ከበቃና ኦብሴ
“… ዜሮ ስድስት (ባዶ ሹድሽተ) ተብሎ የሚጠራ እስር ቤት፤ ለትግራይ ሕዝብ የናዚ ስርዓት የሚፈጽሙበት ነበር፡፡ ይህ ከአደጉ በኋላ (ምስገበሉ) የተመለሱበት ሜዳ ስለነበር፤ ለሞት ተፈርዶ ወደዚሁ ሜዳ የሚላክ እስረኛ፤ ስጋውን በፍጹም አሞራ አልበላውም፡፡ የእስር ቤቱ ጭካኔና ስርዓት አጽረጋ ከተባለው ስፍራ እንደጀመሩት ዓይነት ነበር፡፡ የኢዲህ ደጋፊ ነህ፣ ልጅህ ወይም ወንድምሀ የኢዲህ ታጋይ ነው፣ ተብሎ ይያዝና፤ ወደዚሁ ዜሮ ስድስት “ባዶ ሹዱሽተ” እስር ቤት ይወሰዳል፤ … ለጥቂት ቀን ደህና ቀለብ እየተሰጠው በሁለት በሶስት ቀን ውስጥ ከሌላ ተመሳሳይ እስረኛ ጋር እየተረዳዳ፣ ቢያንስ ሁለት ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ እንዲቆፍር ይታዘዛል፤ የጉድጓዱ ስፋት ወይም ዓይነት የሰው መቃብር አይመስልም፤ እንደ ውሃ ጉድጓድ ጠበብ ብሎ እየተቆፈረ አፈሩ ዙሪያውን ይከመራል፤ እስረኛው የቁም መቃብሩን ጭሮ እንዳበቃ ይወጣና በገመድ እጅና እግሩ ታስሮ፣ ዓለም በቃኝ ወደ ቆፈረው ጉድጓድ ይመልሱታል፡፡ ወያኔዎች እስረኛቸው ከመሞቱ በፊት ሲሰቃይ ማየት በጣም ያረካቸዋል፡፡ ቶሎ እንዳይሞት ትንሽ ቂጣና ጥቂት ውሃ በሜንጦ መሳይ በገመድ(በመገለል) ያቀብሉታል፡፡ ሽንትም ሆነ ዓይነ ምድር መፀዳጃው ከዚያችው ጉድጓድ ውስጥ ነው፡፡ አንዴ ወደ ቆፈራት ጉድጓድ ከተጣለ በኋላ፤ በምንም ተአምር መልሶ መውጣት የለም:: እስረኛው በዚያች ጠባብ ጉድጓድ ውስጥ እግሩን መዘርጋትና፤ በጎኑ መተኛት አይችልም:: ተጨብጦ መቀመጡ ከደከመው፣ አቅሙ ከቻለ ማድረግ የሚችለው መቆም ብቻ ነው::ኩርኩም ብሎ ቀን በፀሐይ ሃሩር፣ ሌሊት በብርድ በጤዛ እየተሰቃየ፤ የተፈጠረባትን ቀንና አገር ዘር ሲረግም፤ ከመሞቱ በፊት ከመሬቱና ከሰውነቱ በሚፈጠሩት ትሎች (ድቁቋ)፤ ሰውነቱ እየተበላ፣ በሰው ላቦትና በመሬት ሙቀት የሚፈጠሩት ትሎችም፤ መርዘኞች ስላልሆኑ ቶሎ አይገድሉትም:: ቆዳውን ሰርስረው፣ ስጋውን በልተው፣ አጥንቱን መፈርከስ ሲጀምሩ፣ እስረኛው በመጨረሻው በአፍና በአፍንጫው በዓይኖቹም ትሎችና ድዱቋዎች ይፍለቀለቁና፣ አሰቃቂ በሆነ መርገም ህይወቱ ከላፈች በሗላ፣ በዚህ የመርገም ትእይንት የማይሰቀቁ ወያኔዎች በጉድጓዱ ዙሪያ ያለውን አፈር መለስ አድርገው፣ እጅ እግሩን ታስሮ እንደ ተኮረኮመ እዚያው ቅብር ያድርጉታል:: … (ሙሉውን አስነብበኝ)
Leave a Reply