
የአዲስ ድምጽ ሬዲዎ ጃንዋሪ 17.2016 3 ሰዎችን፤- 1ኛ. ዶ/ር አረጋዊ በረሄን የትግራዮች ለደሞክራሲያዊ ትብብር ሊቀ መንበር፤ 2ኛ. ዶ/ር በያን አሶቦን ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር 3ኛ/ አቶ ተክሌ የሻውን ከሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት አቅርቦ በኢትዮጵያ ጊዜያዊ ሁኔታ ላይ አወያይቷቸው ነበር። በቅድሚያ አቶ አበበ የተዋንያኑ አመራረጥ የተዋጣለት ስለ መሆኑ ያለኝን አድናቆት ልገልጽለት እወዳለሁ፤ እነሱም ለዚህ መልካም ተግባር ዝግጁ ሆነው መገኘታቸው የሚያስመሰግን ነው።
እኔ ታዲያ ያንን ሰፊ ውይይት ለመተቸት የተነሳሁ አይደለሁም፤ ሀሳብ ልሰጥበት በርዕሰ ስላስቀመጥኩት ጉዳይ መዳረሻ የሚሆነኝን ያህል ብቻ ቀንጨብ አድርጌ ለመያዝ ነው።
አስተናጋጁ ለሁሉም ያቀረበው የጋራ ጥያቄ፤ “ባሁኑ ሰዓት ብዙዎቻችንን እያበሳጨ ያለው በጣም በየጊዜው የተደረገ ነገር ነው፤ አዲስ ነገር አይደለም፤ ነገር ግን አሁን ለሁለትና ለሶስት ወር የቆየ ሊቆም ያልቻለ ማባሪያ የሌለው ግድያ ባገዛዙ በተለይ በኦሮሞ ክፍለሃገር የተለያየ አካባቢ ወገኖቻችን እየተገደሉ፤ እየታሰሩ፤ እየተፈናቀሉ ነው የሚገኙትና እንዴት ነው የተከታተላችሁትና የህብረተሰቡስ ጥያቄ፤ ያለውን ሁኔታ በእናንተ ዕይታ እንዴት ነው ያያችሁት?” የሚል ሲሆን፤ ተጠያቂዎቹን ተራ በማስያዝ መልስ እንዲሰጡ አደረገ። ዶ/ር በያን ጀመሩ፤ ዶ/ር አረጋዊ ቀጠሉ አቶ ተክሌ የሻው አሳረጉ። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል)
Leave a Reply