በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካና ማህበራዊ ቀውስ አስመልክቶ እሁድ ፌብሩዋሪ 14 ቀን፣ 2016 ከቀኑ 2:00pm 7:30 pm በሳን ሆዜ ከተማ ማሶኒክ ሴንተር፤ የተጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ አራት ተናጋሪ እንግዳወች፣ የእምነት አባቶች፣ እንዲሁም ከተለያዩ የሰሜን ካሊፎርኒያ ከተሞች የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት ሲሆን ከፍተኛ የሐገር ፍቅር ስሜት እና የትብብር መንፈስ በታየበት ሁኔታ ተጠናቋል።
አዘጋጅ ኮሚቴውን ወክለው ስብሰባውን የመሩት ዶ/ር አበበ ገላጋይ፤ የውይይቱ ትኩረት ለሱዳን ስለተሰጠው የሀገራችን ለም መሬት፣ በወገናችን ላይ ስለደረሰው የድርቅና የረሀብ አደጋ፣ ስለሰብአዊ መብቶች መጣስ፡ የህዝብ መፈናቀል እና የኢትዮጵያ ህዝብ የአብሮነት ትስስሮች ላይ መሆኑን ገልጸው፤ አላማውም በተለያዩ ምክንያቶች የተራራቀውን ማህበረሰባችን በማቀራረብ የጋራ ችግሮቹን በጋራ ተወያይቶ የጋራ መፍትሄ ለመሻት መሆኑን ገልጸዋል። በመቀጠልም ስብሰባውን በቡራኬ ለመክፈት በሕዝቡ መሃል የተገኙትን የሐይማኖት አባቶች ወደ መድረኩ ጋብዘዋል። በስበሰባው የተገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና የእስልምና እመነት አባቶች፤ አንድ ላይ ቆመው፣ ስለተራበው ህዝብ በጋራ በመጸለይ፣ ስብሰባውን በቡራኬ ከፍተዋል። በተጨማሪም፤ ሁለቱ አባቶች ሀገራችን የተከሰተውን የረሀብ አደጋ ለመታደግ ኢትዮጵያውን ሁሉ መርዳት እንደሚገባቸው በማሳሰብ፤ ስብሰብው የተሳካ እንዲሆን ምክራቸውን በአንድ ድምጽ አስተላልፈዋል።(ሙሉው ዘገባ እዚህ ላይ ይገኛል)
Leave a Reply