• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የስልጣን ተስፈኛ ፖለቲከኞች

March 30, 2016 11:05 pm by Editor Leave a Comment

የኢህአዴግ የቁርጥ ቀን ልጅ ልደቱ አያሌውና ፓርቲው ኢዴፓ ባዲስ ትርፍ የፓርላማ መቀመጫ ፍለጋ ሰሞኑን ከእንቅልፋቸው መንቃታቸውን ሰምቼ ትንሽ ተገረምኩ። በውል ያልተደነቅሁበት ምክንያት ኢዴፓንና ሌሎች በኢህአዴግ-ወለድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ም/ቤት ውስጥ የታጨቁ የስልጣን ተስፈኞች እንጂ ፖለቲካ የሚያውቁ ቁርጠኛ ተቃዋሚዎች ናቸው ብዬ ስለማላውቅ ነው። ደግነቱ ደግሞ ነገሩ እውነት መሆኑ ነው። እነዚህ ኢህአዴግ በልካቸው በሰራላቸው ጉረኖ ታሽገው በኢትዮጵያ ህዝብ መስዋእትነት ስልጣን ለመቀላወጥ በተስፋ የሚያደቡት ኢዴፓና አጃቢዎቹ ሰሞኑን የኢህአዴግ ዙፋን ሲነቃነቅ በፈጠረው የፖለቲካ ስንጥቅ ለመሰካት በጠቅላይ ሚንስትሩ እግር ስር ወድቀው ትራፊ ወንበር እንዲረጥቧቸው ልመና መጀመራቸውን ሰምቼ አፈርኩባቸው።

የኢዴፓ ሊቀመንበር ዶክተር ጫኔ ከበደ አርብ መጋቢት 16 ቀን 2008 ዓም ለአሜሪካ ድምፅ ያማርኛው አገልግሎት በሰጡት ቃለምምልስ ተቃዋሚዎች በፓርላማ የውክልና ወንበር እንዲኖራቸው ለማድረግ ተስፋ እንደተሰጣቸው ያለሀፍረት ሲናገሩ ተደምጠዋል። እስቲ ማን ይሙት በዚህ ወቅት፣ ከአንድ የተቃዋሚ ፓርቲ የሚጠበቅ ይህ ነበር? ፊደል ያልቆጠረው ምስኪኑ የኢትዮጵያ ገበሬ ለዴሞክራሲና ፍትህ የድሃ ደሙን እያፈሰሰ ባለበት በዚህ ወሳን ወቅት የኛ ዶክተር ፖለቲከኞች ሊሞት በሚያጣጥር አምባገነን እግር ስር ወድቀው የፓርላማ ወንበር ይለምናሉ። መጥኔ አቦ! እንዴት ያለ ህሊና ቢኖራቸው ነው ጃል? በህዝብ ደም አሮጌ የስልጣን ወንበር መመኘት።

ክቡር የሆነውን የወገን ደም ማርከስ አይሆንም? እንደወጉ ቁርጠኛ ተቃዋሚ መሆን ባይሳካላቸውና ተፈጥሯቸው ባይፈቅድላቸው እንኳን ገላጋይ ሽማግሌ ለመሆን ቢጥሩ ምን ነበረበት? ህዝብ ለፍትህ ሲጮኽ ብትት እንኳን ሳይሉ የወንበር እርጥባን ሹክሹክታ እንዴት በአንድ ጊዜ አባነናቸው? ጉድ ነውመቼም!

ለነገሩ ይህ ፓርቲና አጋሮቹ ምን ጊዜም ኢህአዴግ ጭንቅ በገጠመው ጊዜ ሁሉ ደራሽና የቁርጥ ቀን አገልጋዮች በመሆናቸው ታሪካቸውን ለሚያውቅ ድርጊታቸው የሚያስገርመው አይሆንም። የቅንጅት ዘመን ሚናቸውን ያስታውሷል። ያኔም ቢሆን ሀገር የከዱት በስልጣን ጥምና ስግብግብ ፍላጎታቸው ነበር። ዛሬም ያው ልማደኛ የስልጣን አራራቸው ተነሳና የህዝብ አስከሬን ላይ ቆመው ስልጣን ይለምኑ ጀመር። አቤት ክፉ ቀን ስንት ክፉ ነገር ያሳያል? ይህን ከመሰሉ አርተፊሻል ተቃዋሚዎች ኢህአዴግ በስንት ጣዕሙ ጃል!

ዛሬ ኢትዮጵያ የምትገኝበት ሁኔታ ልዩ መፍትሄ የሚሻ ነው። አሁን ስልጣንና ወንበር በስሌት የምንከፋፈልበት ጊዜ አይደለም። አሁን ይህች ውብ ሀገር ከገጠማት የታሪክ ፈተና ለማውጣት ሁላችንም (ምናልባትኢህአዴግን ጨምሮ) ሌት ተቀን የምንጨነቅበት ወቅት ነው። ዛሬ ነባር የግልና የቡድን ጥቅማችንን እያሰላን ሆዳችን የሚጮኽበት ጊዜ ሳይሆን በምጥ ላይ የምተገኘውን ሀገራችንን ካንቺ በፊት ያርገኝ የምንልበት ፈታኝ ወቅት ነው። እናም ኢደዓዊያን፣ እባካችሁ ህሊና ግዙ። ይሉኝታም ያስፈልጋል። ሀገር ሰላም ከሆነ ሌት ተቀን የሚያቃዣችሁ የስልጣን ሱስ የሚረካበት ጊዜ ሊመጣ ይችላል። ሀገር ከወደቀች ግን ከነቅዠታችሁ ትቀበራላችሁና አስቡበት። ቢቻል የህዝብን ጩኸት ችላ ብላችሁ በጓሮ በር ስልጣን ለመቀላወጥ ያደረጋችሁት ሙከራ አሳፋሪ ነውና በይፋ ይቅርታ ጠይቁ። ይህ ጨዋነት የማይሆንላችሁ ከሆነ ደግሞ ለገዛ እናታችሁ ቀብር መቆፈር የጀመራችሁትን ቁፋሮ አቁሙ። ኢህአዴግም ይታዘባችኋል። ይህ ካልሆነ ዛሬ ለኢትዮጵያ በቆፈራችሁት ጉድጓድ እናንተው ትገቡበታላችሁ። በጭንቅ ቀን ሀገሩን የከዳ ዋጋው ከዚህ ያነሰ ሊሆን አይችልም። ልቦና ይስጣችሁ! አሜን።


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule