አርቲስት ዳምጠው አየለ አጋጥሞት የነበረው ችግር በኖርዌይ መንግስት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ክፍሎች በኩል እየታየና ወደ መፍትሔ እየቀረበ መሆኑን አስታወቀ። በደረሰበት ያልታሰበ እንግልትና በቤተሰብ ናፍቆት የተነሳ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ቃለ ምልልስ ከሰጠ በኋላ በርካታ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ መጨነቃቸውን ያስታወቀው ዳምጠው አየለ፣ "ያጋጠመኝ ችግር መስመር እየያዘ ነው፤ በጥሩ ሁኔታ ላይ እገኛለሁ። ስሜታችሁን ለገለጻችሁልኝ በሙሉ ምስጋናዬ ታላቅ ነው" ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል። በወቅቱ ከቤተሰብ የቆየ ፍቅር ጋር ተዳምሮ፣ አጋጣሚው ስላበሳጨው ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት በሰጠው ቃለምልልስ አድናቂዎቹና ወዳጆቹ አዝነው በስልክና በተለያዩ መንገዶች ስለላኩለት ማበረታቻ ምስጋና ያቀረበው ዳምጠው፣ በቅርቡ ለወዳጅ ዘመድና አድናቂዎቹ ሰፊ መልዕክት እንደሚኖረው አመልክቷል። ከቃለ ምልልሱ ዋና … [Read more...] about ዳምጠው አየለ “ችግሬ እየተቃለለ ነው” አለ
Interviews
እናውጋ
የዳምጠው አየለ ጥሪ!!
“ሰው ናፈቀኝ፣ ልጆቼና አገሬ ታወሱኝ፣ ባህሌና ልማዴ የት ገባ….?” የሚሉት የአንድ ስደተኛ ጥያቄዎች ለመቶ አለቃ ዳምጠው አየለ ተረት ሆነውበታል። አርቲስት ዳምጠው አየለ ከሁርሶ የመኮንኖች ማሰልጠና ማዕከል የመኮንንነት ትምህርት ተከታትሏል። ለሰላሳ ሁለት ዓመታት በምድር ጦር የሙዚቀኛ ሻለቃ አገልግሏል። በተለይም በባህላዊና አገር በሚያሞካሹ ዜማዎቹ የሚወደደው ዳምጠው አገሩን፣ ሁለት ልጆቹንና ባለቤቱን ጥሎ በስደት ኖርዌይ ከገባ ሰባት ዓመታት አሳልፏል። የስልሳ ሶስት ዓመቱ ዳምጠው ያጋጠመውን ጊዚያዊ ችግር አስመልክቶ ከጎልጉል የአውሮፓ ዘጋቢ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ዳምጠው ችግር እንዳጋጠመው ሲሰማ አስቸኳይ ድጋፍ ላደረጉ ወገኖች፣ ድርጅቶች፣ ማህበሮች፣ ላደረጋችሁት በአርአያነት የሚጠቀስ ተግባር የዝግጅት ክፍላችን በዚህ አጋጣሚ ለማመስገን ይወዳል። “… አዎ፤ እኔም ራሴን … [Read more...] about የዳምጠው አየለ ጥሪ!!