ቀዝቃዛዉ ጥምቀትና የበረከት ስምዖን “ግብረኃይል” በጎንደር

ጥምቀትን ያለ ጎንደር ማሰብ የሚቻል አይደለም። ጥምቀት ከኃይማኖታዊ በዓልነቱ ባሻገር ባህላዊ ገጽታ የሚንጸባረቅበት ጉምቱ የአደባባይ በዓል ነበር። የጎንደር ጥምቀት እንኳን ለቱሪስቶች ለቀየዉ ነዋሪዎችም ታይቶ የሚጠገብ አልነበረም። በየዓመቱ በአማካይ 1500 የሚደርሱ ቱሪስቶች ከተለያዮ የአለማችን ክፍሎች ተሰባስበዉ ጎንደር ላይ ይከትሙ ነበር። ታይቶ የማይጠገበዉን የጥምቀት ትዕይንት ከከተራ እስከ ሚካኤል ንግስ ድረስ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚጎበኙት የዉጭ አገር ቱሪስቶች ብቻ ሳይሆን የአገር ዉስጥ ጎብኝዎችም በስፋት ይታደሙ ነበር። “ነበር እንዲህ ቅርብ ኑሯል ለካ” እንድትል ንግስት ጣይቱ ብጡል፤ የ2009 የጥምቀት በዓል አከባበር በጎንደር፡-ያን አስደማሚ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ትዕይንት “ነበር” አድርጎት አልፏል።

የወልቃት የአማራ ማንነት ጥያቄን አስታኮ የተቀሰቀሰዉ ህዝባዊ አመጽ በቀደመዉ ጊዜ በኦሮሚያ ክልል ከተፈጠረዉ አመጽ ጋር እየተመጋገበ ኢትዮጵያ ሳልሳዊ አብዮት እንድታስተናግድ እያስማጣት ይገኛል።አብዮቱ ይወለዳል ወይስ ይዘገያል የሚለዉ ጥያቄ ሌላ ጥያቄ ነዉ። ይሁንና በአገሪቱ በተለያዮ የክልል ከተሞች የጠቀሰቀሰዉን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የገዥዉ መደብ የግድያና የአፈና እጆች ረዘም ብለዉ ታይተዋል። ይህን ተከትሎ የታወጀዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አገሪቱን ቅርቃር ውስጥ ከቷታል። የዚህ ነጸብራቅ ዉጤት የሆነዉ የጎንደር ጥምቀት እጅግ ቀዝቃዛ በሆነ ድባብ “ተከብሮ” አልፏል።

የበረከት ስምዖን ግብረኃይል

የ2009 የመስቀል በዓል ለአገሪቱ የፖለቲካ ታዛቢዎች በሚደንቅ መልኩ ለገዥዉ መደብ ቁንጮዎች ደግሞ በሚያስበረግግ ሁኔታ በህዝባዊ አድማ ጎንደር ላይ በዓሉ በአደባባይ ሳይከበር እንደቀረ የሚታወስ ነዉ። ይህ ህዝባዊ ህብረት ያስበረገገዉ የገዥዉ መደብ ቁንጮ ህዝባዊ አድማዉ የጥምቀት በዓል ላይ እንዳይደገም በመስጋት በህዳር ወር የመጀመሪያ ሳምንት በበረከት ስምዖን አደራጅነት አንድ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም ተደረገ። ይኅዉ ግብረ ኃይል ከኮማንድ ፖስቱ ጋር እየተናበበ ለጥምቀት በዓል አከባበር አስፈላጊ ቅድመ ሆኔታዎችን በማመቻቸት ላይ ተጠምዶ ከረመ። ይኅዉ ግብረ ኃይል በአሁኑ ሰዓት በአገሪቱ መንግስታዊ መዋቅር ምንም አይነት ሥልጣን ለሌለዉ በረከት ስምዖን በየሳምንቱ ሪፖርት ያቀርብ ነበር። የግብረ ኃይሉ ዓላማ የጥምቀት በዓል እንዳይከበር “እንቅፋት” የሚፈጥሩ ህዝባዊ ኃይሎችን እየመነጠረ ለኮማንድ ፖስቱ አሳልፎ የሚሰጥ ሲሆን፤ ይኄዉ ግብረ ኃይል ከጥምቀት በዓል በኋላ እንዲበተን ታስቦ የተደራጀ ነዉ።

የግብረ ኃይሉ አወቃቀር ከጎንደር ዩኒቨርስቲ፣ ከመምህራን ኮሌጅ፣ ከቴክኒክና ሙያ፤ ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ ከክፍለ ከተማ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊዎች፣ የገዥዉ መደብ ክንፍ ከሆኑት የሊግና ፎረም ማህበራት አመራሮች እንዲሁም የሰሜን ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ዉስጥ ሰርገዉ የገቡ የገዥዉ መደብ ተነጣፊ የቤተ ክህነት ቁንጮ ሰዎችን ባካተተ መልኩ የተዉጣጣ ነበር። የዚህን ግብረ ኃይል የድርጊት መርሀ ግብር አፈጻጸም የሚከታተለዉ በረከት ስምዖን ሲሆን፤ የግምገማዉን ሪፖርት ለመረጃና ደህንነት ዋና ዳይሬክተሩ ጌታቸዉ አሰፋ ያቀርባል።

በዚህ ተዋረዳዊ አሰራር መሰረት የግብረ ኃይሉ አባላት ዋነኛ ስራ በሚሰሩበት መስሪያ ቤትና በመኖሪያ አካባቢያቸዉ የስለላ ስራዎችን በመስራት የደህንነት ስጋት የሚታይባቸዉን አካባቢዎችና ግለሰቦች በመለየት ለኮማንድ ፖስቱ ጥቆማ ያሰጣሉ። ግልባጩንም በሳምንቱ መጨረሻ በግብረ ኃይሉ ጠርናፊ አማካይነት ለበረከት ስምዖን ይላካል። ይህ ግብረ ኃይል ከህዳር ወር የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ የጥምቀት በዓል አከባበርን በተመለከተ በከተማዉ የሚናፈሱ ወሬዎችን በመለቃቀም አደራጅቶ ሪፖርት ያቀርባል። በዓሉ እንዳይከበር “እንቅፋት” ይሆናሉ የሚሏቸዉን ተሰሚነት ያለቸዉን የከተማዋን ወጣቶች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እየተከታተሉ ለኮማንድ ፖስቱ ይጠቁማሉ። ከሁሉ በላይ የሚገርመዉ የዚህ ግብረ ኃይል ክንፍ የሆነዉ የቤተ ክህነት የስለላ መስመሩን የሚመራዉ ቡድን ሲሆን፤ አባላቱ በአርባ አራቱም አብያተ ክርስቲያናት ያሉትን የኃይማኖት አባቶችን፣ ቀሳዉስትን፣ ዲያቆናትንና የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችን ከምኩራብ አስከ ደጀ ሰላም ድረስ ያለዉን እንቅስቃሴቸዉን እየተከታተተሉ ይሰልላሉ፤ “ጸረ-ጥምቀት በዓል” (ጥምቀት አይከበር የሚል) አመለካከት የሚታይባቸዉን የቤተክርስቲያን ሰዎች ለኮማንድ ፖስቱ አሳልፈዉ ይሰጣሉ። በጎንደር ዩኒቨርስቲ፣ በመምህራን ኮሌጅ፣ በቴክኒክና ሙያ፤ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ የመንግስትና የግል ደርጅቶች ዉስጥ ከሚማሩና ከሚሰሩ ተማሪዎችና ሰራተኞች ዉስጥም ተመሳሳይ ዝንባሌ (ጸረ-ጥምቀት) የሚታይባቸዉ በዓሉ ከመድረሱ በፊት እንዲታሰሩ ተደርጓል። በአሁኑ ሰዓት ሁለተኛ ዙር “የተሃድሶ ፕሮግራም” ተሳታፊ እንዲሆኑ በሚል በብርሸለቆ ዉስጥ ታጉረዉ ከሚገኙ የጎንደር ወጣቶች (ካህናትን ጨምሮ) ብዙዎቹ በዚህ ግብረ ኃይል ጠቋሚነት የታፈሱ ናቸዉ።

የግብረኃይሉ ጫና ውጤትና “ቱሪስቶች”

በቃሉ የሚጸናዉ ብዙሃኑ ጎንደሬ ጥምቀት ላይ ላለመታደም የተማማለ ቢሆንም በበረከት ስምዖን አደራጅነት የሚመራዉ ግብረ ኃይል ድራማዊ ድባብ ያለዉ ቀዝቃዛ የጥምቀት በዓል እንዲከበር “የአንበሳዉን ድርሻ” ይዟል። በአንድ ለ አምስት ከተደራጁት ዉስጥ በዓሉ የሚመለከታቸዉ የኦርቶዶክስ ክርስትና አማኞች ከከተራዉ አስከ ሚካኤል ንግስ ዕለት ለሦስት ተከታታይ ቀናት በበዓሉ ላይ እንዲገኙ ተደርጓል። ከአንድ ለ አምስት አደረጃጀት በተጨማሪ የሊግና የፎረም አባላት፣ የልዩ ልዩ ማኅበራት አመራሮችና የጥቅም ተጋሪዎቻቸዉ፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲና በመምህራን ኮሌጅ የነጻ ትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸዉ በመማር ላይ ያሉ የሥርዓቱ አገልጋዮች፣ የዳሽን ቢራ ፋብሪካ ሰራተኞች፣ በማኅበር የተደራጁ “የጎንደር ከተማ አዝማሪዎች ማህበር” አባላት፣ በጎንደር ዙሪያ የሚገኙ የገጠር ቀበሌ አመራሮች፣ የገጠር ቀበሌ የካቢኔ አባላት ለበዓል አሟቂነት በልዩ እንክብካቤ ከከተራዉ ጀምሮ እንዲገኙ ተደርጓል። የገጠር ቀበሌ አመራሮች፣ ተከታይ ጀሌዎቻቸዉ እንዲሁም አበል ተከፋይ አዝማሪዎች ለባህላዊ ጭፈራ አሟቂነት ጥቅም ሲሰጡ ተስተዉሏል።

ዉንብድና የማያልቅበት የገዥዉ መደብ ስብስብ ከወቅቱ የአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ በጎንደር የጥምቀት በዓል የዉጭ አገር ቱሪስቶች ቁጥር ወደ ዜሮ ፐርሰንት ዝቅ እንደሚል ቀደም ብሎ የተረዳ በመሆኑ የተለመደ የማጭበርበር ሥራዉን ሰርቷል። በጎንደርና አካባቢዉ ሰላምና መረጋጋት የሰፈነ ለማስመሰል፤ “ቱሪስት” በሚል ጎንደር ላይ እንዲገኙ የተደረጉት የዉጭ አገር ዜጎች በአብዛኛዉ በአገሪቱ ዉስጥ ያለ ከልካይና አለም አቀፍ ጨረታ ሳይወጣ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ግልጽነት በጎደለዉ መልኩ እንዲሰሩ እድሉ የተሰጣቸዉ የቻይናዉ ሲ.አር.ሲ (CRC) እና የጣሊያኑ ሳሊኒ (SALINI CONSTRUCTION – የህዳሴዉን ግድብ የሚሰራዉ) ደርጅት ተጠቃሽ ናቸዉ። በእነዚህ ድርጅቶች ዉስጥ የሚሰሩ አንድ መቶ ሃያ የዉጭ አገር ዜጎች ከየፕሮጀክት ሳይቶች ተሰባስበዉ በ“ቱሪስት” ስም ከተማዋ ላይ እንዲገኙ ተደርጓል። ወጪያቸዉን የሸፈነዉ ደግሞ የታደሰ ጥንቅሹ መጫዎቻ የሆነዉ የብአዴኑ “ጥረት” ነዉ። ይህ ምስጢር ያልገባቸዉ በደንበኛ ድርቅ ተመተዉ የከረሙት የጎንደር ትልልቅ ሆቴሎች እንግዶቹ የአገልግሎት ክፍያዉን በዶላር እንዲፈጽሙ ቢማጸኑም ሰሚ አላገኙምና ሆቴሎቹ “ይህንስ ማን አየብን” በሚል ሀበሻ በሚስተናገድበት የአገልግሎት ክፍያ በጉዞ ወኪል (ኤጀንት) በኩል ክፍያቸዉ ተፈጽሟል። የጉዞ ወኪሉ የብአዴኑን “ጥረት” የስፖንሰር ወጪ ለመቀነስ በአየር ላይ የተፈጠረ የበረከት ስምዖን ምናባዊ ድርጅት ነዉ።

ቆርጦ ቀጥሉ “የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን” በዜና እወጃ ሰዓቱ መልሶ መላልሶ ጥምቀትን ከተመለከቱ የዜና ፋይል ክምችት ጋር እያቀናበረ “የጥምቀት በዓል በጎንደር ከተማ የክልሉና የፌዴራል ባለስልጣናትና የከተማዉ ነዋሪዎች  በተገኙበት በድምቀት ተከበረ … በበዓሉ የተገኙ የዉጭ አገር ቱሪስቶችም በበዓል አከባበሩ ደስተኛ መሆናቸዉን ገለጹ…” በሚል ለቀዘውቃዛዉ ጥምቀት ሞቅ ያለ ዜና ሰራለት።

ቀዝቃዛዉ ጥምቀት እንዲህ ባለ ዜና ተከሽኖ ቀረበ … እዚህ ደርሰናል!! ዉሸት በአይነት!! ፕሮፖጋንዳ በገፍ!! ሽንፍላ ይመስል ታጥቦ የማይጸዳዉ የገዥዉ መደብ ስብስብ ጥልቅ መበስበሱን ግፋ በለዉ ማለቱን ቀጥሏል …ግን እስከ መቼ ይዋሻል?! የዉሸት እድገት በፕሮፖጋንዳ መልኩ መጠመቃችን ላይበቃ ጥምቀቱንም እንዲሁ?! ድንቄም መታደስ … እኛስ ታዘብን ጥልቅ መበስበስ!!

ቴዎድሮስ ኃይሉ

(ይህ ዘገባ ከፎቶው ጋር በተለይ ለጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ የተላከ ነው፤ ፎቶው ጥምቀት 2009ዓም በጎንደር ከተማ “በተከበረበት” ወቅት)

 

Comments

 1. Tesfa says:

  ጊዜው ረዘመ እንጂ በአንድ የሃገራችን ክፍል የክረምት ትምህርት ግማሽ ቀን እንድንማር ይደረግ ነበር። ትምህርቱ በሂሳብ፤ በመልካምድርና በታሪክና በቋንቋ ላይ ያተኮረ ነበር። ታዲያ የቅርብ ጓደኞቼ እመቤት ክንፉ፤ ጋሻውጠና አምደጽዮን፤ ሙሉ ገ/ሚካኤል ሌሎች አሁን የተረሱኝ ውድ ጓዴኞቼ በናፍቆት የምንጠብቀው አንድ የትምህርት ጊዜ ነበር። እርሱም የታሪክ ክፍለጊዜ ነበር። አስተማሪው ከጀርመን ለእረፍት ቤተሰብ ጥየቃ የመጣ ግርማ ፍስሃ ይባላል። አባቱ በከተማችን አንድ የመድሃኒት መደበር አላቸው። ግርማ የሃገር ፍቅር ያቃጠለው እኛንም በልጅነታችን ያው የወገንና የሃገር ፍቅር እንዲኖረን ይጥር የነበረ ምሁር ነው። በታሪክ ክፍለ ጊዜ “አርሙኝ” ከተሰኘው መጽሃፍ ውስጥ “አልሞትኩም ብየ አልዋሽም” የሚለውን ክፍል ሲያነብልን እንባው ከአይኑ ላይ ጠብ ጠብ እያለና ሲቃ እየተናነቀው ነበር። ወርቃማው ጊዜ! ሰው በዘርና በጎሳው ያልተሰለፈበት። ጥቂቶች አሳዳጅ ብዙሃን ተሰዳጅ ያልሆኑበት ያ ማለፊያው ጊዜ። ታዲያ እኛም እርሱ ታሪኩን በሲቃ ውስጥ ሆኖ ሲያነብልን አብረነው እናለቅስ ነበር። ክፍሉ አንድ ጊዜ የሃዘን ቤት ገጽታ ሲኖረው ሌላ ጊዜ ደግሞ የአቶ ተማቹን ታሪክና የወ/ሮ ጽጌረዳን በጽሁፉ ያላቸውን ድርሻ ሲያነብልን አንዴ የከፋው ፊታችን ፈግግ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንባ ከዓይኖቻችን ላይ ጥብ ሲል እርስ በርስ እየተያየን አይዞሽ አይዞህ እንባባል ነበር። ታዲያ አንድ ቀን በጣም ደስ ብሎት ወደ ክፍል ገባና ግርማ እንደዚህ አለን። ያው እንደምታውቁት የአቶ ተማቹንና የወ/ሮ ጽጌረዳን ታሪክ ባለፈው አንበን ጨርሰናል። ዛሬ የምናነበው “ቡሄ የልጆች ጫዋታን” ነው ሲል ክፍሉ ሁሉ በደስታ ተሞላ። መጽሃፉን ገልጾ ለትንሽ ጊዜ እኛኑ እያየ በጸጥታ አይኖቹን በመረጠብት ሥፍራ ሲያሳርፋቸው ቆየና ሌላ ደስ የሚል ዜና አለኝ። በቅርቡ አንድ ቲያትር አይቼ በጣም ወድጄዋለሁ። እናም ዛሬ እሁድ በድጋሚ ስለሚታይ ከወላጆቻቹህ አስፈቅጄ ለሁላቹሁም የመግቢያ ትኬት ገዝቸላቹሃለሁ። ያው ማክሰኞ ወደ ጀርመን ለትምህርት ስለምመለስ ይህ የእኔ ስጦታ ነው በማለት እንባ ተናነቀው። የቲያትሩ ስም “ሽፍንፍን” ሲባል ደራሲው ስማቸው ጠፋብኝ፡፡ ይመስለኛል አሻግሬ ነው። ታዲያ ይህን ሁሉ ምን አስባለህ ለምትሉ መልሴ እንሆ። ዛሬ ወያኔ በኦሮሞና አማራ ቦታዎች የትምህርት ተቋማትን የጦር ሰፈር ሲያረግ በክልሉ (ትግራይ) የመኪና መገጣጠሚያ፤ አዳዲስ ት/ቤቶች፤ የመንገድ ስራ ባጠቃላይ ትግራይ እንደ አንድ ሃገር ሆና ከተዘረፈው የሃገራችን ሃብት ላይ 12 ሚሊዮን ብር በረሃብ ለተጠቁ ኢትዮጵያውን ሶማሊዎች ተለገሰ ሲባል ከመግረም አልፎ የሚያሳዝን ነው። የሚገርመው ግን ይህ ነው። ይህ የገንዘብ አሃዝ ለዘረፋ እንዲያመቻቸው የሚያመቻቹት መንገድ እንጂ ለተራበው ህዝብ ከምሲን አይደርሰውም። አንድነታችን በዘርና በጎሳ በመከለል ለራሱ ጥቅም 99% ቱን ወታደራዊ ሃይል በራሱ ዘር ያዋቀረው ወያኔ ለማንም ገዶት አያውቅም። ወያኔ ከዘር በሽታው ድኖ ለሃገር ለአንድነት ለመላ የሃገሪቱ ኑዋሪዎች በጎ ነገር ያመጣል ብሎ ማመን ተጨፈኑና ላሞኛቹሁ እንደማለት ይቆጠራል። ወያኔ አረመኔ ነው። በአማራው ህዝብ ላይ የፈጸመውና በመፈጸም ላይ ያለው ዘግናኝ ድርጊት ጣሊያኖች አልሞከሩትም። ወያኔ ግን ከ 2 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የት እንደገባ መናገር አይፈልግም። አፈናውን፤ ግድያውንና ማሰሩን ሳይቋርጥ ከተቃዋሚ ጋር ድርድር ገለ መሌ ቢል ጊዜ ሊገዛበር እንጂ ወያኔ የተለወጠ ልብ የለውም። ሊኖረውም አይችልም። አረመኔና የጠባብ ብሄርተኛ ቡድን ስለሆነ የሚያሰበው ራሱን የበላይ ሌላው ለእርሱ በርሱ ስር የሚኖር እንደ እንስሳ ጀሮውንና አንገቱን የሚጠመዝዘው ሁለተኛ ዜጋ ነው። ወያኔ የጎንደርን ህዝብ ጠምዶ የያዘው ዛሬ ሳይሆን ገና በበረሃ እያለ ነው። ጥላቻው በአማራ ህዝቦች ላይ ያለና የነበረ እንጂ አዲስ አበባ ቤተመግሥት ከገባ በህዋላ የተቃመሰው እኩይ ባህሪ አይደለም። ጥምቀትና ጠበንጃ የወያኔን የእምነት ደረጃ ያሳያል። በውነቱ ወያኔ በትግራይ ህዝብ የሚነግድ፤ ኢትዮጵያዊነትን የሸጠ ድርቡሽ ነው። እነዚያ የክፍል ጓደኞቼ በህይወት ይኖሩ ይሆን? ዛሬ ስላለንበት የሃገራችን ውሽንፍር ምን ይሰማቸው ይሆን? ያኔ አንድ ነበርን። ዘር፤ ጎሳ፤ ሃይማኖት ጭራሽ በማሃላችን ገብቶ አያውቅምና! ዛሬም ኢትዮጵያዊ ነገም ኢትዮጵያዊ። እውቁ አቤ ጎበኛ አልወለድም በተሰኘው መጽሃፉ ላይ እንደሚለን አንድ ጊዜ ኢትዮጵያዊ ሆንን ተወልደናልና እንበርታ!!

 2. Deregu Temelese says:

  The people of Welqait and Tsegede have lived for the past 25 years under Tigray administrative region. This is excluding the 17 years they came under the TPLF before it controlled the state. These people are one of the early and staunch supporters of the TPLF. The TPLF maintained its very head quarters in these regions for most of its bush life, a fact which says a lot about the relationship between the residents and the TPLF.

  So, what happened now? Why now after 17 + 25 years of TPLF rule? I did not hear anything as loud and confrontational as the current disturbance is. Why not then?

  Even more perplexing is the fact that the so-called ‘Welqait is Amhara’ leaders are in fact TPLFite themselves. The likes of Col. Demeke are said to have joined TPLF at 18 and served it until recently. To add to the confusion, the Weyane of today is more Ethiopian, more “Amhara-friendly” than the TPLF of the bush times when it was accused of particularly being hostile towards “Amhara’’ and openly pronounced their warfare as ‘Ant-Amhara” struggle. It makes little sense that a person who not only believed that he was a Tigrayan for over 40 years but actively fought against the “Amhara” would proclaim that after all these years he is in fact an ‘Amhara’ and now intends to do the reverse fight.

  What is really happening? The answer is actually given by none other than Col. Demeke himself. In one of the interviews he gave in Tigringa to VOA, he said if it was not for a ‘mal-administration’, the “Welqait is Amhara’’ question would not have been raised to begin with. I think that says it all. The rest is probably a cover. Here is the interview:

  http://tigrigna.voanews.com/a/colonel-demeke-zewdu-on-welkite-and-tsegedie-question-of-identity-part-2/3258444.html

  So, what is the real cause of all these deaths and destruction? Well, it must have to do with the most illiterate, most incompetent and most despicable person of the TPLF, Abay Armam Woldu. When one is so incompetent and so illiterate, one cannot lead. At the end of the day such people will only alienate their own people. That is what is happening.

  The question is how on earth is it possible for such plain garbage to make it to the top position to begin with? Corruption! TPLF lived only for few months in the 60’s. What is there now is an Adwa PLC, which operates on principles of maximizing profit and benefit to its family members. Armam Woldu is a living proof that the so-called TPLF never existed. Or can I ask those TPLFites what the qualities of this man is to be elected to lead a party? His is from Adi-Abun, Adwa. That is all he got.

  Here is the leaders[CEO] of the for-ptofit TPLF (Adwa PLC):
  Aregawi Berhe ——-1st chairman, from Adwa wereda
  Sibhat Nega———-2nd chairman, from Adwa Wereda
  Meles Zenawi ——– 3rd chairman, from Adwa wereda
  Abay Woldu ——— 4th chairman, from Adwa wereda

  Debretsion Gebremichael (currently deputy, in line to be the next president), again Adwa wereda.
  BTW, the next being groomed to be a deputy is a lady from Adwa. Take my word.

  Obviously this is not just simple corruption, but corruption committed in blood of innocents. Meles Zenawi was found to be not just the 1st but also the 2nd and 3rd ‘traitor’ in the history of TPLF. Per the TPLF “metedaderiya denb” of that time, Meles deserved the death penalty. But Meles repeatedly avoided the death penalty for everybody that brings the charges, that judges it and those who approve the decision were/are all Adwans. Many non-Adwan Tigrayans were put to death for very minor misdemeanors.

  The scheme that worked for them is a brainchild of Sebhat gahgah Nega. Basically they pick, promote and encircle themselves at every level of the party hierarchy. For this, the first step was to make sure that general counsel , an obscure but critical, members of the TPLF to be comprised of at least 90% Adwans or people who have marriage ties to Adwa wereda. These members have the right to elect the “central committee members” and the central committee members in turn will have the right to elect the ‘executive committee members’ of the TPLF. It is this executives who would elect the president and its deputy and run all the affairs of the party. If you are not from Adwa, you got no vote. Sibhat gahgah Nega call this ‘democraciawi’ and nearly all his TPLF members believes him.

  For the pupose of comparison, please compare the so-called TPLF with ANDM. Forget what their political position etc, is. For what they believe in, ANDM IS NOT owned by a single family, ANDM leaders DO NOT hail from one wereda and because of these ANDM DOES NOT promote the most despicable and the most grossly incompetent like Abay Armam Woldu to lead them. There is no wereda/district in Amhara region, that hates the region. In fact, there are likes those openly organized “Oromoiya Zone” but they never raised to be with Oromoiya than Amhara despite the obvious linguistic fact.

  Unlike the Adwa PLC, ANDM people are real revolutionaries who fought for what they believe in. That is the difference between people of principle and people who schemed a system for their own family benefit.
  Sponsored Ads

Speak Your Mind

*