"ምን አባቴ ላድርግ?" አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ. . .እኔ ደግሞ የምለው አይዞት ክቡር ሚኒስትር ፤ አንድ ነገር ብቻ ያድርጉልን. . .እባክዎት ቀፎ መሆኑን ያቁሙልን። እንዴ ደግሞ የምን ቀፎ ነው? ቀፎ ስትል ምን ማለትህ ነው? ብሎ ግራ በመጋባት ለሚጠይቅ. . .ስለ ቀፎ ታሪክ ትንሽ ጀባ ልበል። ነፍሳችውን ይማርና የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለሰ ዜናዊ አገሪቱን እንደዚህ ጉድ በጉድ ወይም የጉድ አገር አድርገው ወደ ማይቀረው ሞት ሲሄዱ እሳቸውን የሚተካ ማን ይሆን? የሚለው ጉዳይ በፓርቲው ውሰጥ መጠነ ሰፊ መገራገጭ ፈጥሮ ነበር። ብዙ መላምቶችም ይመቱ ነበር፡፡ የሆነው ሆነ እና በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ በሚለው ዲስኩር እንዲሁም በብዙ አጀብ አቶ ሃይለማርያም ቦታቸውን ተኩ፡፡ አሊያም ተተክተው ቦታቸው ላይ ተዘፈዘፉ፡፡ በዚያ ወቅት አንዱን "የጊዜው" ሰው የሚባለውን … [Read more...] about ቀፎ አይሁኑ!
Opinions
የኔ ሃሳብ
ዐማራው ከወልቃይት፣ጠገዴ እና ጠለምት ሕዝብ ጥያቄ ጎን ሊቆም ይገባዋል!
የማንኛውም አመፅ መነሻ መሠረቱ፣ ገዥዎች በሕዝብ ላይ የሚያደርሱት፣ የኢኮኖሚ ብዝበዛ፣ የመብት ረገጣ፣ የማንነት ነጠቃ እና የሥነ-ልቦና ሰለባ ልኩን አልፎ ገደብ ሲጥስ የሚፈጥረው ምሬት እንደሆነ ይታወቃል። የትግሬ ወያኔ ዘረኛ እና ከፋፋይ የፋሽስት ሞሶሎኒ ዓላማ አራማጅ ቡድን፣ በወልቃት ፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በሠቲት እና በአርማጭሆ ሕዝብ ላይ በተናጠል፣ እንዲሁም በዐማራው ነገድ ላይ በወል፣ ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ከ1972 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 36 ዓመታት በተከታታይ ፈጽሟል፤ እየፈጸመም ነው። በዚህ ረገድ የወረዳ ግዛቶቹም ሆኑ ነዋሪው ሕዝብ በየትኛውም ጊዜ፣ የትግራይ የግዛት አካል ሆነው አያውቁም። የትግሬ ግዛት ደንበርም ተከዜን ተሻግሮ አያውቅም። ሕዝቡም ጥንትም ሆነ ዛሬ፣ በጉርብትና ከሚናገረው ትግርኛ፣ ዐረብኛ እና መሰል ቋንቋዎች በቀር፣ … [Read more...] about ዐማራው ከወልቃይት፣ጠገዴ እና ጠለምት ሕዝብ ጥያቄ ጎን ሊቆም ይገባዋል!
A Study Summary on the Crime of Ethnic Cleansing Perpetrated on the Amhara of Ethiopia, 1991 – 2016
To: Members of European Parliament, Wiertzstraat 60, B-1047 Brussels, Belgium United Nations Human Rights, Office of the High Commissioner for Human Rights From: Moresh Wegenie Amhara Organization (MWAO) 8221 Georgia Avenue Silver Spring, Maryland, MD 20901 USA. Moresh Wogenie Amara Organization (MWAO), which sponsored the study on the Crime of Ethnic Cleansing Perpetrated on the Amhara of Ethiopia, 1991-2016, is an Amhara Organization based in America. It is legally registered in Maryland, … [Read more...] about A Study Summary on the Crime of Ethnic Cleansing Perpetrated on the Amhara of Ethiopia, 1991 – 2016
የወያኔ የጎሣ ፌደራሊዝም ሲፈተሽ
የወያኔ አስተዳደር የማዕከላዊውን የመንግሥት ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ በሀገሪቱ ተግባራዊ ያደረገው የፌደራል ሥርዓት ጎሣን መሠረት ማድረጉ የሚታወቅ ነው። እንደ ወያኔ አገላለጽ ይህ የጎሣ ፌደራሊዝም በኢትዮጵያ ደም መፋሰስን ያስቀረና ሀገሪቱንም ከመበታተን አደጋ የሚታደግ ነው ይላል። ይሁን እንጂ በተግባር እየተፈፀመ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ስንፈትሽ ይህ ወያኔ-ሰራሽ የሆነው የጎሣ ፌደራሊዝም ዓላማም ሆነ እያስከተለ ያለው ውጤት ከዚህ በተቃራኒ ሆኖ እናገኘዋለን። በመጀመሪያ ምንም እንኳን በሕገ መንግሥቱ ላይ “ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብት አላቸው” ቢልም በተግባር ግን አምስት ብሔሮች ብቻ የራሳቸው ክልል እንዲኖራቸው አድርጓል። ሌሎች ከሰባ አምስት በላይ የሚሆኑ ብሔረሰቦች ወይ ባለብዙ ብሔር ክልል በመፍጠር በዚያ እንዲታቀፉ ሲያደርግ፤ አልያም … [Read more...] about የወያኔ የጎሣ ፌደራሊዝም ሲፈተሽ
ለሞረሽ የዐማራ ድምፅ ሬድዮ አገልግሎት የገንዘብ እርዳታ ጥየቃ ማስታወቂያ
ለሞረሽ የዐማራ ድምፅ ሬድዮ ሥርጭት መጀመር የሚያግዘንን ገንዘብ በተከታታይ እርዳታ መጠየቂያ። ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማስታወቂያና የሕዝብ ግንኙነት … [Read more...] about ለሞረሽ የዐማራ ድምፅ ሬድዮ አገልግሎት የገንዘብ እርዳታ ጥየቃ ማስታወቂያ
“ለሕዝብ ይፋ ካላደረጋችሁት የፋይናንስ ሪፖርቱን እሰጣችኋለሁ”
የሆላንድ ዜምብላ ጋዜጠኞች የኦሮሞ ጸሃፊው የሆነውን ያሶ ካባባን ይዘው ወደ ጊንጪ ያመራሉ። እግረመንገድ ላይ የሚያገኟቸው ገበሬዎችም ሲጠይቋቸው በምስሉ ይታያል። እነዚያ በቀያቸው ማረፍያ እንኳን የሌላቸው ገበሬዎች የጋዜጠኞቹን መኪና ከብበው እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ። "መሬታችንን ቀምተው ለነጮች ሰጡብን። እኛንም በታተኑን..." በገዛ ቀያቸው ስደተኛ የሆኑ እነዚህ ወገኖቻቸን ሰቆቃቸው የከፋ ነበር። በመጨረሻ ተሰባሰቡና መከሩ። ሰባት ሺህ የሚሆኑ የጊንጪ ተወላጆች ሆ! ብለው ወጥተው ይህንን የሁለት ሚሊዮን ዩሮ (ሃምሳ ሚልዮን ብር) ንብረት በሰኮንዶች ውስጥ አወደሙት። ምስላቸውን ለካሜራ ሳይደብቁ፣ ስሜታቸውን እና የወደፊት እቅዳቸውን ይናገራሉ። "ከአምባገነን መንግስት ጋር አብሮ ከመስራት ይልቅ የአካባቢው ነዋሪዎች ሊጠቀሙ በሚችሉበት መንገድ መስራት እንደሚችሉም" ለፈረንጆቹ ይመክራሉ። … [Read more...] about “ለሕዝብ ይፋ ካላደረጋችሁት የፋይናንስ ሪፖርቱን እሰጣችኋለሁ”
የሽብርተኛ ትርጉም
የሚማር የለም እንጂ የሚማር ቢኖር የሽብርተኛነትን ትርጉም ሰሞኑን በቤልጂክ እያየንና እየሰማን ነው፤ በኢትዮጵያ ያሉ የእውቀት ምልክቶችን በዶላር እየገዙ ስማቸው ላይ የለጠፉ ጉልበተኞች ተናገርክ(ሽ) ብለው ብቻ ሳይሆን አሰብህ(ሽ) ብለው ሰፋፊ እስር ቤቶች እያሰሩ ወጣቶችን ሲያጉሩበት ምክንያታቸው ሽብርተኛነት ነው፤ ሽብር ማለት ሰሞኑን በቤልጂክ አውሮጵላን ጣቢያና በባቡር ጣቢያ ላይ እንደታየው ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ አልታየም፤ ከታየም በአገዛዙ ኃይሎች የተፈጸመ ነው፤ ለብዙ ዓመታት ሲፈጸም የቆየ ነው፤ የኢትዮጵያ ጉልበተኞች ከቻሉ ሊያስተውሉት የሚገባ አንድ ነገር አለ፡- ሽብርም ነጻነትን ይፈልጋል፤ በቤልጂክ ሽብሩን የፈጸሙት ሁሉ ነጻነትን ፈልገው ከአገራቸው የተሰደዱና በአገራቸው ያላገኙትን ነጻነት በሰው አገር እየተሞላቀቁበት እንደሆነ የሚያመለክት ነው፤ ትርጉሙ፡- ነጻነት በሌለበት … [Read more...] about የሽብርተኛ ትርጉም
የስልጣን ተስፈኛ ፖለቲከኞች
የኢህአዴግ የቁርጥ ቀን ልጅ ልደቱ አያሌውና ፓርቲው ኢዴፓ ባዲስ ትርፍ የፓርላማ መቀመጫ ፍለጋ ሰሞኑን ከእንቅልፋቸው መንቃታቸውን ሰምቼ ትንሽ ተገረምኩ። በውል ያልተደነቅሁበት ምክንያት ኢዴፓንና ሌሎች በኢህአዴግ-ወለድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ም/ቤት ውስጥ የታጨቁ የስልጣን ተስፈኞች እንጂ ፖለቲካ የሚያውቁ ቁርጠኛ ተቃዋሚዎች ናቸው ብዬ ስለማላውቅ ነው። ደግነቱ ደግሞ ነገሩ እውነት መሆኑ ነው። እነዚህ ኢህአዴግ በልካቸው በሰራላቸው ጉረኖ ታሽገው በኢትዮጵያ ህዝብ መስዋእትነት ስልጣን ለመቀላወጥ በተስፋ የሚያደቡት ኢዴፓና አጃቢዎቹ ሰሞኑን የኢህአዴግ ዙፋን ሲነቃነቅ በፈጠረው የፖለቲካ ስንጥቅ ለመሰካት በጠቅላይ ሚንስትሩ እግር ስር ወድቀው ትራፊ ወንበር እንዲረጥቧቸው ልመና መጀመራቸውን ሰምቼ አፈርኩባቸው። የኢዴፓ ሊቀመንበር ዶክተር ጫኔ ከበደ አርብ መጋቢት 16 ቀን 2008 ዓም ለአሜሪካ … [Read more...] about የስልጣን ተስፈኛ ፖለቲከኞች
በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጣዊ መግለጫዎች
ገዢው አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት በየዕለቱ በሚያደርገው ፀረ-ኢትዮጵያዊ ተግባር፤ የተለያዩ የፖለቲካ ሕዝባዊ ስብስቦች መግለጫ ያወጣሉ። አዳዲስና ነባር የፖለቲካ ድርጅቶች፤ አለን በማለት ስማቸውን በአንባቢዎች ያስመዘግባሉ። ለመሆኑ ጋዜጣዊ መገለጫዎች ለምንድን ጉዳይ ነው የሚወጡት? ማነው የሚያወጣቸው? መግለጫዎችን ተከትሎ የሚተገበሩት ምንድን ናቸው? አሉስ ወይ? መግለጫ አውጪዎቹና መግለጫ ያላወጡ የፖለቲካ ሕዝባዊ አካሎች መለያቸው ምንድን ነው? መግለጫዎችና አውጪዎቻቸው፤ ሕዝባዊ ናቸው ወይንስ ጠባብ ወገንተኛ? መልዕክት አላቸው ወይንስ አደረግሁ ለማለት የተወረወሩ? አስፈላጊነታቸውስ ምን ያህል ነው? በተደጋጋሚ ጋዜጣዊ መግለጫ በተንጎደጎዱ ወቅት የደረሱኝ እጦማሮች ነበሩ። ሁሉም ወቀሳዎች ናቸው። “ለምን መግለጫ አታወጣም?” “ካሁን በፊትም ዝም ብለሃል!” የሚሉና … [Read more...] about በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጣዊ መግለጫዎች
Leadership Gap: The main reason why we keep failing to topple dictatorship
In the last couple of decades, people around the world fought and toppled dictators. Courageous Africans removed dictators from Benin, Zambia, and Ghana in the 90’s and early 2000. The Arab Spring that took place in the northern African countries such as in Tunisia, Egypt, and Libya ousted despots.Likewise, successful revolutions in Asia like the one in Philippines (Yellow Revolution)that took place in 1986 overthrew President Ferdinand Marcos. In the beginning of the new century, Rose, Orange, … [Read more...] about Leadership Gap: The main reason why we keep failing to topple dictatorship









