• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ፀረ-ወያኔ አቋም ለአላቸው የኢትዮጵያውያን የፖለቲካ፣ የሲቪክ እና የሙያ ማኅበራት በሙሉ

January 28, 2016 08:29 pm by Editor 1 Comment

ጉዳዩ፦ መነሻ የመግባቢያ ኃሣብ ስለማቅረብ፦ እስከ አንድነት ለመድረስ የሚያስችል ውጤታማ ትብብር ለማድረግ መከተል ስለሚገባን አካሄድ፤

ማናችንም እንደምንገነዘበው፣ ባለፉት 40 እና 50 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ስንደራጅ የኖርነው በልዩነቶቻችን ላይ ባተኮሩ ዓላማዎች ዙሪያ ነው። ልዩነቶቻችን ደግሞ ከርዕዮተ-ዓለም ባሻገር፣ በነገድ፣ በጎጥ እና በኃይማኖት ጭምር ያጠነጠኑ በመሆናቸው፣ አንድነታችንን አሳሳቢ ደረጃ ላይ አድርሶታል። ከሁሉም በላይ፣ የትግሬ-ወያኔ በባዕዳን ድጋፍ ተበረታትቶ፣ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የፖለቲካ ሥልጣን ሲጨብጥ፣ ያስተጋባው የዲሞክራሲ ቀቢፀ-ተስፋ እውነት መስሏቸው የተከተሉት ወገኖች አይጠፉም። ሆኖም ይህ ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድን በተግባር ሲያከናውን የሚታየው፥ የቋንቋ ፣ የነገድ ፣ የጎሣ ፣ የዘር ፣ የኃይማኖት ፣ ወዘተርፈ ልዩነቶችን መሠረት አድርጎ ሕዝቡ ለዘመናት ገንብቶት በኖረው ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ግልጽ የጥፋት ዘመቻ ማካሄድን ነው። የትግሬ-ወያኔ ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ በአካሄደው የዘር ልዩነት ፖለቲካ ግፊት፣ ሕዝቡ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ችላ እያለ፣ በቋንቋ ማንነቱ ዙሪያ ብቻ እንዲያስብ እና እንዲደራጅ አድርጓል። በዚህም ምክንያት ለሕዝቡ አንድነት ጌጥ እና ውበት፣ ጥንካሬ እና ልዩ መታወቂያ የሆኑት ነባራዊ ልዩነቶች የጠብ እና የብጥብጥ መነሻዎች ሆነዋል። በዚህ ረገድ የአያሌ ዜጎች ሕይዎት መጥፋቱን፣ ንብረት መውደሙን እናውቃለን። በተለይም ኢትዮጵያውያን ዐማሮች የአማርኛ ቋንቋ በመናገራቸው ብቻ ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢ ተለይተው ሀብት ንብረታቸውን እየተዘረፉ መባረራቸውን ማስታወስ ይበቃል። በዐማራ፣ በአኙዋክ ፣ በሶማሌ እና በሌሎች ነገዶች ተወላጆች ላይ የሚደርሰው የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ሊገታ አለመቻሉ የአደባባይ ምስጢር ነው። ስለዚህ ይህ ድርጊት እየተባባሰ በመሄድ ላይ ስለሆነ፣ አፋጣኝ እና መሠረታዊ መፍትሔ የሚሻ ጉዳይ ነው።

የትግሬ ወያኔው አገዛዝ በሥልጣን ላይ ሊቆይ የሚችለው፣ ፍትሐዊ አስተዳደርን በማራመድ ሳይሆን፣ የጀመረውን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲውን እያራቀቀ በመሄድ ብቻ መሆኑ ከእንግዲህ ሊያጠያይቅ አይችልም። ስለሆነም፣ ይህን የትግሬ ወያኔውን አገዛዝ በጠመንጃ ኃይል ከጨበጠው የፖለቲካ ሥልጣን በእርግጠኝነት በማላቀቅ አሽቀንጥሮ ለመጣል ከኢትዮጵያውያን አንድነት የተሻለ አስተማማኝ መሣሪያ አይኖርም። ለዚህ ደግሞ፣ እስካሁን የተጓዝንበትን የልዩነት ጉዞ በመተው፣ በኢትዮጵያዊነት አገራዊ ስሜት በአንድነት መቆም ያስፈልጋል። ስለሆነም ከልዩነቶቻችን ይልቅ በአንድነታችን ላይ አትኩረን በኅብረት መንቀሳቀስ አማራጭ አይኖረውም ። አንድነት ኃይል ነው፤ ጥንካሬ ነው፤ የማድረግ ብቃት ማረጋገጫ ነው።

ሰሞኑን ከየአቅጣጫው የሚሰሙት የ«እንተባበር» እና የ«አንድነት» ጥሪዎች ወቅታዊ ስለሆኑ አዎንታዊ ምላሽ ሊያገኙ ይገባል። ለተግባራዊነታቸው አስተማማኝ መሠረት ለመጣል ደግሞ፣ «በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል» የሚሉ ወገኖችን ሁሉ አካትቶ፣ ለሚታሰበው አንድነት ጉዞ ፈር ቀዳጅ የሆነ የምክክር መድረክ ይዋል ይደር ሳይባል መፈጠር ይኖርበታል። ለዚህ ሂደት ውጤታማነት ተሞክረው ለግብ ካልበቁ የስምምነት ሙከራዎች ትምህርት ሊቀሰም ይገባል። እንዳለፉት ስምምነቶች ሁሉ የተፈረመባቸው ቀለም ሳይደርቅ ወደ ነበሩበት የመመለስ ሁኔታ እንዳይገጥም፣ የተስማሚ ወገኖችን ይሁንታ ያገኘ የመግባቢያ ሰነድ ሊዘጋጅ ይገባል። ይህ ሰነድ ወደ ዋናዎቹ የስምምነት ጉዳዮች ለመግባት ተስማሚዎቹ ወገኖች አምነውና ዐውቀው፣ የውዴታ ግዴታ የሚገቡበት አስገዳጅ እና ተፈጻሚነት ያለው ይዘት ሊኖረው ይገባል። ሰነዱ ከተዘጋጀ እና ሁሉም አንድነት ፈላጊዎች ተስማምተው ከፈረሙበት በኋላ፣ ለሕዝብ ይፋ ሆኖ ሂደቱን ሕዝቡ በባለቤትነት እንዲከታተለው እና ተስማሚ ወገኖችም የተጠያቂነትና የኃላፊነት ስሜት እንዲያድርባቸው ማድረግ ይገባል።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት አገራችን ኢትዮጵያ የገባችበትን አሳሳቢ ሁኔታ በመግለጽ እና በአስቸኳይ ቢወሰድ አደጋውን ሊያስወግድ ይችላል ብሎ ያመነበትን የመፍትሔ ኃሣብ በመጠቆም ከዚህ በላይ የሰፈረውን አቅርቧል። ለአፈጻጸም ይረዳ ዘንድም፣ ከዚህ በታች የተመለከቱት አስፈላጊ እርምጃዎች በውል እየተጤኑ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያሳስባል።

1. ስምምነቱን የሚመራ ኮሚቴ ሊመሠርት የሚችል የጋራ መድረክ መፍጠር

(ሀ) ይህ መድረክ ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መጠራት ይኖርበታል።

(ለ) መድረኩ ኃላፊነት በወሰዱ ወይም በሚወስዱ ድርጅቶች አማካኝነት ይጠራል።

(ሐ) ለመድረኩ እያንዳንዱ በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ የፖለቲካ፣ የሲቪክ እና የሙያ ማኅበራት በአምስት በአምስት ሰዎች ይወከላሉ፤ ታዋቂ ግለሰቦች እና የኃይማኖት ድርጅቶች እያንዳንዳቸው በአንድ ሰው የሚወከሉ ይሆናል።

(መ) የመድረኩ ኃላፊነትም ለቀረበው የአንድነት ጥሪ አዎንታዊ መልስ ለመስጠት የሚያስችል አስማሚ ኮሚቴ መመሥረት እና አስማሚ ኮሚቴው ሊያተኩርባቸው በሚገባቸው የመግባቢያ ሰነዶች ይዘት ላይ ለመወሰን ይሆናል።

2. የአስማሚ ኮሚቴ አባሎች አመራረጥ

(ሀ) በተዘጋጀው መድረክ በተገኙ አባሎች አማካኝነት በሚደረግ ውይይት ቁጥራቸው ከአሥራ አምስት እስከ ሃያ አንድ የሚሆኑ የኮሚቴ አባሎችን የያዘ ኮሚቴ መመሥረት ።

(ለ) የኮሚቴ አባላቱም ከሚከተሉት አንዱን ወይም ከሁሉም በማቀላቀል መመሥረት ይቻላል።

3. የኮሚቴው አባላት ይዘት

(ሀ) በሁሉም ተስማሚዎች አመኔታና አክብሮት የተቸራቸው ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች፣

(ለ) በኢትዮጵያ ካሉት ነገዶች እና ጎሣዎች ከአምስት መቶ ሺህ ሕዝብ በላይ ያላቸው የነገድ እና የጎሳ ተወካዮች፤

(ሐ) ከኢትዮጵያ ታላላቅ ኃይማኖቶች ታዋቂ አባቶች፤

4. የቴክኒክ የሥራ ቡድን ስለ ማቋቋም

(ሀ) ለሚቋቋመው አስማሚ ኮሚቴ ሥራ መቃናት እና መቀላጠፍ የሚያግዙ በሁሉም ተስማሚ ወገኖች ይሁንታ ያገኙ፣ ወይም ከተስማሚ ወገኖች ተመጣጣኝ ውክልና ያላቸው የቴክኒክ የሥራ ቡድኖች መቋቋም አለባቸው።

(ለ) የእነዚህ የሥራ ቡድኖች ተግባርና ኃላፊነታነታው በግልጽ የሰፈረ፣ ከአስማሚ ኮሚቴው ጋር ሊኖራቸው የሚችለው የሥራ ግንኙነት በማያሻማ መንገድ የተገለጸ መሆን ይኖርበታል።

5. የኮሚቴው የሥራ ጊዜ እና የአፈጻጸም ጉዳዮች

(ሀ) አስማሚ ኮሚቴው በሥራ ላይ የሚቆይበት ጊዜ የተወሰነ መሆን ይኖርበታል።

(ለ) ኮሚቴው ዝርዝር የሥራ አፈጻጸም መመሪያዎችን ያዘጋጃል።

(ሐ) ኮሚቴው የተሳታፊ ድርጅቶችን እና ና ግለሰቦችን አመራረጥ መስፈርት ያዘጋጃል።

(መ) የስምምነቱ ሥነሥርዓት የሚገዛበት ደንብ እና የአሠራር ቅደም ተከተል መመሪያዎች በኮሚቴው ይዘጋጃሉ።

6.ትኩረት የሚጠይቁ ሌሎች ጉዳዮች

(ሀ) ተስማሚዎቹ ወገኖች ከስምምነት ከደረሱ በኋላ ማከናወን ያለባቸውን አንኳር አገራዊ ጉዳዮችን ለይቶ ማስቀመጥ፣

(ለ) ከወያኔ ውድቀት በኋላ ኢትዮጵያ ልትከተለው ስለሚገባ የአስተዳደር እና የፖለቲካ ሥርዓት በአገር አንድነት ከተስማሙ ወገኖች የቀረቡ ኃሣቦችን ማቀናጀት፤

(ሐ) ስምምነቱ የሚካሄድበት አገር፣ ከተማ እና ጊዜ መወሰን፤

(መ) በመግባቢያ ሰነዱ የተስማሙ ድርጅቶችን፣ ቡድኖችን፣ ስብስቦችን እና ማኅበሮችን ማንነትና የሚወክሏቸውን ሰዎች ማንነት ለይቶ መመዝገብ፤

(ሠ) የስምምነቱ ሂደት እና ውጤት የሚገለጽባቸውን ቋንቋዎች መወሰን፤

(ረ) ስምምነቱ በሚገለጽባቸው ቋንቋዎች መካከል የትርጉም ልዩነት ቢከሰት፣ በዋናነት የሚወሰደውን ቋንቋ ለይቶ መወሰን፤

7. ተጨማሪ ማሳሰቢያ

(ሀ) አንድነት የሚፈጥሩ ቡድኖች የሚለያዩባቸው አቋሞች ቢኖሯቸውም የአገር አንድነትን በተመለከተ የሚጋሯቸው እሴቶች ምን እንደሆኑ ተለይተው መቀመጥ ይኖርባቸዋል።

(ለ) በመስማሚያው ወይም መግባቢያው ሰነዱ እና በአሠራሩም ቅደም ተከተል ስምምነት ከተደረገ በኋላ፣ ወደ ዋናው ጉዳይ ሲገባ፣ ስምምነቱ በቀና እና በታሰበው ጊዜ እንዲከናወን፣ ተሳታፊዎች «አሉኝ» የሚሏቸውን የአቋም ጥያቄዎች በክብደታቸው ቅደም ተከተል መሠረት አስማሚው ኮሚቴው በሚወስነው የጊዜ ገደብ ውስጥ በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ማድረግ ሥራን ያቀላጥፋል። ከዚህ በተጨማሪ ስምምነቱም በእነዚያ ነጥቦች ዙሪያ ብቻ እንዲያተኩር መወሰኑ በውይይቱ ወቅት ሰጥቶ ለመቀበልም ሆነ፣ «ይህ ካልሆነ» ብሎ አቋምን አጠንክሮ ለመጓዝ ይረዳል።

እነዚህና መሰል ጉዳዮችን የሚያካትት ሰነድ መዘጋጀት ለሚታሰበው አንድነትና የትብብር ጥሪ ውጤታማነት ያገለግላል ብሎ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ያምናል።

ሐሙስ ጥር ፲፱ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም.

(Thursday January 28, 2016)                                                                

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Firew Ayenachew says

    January 29, 2016 06:19 pm at 6:19 pm

    kegonachihu nen bertu fikir yistachihu

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule