎ የፈረጀ ነው። በኢትዮጵያና በህዝቧ፣ 1ኛ፣ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አውዳሚ፣ 2ኛ፣ አንድነቱን ጠብቆ ለዘመናት አብሮ የኖረውን የኢትዮጵያ ህዝብ በጎሳ በዘር ለመበታተን ተደምሮና ተቀንሶ የተቀነባበረ አደገኛ … [Read more...] about የህወሓት ተስፋፊነት በኢትዮጵያ
ፍልስፍና አልባ የሆነ አገዛዝና የፖለቲካ ትግል እና ውጤቱ
ከረዥም ጊዜ ጀምሮ በብዙ አፍሪካ አገሮች የሚታየው የአስተዳደር ብልሹነት፣ የህዝቦች ኑሮ መዘበራረቅና ዓላማ-ቢስ መሆን፣ እንዲያም ሲል በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ህዝብ በሃይማኖትና በጎሳ አሳቦ ርስ በርሱ እንዲጠላላ ማድረግና፣ የመጨረሻ መጨረሻም ወደ ርስ በርስ መተላለቅ እንዲያመራ መንገዱን ማዘጋጀት፣ በተራ አነጋገር ከመልካም አስተዳደር እጦት፣ ከአምባገነናዊ አስተዳደር መስፈንና ከዲሞክራሲ አለመኖር ጋር ሲያያዝ ይታያል። አንዳንዶች እንዲያውም እንደዚህ ዐይነቱን ዓላማ-ቢስ የህብረተሰብ ጉዞ የአፍሪካ መሪዎች ወይም የጥቁር ህዝብ ችግር አድርገው የሚመለከቱ አሉ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ፍልስፍና አልባ የሆነ አገዛዝና የፖለቲካ ትግል እና ውጤቱ
ህብረት ህብረት ህብረት አሁንም ህብረት
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ግፍና የፍትህ መጥፋት ስለበዛ ህዝባዊ አመጽ በሁለት መንገድ ሊነሳ ይችላል ሲሉ ቆይተዋል አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች። አንደኛው ህዝብ ራሱ ድንገት የሚያነሳውና የሚመራው (spontaneous አመጽ) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በፖለቲካ ወይም በሲቪክ በተደራጁ ሃይላት ታቅዶ የሚመራ በቅስቀሳና በጥሪ የሚነሳ ሊሆን ነው። ከወር በላይ የሆነውና በኦሮሞ ክልል ውስጥ በሰፊው የተነሳው ተቃውሞ የአዲስ አበባውን ማስተር ፕላን ተከትሎ የተፈጸመውን ማፈናቀል እንደ ማቀጣጠያ አድርጎ የተነሳ በህዝብ የተመራ ህዝባዊ አመጽ ሆኖ ብዙ ሰው በሚገባ እንደተረዳው የህዝቡ ጥያቄ የመንግስት ለውጥ ጥያቄ ነው። ለብዙ ዓመታት ታምቆ የቆየ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ እጦት፣ የመሬት ነጠቃው ጉዳይ ናቸው ዛሬ ይህን ህዝብ አስመርረው- አስመርረው ጎዳና ላይ ያወጡት። ህዝቡ በየቦታው … [Read more...] about ህብረት ህብረት ህብረት አሁንም ህብረት
ድንበር
መግቢያ “ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” በሚል ርእስ ይህች ጦማር የፈለቀችበት ዘመን፤ ኢትዮጵያን ከጎረቤት አገር የሚያዋስኗት ድንበሮችና፤ በውስጥም ዜጎቿ ተከባብረውና ተዋደው የሚኖሩባቸው ወሰኖች የፈረሱበት፤ ረዥም ዘመን የኖሩ ዛፎች የተጨፈጨቡት፤ መልሰው እንዳያቆጠቁጡ፤ (እንዳያንሰራሩ) ግንዶች ከነስራቸው የነገሉበት ዘመን ነው። ለ 25 ዓመት ኢትዮጵያን የገዛው የወያኔ መንግሥት፤ አገሪቱን ከተቆጣጠረበት ቅጽበት ጀምሮ በቅርብ የሚታየው ከሩቅ የሚሰማው መፍረስና መገሰስ ቢሆንም፤ በየዘመኑ ድንበር እየጣሱ ከመጡ ወራሪዎች ጋራ ለዳር ድንበር ስትፋለም የኖረች ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተውህዶ ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ወቅት ምን ትላለች?የሚለው ጥያቄ በኢትዮጵያውያን መካከል ብቻ ሳይወሰን፤ የኢትዮጵያን ታሪክ በሚያውቁ በውጭ አገር ሊቃውንት መካከልም መነጋገሪያ … [Read more...] about ድንበር










