• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮጵያ ሀገራችን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ልጇን አጣች

February 28, 2016 12:08 am by Editor 1 Comment

በሰብአዊ መብት ተሟጋችነታቸው፣ ለሰላምና ለዲሞክራሲ መስፈን ታጋይነታቸው የሚታወቁት ዶ/ር ማይገነት ሽፈራው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ዶ/ር ማይገነት ሽፈራው ስለ ሰላም የሰበኩ ያስተማሩና የጻፉ ቀንዲል ኢትዮጵያዊ ነበሩ። ድህነትና በሽታ፣ ርሐብና ስደት፣ አምባገነንትና ጦርነት እያለ የኢትዮጵያ ሴቶች መብት መከበር፣ የሰብአዊ መብት መረጋገጥ፣ ዲሞክራሲና ሰላምን ማስፈን አይቻልም በሚል እምነታቸው በጽናት ታግለው ያታገሉ የዘመናችን ጣይቱ ነበሩ። የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ የመናገር የመጻፍ የመሰብሰብ የመደራጀትና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞን የማሰማት መሠረታዊ መብቶች እውን እንዲሆኑ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብአዊ መብት መከበር፣ ለሃገራችን ሰላም፣ የሃገራችን የፖለቲካ ችግር በዲሞክራሲ፣ በመቻቻልና በሰከነ ውይይት እንዲፈታ፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እድሜያቸውን ሙሉ ታግለው ያታገሉ እናት፣ እህትና ወገን ነበሩ።

ዶ/ር ማይገነትሽፈራው (Ethiopian Women for peace and development (EWPD)) እ.ኤ.አ. በ1991 ዓም ከመሥራቾቹ አንዷ በመሆን ለ21 ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን በ2012 ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ጉባኤ ባደረገውም ተከታታይ ስብሰባ የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ማዕከልን (Center for Rights of Ethiopian Women (CREW)) ሲመሠረት ሀሳቡን ከመጠንሰስ ጀምሮ በምሥረታው ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረጉትና ከመሥራቾቹ አንዷ ናቸው።ከተመሠረተም በኋላበ ተደጋጋሚ በመመረጥ ድርጅቱን በብቃት የመሩ የመሪነት ችሎታቸውን በተግባር ያስመሰከሩ ናቸው።

ይህ አዲስ የተወለደው የሴቶች ማዕከል የተነሳበት ዓላማና የሚታገልላቸው ጥያቄዎች የኢትዮጵያ ሴቶች የሰላምና የልማት ድርጅት (EWPD) ለ21 ዓመታት ሲታገሉላቸው ከነበሩት ዓላማዎች ጋር አንድ በመሆናቸው ተመሳሳይ ድርጅት ለየብቻ ሆኖ ኃይልና ጉልበትን ከመከፋፈል በአንድ ላይ ሆኖ ያለውን ጉልበት አሰባስቦ ጠንክሮ ለውጤት በመሥራት የተሻለና ጠንካራ የሴቶች ድርጅት በመሆን ለኢትዮጵያ ሴቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማህበራዊ ፍትህ፣ለሰብአዊ መብት መከበር፣ ለዲሞክራሲ መብት መስፈን እየታገሉ የሴቶችን በራስ የመተማመን አቅም ለማጎልበት እጅለ እጅ ተያይዞ መሥራት የወቅቱ ቁልፍ መፍትሔ መሆኑን በማመን ለ21 ዓመት በጽናት የቆዬውን የኢትዮጵያ ሴቶች የሰላምና የልማት ድርጅት የሠራቸውን ሕዝባዊ ሥራዎችንና ያካበተውን የትግል ልምድ ይዞ ኢትዮጵያ ሀገራችን የሰብአዊ መብት የሚከበርባት፣ የሕግ የበላይነት የሚያብባት፣ ሰላም የሰፈነባትና የሴቶች ስብእናቸው የሚከበርባት አገር እንድትሆን በጋራ ቆሞ ለመሥራት ከኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ማዕከል ጋር አንድ በመሆን ሲዋሃድ ዶ/ር ማይገነት ሽፈራው ውህደቱን እውን እንዲሆን ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል::

ዶ/ር ማይገነት ሽፈራው የኢትዮጵያ ሴቶች ጠንካራ ተቋም እንዲኖራቸውና በሃገራቸው የፖለቲካ፣ የኤኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዲኖራቸው በነበራቸው ከፍተኛ አላማና ምኞት ንቃተ ህሊናቸውን ለማሳደግ የመጀመሪያው እርምጃ ሴቶች ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ እንዲማሩ የሚያበረታቱና የሚያስተምሩ ኃላፊነት የሚሰማቸው አብነታቸው ብዙዎችን የሚያነሳሳ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሴቶችን ለመሪነት ማብቃት ለነገ የማይባል ግዴታችንና ኃላፊነታችን ነው ብለው የሚያምኑ ለዚህም ሳያሰልሱ ያስተማሩ ምርጥ መምህር ነበሩ።

የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ማእዕከል (CREW) መሪውን በማጣቱ የተሰማውን ከፍተኛ ኃዘን እየገለጸ ዶ/ር ማይገነት በተውሉንን መልካም ሥራዎቻቸውንና በጎ ሀሳባቸው እየተጽናናን የደከሙበትንና የታገሉለትን አላማና አርማ ቀጣዩ ትውልድ በማንሳት የነገይቱ ኢትዮጵያ የሃገራችን የፖለቲካ ችግር በዲሞክራሲና በሰከነ ውይይት ተፈትቶ የሴቶች መብት የሚሰፍንባት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብአዊ መብት የሚከበርበት፣ የመልካም አስተዳደር መሠረት የሚጥልበት እንደሚሆን ጥርጥር አይኖረንም።

“ዞሮ ዞሮ ከቤት ኖሮ ኖሮ ከመሬት” የማይቀርበት የህይወት ጉዞ ነውና ለዶ/ር ማይገነት የሰላም እረፍት እንዲሆንላቸው እየጸለይን፤ እንዲሁም ለባለቤታቸው፣ለልጆቻቸው፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብርታትና መጽናናትን እንመኛለን።

የኢትዮጵያሴቶችየመብትማእዕከል (CREW)

የዶ/ር ማይገነት ሽፈራው የቀብር ስነስርአት ፕሮግራም የሚካሄደው ሰኞ ፌብሩዋሪ 29, 2016 ነው፡፡ የቤተክርስትያን ስነስርአት የሚፈዐመው፡ ከ 10፡00 ኤ.ም – 1፡00 ፒ.ኤም
ቦታው፡ ቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን
አድራሻ፡ 2601 Evarts St. N.E Washington DC 20018

የቀብር አገልግሎት የሚከናወነው፡ 2፡00ፒ.ኤም

የቀብር ቦታ አድራሻ፡ 9500 Riggs RD Adelphi, MD,20783

ከቀብር ስነስርአቱ ፍፃሜ በኋላ የምሳ ፕሮግራም በቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ተዘጋጅቷል፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Yikir says

    March 29, 2016 10:51 pm at 10:51 pm

    Toomoosgen ale weyane.Bekaliti biretabiret dimitsu. Lekas Kaliti yeweyane “oshutiz” oshutiz magoriyaw new. BEKALITI ANEGAGER LESEW MEBIT YEMITAGELU SEWOCH SIMOTU GINBOT 19 new.BENEGATAW GINBOT 20 malet new.”

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule