የማንኛውም አመፅ መነሻ መሠረቱ፣ ገዥዎች በሕዝብ ላይ የሚያደርሱት፣ የኢኮኖሚ ብዝበዛ፣ የመብት ረገጣ፣ የማንነት ነጠቃ እና የሥነ-ልቦና ሰለባ ልኩን አልፎ ገደብ ሲጥስ የሚፈጥረው ምሬት እንደሆነ ይታወቃል። የትግሬ ወያኔ ዘረኛ እና ከፋፋይ የፋሽስት ሞሶሎኒ ዓላማ አራማጅ ቡድን፣ በወልቃት ፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በሠቲት እና በአርማጭሆ ሕዝብ ላይ በተናጠል፣ እንዲሁም በዐማራው ነገድ ላይ በወል፣ ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ከ1972 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 36 ዓመታት በተከታታይ ፈጽሟል፤ እየፈጸመም ነው። በዚህ ረገድ የወረዳ ግዛቶቹም ሆኑ ነዋሪው ሕዝብ በየትኛውም ጊዜ፣ የትግራይ የግዛት አካል ሆነው አያውቁም። የትግሬ ግዛት ደንበርም ተከዜን ተሻግሮ አያውቅም። ሕዝቡም ጥንትም ሆነ ዛሬ፣ በጉርብትና ከሚናገረው ትግርኛ፣ ዐረብኛ እና መሰል ቋንቋዎች በቀር፣ የትግሬነት ባህል፣ ታሪክ፣ ወግ፤ ሥነልቦና እና መሰል የማንነት ማረጋገጫ ዕሴቶች ኖሮት አያውቅም፤ እንዲኖረውም አይሻም።
የትግራይ ሕዝብ በተከታታይ በድርቅ እና በርሃብ ሲጠቃ እየፈለሰ የተጠጋው በእነዚህ የሰሜን ጎንደር ወረዳዎች ነው። ስለዚህ በድርቅ እና በርሃብ ምክንያት ከትግራይ የሚሰደዱት ሰዎች ኑሯቸውን ሲደጉሙ የኖሩት በቀን ሠራተኝነት እየተቀጠሩ የወልቃይቶችን የሠሊጥ እና የማሽላ አዝመራ በማረስ፣ በማረም እና በመሰብሰብ እንደነበረ የቅርብ ዘመን ትውስታችን ነው። ሆኖም፣ «እንግዳ ሲሰነብት፣ ባለቤት የሆነ ይመስለዋል» የሚሉት አባባል ዕውነት ሆኖ፣ የዐማራው ነገድ ባለው የእንግዳ ተቀባይነት የዳበረ ባህሉ ተቀብሎ ባስተናገዳቸው ሰዎች የውስጥ አርበኝነት፣ ወያኔ ዐማራን በአውራ ጠላትነት ፈርጆ ለማጥፋት ላደረገው ዝግጅት፣ የጥቃቱ የቅድሚያ ሰላባ የሆነው በነዚህ ወረዳዎች ይኖሩ በነበሩ ዐማሮች ላይ እንደነበር በተደጋጋሚ ለሕዝብ ይፋ መደረጉ ይታወሳል። በዚህም መሠረት በወልቃይት ፣ በጠገዴ ፣ በጠለምት ፣ በሠቲት እና በአርማጭ ሕዝብ ላይ የትግሬ ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ከፈጸማቸው እጅግ የበዙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች መካከል የሚከተሉት ለናሙና ያህል የቀረቡ በጣም ጥቂቶቹ ናቸው።
ሀ) በ1972 ዓ.ም. የትግሬ-ወያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ የትግራይ እና የጎንደር ክፍለ ሀገሮች የተፈጥሮ ወሰን የሆነውን የተከዜን ወንዝ ተሻግረው የሚከተሉትን ያገር ዘቦች በግፍ ገደሉ። እነዚህም፦
- አቶ ማሞ ዘውዴ፣
- አቶ እንደሻው ታፈረ፣
- አቶ አያሌው ሰሙ፣
- አቶ በርሄ ጎይቶም፣
- አቶ ሐጎስ ኃይሉ፣
- አቶ ልጃለም ታዬ፣
- ግራዝማች ወልዴ የኔሁን፣
- ቄስ በለጠው ተስፋይ፣
- ቄስ ትዕዛዙ ቀለመወርቅ፣
- ቄስ አለነ ቀለመወርቅ፣
- ወጣት ግዛቸው ዳኜው፣
- ወጣት አዲስይ ልጃለም፣
- ወጣት ደረጀ አንጋው፣
- ወጣት ዋኘው መንበሩ፣
- ወጣት ሕይዎት አብርሃ፣
- ወጣት ታደለ አዛናው፣
- ወጣት ማሞ አጀበ ናቸው።
ለ) በ1986 ዓ.ም. «ርዋሳ» የተባለውን ከ500 በላይ ቤቶች የነበሩበትን የገበሬ መንደር አቃጥለው ትግሬ አሰፈሩበት። በዚህ ቀበሌ ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ ለከፍተኛ ችግር ከተጋለጡት መካከል አቶ ጫቅሉ አብርሃ፣ አቶ አብርሃ ሣህሉ፣ ወይዘሮ ስንዱ ተስፋይ፣ አቶ ዋኜው ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው።
ሐ) ከ1988 እስከ 1989 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ከ3,000 (ሦስት ሺህ) በላይ ጥማድ በሬዎች ባለቤቶች የነበሩ ገበሬዎችን ገድለውና አሰድደው ትግሬ አስፍረውበታል። ሠፈራ የተካሄደባቸው ቦታዎችም ማይደሌ፣ አንድ አይቀዳሽ፣ እምባ ጋላይ እና ትርካን ናቸው።
መ) ከ1986 ዓ.ም. ጀምሮ ማይ ኽርገጽ፣ ቤት ሞሎ፣ ማይ ጋባ፣ ቃሌማ፣ እጣኖ፣ መጉዕ ወዘተ ይኖሩ የነበሩ ነባር የዐማራ ነገድ ተወላጆችን አባረው ትግሬን አስፍረዋል። በአጠቃላይ በጎንደር ለም መሬቶች ከ500,000 (አምስት መቶ ሺ) በላይ ትግሬ እንዲሰፍር ተደርጓል።
ሠ) የትግሬ-ወያኔዎች ዐማራዎችን የጎንደር ክፍለሀገር ተወላጆችን አደህይተው እና አዋርደው፣ ከሰው በታች አድርገው ይገዛሉ። በአካባቢው የትግሬን የበላይነት አስፍነው ቀጥቅጠው እና አዋርደው ለመግዛት እንዲያመቻቸው የአካባቢውን ታዋቂ እና ባለሀብት ሰዎች አስረዋል፣ ገድለዋል፣ ሀብት ንብረታቸውን ዘርፈዋል። በዚህ ረገድ ለአብነት ከሚጠቀሱት መካከል የሚከተሉት አዛውንቶችን የቁም ከብቶቻቸውን መዘረፋቸውን የወልቃይት ጠደገዴ ተወላጆች ያስረዳሉ።
- ከአቶ ዘነበ ሐጎስ ከ450 ባላይ የቀንድ ከብቶች ዘርፈዋል፤
- ከአቶ ባየው ቢያድግልኝ ከ600 በላይ ከብቶች እና ፍየሎች ዘርፈው በመጨረሻም ባለሀብቱን ገድለዋቸዋል፤
- ከአቶ ገብረሕዎት ኃይሌ ከ80 በላይ የቀንድ ከብቶች እና ፍየሎች ዘርፈዋል፤
- በ1981 ዓ.ም. ከአቶ አለባው ሕደጎ ከ500 በላይ የቀንድ ከብቶች እና በርካታ ኩንታል እህል ተዘርፏል።
- የቀኛዝማች ገብሩ ገብረመስቀል 24 በሬዎቹ ታርደው ከ900 መቶ ባላይ ማድጋ እህል ተወርሷል።
ረ) የካቲት 21 ቀን 1972 ዓ.ም. የትግሬ-ወያኔ የቃብትያ አዲህርድ ከተማን ለመቆጣጠር በነዋሪው ላይ በከፈተው ጦርነት 9(ዘጠኝ) ሰዎችን ገድሎ 18(አሥራ ስምንት) ማቁሰሉን የዓይን እማኝ የሆኑት ተሰደው በብሪዝበን ከተማ፣ አውስትራሊያ፣ ነዋሪ የሆኑት አቶ ፈረደ ያስረዳሉ። በዚያ በትግሬ-ወያኔ እና በነዋሪው መካከል በተደረገው ጦርነት ከሞቱት እና ከቆሰሉት መካከል ስማቸውን ማስታወስ የተቻለው የሚከተሉት ይገኙበታል።
- አቶ የልፋዓለም ተኮላ፣ ዕድሜ 65፣
- አቶ ጎኦይ መብራቱ፣ ዕድሜ 30፣
- አቶ አለነ ክንድሽ፣ ዕድሜ 60፣
- አቶ አታላይ አበራ፣ ዕድሜ 64፣
- አቶ ባሕታይ ወንድምአገኘሁ፤
- አቶ በለጠ ወንድምአገኘሁ፤
- አቶ በየነ ያዕብዮ፣ ዕድሜ 70፣
- አባ ኃይሌ፣
- አቶ ገብሩ ጋሼ፣ ሲሆኑ
ከቆሰሉት መካከል ደግሞ፦
- አቶ አሰፋ ገብረመድኅን፣
- ሙላው ኃይሌ (አለቃቸው ኃይሌ)፣
- አቶ መብራቱ ዋሴ፣
- አባ ጎላ ዘለለው፣
- አቶ አነጋው ገብረእግዚአብሔር፣
- አቶ አበራ አጀቢ፣
- አቶ ጥሩነህ ከሰተ፣ እና
- አቶ ፈቃዱ ይገኙበታል።
ሰ) ነሐሴ 10 ቀን 1972 ዓ.ም. ወያኔ ከወልቃይት እና ከጠገዴ ወረዳዎች አስሮ የወሰዳቸው እና እስካሁን የደረሱበት ያልታወቁ የአገር አዛውንቶች የሚከተሉት ናቸው።
- አቶ ሞላ ዘውዴ፣
- አቶ ተበጄ በቀለ፣
- አቶ አያሌው ሰሙ፣
- አቶ እንደሻው ታፈረ፣
- አቶ እሸቴ አያልነህ፣
- አቶ ጎኢቶም ሐጎስ፣
- አቶ በርሄ ሐጎስ ታፈረ፣
- አቶ በየነ አየልኝ፣
- አቶ ኃይሉ ልዩነህ፣
- አቶ አብርሃ ነጋ፣
- አቶ አለባቸው መብራት፣
- አቶ ድራር ገሠሠው፣
- አቶ ገብረሥላሴ ረዳ፣
- አቶ ገብረሕይዎት ባሕታ፣
- አቶ ኃየሎም ይርጋ፣
- አቶ አለባቸው ደፈርሻ፣
- አቶ ሊላይ ሐድጎ፣
- አቶ ጎኢቶም ምህረት፣
- አቶ ታገለ ወርቄ፣
- አቶ መሓሪ አዱኛ፣
- አቶ ባየው ቢያድግልኝ፣
- አቶ ሢሣይ ዘነበ፣
- አቶ አታላይ ዘነበ፣
- አቶ ተፈራ ሊላይ፣
- አቶ ገብረመድኅን የኋላ፣
- አቶ ነጋሺ ተበጄ (አራት አንበሣ ገዳይ የነበረ ጀግና፣ ሆኖም በመኮንን ዘለለው የታፈነ)
- ወጣት ግፋባቸው ዳኛቸው፣
- አቶ ጌትየው ታምሬ፣
- አቶ ርስቀይ ኃይሌ፣
- አቶ ተድላ ርስቀይ፣
- ቄስ ትዛዙ ቀለመወርቅ፣
- ቄስ አለነ ቀለመወርቅ፣
በአጠቃላይ ከ1970 ዓ.ም. ጀምሮ የትግሬ-ወያኔ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት እና በሠቲት ወረዳዎች ዐማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ግድያ፣ አፈና እና ደብዛ ማጥፋት እጅግ ብዙ ትላልቅ ጥራዞች እንደሚሆን ይታመናል። ሆኖም ሞረሽ-ወገኔ ካሰባሰባቸው መረጃዎች መካከል ለአብነት የሚከተለው ሠንጠረዥ በዝርዝር ቀርቧል።
ሠንጠረዥ፦ በወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች ላይ ወያኔ ግፍ የፈጸመባቸው ሰዎች በከፊል፣
ተራ ቁጥር | ሙሉ ስም | ተራ ቁጥር | ሙሉ ስም | ተራ ቁጥር | ሙሉ ስም |
1 | አባቴ እሸቴ | 2 | አባው ጠጅነህ | 3 | አበበ ይርጋ |
4 | አበራ ኃይሌ | 5 | አበጄ ክፍሌ | 6 | አበራ ዓለማዬሁ |
7 | አበራ ገብረመስቀል | 8 | አበራ አስረስ | 9 | አበራ ሐጎስ |
10 | አብርሃ አዳነ | 11 | አብርሃ አርጉ | 12 | አብርሃ ነጋ |
13 | አብራሃ በላይ | 14 | አቻምየለህ ሽታዬ | 15 | አቸናፊ ጽጌ |
16 | አዳነ ደረሰ | 17 | አዳነው ርስቴ | 18 | አዲስ አብተው |
19 | አዲሱ አበበ | 20 | አደበ ዓለም | 21 | አደራጀው ገብሬ |
22 | አዲስ ልጃለም | 23 | አላቸው ልጃለም | 24 | አላቸው ገብረመድኅን |
25 | አለባቸው ደፈርሻ | 26 | አለበል ይርጋ | 27 | አለኸኝ መሥፍን |
28 | አለማው ታረቀ | 29 | አለማይ ካሣ | 30 | ዓለሙ ጌታቸው |
31 | ዓለሙ ፈንታይ | 32 | ዓለሙ ለገሠ | 33 | አለነ ክንዲሽ |
34 | አማረ ፈንቴ | 35 | ዓለማየሁ አበጠለው | 36 | አንዶም ካሣ |
37 | አንገረብ ተሰማ | 38 | አረፈዓይኔ መኮንን | 39 | አረፈ በለጠ |
40 | አረፈ ግደይ | 41 | አረጋ ወልዴ | 42 | አረጋው አየነው |
43 | አስማረው ግደይ | 44 | አስማረው መለሰ | 45 | አጥናፈይ ዓለማየሁ |
46 | ዐወቀ ዘውዱ | 47 | አያሁነኝ ወንዶሻል | 48 | አያሌው ሰሙ |
49 | አያና ገብሬ | 50 | አየነው ሙሉ | 51 | አየነው ርስቴ |
52 | አየነው በየነ | 53 | ኣዛናው ቸሬ | 54 | ኣዛናው ይደግ |
55 | አዛናው ጽጌ | 56 | አዘነህ ልጃለም | 57 | ባሕታ ፈንታይ |
58 | ባሕታ መኩሪያ | 59 | ባሕታ ወንድምአገኝ | 60 | ባሕታ ረዳ |
61 | ባሕታ እርትብ | 62 | ባሕታ መንግሥቱ | 63 | ባየው ባሕታ |
64 | ባየው ቢያረግልኝ | 65 | ባየው ልጃለም | 66 | በዕዱ ወንድም አገኝ |
67 | በላይ ሙሉ | 68 | በላይ ታደሰ | 69 | በላይ መኮንን |
70 | በለጠ ዓለምመብራት | 71 | በለጠ ተስፋዬ | 72 | በልጤ ወንድም አገኝ |
73 | በራ የማነ | 74 | በራ ወልደሥላሴ | 75 | በርሄ ሐጎስ |
76 | በሪሁን ይርጋ | 77 | በሪሁን ይግዛው | 78 | ቻላቸው ታደለ |
79 | ጫሉ ይዘዘው | 80 | ጫኔ ይርጋ | 81 | ዳኜው ሢሣይ |
82 | ደቢል ዘነበ | 83 | ደቢል ተክለሃይማኖት | 84 | ደገፋ ጎኢቶም |
85 | ደሣለኝ ዋርካው | 86 | ደስታ ሠርጸ | 87 | ድራር ገሠሠው |
88 | እንዳልካቸው ጠጆ | 89 | እንደሻው ታፈረ | 90 | እንግተይ አየልኝ |
91 | እሪበይ ገብሩ | 92 | እሸቴ አያልነህ | 93 | እሸቱ መሥፍን |
94 | ፋንታዬ አየልኝ | 95 | ፋንቱ ሢሣይ | 96 | ፈለቀ ግርማይ |
97 | ፈረደ ዘራይ | 98 | ፈረደ ፍሉይ | 99 | ፈንቴ ዘነበ |
100 | ፈንቴ ገብራይ | 101 | ፍሬይ ተወልድ | 102 | ፍታለው ታፈረ |
103 | ገብረሕይዎት ባሕታ | 104 | ገብረሕይዎት ገዛኸኝ | 105 | ገብረማርያም አረፈዓይኔ |
106 | ገብረመድኅን ዘርፉ | 107 | ገብረመድኅን የኋላ | 108 | ገብረመስቀል ጥርፊነህ |
109 | ገብረስላሴ ረዳ | 110 | ገብሬ ሐጎስ | 111 | አስማረው አስረስ |
112 | አስማረው ወልዴ | 113 | አስፋው መንግስቴ | 114 | አስረስ ታከለ |
115 | አስፋው ወርቁ | 116 | አስገዶም ጥሩነህ | 117 | አሸናፊ ወንዱ |
118 | አስመላሽ ይገዙ | 119 | አታላይ አበራ | 120 | አታላይ አማረ |
121 | አታላይ ዘነበ | 122 | በሪሁን ደስታ | 123 | በየነ ፍሬይ |
124 | በየነ አየልኝ | 125 | ቢያድግልኝ ዘውዴ | 126 | ብላታ አብርሃ |
127 | ብርሃኔ ማሞ | 128 | ብርሃ ኑ ዳኛቸው | 129 | ብርሃኑ ሽታዬ |
130 | ጫቅሌ ገበየሁ | 131 | ቻላቸው ታደሰ | 132 | ቻላቸው አበራ |
133 | ገብረሕዎት ኃይሌ | 134 | ገረመው ዳኜ | 135 | ገሪማ ተኽሌ |
136 | ጌታቸው ተገኜ | 137 | ጌታቸው ብዙነህ | 138 | ጌታቸው ብዙነህ |
139 | ጌቴው ታምሬ | 140 | ጌቱ ጠለለው | 141 | ግደይ ማሙ |
142 | ግደይ ካሣ | 143 | ጊፍታቸው ዳኜው | 144 | ግንባይ ጌታሁን |
145 | ወልዴ የኔሁን | 146 | ግርማ ይደግ | 147 | ግርማ ትኩዕ |
148 | ግርማ ጥቄ | 149 | ጎኢቶም ምኅረት | 150 | ጎኢቶም ሐድጎ |
151 | ጎርፉ ገብሩ | 152 | ጎሹ አሰፋ | 153 | ጎሹ ትርፍነህ |
154 | ጉበን ፈያሃጸን | 155 | ጊዎይ መብርሃቱ | 156 | ጉዎይ አዳነ |
157 | ሀብቱ ይርጋ | 158 | ሀፍቴ ዘነበ | 159 | ሐጎስ ገብራይ |
160 | ሐጎስ መንግሥቱ | 161 | ሀጎስ ይስፋ | 162 | ኃይሉ ልዩነህ |
163 | ኃየሎም ይርጋ | 164 | ካሂሱ ንጉሡ | 165 | ካህሱ ጌታሁን |
166 | ካሳሁን ሲሣይ | 167 | ካሣ መብራት | 168 | ከሰተ ይርጋ |
169 | ካሡ ንጉሤ | 170 | ሢሣይ አበራ | 171 | ለማ ታደሰ |
172 | ክንፈ ከበደ | 173 | ክንፈ ናሁ | 174 | ልጃለም በላይ |
175 | ልዑል ገብረ መስቀል | 176 | ልጃለም ታዬ | 177 | ማለፊያ ጉዎይ |
178 | ሊላይ ሐድጎ | 179 | ሉሌ መሥፍን | 180 | ማማይ አብርሃ |
181 | ማሌ ዘነበ | 182 | ማማይ ረዳቴ | 183 | ማማይ ሙሉ |
184 | ማማይ በላይ | 185 | ማማይ አየልኝ | 186 | ማማይ በላይነህ |
187 | ማማይ ፈረደ | 188 | ማማይ አለዩ | 189 | ማሙ ዋርካው |
190 | ማሞ ደስታ | 191 | ማሞ ዘውዴ | 192 | ማሙነህ ይደግ |
193 | ማሙ ቸሬ | 194 | ማሙ ታደሰ | 195 | መሓሪ አዱኛ |
196 | መብርሃቱ ይግዛው | 197 | መብርሃቱ ገብረእግዚአብሔር | 198 | መኳንንት ዋርካው |
199 | መኮንን ለውጤ | 200 | መኮንን አበራ | 201 | መርዕድ ገብረሚካኤል |
202 | መኩሪያ ገብረማርያም | 203 | መንገሻ ሙሉጌታ | 204 | ሞላ ጠለለ |
205 | መሣፍንት ዳኜው | 206 | ምራጭ ተሰማ | 207 | ሙሉዓለም ዋርካው |
208 | ልዕልቲ ወንድምአገኝ | 209 | ሙኮጠይ ታደሰ | 210 | ሙሉ አማረ |
211 | ሙላው ዞፌ | 212 | ሙሉ አታላይ | 213 | ሙሉነህ ደመወዜ |
214 | ሙሉ በርሄ | 215 | ሙሉ ገብረኪዳን | 216 | ነጋ ጌታሁን |
217 | ነጋ ተበጄ | 218 | ነጋ አስረስ | 219 | ነጋ በበል |
220 | ነጋ ምትኩ | 221 | ነጋ ሐጎስ | 223 | ንጉሡ አብርሃ |
224 | ንግሸት ሐድጎ | 225 | ንጉሤ ቀለመወርቅ | 226 | ረዳኢ ለማ |
227 | ፓስረት በለጠ ተስፋይ | 228 | ቁዊይ ተዘራ | 229 | ርስከይ ይልማ |
230 | ርስከይ ኃይሌ | 231 | ርስከይ ምንተስኖት | 232 | ሰረበ ረዳ |
233 | ርስከይ መለሰ | 234 | ሮስኬ ማንጆስ | 235 | ሸንቆ በለጠ |
236 | ሰጠኝ እንዳለው | 237 | ሰጠኝ ሽታዬ | 238 | ሽፈራው ንጉሤ |
239 | ሽፈራው ውብነህ | 240 | ሽፈራው ተስፋይ | 241 | ሺሙዬ አለሜይ |
142 | ሽሁን ኪዳኔ | 243 | ሺሙዬ ማሙ | 244 | ስማቸው ዓለሙ |
245 | ሺሙዬ ደምሰው | 246 | ስማቸው ማሙ | 247 | ታደሰ ከሽ |
248 | ሢሣይ ተስፋሁነኝ | 249 | ታደለ አባተ | 250 | ጣሌ ገብሬ |
251 | ታፈረ ሊላይ | 252 | ታገል ተድላ | 253 | ተበጄ በቀን |
254 | ጣሰው አሰፈ | 255 | ተበጄ መለሰ | 256 | ተካልኝ አበበ |
257 | ተገኜ ነጋ | 258 | ተገኜ ደምሴ | 259 | ተስፋ ፀጋዬ |
260 | ተካልኝ መንግሥቱ | 261 | ጤላ ኃይሌ | 262 | ተስፋይ መኮንን |
163 | ተስፋይ ኃይሉ | 264 | ተስፋ አብርሃ | 265 | ተሾመ ፈረደ |
266 | ተስፋይ አጽብሃ | 267 | ተሻገር ገብረመድኅን | 268 | ተሰማ ፍሬይ |
269 | ተሾመ ጠለለ | 270 | ተሰማ አብቅሃለሁ | 271 | ጥላሁን ታደሰ |
272 | ጥጋቡ መክንንት | 273 | ጥላሁን ተወልደ | 274 | ፀጋዬ አበበ |
275 | ጥሩነህ መብራቱ | 276 | ቶጋ ተገኜ | 277 | ጽይተይ አብርሃ |
278 | ፀጋዬ የኔሁን | 279 | ፀጉ ዘነበ | 280 | ወረታ ገብሩ |
281 | ዋኜው መንበሩ | 282 | ወግሃታይ መንበሩ | 283 | ወንድም ፍስሃ |
284 | ወልዴ የኢብዮ | 285 | ወልዴ የኔሁን | 286 | ወንድምአገኘሁ ታረቀኝ |
287 | ወንድም ጠለለ | 288 | ወንድም ጠጋ | 289 | የኋላሸት ዘለቀ |
290 | ወርቅየ ገብረመድኅን | 291 | ወርቅነህ አታላይ | 292 | ይዘዘው ገብረመስቀል |
293 | የሻለም በሪሁን | 294 | የሻለም ጽጌ | 295 | ይደግ አያሌው |
296 | ይበይን ገብረእግዚአብሄር | 297 | ይደግ አየነው | 298 | ይስፋ ፋንታይ |
299 | ይላቅ ተዘራ | 300 | ይርጋ ደምሰው | 301 | ዘሩ በላይ |
302 | ዘለቀ ግርማይ | 303 | ዘራይ መርሻ | 304 | ዘውዱ መርሻ |
305 | ዘውዴ ሢሣይ | 306 | ዘውዱ ሺበሽ | 307 | ዘሩ መርሻ |
ይህ እንግዲህ በግልጽ መረጃ የተገኘላቸው ናቸው። ዛሬ በእነዚህ ወረዳዎች የእህት ልጅ እንጂ፣ የወንድም ልጅ የሚባል አለመኖሩ የትግሬ-ወያኔ ወንዱን አንድም አስሮ መግደሉን፣ ሁለትም በገፍ ማሰደዱን የሚያመለክት ነው። የትግሬ-ወያኔ በድብቅ አስሮ የገደላቸው ቤታቸው ይቁጠራቸው። የእነዚህ ወገኖቻችን ደም ይጣራል።
ሰሞኑን የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የጠለምት፣ የሠቲት እና የአርማጭሆ የዐማራ ነገድ ተወላጆች፣ የትግሬ-ወያኔ ራሱ «ሠራሁት፣ የኢትዮጵያን ብሔር፣ ብሔረሰቦች ዕኩል አደርኩ» እያለ በሚደሰኩርበት እና በያመቱ «የብሔረሰቦች ዕኩልነት ቀን» እያለ ገንዘብ የሚያጋብስበትን ሕገመንግሥት ተብየ የሚለውን የማንነት ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ማቅረብ ከጀመሩ ጊዜ ወዲህ 116(አንድ መቶ አሥራ ስድስት) የወልቃይት-ጠገዴ ሰዎች በወያኔ ታፍነው የደረሱበት አለመታወቁ ታውቋል። በተለያዩ ጊዜዎች የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን ለማፍራረስ፣ ዐማራን ፈጽሞ ለማጥፋት እና ለማጽዳት ላቀድነው ዕቅድ አስቸጋሪ ይሆናሉ ብለው የገመቷቸውን የወልቃይት-ጠገዴ ተወላጆች እያፈኑ ወደ ሱዳን እንደሚወስዷቸው እና የደረሱበት የማይታወቁት ቁጥር እጅግ በርካታ እንደሆነ ከአካባቢው የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ወያኔ በጠበንጃ አፈሙዝ ወደ ትግራይ በከለላቸው ወረዳዎች በአማርኛ መማር ከመከልከሉም በላይ፣ ቋንቋውን መናገር እንደወንጀል ተቆጥሮ አማርኛ የሚናገሩ ሰዎች ግፍ እንደሚፈጸምባቸው ለማወቅ ተችሏል። በትግርኛ ትምህርት ሲሰጥ፣ «ኀ፣ ሠ፤ እና ፀ» የተሰኙት ፊደሎች የአማርኛ ድምፅ ወኪሎች በመሆናቸው፣ ፊደሎቹ ራሳቸው እንደዐማራ የተጠሉ መሆኑን በአካባቢው ስለጉዳዩ ጥናት ያደረጉ ቡድኖች እና ግለሰቦች ያስረዳሉ። በወልቃይት-ጠገዴ አማርኛ መናገር የሚያዘውትሩትን ሰዎች «የኢሕአፓ ቅሬቶች» የሚል መጠሪያም እንደሰጡዋቸው እና ምናምን እንደያዘው ሰው በመቁጠር በመጠየፍ እና በመናቅ እንደሚያንቋሽሿቸው ታውቋል።
ከላይ ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው ወደ ትግራይ ባጠቃለሉዋቸው ወረዳዎች ይኖሩ የነበሩ ዐማሮችን ገድለው፣ አስረው እና አሰድደው በቦታው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺ) በላይ ትግሬዎች አስፍረውበታል። ከሁሉም በላይ ዳንሻ ላይ እንዲሰፍሩ የተደረጉት የትግሬ-ወያኔ ተዋጊዎች የነበሩ 30,000(ሰላሳ ሺ) ወታሮች መሆናቸውን ስናስብ፣ ወያኔ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ለሚነሳ የማንነት ጥያቄ በቶሎ አፍነው ለመጨፍለቅ ያለውን ቅድመ ዝግጅት አመልካች ነው። የትግሬ-ወያኔ በዐማራው ላይ ያለው «የጥቁር አፓርታይድ» ጥላቻ ከሚገለጽባቸው መልኮቹ አንዱ አዘውትረው ለወልቃይት-ጠገዴ ነዋሪዎች የሚሉት ቃል ነው። ይኸውም፦ «እኛ ወልቃይት-ጠገዴን መሬቱን እንጂ፣ ሰውን አንፈልገውም» የሚሉት ነው። በዚህ አቋማቸውም በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ የጅምላ የዘር ፍጅት ፈጽመውበታል።
ከሁሉም በላይ በወልቃይት-ጠገዴ ዐማሮች ላይ የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ ቡድን ከሚፈጽማቸው ዘግናኝ ግፎች፣ ለአቅመ-ሔዋን ያልደረሱ ሴት የዐማራ ሕፃናት ተማሪዎችን ዘወትር የትግሬ መምህራኖችን ቤት በተራ እንዲያጸዱ የሚል ትዕዛዝ በመስጠት፣ ይህን ትዕዛዝ አክብረው የሚሄዱትን ሴት ሕፃናት መምህራኖቹ በመድፈር አሳዳጊ የሌላቸው ልጆች እንዲወለዱ፤ ሴቶቹም ከትምህርት ገበታ እንዲያቋርጡ እየተደረገ እንደሆነ ታውቋል። ይህ ድርጊት የትግሬውን ቁጥር ለማበራከት እና የነዋሪውን ሥብጥር ትግሬ-ጠቀም ለማድረግ ከሚሠራው ሤራ አንዱ ክፍል እንደሆነ ግልፅ ነው።
በአጠቃላይ፣ በወልቃይት-ጠገዴ ሕዝብ ላይ ላለፉት 36(ሰላሣ) ዓመታት የትግሬ-ወያኔ የፈጸመው ግፍ እና መከራ በዐማራው ላይ የተፈጸመ የዘር ጥቃት በመሆኑ፣ የዐማራው ነገድ ብቻ ሳይሆን፣ ለሰብአዊነት የሚቆረቆር ማናቸውም ሰው ከወልቃይት-ጠገዴ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ጎን ሊቆም ይገባዋል። ዛሬ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በሠቲት እና በአርማጭሆ ያሉ ወገኖቻችን የጀመሩት «ማንነታችን ይከበር» ጥያቄ ወያኔ ባቀደው መልኩ በድፍጠጣ የሚዳፈን ከሆነ፣ ነገ የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋ፣ የቀሪው ጎንደር ነዋሪ፣ በአጠቃላይ የዐማራው ነገድ በተናጠል እንዲመታ መንገድ መክፈት እና ድርጊቱ እንዲፈጸም በለሆስታ ፈቃድ መስጠት እንደሆነ ስለሚቆጠር፣ የዐማራው ነገድ በያለበት ከወገኖቻችን ጎን ልንቆም ይገባል።
ይህን በተመለከተ የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ከአገር ውጭ የሚኖረው የዐማራው ነገድ ለወልቃይት-ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ተገቢ የሆነ መልስ እንዲያገኝ፣ ጥያቄ ያነሱት ወገኖች ለሚያስፈልጋቸው የገንዘብ፣ የቁሳቁስ እና የመረጃ ድጋፍ በተቀናጀ መንገድ መስጠት እንዲቻል አጠቃላይ የስልክ ስብሰባ ለማድረግ አቅዷል። የስብሰባው ቀን እና ጊዜ ወደፊት በማስታወቂያ ስለሚገለጽ፣ ሁሉም የዐማራ ልጅ በስብሰባው በመገኘት ለወገኖቻችን የምንችለውን በማድረግ አጋርነታችንን እንድናሳያቸው ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በአክብሮት ይጋብዛል።
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ-ማንነት ጥያቄ በተባበረ ትግላችን ይመለሳል!
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
Yikir says
God bless amhara.AMARAW min hone ?mezifen enkuwa akatew.ZEMENU KERIBOWAL ENA BE ANDINET KUMU .GETAM YEBEDELEGNOCHIN MEKERA YIKOTIRAL.
geresu says
ጎበዝ ንቃ! ንቃ! ወያኔ አማራና ኦረሞን በማጋጨት የአገዛዝ ጊዜውን ማራዘም ባለመቻሉ አብዶ እየተቅበዘበዘ ነው! እናም በመልካም አስተዳደር ስም ጭምብል ለብሶ የህዝብ ወገንተኝነት ያላቸውንና በፍረሀት የሚጠረጥራቸውን ካድሬዎቹን በህዝብ ተገመገሙ በማለት ከሀላፊነት ማውረድ: መወንጀልና መክሰስ የወያኔ የተለመደ ሴራ ስለሆነ ይህን ድርጊት ከመቀበል ይልቅ የተባረሩትን መደገፍና ወደህዝቡ ትግል እንዲቀላቀሉ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ነው:: ሰው በሙስና የሚገመገምና የሚባረር ቢሆን ኖሮማ ግምገማው መጀመር ያለበት በከንቱ የድሀ ልጆችን ደም እየጠጡ ባሉት ከፍተኛ ባለስልጣናት አባይ ፀሀይ: ሳሞራ: ደብረፅዮን: በረከት: ደመቀ: አባይ ወልዱ: ተፈራ ዋልዋ: አዲሱ ለገሰ: አባዱላ: ሲራጅ: እና የአጋዚ ጦር ላይ ነበር:: ግን ይህ ለነሱ ካካ ነው:: ስለዚህ ይህ ሁሉ ንፁህ የኦረሞና የአማራ የዩኒበርስቲ ህፃናት ህይወት ጠፍቶ! ይህ ሁሉ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ድራሹ ያለበት ጠፍቶ: ታስሮና ተገርፎ: ንብረቱን ተነጥቆ እያለ ወያኔ ይገዛል ማለት ሴት ቆማ ትሸናለች ማለት ነው:: ስለዚህ የአማራና ኦረሞ ክልል መሪዎች: የብአዲንና ኦህዲድ አባላት: መላው ህዝብ መምህራን: ተማሪዎች: ፖሊስ: መከላከያ: አርሶ አደር ወዘተ… የየድርሻችሁን ተወጡ:: ለዝንተ አለም በወያኔያዊ ሂትለርነ ሞሶሎኒወች ስንረገጥ መኖር የለብንም:: ያውም በጣት ለሚቆጠሩ:: እናሸንፉለን! አንጠራጠርም!!!
geresu says
ሚዳ ለምትከታተሉ ኢትዮጵያውያን አንድ ነገር ላስታውሳትሁ? ይገርማል! የትግራይ ክልልን ሚዲያና የሌሎች ክልሎች ሚዳዎችን ታዝባችሁ ከሆነ አብዛኛው የትግራይ ክልል የሚዳ ሽፋን በቀረርቶ: በፉከራና የጦርነት ጀብድ በሚያቀነቅኑ የባህል ገናናነት ላይ የሚያተኩሩ ናቸው:: ይህ የሚያሳየው ደግሞ ኢትዮጵያዊ ጀግንነትን በጠባቡ የተቀረፀ ትግሪያዊና ወያኔያዊነትን ብቻ ነው:: ለዚህ ምክነያቱ ደግሞ ከላይ እስከታች ሚዲያውን የተቆጣጠሩት ወያኔዎች ብቻ በመሆኑ በሌሎች ክልሎች ሚዳዎች እነዚህ ወኔ ቀስቃሽ ባህላዊ እሴቶች እንዳይተላለፉ በወያኔዎቹ ሳንሱር እየተደረጉ ስለሆነና ይህንንም ያልተፈቀደ ወኔ ቀስቃሽ የፈጠራ ስራ ያስተላለፈ የሚዲያ ባለሙ በወያኔዎቹ ስለሚጠየቅም እንደሆነ ያውቃሉ? ግን እስከመቼ? ለግንቦት 20: ለህወሀት አመታዊ በአል አከባበር ያለውን ድንፋታና ፋከራ እስኪ ከታላቁ የአደዋ በአል አከባበር ጋር አነፃፅሩት? ለአደዋ በአል እኮ አንዲት ቀረርቶ ወይም ፉከራ ለአንድ ሰከንድ ብልጭ ብላ ድርግም የምትደረግበት ምክነያትና ይህ የተላ ሀገር ሻጭ ወያኔ በአፍሪካ ከአደዋ ታሪክ በላይ ታሪክ ሰሪ ነኝ ብሎ የሚደነፋው: የሚፎክረው እኮ በአማራ ህዝብ እና በመላው ኢትዮጵያ ህዝቦች የብሶት ትግል በግሉ ታግሎ እንዳገኘው አድርጎ ሰማይ ሰንጥቄ ልግባ አይነት ጀግንነት ከየት የመጣ ነው! አረ ጉድ! ግን ያንን የዋህ ኢትዮጵያዊነቱን የሚወድ ኩሩና ሀቀኛ ህዝብ ከኢትዮጵያዊ ወንድሞቹ ጋር በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በሰላም እንዳይኖር ያዘኑለት መስለው እያሳሳቱትና የስልጣን ማቆያ ኮርቻ አድርገው እየተጠቀሙበት መሆናቸው በጣም ያሳዝናል!! የትግራይን ማታለሉ ግን አሁን የተጀመረ አይደለም:: ወያኔና ሻእቢያ የትግራይ እንዳይሰማ ጦርነቱ እስከሚጠናቀቅ በሚስጥር ይያዝ ተባብለው ሻእቢያ ባድሜን:ሽራሮንና አካባቢውን ወደኤርትራ እን