• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሽብርተኛ ትርጉም

March 31, 2016 01:31 am by Editor 1 Comment

የሚማር የለም እንጂ የሚማር ቢኖር የሽብርተኛነትን ትርጉም ሰሞኑን በቤልጂክ እያየንና እየሰማን ነው፤ በኢትዮጵያ ያሉ የእውቀት ምልክቶችን በዶላር እየገዙ ስማቸው ላይ የለጠፉ ጉልበተኞች ተናገርክ(ሽ) ብለው ብቻ ሳይሆን አሰብህ(ሽ) ብለው ሰፋፊ እስር ቤቶች እያሰሩ ወጣቶችን ሲያጉሩበት ምክንያታቸው ሽብርተኛነት ነው፤ ሽብር ማለት ሰሞኑን በቤልጂክ አውሮጵላን ጣቢያና በባቡር ጣቢያ ላይ እንደታየው ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ አልታየም፤ ከታየም በአገዛዙ ኃይሎች የተፈጸመ ነው፤ ለብዙ ዓመታት ሲፈጸም የቆየ ነው፤ የኢትዮጵያ ጉልበተኞች ከቻሉ ሊያስተውሉት የሚገባ አንድ ነገር አለ፡- ሽብርም ነጻነትን ይፈልጋል፤ በቤልጂክ ሽብሩን የፈጸሙት ሁሉ ነጻነትን ፈልገው ከአገራቸው የተሰደዱና በአገራቸው ያላገኙትን ነጻነት በሰው አገር እየተሞላቀቁበት እንደሆነ የሚያመለክት ነው፤ ትርጉሙ፡- ነጻነት በሌለበት ሽብር አይኖርም፤ እንዴት ብሎ? የት ተደብቆ? የት ሸምቆ?

ሽብርን የጸነሰውን እንዳያስብ አፍኖ፣ እንዳይናገር አንደበቱን መርጎ፣ እንዳይንቃሳቀስ በዳኛ ትእዛዝ ወህኒ ቤት ውስጥ ቆልፎ ሽብርን ማቆም አይቻልም፤ የሚቻለው፣ እየሆነ ያለውም ዝንባሌው ያላቸው ኢትዮጵያውያን ለሽብር ትምህርት ወደአውሮፓና ወደአሜሪካ እንዲሄዱ የሚገፋፋቸው ነው፤ የዚህን ግፊት ውጤት የኢትዮጵያ ጉልበተኞች የሚወዱት አይመስለኝም፤ መጠቃት እንደማጥቃት አያስደስትም!

የእኛ ጉልበተኞች ሽብር ምን እንደሆነ አያውቁም፡፡

የእኛ ጉልበተኞች በንግግርና በተግባር መሀከል ያለውን ልዩነት አያውቁም፤ በቤልጂክ ሽብር የተባለው ሠላሳ አንድ ያህል ሰዎች የሞቱበት፣ ወደሦስት መቶ ሠላሳ ያህል ሰዎች የተጎዱበት ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ያለ ነገር ደርሶ ያውቃል? እንዴታ! በዙ ጊዜ፤ ግን ሽብርተኞች በተባሉትና በታሰሩት አይደለም፤ በተመቻቸውና ሕግ በማይደርስባቸው ሌሎች ጉልበተኞች የተፈጸመ ነው፡፡

የእኛ ጉልበተኞች በፍርሃት የደነዘዘው አንጎላቸው ዓይናቸው እውነቱን እንዲያይ፣ ጆሮአቸው እውነትን እንዲሰማና ልባቸው ወደመወያየትና ወደእርቅ እንዲያቀና አያደርጋቸውም፤ ወላጆቻቸውን ንቀው ብቻቸውን የቆሙ ስለሆኑ መካሪ የላቸውም፤ መንፈስ ስለሌላቸው መንፈሳዊ አባት የላቸውም፤ ያሳዝናሉ፡–

ሀሳቤን አንዱ ግጥሜ ይገልጽልኛል መሰለኝ፡– የሞተ ኅሊና

የማይጣላ ኅሊና ያለው

እንዴት የታደለ ነው!

እግዜር ብቻ ነው ኅሊና የሌለው፤

የማይሳሳት የማየወቆጨው፡፡

ሰው ሰውነቱ፣ ጭንቀቱና ልፋቱ፣

ኅሊናው ከስሜቱና ከፈላጎቱ መጣላቱ፣

የሚረሳ የሚሳሰት፣ የማይታየው የፊቱ፣

የሚወድ፣ የሚጠላ፣ የሚፈራ፣ ኧረ ስንቱ!

ከሳሽ፣ ተከሳሽ፣ ዳኛ መሆን

እንዴት ይችላል መበየን?

ሲያፍነው ግን ኅሊናውን

አይለይም ጨለማውን ከብርሃን!

ኅሊናውን ገደለ ሰው

ማን ሊቀረው? ምን ሊያቅተው?

የጉልበቱ መሣሪያ ነው፤

ጊዜ ጉልበቱን እስቲሰብረው! … …

እውነተኞቹ ሽብርተኞች በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ከሥልጣን ውጭ አይደሉም፤ ከሥልጣን ውጭ ሆነው ቅራኔ የሚያሰሙ ጉልበታቸው እዚያው ላይ ያበቃል፤ በምድረ ኢትዮጵያ ሽብርን መቃወም ሽብርተኛ ያደርጋል፤ ወህኒ ያስገባል፤ ተመስገን ደሳለኝ፣ እስክንድር ነጋ፣ አብርሃ ደስታ፣ … በወህኒ ቤት የሚማቅቁት ቅንጣት የሚያህል የሽብር ተግባር ፈጽመው አይደለም፤ ሽብር እንዳይፈጸም ስለታገሉ ነው፤ ሽብር ከነገሠ ሰላም ወንጀል ይሆናል፤ በኢትዮጵያ ሰላም ዋጋ እያጣ መሄድ ላይ መሆኑን የሚጠራጠር የለም፤ ከባሕር ማዶ የተጀመረው ቀረርቶ ወደተግባር ሲለወጥ መፍራት ፋይዳ የለውም፤ ለጉልበተኞቹ የሚያዋጣው የፍርሃት ጊዜው አሁን ነው! እንደሳዳም ሁሴንና እንደጋዳፊ እንደአይጥ ከተሸጎጡበት ስርቻ እየተጎተቱ ሲወጡ አይደለም፡፡

መጋቢት 2008

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. eunetu says

    April 13, 2016 05:47 pm at 5:47 pm

    እጅግ የማከብርዎትና የምወድዎት የተከበሩ ፕ/ር መስፍን
    ከእርስዎና ከመሳሰሉት ለራሳቸው ከማይኖሩ ስጦታዎቻችን
    የመማር ልብ የሌለው ሰው በምድሪቷ ላይ የሌለ ቢመስልም
    አንዳንዶቻችን ስለእውነት መኖር ማለት ምን ማለት እንደሆነ
    ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ቀጥሎ ከእርስዎ ተምረናል!
    እየተማርንም ነውና የዘመናት ጮኸትዎ ባዶ እንዳልቀረ
    ላረጋግጥልዎ እወዳለሁ!!! እንዲያውም ከ 12 ዓመት
    በፊት ስለየወት ”ካለመጽሐፍ ቅዱስ ወንጌል ሰባኪ ወንጌላዊ” ብየ
    በአንድ አርቲክል ላይ ስም አውጥቼልዎት ነበር!!!ከተቀበሉኝ
    ታዲያ ወንጌል ቢጨመርበት ምን ይሆን እንደነበር እንገምት???
    ጤ ና ዎ ት ን እግዚአብሔር ይጠብቅ !!!

    በሐርያት ሥራ 8፡26 ላይ የተገለጸው ኢትዮጵያዊው ጃንዳረባ የንግሥቲቷ ባለሟል ሆኖ ሳለ ለመሳለም ሩቅ መንገድ ቢጓዝም እንደማያውቅ ተረድቶ የሚያነበው የሕይወት መጽሐፍ እንዳልጋባው በግልጽነት በመናገሩ ለችግሩ መፍትሔ በማግኘት ደስተኛ ሆነ። ከዚህ በሳልና የግል ስም እያለው ኢትዮጵያዊ ተብሎ ከተጠራ ሰው የምንማራቸው ሁለት ነገሮች፡ 1/ የሂሳብ ባለሙያ ቢሆንም የማይገባውን መጽሃፍ የሚያነብና አገር አቋርጦ በመሄድ ሊሳለመው የፈለገው ሁሉን ቻይ አምላክ በቦታ የማይወሰን እንደሆነ አለማወቁን ባለመደበቁ የደስታ ምንጭ የሆነውን እውቀት መቀበሉን፣ 2/ የተቀዳንበት እውተኛው ምንጭና ያሁኑ የእኛ ማንነት(አንዳችን ካንዳችን ከመማር ይልቅ ሁሉን አውቃለሁ ባይነት)ፈጽሞ የማይገናኝ በመሆኑ ይባስ ብሎ ኢትዮጵያ የሚለውን የጋራ መጠሪያ ስም መስማት የማይፈልግና የራሱን ታሪክ የማያውቅ አዋቂ ትውልድ ተነስቷል። ጉድ ያለው ገንፎ አድሮ ይፋጃል ይሏል ይሄ ነው!!!

    በእርግጥ አገራችን የአዋቂወች/ያስተማሪዎች ደሃ አይደለችም!እደግመዋለሁ አይደለችም!!! ከራሳችን ሰዎች ለመማር የቀና ልብ ስላጣን እንጂ! ወይም በሌላ ቋንቋ እንደ ኮከብ ብልጭ ሲሉ በብዙዎቻችን ውስጥ ባለው ጨለማ ለሞት አሳልፈን ስለምንሰጣቸው!(በደቂቀ እስጢፋኖስ መጽሐፍ ላይ እርስዎና ፕ/ር ጌታቸው ሃይሌ እንደገለጻችሁልን) ስለዚህ እኔ በበኩሌ ከነጭ አዋቂዎች ብቻ ሳይሆን እንደናንተ ካሉ አባቶቼ/ወገኖቼ በተለይ ማንነቴን የበለጠ ለመማር 100% ዝግጁ ነኝና እስከ ነፍስ ህቅታ ድረስ በርቱ! ደግሞም በነቢዩ ዳንኤል እንደሆነው ቅንነትን የራበው አንበሳ እንኳ አይበላውምና ከመምሸቱ በፊት በርቱ! በርቱ!! በርቱ!!!እናንተ አላዋቂ የሆናችሁ አዋቂ ወገኖቻችንም ቆም ብላችሁ አጠገባችሁ ካለው ወገናችሁ ተማሩ እንማር?ለነገሩ ተማር ያላለው በ40 ዓመቱም አይማርም! ይባል የለ!!! በእውነት ይህ አይሁንባችሁ!!!

    እግዚአብሔር የኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ልብ ይስጠን!!! የገባው አሜን ይበል?
    ፕሮፌሰሮቻችንም አሜን ብትሉ ታተርፋላችሁ እንጂ አትከስሩም።
    ፕ/ር መስፍን ትክክል አይደለሁም?

    እውነቱ /eunethiwot@gmail.com/ ነኝ
    እንድኖር ተፈቅዶልኝ ካለሁበት!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule