መንደርደሪያ
ባሁኑ ጊዜ በሃገራችን ለፍትህ፤ ለነጻነትና ለዴሞክራሲ የሚደረገውን ትግል አስመልክቶ፤ ተደጋግሞ የሚነሳው ጥያቄ ተቃዋሚዎች ለምን ተባብረው አይታገሉም? የሚለው ነው። ጥያቄውን ያነሳው ማን ነው ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ ማን ያላነሳው አለ ብሎ መጠየቁ ተገቢ ይመስለኛል። እኔም አልደግመውም።
የሃገሪቱን የተወሳሰበ ሁኔታ ስናጤን፤ በመተባበር ለመታገል በቅድሚያ በሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ግልጽ የሆነ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የሞትና የሽረት ጥያቄ አድረጎታል። እነዚህ ሁለት ሁኔታዎችም፤ የትግራይ ሕዝብ ነጻነት ግንባር (ወያኔ) የባርነት አገዘዝ መወገድ አለበት የሚለው ባንድ ወገን፤ ከባርነት አገዛዙ መወገድ በሁዋላ የምትገነባው ኢተዮጵያ በሌላው ወገን ናቸው።
ቀዳሚውን የትግራይ ሕዝብ ነጻነት ግንባር (ወያኔ) የባርነት አገዛዝ መወገድ አለበት የሚለውን በተመለከተ፤ በተለያየ አቅጣጫ ተደራጅተው ሕዝባዊ እንቢተኝነትንም ሆነ፤ ሕዝባዊ አመጽን መርጠናል ብለው በሚታገሉት በኩል ብቻ ሳይሆን፤ ባጠቃላይ ነፍስ
ያወቀ ኢትያጵያዊ ሁሉ በማያሻማ መልኩ ስምምነት የደረሱበትና ጠጠሩም ሁሉ በወያኔው ላይ ያነጣጥር በሚለው መፈክር ጥላ ስር መሰባሰባቸውን እናያለን፤ በኔ እምነት በዚህ መልክ የሚታየው መሰባሰብ ተቃዋሚዎች ለምን አይተባበሩም ለሚለው ጥያቄ ግማሽ መልስ የሰጠ ነው ብዬ ነው የማምነው። በዚህ ላይ የምጨምረው የለኝም፤ (ሙሉውን መልዕክት ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply