የአዲስ ድምጽ ሬዲዎ ጃንዋሪ 17.2016 3 ሰዎችን፤- 1ኛ. ዶ/ር አረጋዊ በረሄን የትግራዮች ለደሞክራሲያዊ ትብብር ሊቀ መንበር፤ 2ኛ. ዶ/ር በያን አሶቦን ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር 3ኛ/ አቶ ተክሌ የሻውን ከሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት አቅርቦ በኢትዮጵያ ጊዜያዊ ሁኔታ ላይ አወያይቷቸው ነበር። በቅድሚያ አቶ አበበ የተዋንያኑ አመራረጥ የተዋጣለት ስለ መሆኑ ያለኝን አድናቆት ልገልጽለት እወዳለሁ፤ እነሱም ለዚህ መልካም ተግባር ዝግጁ ሆነው መገኘታቸው የሚያስመሰግን ነው። እኔ ታዲያ ያንን ሰፊ ውይይት ለመተቸት የተነሳሁ አይደለሁም፤ ሀሳብ ልሰጥበት በርዕሰ ስላስቀመጥኩት ጉዳይ መዳረሻ የሚሆነኝን ያህል ብቻ ቀንጨብ አድርጌ ለመያዝ ነው። አስተናጋጁ ለሁሉም ያቀረበው የጋራ ጥያቄ፤ "ባሁኑ ሰዓት ብዙዎቻችንን እያበሳጨ ያለው በጣም በየጊዜው የተደረገ ነገር ነው፤ አዲስ ነገር … [Read more...] about በሪሞት ኮንትሮል ትግል መምራት አለመቻልና ሕብረት በዲያስፖራ
Opinions
የኔ ሃሳብ
ኢትዮጵያ ሀገራችን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ልጇን አጣች
በሰብአዊ መብት ተሟጋችነታቸው፣ ለሰላምና ለዲሞክራሲ መስፈን ታጋይነታቸው የሚታወቁት ዶ/ር ማይገነት ሽፈራው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ዶ/ር ማይገነት ሽፈራው ስለ ሰላም የሰበኩ ያስተማሩና የጻፉ ቀንዲል ኢትዮጵያዊ ነበሩ። ድህነትና በሽታ፣ ርሐብና ስደት፣ አምባገነንትና ጦርነት እያለ የኢትዮጵያ ሴቶች መብት መከበር፣ የሰብአዊ መብት መረጋገጥ፣ ዲሞክራሲና ሰላምን ማስፈን አይቻልም በሚል እምነታቸው በጽናት ታግለው ያታገሉ የዘመናችን ጣይቱ ነበሩ። የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ የመናገር የመጻፍ የመሰብሰብ የመደራጀትና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞን የማሰማት መሠረታዊ መብቶች እውን እንዲሆኑ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብአዊ መብት መከበር፣ ለሃገራችን ሰላም፣ የሃገራችን የፖለቲካ ችግር በዲሞክራሲ፣ በመቻቻልና በሰከነ ውይይት እንዲፈታ፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እድሜያቸውን ሙሉ ታግለው ያታገሉ … [Read more...] about ኢትዮጵያ ሀገራችን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ልጇን አጣች
የጥቁር ሕዝብ ኩራት!
መጪውን የአድዋ ቀን ስናስብ “እምዬ ምኒልክ ምን ዓይነት ውርስ ትተውልን ሄዱ?” ብለን እንድንጠይቅ የሚያደርገን ነው፡፡ በመሆኑም ወደ ጦርነት ለመግባት ሳይፈልጉ “በግድ” ወደሄዱበት የጣሊያን ጦርነት መለስ ብለን የሆነውን እንድናስብ ወደድን፡፡ ክተት፡- “እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላትን አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፡፡ እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡ እንግዲህ ብሞትም ሞት ለሁሉ ነውና ስለ እኔ ሞት አላዝንም፤ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፤ እንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፋ፣ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን የባሕር በር አልፎ መጥቷልና እኔም ያገሬ ከብት ማለቁንና የሰዉን መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር፡፡ አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት … [Read more...] about የጥቁር ሕዝብ ኩራት!
ተሰማ ናደው
ለዛሬ የማስታውሳቸው በዚህ ምስል ላይ የሚታዩት የአደዋ ጀግና የአጤ ምንሊክ ታማኝ የጦር አዝማች አቤቶ ልጅ እያሱ ባውሮጳ አቆጣጠር1913 ዘውድ ሲጭኑ እንደራሴ ወይም የቅርብ አማካሪ በመሆን ያገለገሉት ራስ ተሰማ ናደው ናቸው ። በተጨማሪ ራስ ተሰማ እቴጌ ጣይቱ ከምንሊክ ቤተ መንግስት ለቀው እንጦጦ ጋራ ላይ ካለው ዕልፍኝ ውስጥ ከቅጥር ግቢው እናዳይወጡ ታግደው እንዲቀመጡ ካዘዙት መኳንንቶች አንዱ ናቸው። ይህ ድርጊት በእቴጌ ጣይቱ ላይ የተፈጸመው እቴጌ ብልህ ስለነበሩ ከሌሎች ሃይሎች ጋር ተባብረው ልጅ እያሱን ከጥልጣን ያወርዳሉ በሚል ፍራቻ ነበር። ራስ ተሰማ በ1916 ዓም ላይ በራስ ተፈሪ እና ልጅ እያሱ መካከል በተደረገው የሰገሌው የዘውድ ሽኩቻ ጦርነት ላይ ተሳትፈዋል። (ምንጭ: Eduardo Byrono ፌስቡክ ገጽ) … [Read more...] about ተሰማ ናደው
What We Need is Values-Based Leadership
Americans are busy voting for Presidential candidates. Have you asked yourself the parameters they use to choose one candidate over the other? Not just in the US, in those countries where there is true democracy, people tend to vote for those candidates with whom they share key values. That is why the same candidate is loved by some and hated by other voters depending on his values. For instance, on February 2 2016, Fox News Channel reported, “According to entrance polling of Republican … [Read more...] about What We Need is Values-Based Leadership
“ብሔራዊ መግባባት አጀንዳ ባለቤት አገኘ”
በአቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመራው ሰሞኑን በአሜሪካን ሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ በጠራውና "ለመተማመን እንነጋገር" የሚል መሪ መፈክር በያዘው ስብሰባ ላይ ለመገኘት እድሉ አጋጥሞኝ ነበር፡፡ ስብሰባው የጀመረው ከተባለበት ሰዓት "በባሕላችን መሠረት" አንድ ሰዓት ዘግይቶ ቢሆንም ስብሰባው ላይ የተካሄዱት ቁምነገራም ሀሳቦች የስብሰባውን አርፍዶ መጀመር አላስታወሰኝም። በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ ከአውሮፓ ከአውስትራሊያና ከአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የመጡ ኢትዮጵያውያን አሁን ሀገራችን የምትገኝበት እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ እንቅልፍ ያሳጣቸውና የበኩላችንን ማድረግ አለብን ብለው የቆረጡና ኢትዮጵያ የምንላት ሀገራችንን ከሞላ ጎደል የሚወክሉ ተሳታፊዎች ነበሩ። በርግጥም ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታና በውስጧ ያለውን ውስብስብ ችግር ያለምንም አድርባይነትና አስመሳይነት የሚታያቸውን መግለጽ የሚችሉ “ከዘረኝነት … [Read more...] about “ብሔራዊ መግባባት አጀንዳ ባለቤት አገኘ”
“በመጨረሻም ፍትሕ ከጎናችን ትቆማለች”
ነሐሴ 21/2003 ከምሠራበት ቦታ በስልክ ተጠርቼ በተለምዶ ማዕከላዊ ተብሎ ከሚጠራው የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ተወስጄ ከአንዲት ትንሽ ጨለማ ክፍል ውስጥ ከተወረወርኩ በኋላ በማግስቱ አራዳ ወረዳ ፍ/ቤት ቀርቤ የሃያ ስምንት ቀን የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆብኝ ተፈቅዶላቸው፣ ያም ሲያልቅ እንደገና ሌላ ቀጠሮ ተጠይቆ ተፈቅዶላቸው፣ የማይመለከቱኝን ጥያቄዎች ስጠየቅና ስመልስ ቆይቼ ጥቅምት 3/2004 በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቤ የክስ ወረቀት ደርሶኝ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተልኬ እነሆ እስከዛሬ ድረስ ዞን አንድ ቅጣት ቤት ተብላ በምትጠራው ቤት እገኛለሁ፡፡ የቀረበብኝ ክስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀጽ 241 የተመለከተውን በመተላለፍ የአገሪቱን የፖለቲካና የግዛት አንድነት በመንካት ወንጀል ሲሆን ዝርዝሩ፡- “የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦ.ነ.ግ./ … [Read more...] about “በመጨረሻም ፍትሕ ከጎናችን ትቆማለች”
የህወሃት ግፍ እና የሕዝብ ፍጹም ምሬት
በኦሮሚያ የተማሪዎች ተቃውሞ የተጀመረው በኖቬምበር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጊንጪ በመባል በምትታወቀው ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ በስተ ደቡብ ምዕራብ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው አነስተኛ ከተማ ሲሆን መንስዔውም የመንግስት ባለስልጣን አካላት በአካባቢው የሚገኘውን ደን ለኢንቨስትመንት ልማት በሚል ለመመንጠር በመሞከራቸው ነው፡፡ ተቃውሞው ወዲያው ወደ ሌሎች የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የተስፋፋ ሲሆን የተቃውሞው ጥያቄም በመስፋት የአዲስ አበባ የተቀናጀ የልማት ማስተር ፕላን በመባል የሚታወቀውን የአዲስ አበባ ማዘጋጃቤት ድንበር የማስፋፋት እቅድ ተቃውሞ ያካተተ ሆኗል፡፡ ተቃውሞው እስከ ዲሰምበር ወር ሲቀጥል ገበሬዎች እና ሌሎችም ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል፡፡ በርካታ ተቃውሞ አድራጊዎች እንዳስታወቁት መንግስት ተቃውሞውን በጉልበት ለማስቆም የፈጸመው ተግባር እና በዚህም … [Read more...] about የህወሃት ግፍ እና የሕዝብ ፍጹም ምሬት
ተቃውሞ አድራጊዎች ላይ የሚደረገው አፈና አልቀነሰም
ከኖቬምበር ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በስፋት እየተካሄደ ያለውን ሰላማዊ ተቃውሞ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይል በጉልበት እያፈነው እንደሚገኝ ሂውማን ራይትስ ወች ዛሬ አስታወቀ፡፡ ከ2016 ዓ.ም. መነሻ ጀምሮ በእየለቱ ሰዎች እንደሚገደሉ እና በዘፈቀደ እንደሚታሰሩ ሂውማን ራይትስ ወች አስታውቋል፡፡ የወታደራዊ ሰራዊትን ያካተተው የጸጥታ ሃይል ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ላይ የሚገኙ በርካታ ሰዎችን ቀጥታ በመተኮስ ገድሏል፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረው ያለምንም ክስ እንደታገቱ ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሳምንታት የተቃውሞው ድግግሞሽ የቀነሰ መስሎ ቢታይም አፈናው ግን ቀጥሏል፡፡ “ኦሮሚያን በበርካታ የጸጥታ ሃይሎች የማጥለቅለቅ እርምጃ የሚያመለክተው በተማሪዎች፣ ገበሬዎች እና ሌሎች ተቃዋሚዎች የሚደረገውን ሰላማዊ ተቃውሞ ባለስልጣን አካላቱ በከፍተኛ ሁኔታ አለመፈለጋቸውን … [Read more...] about ተቃውሞ አድራጊዎች ላይ የሚደረገው አፈና አልቀነሰም
ከአሜን ባሻገር በበዕውቀቱ ስዩም
ከአሜን ባሻገር በ19 ምዕራፎች የተቀነበበች246 ገጽ የሆነች ተነባቢ መፅሃፍ ነች። የዞን ዘጠኙ በፍቃዱ እንደነገረን ከሆነ አብዛኛዎቹ ምእራፎች በመጽሄትም በጋዜጣም የወጡ ስለነበሩ አዲስ አይደሉም ብሏል። በመጽሄትና በጋዜጣ የሚወጡ መጣጥፎች ማጣቀሻ ዋቢ ስለማያክሉ ከጊዜ ብዛትም ጸሀፊውም ስለሚረሳቸው የይድረስ ይድረስ ነገር ሻጥ ሻጥ ይደረጋሉ። የበዕውቀቱ ከአሜን ባሻገር በዚህ ረገድ ጉልህ ጎደሎነት አሳይቷል። ከቤተ አማራ ፖለቲካ አቀንቃኞችንም ጋር እሰጥ አገባ ያስገባው ይሄ የመጽሃፉ ደካማ ጎን ለምንጭ ለዋቢ የሚሰጠው ግምትና ቦታ። በሁለተኛው እትም ይስተካከላሉ የሚል ግምት አለኝ። ስለ 19ኞቹ መጣጥፎች በዕውቀቱ በ13 ቃላት በሁለት አረፍተ ነገር ሲገልጽ “መጣጥፎቼ የእንጉርጉሮና የልግጫ ድብልቅ ናቸው። የሐሳብ አርአያዎቼ አንጎራጓሪ ሴቶች እንጂ ፕሮፌሽናል ፖለቲከኞች … [Read more...] about ከአሜን ባሻገር በበዕውቀቱ ስዩም










