• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከትናንት ወዲያ፣ ትናንትና ዛሬ

August 29, 2016 09:21 am by Editor Leave a Comment

ዛሬ ላይ ቆሜ ወደኋላ ሳይ የትናንት ወዲያው ይናፍቀኛል፤ ትናንት ወዲያን አይቼዋለሁ፤ አውቀዋለሁ፤ ትናንትንም አይቼዋለሁ፤ አውቀዋለሁ፤ ዛሬንም እያየሁትና እያወቅሁት ነው፤ ከትናንት ወዲያ በጃንሆይ ዘመን የአገዛዙ ነቃፊ ነበርሁ፤ የወደፊቱን የማየት ችሎታ ስለሌለኝ የጃንሆይን አገዛዝ ነቃፊ ነበርሁ፤ በትናንት ወዲያ ላይ በጃንሆይ ዘመን ላይ ቆሜ ዛሬን የማየት ችሎታ ቢኖረኝ የጃንሆይን አገዛዝ ነቃፊ አልሆንም ነበር፤ ትናንትን፣ የደርግን ዘመን ከዛሬው ከወያኔ ዘመን በመሠረቱ እምብዛም የማያለይ በመሆኑ አይናፍቀኝም፤ የዛሬው የወያኔ ዘመን አስመረረኝ፤ ምርር ብሎኛል፤ እንዳልሰደድ ቀዳማዊ ምኒልክ ያለውን ተከታይ ነኝ፤ እንዲህ ብሏል፡–

‹‹እናቴንና አገሬን እተው ዘንድ አይቻለኝም፤›› እናቴ ‹‹በጡቶቿ አምላኛለችና››፡፡

እናትና አባቴ የኢትዮጵያን ምድር ሆነዋል፤ አባቴ በማይጨው ዘምተው በጥይት ቆስለዋል፤ የመርዙንም ጋዝ በትንሹ ሳንባቸውን ሳይጠብሰው አልቀረም፤ ይቺን እናትና አባቴ አፈር የሆኑላትን አገር ትቼ መሰደዱ ስለማይሆንልኝ እየመረረኝ የመድኃኔ ዓለምን ምሕረት እጠብቃለሁ፡፡

torture123ለምን የጃንሆይ ዘመን ይናፍቅሃል? ለሚለኝ የምሰጠው መልስ የሚከተለው ነው፤ በጃንሆይ ዘመን ኢትዮጵያ የታሪክ ክብርዋ ርዝራዥ ነበረ፤ ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱን ችሎ በነጻነት የኖረ፣ በተደጋጋሚ የመጡበትን የተለያዩ ወራሪዎች እያሳፈረ የመለሰ ቆራጥ፣ ጀግናና ኩሩ ሕዝብ መሆኑን ዓለም በሙሉ አምኖ የተቀበለው ጉዳይ ነበር፤ በዘመኑም ከተባበሩት መንግሥታት ጦር ጋር ኮሪያ የዘመተው የኢትዮጵያ ጦር ከአሥራ ሰባት አገሮች አንዱ ቢሆንም አንድም ምርኮኛ፣ አንድም ሬሳ በጠላት እጅ ሳያስገባ የተመለሰ ብቸኛ ጦር ነበር፤ ያኮራል፡፡

ከኢትዮጵያ ለመውጣት ቪዛ ማገኘት ቀላል ነበር፤ በዚያን ጊዜ ምን ዓይነት ኢትዮጵያዊ ነው ለመሰደድ የሚያስብ? አሜሪካ በየዓመቱ የሚመድበውን የኢትዮጵያን የስደት ድርሻ የሚጠቀሙበት ጥቂቶች ግሪኮችና አርመኖች ነበሩ፤ አርባ ሺህ ግድም ጦር ይዛ የምትፈራ፣ ደሀ ሕዝብ አቅፋ የምትኮራና የምትከበር፣ ጮሃ ሳትናገር የምትሰማ አገር ነበረች፤ እምነት የሚጣልበት የጨዋ ሕዝብ አገር ነበረች፤ ይህ ነው የናፈቀኝ! police12

ዛሬ በየጋዜጣው ላይ የማነበውና የማየው ፎቶግራፍ አሳፈረኝ! ውርደቱ አንገፈገፈኝ! ከሁሉም ይበልጥ ደግሞ ምንም ማድረግ አለመቻሌ፣ ኢምንትነቴ ያንገበግበኛል፤ አንድ ወጣት በባቡር መንገድ ላይ ወድቆ አምስትና ስድስት ፖሊሶች እየተሻሙ በዱላ ሲደበድቡት፣ በጫማቸው ቦታ ሳይመርጡ ሲረግጡት እነዚህ ከኛው የተወለዱ፣ በእኛው ባህልና እምነት ያደጉ፣ ለሕዝብ ደኅንነት የተሰማሩ ናቸው ወይ? የሚፈጽሙት ግፍ ጀግንነት ይመስላቸው ይሆን ወይ? ልጆች ያላቸው ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው እነዚህን የግፍ ምስሎች በጋዜጣም ሆነ በቲቪ ሲያዩ እንደሚያማቸው ይገነዘባሉ ወይ?

በሚያዝያ 30/1997 በሚልዮን የሚቆጠር ሕዝብ በጨዋነት ወጥቶ በጨዋነት ተበተነ፤ ለምን አይቀጥልም? እስከመቼ ተፈራርተን እንኖራለን? በሠለጠነ መንገድ መነጋገር አልቻልንም፤ በሰላማዊ ትግል መነጋገር አልቻልንም፤ በግድ ወደሕገ አራዊት መግባት አለብን?

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ነሐሴ 2008

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule